4 days ago
በሀገር ውስጥ አቅም ውስብስብ የልብ ቀዶ ጥገናን በተሳካ ሁኔታ ማካሄድ መቻሉ ተገለፀ
****************
በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ለሁለት ሕፃናት ህይወታቸውን የሚታደግ ውስብስብ የልብ ቀዶ ጥገና በተሳካ ሁኔታ ማካሄዱን ገለፀ።
ቀዶ ጥገናው የተደረገው ለ6 ዓመት እና ለ8 ወር ሕፃናት ሲሆን፣ ከቀዶ ጥገና ህክምናው በኋላ የህጻናቱ ጤንነት በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ህክምናውን በዶክተር ፍፁም አርጋው የሚመራ የሀገር ውስጥ የልብ ቀዶ ጥገና ቡድን የመራው ሲሆን፣ በዶክተር ሜሮን ተስፋዬ የሚመራው የፅኑ ህክምና ቡድንም ለህፃናቱ ማገገሚያ የሚሆን ልዩ ክትትል እያደረገ መሆኑን ከማዕከሉ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።
እንዲህ ያሉ ውስብስብ የልብ ቀዶ ጥገናዎች በሀገር ውስጥ መከናወናቸው የህፃናትን ሕይወት ከመታደግ ባለፈ የሀገሪቱን የልብ ሕክምና አቅም እየጎለበተ ስለመሆኑ የሚያሳይ ነው ተብሏል።
በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከ7,000 በላይ ታካሚ ሕፃናት የልብ ቀዶ ጥገና ለማግኘት በረጅም የተጠባባቂነት ሰልፍ ላይ ይገኛሉ።
እንደዚህ ያሉ ውስብስብ ቀዶ ጥገናዎች በውጭ ሀገራት ለማካሄድ እስከ ሺዎች ዶላር የሚጠይቁ በመሆናቸው፣ ማዕከሉ በነጻ የሚሰጠው ይህ አገልግሎት ለታካሚ ቤተሰቦች ከፍተኛ የፋይናንስ እፎይታን ሰጥቷል።
ከዚህም በላይ የውጭ ሀገር የበጎ አድራጎት ቡድኖችን ሳይጠብቁ በሀገር ውስጥ የልብ ስፔሻሊስቶች አቅም ብቻ መከናወኑ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን የሕክምናና የቴክኖሎጂ አቅም ወደ አዲስ ደረጃ ማሸጋገሯን ማሳያ መሆኑ ተጠቅሷል።
በኢንቲሀድ አብራር

6 days ago
እነሆ ''ተስፋን እንትከል'''
#ethiopia | "ዛፍ ለመትከል የተሻለው ጊዜ ከ20 ዓመታት በፊት ነበር፤ ሁለተኛው የተሻለው ጊዜ ደግሞ አሁን ነው" እንደሚባለው ሁሉ፣ ዛፍ መትከል ተስፋን መትከል በመሆኑና ሕይወታችንን ሰናይ ለማድረግ ደኖቻችንን ማልማት አስፈላጊ ነው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የምድራችን 31 ከመቶ የሚሆነው አካል በደን የተሸፈነ ቢሆንም፣ የደን ሽፋን በየጊዜው እያቆለቆለ በመምጣቱ እስከ እ.ኤ.አ 2030 ድረስ 1 ትሪሊዮን ዛፎችን ለመትከልና ለመንከባከብ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል።
በሀገራችን በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ 40 ከመቶ የነበረው የደን ሽፋን ለእርሻ መሬት መስፋፋት ሲባል ተመንጥሮ ወደ 2 ከመቶ ወርዶ የነበረ ቢሆንም፣ ባለፉት አምስት ዓመታት በተደረገው ከፍተኛ ጥረት የደን ሽፋኑ በ2023 ወደ 23.6 ከመቶ ማደግ ችሏል።
በዚህ መነሻም የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆኑ ሀገራዊና ማህበራዊ ልማቶችን አከናውኗል።
በኢንስቲትዩቱ "ተስፋን እንተክላለን" በሚል ሀገራዊ ራዕይ የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በማካሄድ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመተባበር በቦቢቾ ቀበሌ ለምግብነትና ለአካባቢ ጥበቃ የሚውሉ 5 ሺህ ችግኞችን ተክሏል።
ከችግኝ ተከላው ጎን ለጎንም በጀሎ ናረሞ ቀበሌ "የዛሬ ህፃናት የነገ ተስፋ ናቸው" በሚል መሪ ቃል የነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናትን አእምሯዊ እድገት ለመደገፍ የሚያስችል ዘመናዊ የመዋዕለ ህፃናት ግንባታ መሠረት ድንጋይ አኖሯል።
በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ኢንስቲትዩቱ ከግንባታው ባሻገር ለአንድ ሺህ ተማሪዎች የሚሆን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ለሆሳዕና ከተማ ከንቲባ ለአቶ ሳሙኤል ሽጉጤ እና ለትምህርት ጽሕፈት ቤት ሃላፊው አስረክቧል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሀገራዊ አንድነትን እንደሚያጠናክር ገልጸው፣ ደረጃውን የጠበቀ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የትምህርት ቁሳቁስ የሚሟላለት ይህ መዋዕለ ህፃናት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ ለአገልግሎት እንዲበቃ አስፈላጊው ክትትል እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።
የሆሳዕና ከተማ ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሽጉጤ እና የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች ለተከናወኑት የልማትና የበጎ አድራጎት ሥራዎች ለኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ሠራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ለ Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) ሚዲያና ኮሙኒኬሽን
ያፌት ገ/ህይወት
ከሀዲያ ዞን ፤ ሆሳዕና

7 days ago
ኢትዮጵያ ሆይ ! - ስደተኛው ልጅሽ ከ27 ዓመታት በኋላ መጥቷል! - ደስ ይበልሽ!"
· አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ፦ የሰዎች ህመም የሚሰማቸው፣ ተስፋን በተግባር የሚተረጉሙት ስራ ፈጣሪ
“Life’s most persistent and urgent question is, 'What are you doing for others?'”
(የህይወት ዘወተር እና አጣዳፊው ጥያቄ፦ ‘ለሌሎች ሰዎች ምን እያደረግክ ነው?’ የሚለው ነው።)
— ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር
በማህበረሰብ ውስጥ የሚታዩ ክፍተቶችን አይቶ ከመቆጨት ይልቅ የመፍትሔ አካል ለመሆን መነሳት የትልልቅ ሰዎች መለያ ባህሪይ ነው። በትውልደ ኢትዮጵያዊው ስራ ፈጣሪ አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ ዘንድም የሚታየው ይህ ህያው እውነት ነው፤ ጥበብን፣ የበጎ አድራጎት መንፈስን እና ዘመናዊ የህክምና አገልግሎትን በማስተሳሰር በሀገራችን ልዩ የለውጥ አሻራ በማስቀመጥ ላይ ይገኛሉ።
የተድላ አምቡላንስ መወለድ፦
የህይወት አድን አገልግሎት ራዕይ
አቶ ሳሚ ካህሳይ በሀገራችን በህክምና ትራንስፖርት ዘርፍ ያለውን ትልቅ ክፍተት በጥናት በመረዳት ነው "ተድላ አምቡላንስን" ወደ ስራ ያስገቡት። በተለይም አካል ጉዳተኞች፣ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት (ኦቲዝም) ያለባቸው፣ የዳያሊሲስ ህመምተኞች እና አረጋውያን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚያጋጥማቸውን የእንቅስቃሴ እና የትራንስፖርት እንግልት በመመልከት፣ ደረጃውን የጠበቀና ዘመናዊ የድንገተኛ እና ድንገተኛ ያልሆነ የህክምና መጓጓዣ አገልግሎት እንዲመሰረት አድርገዋል።
ድርጅቱ ከንግድ ስራ በላይ የማህበረሰብ አለኝታነትን መርሁ በማድረግ፦
· ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን ያቀረበ፣
· በገንዘብም ሆነ በአገልግሎት ደረጃ አቅም የሌላቸውን ለመደገፍ የተጋ፣
· ለሁሉ አቀፍ ተደራሽነትና ለዜጎች ክብር የቆመ ተቋም ሆኖ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።
“The best way to find yourself is to lose yourself in the service of others.”
(ራስህን ለማግኘት የሚቻለው የተሻለው መንገድ በሌሎች አገልግሎት ውስጥ ራስህን ስትሰጥ ነው።)
— ማሃትማ ጋንዲ
“ማንም የላት”፦
ጥበብ ለሰብአዊነት እና ለማህበራዊ ንቅናቄ
አቶ ሳሚ ከስራ ፈጣሪነታቸው ባሻገር፣ ጥበብ ለማህበራዊ ለውጥ ያላትን ትልቅ ሀይል በመረዳት ከ1.2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ “ማንም የላት” የተሰኘውን ታሪካዊ የኅብረት ዜማ ፕሮዲዩስ አድርገዋል።
ይህ ስራ በግጥም ናትናኤል ግርማቸው፣ በዜማ አህመድ ተሾመ (ዲንቢ)፣ በቅንብር ታምሩ አማረ (ቶሚ) እንዲሁም በዳይሬክቲንግ ነፃዓለም አብዲ የተቃኘ ሲሆን፤ ድምፃውያን ማስተዋል እያዩ፣ ሄዋን ገብረወልድ፣ ሀና ግርማ እና አብርሃም በላይነህ (ሻላዬ) ድምፃቸውን ሰጥተውበታል። ከ50 በላይ የሙያ አጋሮች የተሳተፉበት ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፣ ህብረተሰቡን ስሜታዊ ጉዳት ውስጥ ሳይከት በደማቅ ቅንብር የችግሩን አሳሳቢነትና የለውጥ አስፈላጊነት ያሳያል።
አካል ጉዳተኝነት የችግር ምንጭ ሳይሆን፣ እንደ ማህበረሰብ የፈጠርነው የመዳረሻ እና የትራንስፖርት እጥረት ዋናው ክፍተት መሆኑን ማሳወቅ ነው። “ማንም የላት” የሚለውን ስሜት “እኛ አለንላት!”በሚል አዎንታዊ ምላሽ ለመተካት ያለመ ማህበራዊ ንቅናቄ ነው።
አቶ ሳሚ ካህሳይ እና ድርጅታቸው ተድላ አምቡላንስ ቃላቸውን በተግባር በማስመስከር፤ ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ በተደረገ ስነ-ስርዓት፦የሙዚቃ ቪዲዮውን ገቢ፦ በሰይፉ ኦን ኢቢኤስ (Seifu on EBS) የዩቲዩብ ቻናል ተለቆ የሚሰበሰበው ሙሉ ገቢ ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማዕከል እንዲሆን አስረክበው ነበር።
በርካታ ዊልቸሮች፣ ዘይት፣ ላርጎ እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለመቄዶንያ መስራች ለዶ/ር ቢንያም በለጠ በአካል አስረክበዋል።
ተድላ አምቡላንስ ለማንኛውም ሰዓት ለመቄዶንያ ማዕከል ነፃ የአምቡላንስ አገልግሎት ለመስጠት በይፋ ቃል ገብተዋል።
የአቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ ህልም በዋና ከተማው አዲስ አበባ ብቻ የተገደበ አይደለም። በክልሎች፣ በገጠራማ አካባቢዎች እና ክፍለ ሀገራት የሚኖሩ፣ አማራጭ ያጡ ዜጎች ዘንድ ይሄው ዘመናዊና የተከበረ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲደርስ ከመንግስት እና ከተለያዩ አካላት ጋር በትስስር ለመስራት አቅደዋል።
“No one has ever become poor by giving.”
(መስጠት ማንም ሰው ደሃ አያደርግም።)
— አን ፍራንክ
አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ በስራ ፈጠራቸው ሀገራዊ ክፍተትን የደፈኑ፣ በጥበብ ስራቸው የማህበረሰብ ህሊናን ያነቁ፣ በበጎ አድራጎታቸው ደግሞ የብዙዎችን እምባ ያበሱ የዘመናችን አርአያ ናቸው።
ተድላ አምቡላንስ “ሕይወትን ለማስቀጠል እየመጣን ነው!” በሚለው መሪ ቃሉ፣ የብዙዎችን ህይወት የመታደግ እና ተስፋ የመንዛት ታላቅ ሀገራዊ አገልግሎቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።
መደምደሚያ
አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ ከ 27 ዓመታት ሰድት በኋላ አገር ቤት መጥተዋል። የእናት ሀገር ኢትዮጵያ ጥሪ ተቀብለው "እናቴ፤ ኢትዮጵያ ሆይ ! - ስደተኛው ልጅሽ ከ27 ዓመታት በኋላ መጥቷል! - ደስ ይበልሽ!"
የሀገር ጥሪን የመለሰ የዲያስፖራ ተሳትፎ፦ ህልምን በሀገር ላይ መተርጎም እንደነሳሚ ነው።
“Ask not what your country can do for you — ask what you can do for your country.”*
(ሀገሬ ምን አደረገችልኝ ሳይሆን፣ እኔ ለሀገሬ ምን አደረግሁ ብለህ ጠይቅ።)
— ጆን ኤፍ. ኬኔዲ
አቶ ሳሚ ካህሳይ በምዕራቡ ዓለም (በአሜሪካ) ያካበቱትን የሙያ ልምድ፣ እውቀትና ሀብት ይዘው ወደ ሀገራቸው በመመለስ በህክምናና በትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩት በምክንያት ነው። መንግስትና የሀገር ጥሪ ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ያቀረቡትን ጥሪ መሰረት በማድረግ፣ በውጭ ሀገር ያዩትን ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥና ህልማቸውን በሀገራቸው ምድር ላይ ተግባራዊ አድርገዋል።
ይህ እርምጃቸው ክፍተቶችን በመሙላት ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከተ ሲሆን፤ ሌሎች በውጭ ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንም በየተሰማሩበት የሙያ ዘርፍ መጥተው ሀገራቸውንና ህዝባቸውን እንዲያገለግሉ ትልቅ ማነቃቂያና መንገድ ጠራጊ አርአያ የሚሆን ነው።
እናንት ያገሬ ልጆች
ግልጽነት ለዘላለም ይኑር!
መሥራት ጀግንነት ነው፤ ማድነቅ ደግሞ ጀግንነት ነው!
ለሥራቸው፤ ለሰበአዊነታቸው እጅ እንነሳለን!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
"ሕይወትን ማዳን፤ የመጀመሪያ ቅድሚያችን!"
– ተድላ አንቡላንስ
📞 ለአስቸኳይ ጥሪዎች 24 ሰዓት፣ 7 ቀናት ዝግጁ
☎️ +251 985 585 888
📞 8558
የማኅበራዊ ሚዲያ ሊንኮች ናቸው - ይከተሉን፦
Facebook: fb.com/Tedlaambulance
Instagram: instagram.com/tedlaambulance
Telegram: t.me/tedlaambulanceservice
TikTok: tiktok.com/tedlaambulance

መልካም የእረፍት ቀን!
የተቸገሩትን ለመደገፍና የበጎ አድራጎት ማኅበራትን ለማገዝ የደግነት እጅዎን መዘርጋት አሁን በሞባይልዎ ቀላል ሆኗል።
የቴሌብር መተግበሪያዎን በመክፈት የበጎ አድራጎት መድረኩን ይጎብኙ፤ በጥቂት ቅጽበቶች በልበ ሙሉነት ይላኩ፤ የብዙዎችን ሕይወት በጋራ እንቀይር!
ቴሌብር ሱፐርአፕን
https://bit.ly/telebirr_Su... ጭነን ስንደጋገፍ እንዲህ ነን!
#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን #ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን #ስንጭን_እንዲህ_ነን #ስናስጀምር_እንዲህ_ነን

10 days ago
ይድረስ ለአራቱ ድምፃውያን
– “ማንም የላት” ከተሰኘው የኅብረት ዜማ ጋር በተያያዘ
ከተመስገን ኡካሬ (የሐጌ ልጅ)
#ethiopia | "ማንም የላት" የተሰኘው የኅብረት ዜማ ሙዚቃ ብቻ አይደለም፤ የህሊና ጥሪ፣ የማህበራዊ ኃላፊነት ማንቂያ እና የሰብአዊነት መልዕክት ነው። ይህ ስራ የአካል ጉዳተኞችንና የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያላቸውን ወገኖች በርኅራኄ ከመመልከት ይልቅ፣ እንደ ሙሉ መብት ባለቤቶች እንድናያቸው ያስጠይቃል።
ሙዚቃው የሚያነሳው ዋና ጥያቄ አካል ጉዳተኝነት ሳይሆን፣ እኛ እንደ ማህበረሰብ የፈጠርነው የመዳረሻ እጥረት ነው። ትራንስፖርት፣ ትምህርት፣ ስራ፣ የህዝብ አገልግሎቶች እና ማህበራዊ ተሳትፎ ለሁሉም እኩል ተደራሽ ናቸው ወይ? የሚለውን ጥያቄ በጥልቅ ያቀርባል።
የኅብረት ዜማዎች ሁልጊዜም የዘመናቸውን ማህበራዊ ጉዳይ ያንጸባርቃሉ። "ማለባበስ ይቅር"፣ "ስደት"፣ "ሰላም ለሀገራችን" እና ሌሎችም እንደ ነበሩት ሁሉ፣ "ማንም የላት" ደግሞ የዚህ ዘመን የህሊና ጥሪ ሆኖ ተገኝቷል።
ይህ ስራ በስሜት ብቻ የተሞላ አይደለም፤ መፍትሄ የሚፈልግ ጥያቄ ያቀርባል። "ማንም የላት" የሚለውን አባባል "እኛም አለን" በሚል ተግባራዊ መልስ እንድንተካው ይጋብዘናል።
በዚህ ዜማ ላይ የተሳተፉት ድምፃዊ ማስተዋል እያዩ፣ ድምፃዊት ሀና ግርማ፣ ድምፃዊ አብርሃም በላይነህ (ሻላዬ) እና ድምፃዊት ሄዋን ገብረወልድ እያንዳንዳቸው መልዕክቱን በሚመጥን ስሜት አቅርበዋል።
ግጥሙን ናትናኤል ግርማቸው፣ ዜማውን አህመድ ተሾመ (ዲንቢ)፣ ቅንብሩን ደግሞ ታምሩ አማረ (ቶሚ) በሙያዊ ብቃት አስውበውታል። የግጥሙ፣ የዜማው፣ የድምፅ አቀራረቡና የቅንብሩ መዋሃድ ሙዚቃውን ከመዝናኛነት በላይ ወደ ማህበራዊ ንቅናቄ አሳድጎታል።
ይህ ዜማ የሚያስታውሰን አንድ እውነት አለ፤ ሰብአዊነት በቃላት ሳይሆን በተግባር ይለካል። አካል ጉዳተኞች ርኅራኄ አይፈልጉም፤ እኩል ዕድል፣ ተደራሽነትና ክብር ይፈልጋሉ።
ይድረስ ለአራቱ ድምፃውያን፤ ለህዝብ የሚያስብ፣ ህሊናን የሚያነቃ እና ማህበረሰብን ወደ በጎ ለውጥ የሚጋብዝ ስራ ስላቀረባችሁ ምስጋና ይገባችኋል። ይህ ዜማ በሙዚቃ ታሪክ ውስጥ እንደ ዜማ ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ማህበራዊ ጥሪ የሚታወስ ስራ ይሆናል።
አቶ ሳሚ ተድላ ( የተድላ አምቡላንስ መሥራችና ባለቤት ) "ማንም የላት" የተሰኘው የኅብረት ዜማ ፕሮውዲሰር ምስጋና ይገባቸዋል።
በተለይም ጥበብንና በጎ አድራጎትን አጣምሮ በመያዝ፣ አቅም የሌላቸውንና ረዳት ያጡ ወገኖችን ድምፅ ለማሰማት ያደረጉት ጥረትና ያወጡት ወጪ የሚወደስ ነው።
በተጨማሪም በተድላ አምቡላንስ በኩል የሚያደርጉት ድገስ የሕክምና አገልግሎትና የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ፣ በኅብረተሰቡ ዘንድ ትልቅ አክብሮትና ምስጋና የሚያሰጣቸው ያደርጋቸዋል። እንደዚህ ያሉ በጎ አድራጊ ባለሃብቶችና ድርጅቶች ለሌላውም አርአያ የሚሆኑ ናቸው።

“አደይ አዲስ ዓመት ታላቅ የንግድ ኤክስፖ እና ፌስቲቫል” ይፋ ሆነ
#fastmereja I የ2019 አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ በአዲስ ኮንቬንሽን ሴንተር ሊካሄድ የታቀደው “አደይ አዲስ ዓመት ታላቅ የንግድ ኤክስፖ እና ፌስቲቫል” ይፋ ተደርጓል። ኤክስፖው ከነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 05 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለ15 ቀናት እንደሚቆይ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
ይህ ታላቅ የንግድ እና የፌስቲቫል መድረክ በማስተር ፒስ ትሬዲንግ እና ራይት ኤቨንትስ ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን፣ አዘጋጆቹ ለሚዲያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት ዝግጅቱ ለስሚት እና ለአካባቢው ነዋሪዎች የገበያ አማራጮችን በቅርበት የሚያቀርብ ነው። በኤክስፖው ላይ ከ200 በላይ የሀገር ውስጥ አምራቾች፣ አስመጪዎች፣ የዕደ-ጥበብ ባለሙያዎች እና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ምርትና አገልግሎታቸውን በተፎካካሪ እና በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚያቀርቡ ተገልጿል።
ከንግድ እንቅስቃሴው ጎን ለጎን ፌስቲቫሉ በየቀኑ 15 አርቲስቶች የሚሳተፉበት የቀጥታ የሙዚቃ ኮንሰርት፣ የፋሽን ሾው፣ የህፃናት መጫወቻዎች እና የበጎ አድራጎት ስራዎችን ያካተተ እንደሚሆን ተጠቅሷል። በተጨማሪም የኪነ-ጥበብ መድረኮችን ጨምሮ የመጽሐፍት አውደ ርዕይ እና ሽያጭ ይካሄዳል።
በ15 ቀናቱ የፌስቲቫል ቆይታ ከ80,000 በላይ ጎብኚዎች እና ደንበኞች ይገበያያሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ አዘጋጆቹ ቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናቀው የኤግዚቢሽን ቦታዎችን በመሸጥ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
#ኹነት

Sponsored by
Surafel
12 days ago
ዳንጎቴ የሀብታቸው ሲሶ ለድሆች ሊሰጡ ነው
#ethiopia | የአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለሀብት የሆኑት ናይጄሪያዊው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ ከሀብታቸው አንድ ሶስተኛውን ለበጎ አድራጎት ስራዎች ለማዋል ማቀዳቸውን ይፋ አደረጉ።
የቢሊየነሩ ልጅ ሀሊማ ዳንጎቴ ለብሉምበርግ (Bloomberg) በሰጡት ቃለ ምልልስ እንደገረጹት መላው የዳንጎቴ ቤተሰብ በዚህ ውሳኔ ላይ ሙሉ ድጋፋቸውን መስጠታቸውን ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት የዳንጎቴ ሀብት ከ35 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚገመት የሚነገር ሲሆን 33 በመቶው ለበጎ አድራጎት ሲውል ከ11 እስከ 12 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ይሆናል።
ይህም በአፍሪካ ታሪክ በግል ባለሀብት ከተደረጉ ትላልቅ የበጎ አድራጎት ስጦታዎች አንዱ ያደርገዋል ነው የተባለው።
ስጦታው በዋናነት በጤና፣ በትምህርት፣ በምግብ ዋስትና እና በሰብአዊ እርዳታዎች ላይ ያተኮሩ የረጅም ጊዜ ፕሮጀክቶችን ለመተግበር ይውላል ነው የተባለው።
ይህ ውሳኔ ይፋ የሆነው ዳንጎቴ የንግድ አቅማቸውን ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ በሚሰሩበት እና ለልጆቻቸው የኃላፊነት ሽግግር እያደረጉ ባሉበት ወቅት ነው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #nigeria #alekodangote #donation

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተሳታፊዎች ቁጥር ወደ 60 ሺህ አደገ
**********************
26ኛው ባንክ ኦፍ አሜሪካ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ የምዝገባ መርሐ ግብር "ሩጫዬ ቀለሜ" በሚል መሪ ቃል ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።
ከ"ባንክ ኦፍ አሜሪካ" ጋር በተደረገው አጋርነት፤ አዲስ ምዕራፍ የከፈተው የዘንድሮው ውድድር፣ ከ60 ሺህ በላይ ተሳታፊዎችን ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል።
በይፋዊ የማስጀመር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) እንደገለፁት፣ ታላቁ ሩጫ ከስፖርታዊ ውድድርነቱ ባሻገር የኢትዮጵያን እምቅ የቱሪዝም ሀብት ለዓለም የሚያስተዋውቅና ለዘርፉ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ትልቅ መድረክ በመሆኑ መላው ህዝብ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ መኪዮ ሙሐመድ በበኩላቸው፣ ታላቁ ሩጫ ባለፉት 26 ዓመታት ከውድድር አዘጋጅነት ወደ ጠንካራ ተቋምነት በመሸጋገር ዓለም አቀፍ ብራንድ መሆን መቻሉን ገልፀዋል።
አክለውም ውድድሩ ስፖርትን የዕለት ተዕለት ባህል ለማድረግና የሀገርን ገፅታ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ትልቅ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መስራች ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ፣ ባንክ ኦፍ አሜሪካን የመሰለ ግዙፍ ተቋምን ከውድድሩ ጎን ማሰለፍ መቻሉ ትልቅ ስኬት መሆኑን ጠቁሞ፣ ዋና ዓላማው ታላቁ ሩጫን ከዓለም ቀዳሚ ከሆኑ ውድድሮች ጋር ማስጠራት እንደሆነ ገልጿል።
አትሌት ኃይሌ አክሎም ከዚህ በኋላ የሚደረጉ ውድድሮች በሙሉ ሰዓታቸው የሚመዘገብ በመሆኑ ተሳታፊዎች ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ በበኩሏ፣ ውድድሩ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ሀገራዊ ሀብት መሆኑን ጠቁማ፣ ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመሆን ውድድሩን በዓለም ደረጃ ቁጥር አንድ የማድረግ ህልም ተይዞ እየተሰራ ይገኛል ብላለች።
ጎን ለጎንም የበጎ አድራጎት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነው ዳግማዊት የገለጸችው።
በአዲስ የሺዋስ
#ethiopianbroadcastingcorporation #ታላቁሩጫበኢትዮጵያ #greatethiopianrun #ቱሪዝም

13 days ago
''I Love You''
የነጻ ምሳ የሚበላበት ሬስቶራንት
#ethiopia |የሆሊውዱ ኮከከብ የዊል ስሚዝ ሁለተኛ ልጅ ድምጻዊና ተዋናይ ጄደን ስሚዝ የራሱን ገቢ ማሳደጊያ የሚሆን ውድ የከበርቴዎች ምግብ ቤት ከመክፈት ይልቅ ቤት አልባዎች በነፃ የሚመገቡበት የበጎ አድራጎት ድርጅት በመስረት ለጎዳና ተዳዳሪዎች አርአያነት ያለው ደግነት እያሳየ ይገኛል።
እ.ኤ.አ. በ2019 "አይ ላቭ ዩ" (I Love You) በሚል ስያሜ በተንቀሳቃሽ የምግብ መኪና የተጀመረው ይህ ጥረት በሎስ አንጀለስ በሚገኘው 'ስኪድ ሮው' ለሚኖሩ ቤት አልባዎች ነፃ የእፅዋት ተወፅኦ ምግቦችን በማቅረብ ስራውን ጀምሯል።
ይህ በጎ አድራጎት በአሁኑ ወቅት አቅሙን በማሳደግ ትኩስ ምግቦችን፣ የታሸጉ ውሃዎችንና የተለገሱ አልባሳትን ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚያቀርብ ተቋም ሆኗል።
በአንዳንድ አጋጣሚዎች በአንድ መርሃ-ግብር ብቻ እስከ 500 የሚደርሱ ነፃ ምግቦችን የሚያከፋፍለው ይህ ድርጅት በቀጣይም በዚሁ አካባቢ ቋሚ ህንፃ በመገንባት በየቀኑ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት በነፃ ለማቅረብ እንዲሁም የስራ እድልና አዎንታዊ የማህበረሰብ መኖሪያ ቦታ ለመፍጠር አልሞ እየሰራ ይገኛል።
የዚህ ወደፊት የሚገነባው ምግብ ቤት አሰራር አቅም የሌላቸው ወገኖች በነፃ እንዲመገቡ የሚያደርግ ሲሆን የገንዘብ አቅም ያላቸው ደንበኞች ደግሞ የሌሎችን ምግብ የሚሸፍን ክፍያ እንዲከፍሉ በሚያስችል የመረዳዳት መርህ ላይ የተመሰረተ እንቅስቃሴ ያደርጋል።
ጄደን ስሚዝ ይህንን ተቋም "አይ ላቭ ዩ" ብሎ የሰየመበት ዋና ምክንያት ''ፍቅር በቃል የሚነገር መፈክር ብቻ ሳይሆን በተግባር የሌላውን ሰው ረሃብ በማስወገድ የሚገለጽ እውነተኛ ሰብአዊነት በመሆኑ ነው'' ብሏል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

15 days ago
በሰው ህይወት ማዳን የሚለካው ደም ልገሳ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የክረምቱ ወራት ወጣቶችና ተማሪዎች እንዲሁም የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች እረፍት ላይ የሚገኙበት ወቅት በመሆኑ በርካታ ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ የበጎ አድራጎት ስራዎች ይከናወናሉ፡፡
ከዚህም መካከል በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ በመሰማራት የሰው ህይወትን ለመታደግ የሚያስችለው የደም ልገሳ ነው፡፡ ደም ልገሳ በበጎ ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ለሰዎች የመድረስ እና የመደጋገፍ ሂደት ነው፡፡
በጤና ተቋማት ለበርካታ ጊዜያት የደም እጥረት እያጋጠመው እንደሆነ ይናገራል፤ በመሆኑም በማንኛውም ሰዓት በመሄድ ከሚለገሰው በተጨማሪ ማህበረሰቡን ለማነቃቃት የሚጠቅሙ የደም ልገሳ መርሀ ግብሮችን ያዘጋጃል፡፡
ቀደም ባሉት ጊዜያት ሰዎች ደም መለገስን ከእምነት ጋር የሚጋጭ ነገር አድርገው በማሰብ፣ ራሳቸውን ከሂደቱ ያገልሉ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን የተለያዩ ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች በመሰራታቸው የበጎ ፈቃድ ደም ለጋሾች መጠን እያደገ መጥቷል፡፡
የሰው ልጅ ተፈጥሮው ደግነት እንደሆነ ይታመናል፤ ተጋግዞና ተደግፎ በጋራ በመቆም ሀገር መገንባትን ይዞ የሚነሳው የመደመር ፍልስፍና መከፋፈልና በጋራ አለመቆም ለሀገር እንደማይበጅ በማስቀመጥ የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህል ማዳበር እንዳለብን ይጠቁማል፡፡
ሰዎች በአካባቢው ባለ ማህበረሰብ ይቀረፃሉ፣ ለነገሮች ያለንን እይታ፣ በጎ ነገር ማድረግን ለማህበረሰብ መቆምን ከምንኖርበት አካባቢ እንማራለን። ኢትዮጵያውያን ባህላችንና የአኗኗር ስርአታችን አብሮነትን የተደገፈ ነው፡፡
የመተጋገዝ፣ የመረዳዳት ብሎም ችግሮችን በጋራ የመፍታት ልምዱ አለን።
አባቶቻችን እንዳሳዩን የኢኮኖሚ ችግሮችን ተሰብስቦ እቁብ በመጣል፣ የሀዘንና የደስታ ጊዜዎችን በምንኖርበት አካባቢ ዕድርና ማህበር በመመስረት መረዳዳትን ባህል አድርገን ዘልቀናል፡፡
ዛሬም የተለመደው የመተጋገዝ ባህላችንን መሰረት አድርገን ደም ስንለግስ ለታመመ ለመድረስ፣ በወሊድ ጊዜ ደም የሚፈሳቸው እናቶችን እንዲሁም ሌሎች በደም እጥረት የተነሳ ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎችን ለመታደግ እንደሆነ በማመን ነው፡፡
ባለፉት ዓመታት የመደመር መንግሥት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተቋማዊ ቁመና ይዞ በጋ ከክረምት እንዲተገበር እያደረገ ሲሆን፤ በመላ ሀገሪቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች ተሳትፎ ያደርጋሉ።
በዚህም በቢሊየን ብሮች የሚገመቱ አገልግሎቶች ለህብረተሰቡ ይሰጣል።
ከአገልግሎቶቹ መካከል በገንዘብ ሳይሆን በሰው ህይወት ማዳን የሚገመተው የደም ልገሳ ዋናው ተግባር ነው።
በቤተልሔም ግርማ

የበጎነት ዋጋ በቢሊዮኖች ሲሰላ፡ ያልተነካው የሀገር ውስጥ አቅም
*****************
(የዕለቱ መልዕክት)
ያለአንዳች ደመወዝ የሚሰራ፣ ነዳጅ የማይጠይቅ፣ ነገር ግን በቢሊዮኖች የሚቆጠር ሀብት በማዳን የሀገርን ሸክም የሚያቀል ግዙፍ የኢኮኖሚ ሞተር አለ ብንልዎስ? ይህ ከርህራሄና ከሰብዓዊነት ካባ ጀርባ የማክሮ ኢኮኖሚውን መዋቅር በፀጥታ እያንቀሳቀሰ የሚገኘው ‘የበጎ ፈቃድ አገልግሎት’ እውነተኛ ገፅታ ነው፡፡
የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ስናስብ፣ አእምሯችን ቀድሞ የሚስለው የበጎ አድራጎትን ሰብዓዊነት ቢሆንም በዘመናዊ የምጣኔ ሀብት እሳቤ ግን ይህ ዘርፍ በቀጥታ በሀገር ጠቅላላ ምርት (GDP) ውስጥ ያልተካተተ ግዙፍ "የህዝብ ካፒታል" ነው።
የዓለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት (ILO) እና የተባበሩት መንግስታት ሪፖርቶች እንደሚያረጋግጡት የበጎ ፈቃድ ዘርፍ መንግስታት ሊያወጡት የሚችሉትን በጀት የሚተካ እና በመንግስትና በግሉ ዘርፍ መካከል ያለውን ክፍተት የሚሞላ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ሞተር ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ ለዚህ ጥልቅ እሳቤ ባዳ አይደለችም፤ ማህበረሰባችንን ለዘመናት አስተሳስረው ያቆዩት እንደ ደቦ፣ እድር እና እቁብ ያሉ ሀገር በቀል የትብብር ተቋማት የዚሁ ማህበራዊ ካፒታል መገለጫዎች ናቸው።
ኖርጂያን ‘ዱግናድ’ በሚሉት የትብብር ባህላቸው እንዲሁም አሜሪካና ካናዳ በቢሊዮን ዶላሮች በሚገመት የዜጎቻቸው ነፃ አገልግሎት የፈጠሩትን የኢኮኖሚ አቅም፣ እኛም ዛሬ በራሳችን ዐውድ እና ጥበብ በተግባር እያሳየነው እንገኛለን።
በተለይም ከ2010 ዓ.ም ወዲህ "የመደመር ትውልድ" በሚለው ሀገራዊ እሳቤ አማካኝነት ይህ ዘርፍ መሰረታዊ እና መዋቅራዊ ለውጥን አስተናግዷል።
ያለፈውን ስብራት የመጠገን፣ ያለውን የማፅናት እና የነገውን አቅም የመገንባት ጥልቅ ትልም በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ውስጥ በተግባር ሲተረጎም በመንግስት አቅም ብቻ ሊሸፈን የማይችለውን ግዙፍ የልማት ክፍተት በመድፈን ተጨባጭ ማክሮ-ኢኮኖሚያዊ ትርጉም አምጥቷል።
በየዓመቱ በአማካይ ከ20 እስከ 25 ሚሊዮን ዜጎች በሚሳተፉበት በዚህ ሀገራዊ ንቅናቄ የተገኙት ውጤቶች በገንዘብ ሲተመኑ ሀገርን የታደጉበት መጠን እጅግ አስገራሚ ነው። ለአብነት ያህል በክረምት ወራት በተከናወኑ የአቅመ ደካማ ቤቶች እድሳት ስራዎች ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የመንግስት የኮንስትራክሽን እና የማህበራዊ ዋስትና በጀት መታደግ ተችሏል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በተተገበረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች በዜጎች ነፃ ጉልበት በመትከልና በመንከባከብ በዋጋ ሊተመን የማይችል ግዙፍ ሀብት ተፈጥሯል።
ይህ መነቃቃት በጤናውና በትምህርት ዘርፉም ደማቅ አሻራ አሳርፏል፤ በየዓመቱ ከ300 ሺህ ዩኒት በላይ ደም በመለገስ የህክምና ግብዓት ወጪን ከማዳንም ባሻገር የበርካታ ዜጎች ህይወት የታደገ ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደብተሮች፣ የማጠናከሪያ ትምህርቶች እና የቁሳቁስ ድጋፎች ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦችን ጫና በእጅጉ አቅልለዋል።
የዚህ ሁሉ ሀገራዊ ጥረት ትልቁ ድል፣ የበጎ ፈቃድ ስራ ከ"ክረምት የዘመቻ ስራነት" ተላቆ ዓመቱን ሙሉ የሚተገበር ተቋማዊ ባህል እና የኑሮ ዘይቤ መሆኑ ነው። ይህ ወደ ዘላቂነት የተደረገ ሽግግር ወጣቶች ቋሚ የስራ ልምድ፣ የጊዜ አጠቃቀም እና የአመራር ክህሎት እንዲያገኙ በማድረግ ለስራ ገበያው ብቁ እያደረጋቸው ይገኛል።
ይህ ሂደት በተዘዋዋሪ የስራ አጥነትን ጫና ከማቃለሉም ባሻገር፣ አምራች ኢንዱስትሪዎች እና ተቋማት የሰለጠነ እና ስነ-ምግባር ያለው የሰው ኃይል በቀላሉ እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል። ከሚያመነጨው ቁሳዊ ትርፍ በዘለለም፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተለያየ ዳራ፣ ባህል እና እምነት ያላቸውን ዜጎች በአንድ የጋራ ዓላማ በማሰባሰብ "የእኔ" ከሚለው ጠባብ አስተሳሰብ ወደ "የእኛ" ሰፊ ሀገራዊ ማንነት እያሸጋገራቸው ይገኛል።
በዚህ የበጎነት መድረክ አዛውንቶች የህይወት ተሞክሯቸውን ሲያካፍሉ ወጣቱ ደግሞ ጉልበቱንና የዘመኑን እውቀት ይለግሳል፤ ይህ ውብ የትውልድ ቅብብሎሽ ማህበረሰባዊ መተማመንን በማሳደግ በፍትህና ፀጥታ ተቋማት ላይ ያለውን ጫና በእጅጉ ይቀንሳል።
ጠንካራ መተማመን እና ትስስር ያለው ማህበረሰብ ደግሞ ተፈጥሯዊም ሆነ ሰው ሰራሽ ቀውሶችን በጋራ የመቋቋም አቅሙ እጅግ የላቀ ነው።
የኢኮኖሚ እድገት ትክክለኛ ትርጉም እና ጣዕም የሚኖረውም የተሳሰረ እና አንዱ ለአንዱ የሚቆረቆር ጠንካራ ማህበረሰብ ሲኖር ነው። በገንዘብ ሲተመን በቢሊዮኖች የሚገመት ሀብት የፈጠረውን ይህን ግዙፍ ሀገራዊ ካፒታል ይበልጥ ለማሳደግ እና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ ዘመኑ በሚጠይቀው የቴክኖሎጂ ስርአት መደገፍ የግድ ይላል።
በመሆኑም የሚመለከታቸው አካላት የምዝገባ እና የዕውቅና አሰጣጥ ስርአቱን በማዘመን፣ ይህ ያልተነካ የህዝብ ካፒታል በማክሮ ኢኮኖሚ እቅድ ውስጥ እንደ አንድ ራሱን የቻለ የሀብት ምንጭ ተደርጎ በይፋ ሊሰላ እና የበለጠ ሀገራዊ ትኩረት ሊያገኝ ይገባል
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

23 days ago
ከሊዮኔል ሜሲ ጋር በፎቶ የተነሳው ህጻን ላሚን ያማል መሆኑ ዩኒሴፍ የእውነተኝነቱን ምስክርነት ሰጠ
#fastmereja I በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ሲዘዋወር የነበረውና ታዋቂው የእግር ኳስ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ አንድን ህጻን ሲያጥብ የሚያሳየው ፎቶግራፍ እውነተኛ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ይፋዊ መግለጫ ሰጥቷል። በፎቶው ላይ የሚታየው ህጻን የስፔኑ ወጣት ኮከብ ላሚን ያማል መሆኑ ተረጋግጧል።
ይህ ታሪካዊ ፎቶግራፍ የተነሳው ከ18 ዓመታት በፊት በዩኒሴፍ (UNICEF) የገቢ ማሰባሰቢያ የበጎ አድራጎት ፕሮግራም ላይ እንደነበር ተገልጿል። በወቅቱ ገና ህጻን የነበረው ላሚን ያማል ከእናቱ ሺላ ጋር በመሆን ከሊዮኔል ሜሲ ጋር እንዲገናኝ የተደረገ ሲሆን፣ ፎቶግራፉን ያነሳው ታዋቂው ጆአን ሞንፎርት (Joan Monfort) መሆኑ ታውቋል።
ዩኒሴፍ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ ሁለቱ የእግር ኳስ ኮከቦች በአሁኑ ወቅት በሜዳ ላይ ከሚያሳዩት ድንቅ ብቃት ባሻገር፣ ከሜዳ ውጪም የዩኒሴፍ የበጎ ፈቃድ አምባሳደሮች በመሆን በመላው ዓለም ለሚገኙ ህጻናት መብትና ደህንነት በጋራ እየሰሩ እንደሚገኝ በኩራት ገልጿል።
በአሁኑ ወቅት ሁለቱ ተጫዋቾች በዓለም ዋንጫ ፍጻሜ እሁድ ይፋለማሉ።

24 days ago
"በሚሊዮን አንድ ጊዜ የሚከሰት ታሪክ!"
*********
ሊዮኔል ሜሲ እና ላሚን ያማል በ2026ቱ የፊፋ ዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ሜዳ ላይ ለመገናኘት ተዘጋጅተዋል።
ነገር ግን በመካከላቸው ያለው አስገራሚ ግንኙነት የተጀመረው ከሁለት አስርት ዓመታት ገደማ በፊት ነበር።
እ.አ.አ. በታኅሣሥ 2007 የ20 ዓመቱ ወጣት ሊዮኔል ሜሲ ለባርሴሎና ፋውንዴሽን የበጎ አድራጎት ቀን በሚዘጋጅ የፎቶ ግራፍ መርኃ ግብር ላይ ተሳትፎ ነበር።
በወቅቱ ሜሲ አምስት ወር ከሆነው ሕፃን ላሚን ያማል ጋር አብሮ ፎቶ የተነሳ ሲሆን፣ ሕፃኑን በገንዳ ውስጥ ሲያጥበውና ሲንከባከበው የሚያሳዩት እነዚህ ምስሎች ለዩኒሴፍ እና ለሌሎች በጎ አድራጎት ድርጅቶች ገቢ ማሰባሰቢያነት ታትመው ወጥተዋል።
ይህን ታሪካዊ ምስል የቀረጸው ፎቶ ግራፍ አንሺ ጆአን ሞንፎርት በሰጠው አስተያየት፤ በወቅቱ የወደፊቱን ማንም እንዳልገመተው ተናግሯል።
በዚያን ጊዜ ሜሲ የምንግዜም ታላቁ እግር ኳስ ተጫዋች ለመሆን ገና ጉዞውን የጀመረበት ወቅት የነበረ ሲሆን፣ ያማል ደግሞ በፕሮጀክቱ ላይ ከተሳተፉት በርካታ ሕፃናት መካከል አንዱ ነበር።
ይህ ታሪካዊ ፎቶ ግራፍ የመገናኛ ብዙኃንን ትኩረት የሳበው በ2024ቱ የአውሮፓ ዋንጫ ወቅት የያማል አባት በማኅበራዊ ሚዲያ ካጋሩት በኋላ ነበር።
ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ምስሉ የሁለቱን የባርሴሎና ትውልድ ኮከቦች የሚወክል የእግር ኳስ ታሪክ ተምሳሌት ሆኗል።
ያማል በ2014 የባርሴሎናውን ላማሲያ አካዳሚን የተቀላቀለ ሲሆን፣ ፈጣን ዕድገት በማሳየት ገና በ15 ዓመቱ ለዋናው ቡድን መጫወት ችሏል።
አሁን ላይ የስፔን እግር ኳስ ትልቁ ተስፋ የሆነው ያማል፣ በባርሴሎና ቤት የሜሲን ታሪካዊ የ10 ቁጥር መለያ የሚለብስ ሲሆን በብዙዎች ዘንድም የሜሲ ተተኪ ተደርጎም ይወሰዳል።
አሁን ግን የእግር ኳስ ታሪክ አስደናቂውን ምዕራፍ ሊያሳየን ተቃርቧል።
በአንድ ወቅት በሜሲ እቅፍ ውስጥ የነበረው ያ ሕፃን፣ አሁን በትልቁ መድረክ ማለትም በዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ላይ የልጅነት አርአያውን ፊት ለፊት ለመጋፈጥ እየተዘጋጀ ይገኛል።
ፎቶግራፍ አንሺው ጆአን ሞንፎርት ይህንን ታሪክ "በሚሊዮን አንድ ጊዜ ብቻ የሚከሰት" ሲል ገልጾታል።
በእሱባለው ተሾመ
#worldcup #sports #messi #lamineyamal #ebc

25 days ago
“ኢንቲማ ሄልዝ ኬር ሲቲ ” ቢሾፍቱ ከተማ ሊገነባ ነው
#ethiopia | ለዓመታት በልብ ህክምና በጎ አድራጎት ስራ ላይ የተሰማራው “ኸርት አታክ ኢትዮጵያ”፣ የበጎ አድራጎት አገልግሎቱን ይበልጥ ዘላቂና ተደራሽ ለማድረግ “ኢንቲማ ሄልዝ ኬር ሲቲ” የተሰኘ የህክምና ማዕከል ለመገንባት በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታወቀ።
ቢሾፍቱ እየተገነባ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርፖርት አቅራቢያ በ10 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፈው ፕሮጀክት፣ ትርፍንና በጎ አድራጎትን ባጣመረ ማህበራዊ የንግድ ስራ መርህ የሚመራ ነው።
የፕሮጀክቱ መጀመር ይፋ የሆነው ድርጅቱ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ታሪካዊ ስምምነት በተፈራረመበት ወቅት ሲሆን፣ በፊርማ ስነ-ስርዓቱም ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ፣ እና የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የድርጅቱ ተባባሪ መስራችና የልብ ሀኪም የሆኑት ዶክተር ተስፋዬ ተሊላ እንደገለጹት፣ ሃርት አታክ ኢትዮጵያ እስካሁን የ660 ታካሚዎችን ህይወት መታደግ ቢችልም፣ ካለው ሰፊ የልብ ህመም ችግር አንጻር የበጎ አድራጎት ስራ ብቻ በቂ ባለመሆኑ ወደዚህ አዲስ አሠራር መሸጋገር አስፈልጓልብለዋል።
ይህ አዲስ መዋቅር አቅም ያላቸው ታካሚዎች እየከፈሉ እንዲታከሙ፣ አቅም የሌላቸው ደግሞ በነጻ የህክምና እድል እንዲያገኙ በማድረግ ዘላቂነት ያለው ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል።
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የተደረገው ስምምነት የኢትዮጵያውያንን የውጭ ሀገር የህክምና ፍሰት ከመቀነስ ባለፈ፣ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ታካሚዎችን ወደ ሀገሪቱ ለመሳብ የሚያስችል “ፍላይት ቱ ሂል” (Flight to Heal) የተሰኘ ፕሮግራም ለማስጀመር ትልቅ በር ይከፍታል። የልብ ህክምናን ጨምሮ የእናቶችና ህጻናት ጤናን፣ ካንሰርን፣ የነርቭ እና የድንገተኛ አደጋ ህክምናዎችን ያካተቱ ዘመናዊ የህክምና ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሀገር ውስጥ የሚያስገባው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፣ በሀገር ውስጥ የመድኃኒት ማምረቻን ለማስፋፋትና ባለሙያዎችን በህንድ ሀገር በልዩ ሁኔታ ለማሰልጠን አቅዷል።
በተጨማሪም በህክምና ከተማው ውስጥ የሚመሰረተው የህክምና ትምህርት ቤት ቀጣዩን የኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎች ትውልድ በራሱ አቅም ለማስተማርና ለማብቃት ታላቅ ራዕይ ሰንቆ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
ጌትነት ተመስገን
📷 ከበደ መክብብ
#ethiopia #intimahealthcity #heartattackethiopia #ethiopianairlines #medicaltourism #healthcareafrica #flighttoheal #africahealthcare

29 days ago
የዘውዲቱ ሆስፒታል በ90 ቀናት ውስጥ 17 ሺህ ለሚጠጉ ሰዎች ነጻ ህክምና ለመስጠት እቅድ መያዙን አስታወቀ
የዘውዲቱ ሆስፒታል የአስተኝቶ ህክምና ዲፓርትመንት ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ወንደሰን በላችሁ ለብስራት ሬድዮ እንደገለጹት ሆስፒታሉ በክረምት የበጎ አድራጎት መርሃ ግብር በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል።በተለያዩ ቦታዎች በመገኘትና ድንኳን በመትከል ነጻ የህክምና እና የዕይታ ልየታ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በዚህም ክብር ለአረጋውያን የበጎ አድራጎት ድርጅት ማቆያ ውስጥ በመገኘት አራት ሀኪሞች፣ ስድስት ነርሶች፣ የአይን፣ የጥርስ እና የስነ-አእምሮ ባለሙያዎችን ባካተተ ቡድን ለዜጎች ህክምና ሰጥቷል።200 ለሚሆኑ ሰዎች የዕይታ እና የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል።ከተጠቃሚዎቹ መካከል ከዚህ ቀደም የደም ግፊትና የስኳር ህመም የነበረባቸው ሰዎች የተገኙ ሲሆን እዛው ህክምናቸውን እንዲቀጥሉ ምክር ተሰጥቷቸዋል።
ዶክተር ወንደሰን አክለው እንደተናገሩት አራት ሰዎች በአይን ሞራ ግርዶሽ ፤ ሁለት ሰዎች በትራኮማ በሚመጣ የአይን ኢንፌክሽን ተጠቅተዋል።ሶስት ሰዎች ደግሞ የዕይታ ችግር ስላለባቸው መነጽር እንደሚያስፈልጋቸው ተለይተዋል። ይህ የነጻ ህክምና መርሃ ግብር ለ90 ቀናት ሲቆይ በሁለት የአረጋውያን መርጃ ድርጅቶች በቀጣይ ተመሳሳይ አገልግሎት ለመስጠት ታቅዷ ።17 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በነጻ ህክምናዉ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
Seledadotio

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በታይላንድ ባንኮክ በተካሄደው ታላቅ የውበትና የሞዴሊንግ ውድድር ላይ ሀገሯን ኢትዮጵያን ወክላ የተሳተፈችው ሞዴል ሩት ሸዋታጠቅ የ"Miss Classy Model Earth 2026" አሸናፊ በመሆን አኩሪ ስኬት አስመዝግባለች።
ይህ ስኬት ለሩት የመጀመሪያዋ አይደለም። ከዚህ ቀደም የ"Miss Popularity" አሸናፊ መሆን የቻለች ሲሆን፣ በ"Miss International Ethiopia" እና በ"Miss ውበት Ethiopia" የውበት ውድድሮች ላይም ተሳትፋ የክብር ዘውድ ለመድፋት በቅታለች።
ሩት ሸዋታጠቅ ለስኬቶቿ ሁሉ መሠረት የሆኑትን ሁለገብ ስብዕናዎቿን ስታብራራ፣ በፈጣሪ ላይ ያላት ጠንካራ እምነት፣ በታዋቂው የናዝሬት ትምህርት ቤት ያሳለፈችው የትምህርት ቆይታ፣ በልጅነቷ በጀርመን ሀገር መኖሯ፣ እንዲሁም ሁለቱም ዶክተር ከሆኑት እናት እና አባቷ ያገኘችው አስተዳደግና ድጋፍ ለዛሬ ማንነቷ መገንባት ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ለዘ-ሐበሻ ገልጻለች።
ከተሳካው የሞዴሊንግ ህይወቷ ባሻገር በትምህርቷ እጅግ አስደናቂ ውጤት ያላት ሩት፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርቷን በማዕረግ ያጠናቀቀች ሲሆን፣ በሀገር አቀፉ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ላይም ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የህግ ዲግሪ ባለቤት መሆን ችላለች። አሁን ላይም የህክምና ባለሙያ የሆነውን የአባቷን ፈለግ በመከተል በህክምና ትምህርት ዘርፍ የ"C2" ተማሪ ሆና ትምህርቷን እየተከታተለች ትገኛለች። በቆይታዋም የህክምና ተማሪዎች ማህበር ፕሬዝዳንት በመሆን በምርጫ ተሰይማ በተሳካ ሁኔታ አገልግላለች።
ከእነዚህ ሙያዎቿ በተጨማሪ በስነ-ጥበብ ዘርፍ የዘፈንና የቅኔ (ግጥም) ተሰጥኦ ያላት ሲሆን፣ በተለይም በማህበራዊ ኃላፊነት ላይ በንቃት እየተሳተፈች ትገኛለች። ሩት "Ruth Drops" የተሰኘ የበጎ አድራጎት ተቋም በመመስረት በርካታ የህክምና እና ማህበራዊ ድጋፎችን ለህብረተሰቡ እያበረከተች ሲሆን፣ ከተግባራቶቿም መካከል በተስፋ አዲስ የካንሰር ማዕከል፣ በብሔራዊ የደም ባንክ እና በተለያዩ ሆስፒታሎች የሚገኙ ህሙማንን በቁርጠኝነት መርዳቷ በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው።
እንኳን ደስ ያለሽ፣ ሩት!

1 month ago
የአፍሪካ ህጻናት ቀን "በስለ እናት" የበጎ አድራጎት ድርጅት
“ስለ እናት” የበጎ አድራጎት ድርጅት ለ1,500 ህጻናት የትምህርት ቁሳቁስ ማሰባሰብ ጀመረ!
#ethiopia | የዘንድሮው የአለም የአፍሪካ ህጻናት ቀን “በአፍሪካ ለሚገኙ ደህንነቱና ንፅህናው የተጠበቀ አካባቢ ለሁሉም ህፃናት" በሚል አህጉራዊ መሪ ቃል በአዲስ አበባ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።
“ስለ እናት” የበጎ አድራጎት ድርጅት (SECO) በዓሉን ምክንያት በማድረግ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ አቅመ-ደካማ ወላጆችን ለመደገፍና ህጻናትን ከትምህርት ማቋረጥ ለመታደግ ያለመ የ1,500 ህጻናት የክረምት የትምህርት ቁሳቁስ ማሰባሰብ ንቅናቄ በይፋ መጀመሩን አስታውቋል።
የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ አብዱ እንደገለፁት፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ማግኘት፣ ጤናማና ንጹህ አካባቢ መፍጠር እንዲሁም መሰረታዊ የንጽህና ቁሳቁሶችን ማቅረብ ችሮታ ሳይሆን የማንኛውም ህጻን መሰረታዊ ሰብአዊ መብት መሆኑን አብራርተዋል።
አሁንም በአህጉሪቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህጻናት በውሃ ወለድ በሽታዎች እየተጠቁና ሴት ህጻናት ደግሞ በቂ የንፅህና መጠበቂያ ባለመኖሩ ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እየቀሩ መሆናቸውን የጠቀሱት ዋና ስራ አስኪያጁ፣ ማህበረሰቡ፣ መንግስታዊ አካላትና አለምአቀፍ አጋሮች ለWASH (የንጹህ ውሃ እና ንፅህና) ተደራሽነት መስፋፋት በጋራ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።
ድርጅቱ አሁን ላይ በአገሪቱ ካለው የኑሮ ውድነት አንጻር በርካታ አቅመ-ደካማ ወላጆች ለልጆቻቸው መሰረታዊ የትምህርት ቁሳቁሶችን ማሟላት ብርቱ ፈተና እንደሆነባቸው ገልጿል።
ይህንን ክፍተት ለመሙላትም በመጪው አዲስ የትምህርት ዘመን የኢኮኖሚ አቅም ማነስ የትምህርት እክል ሊሆንባቸው የሚችሉ 1,500 እና ከዚያ በላይ የሚሆኑ ህጻናትን በደብተር፣ በቦርሳና በሌሎች የትምህርት ቁሳቁሶች ለመደገፍ ዘመቻ መጀመሩን አስታውቆ፣ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ በጎ አድራጊዎች በቁሳቁስም ሆነ በገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቋል።
በሌላ በኩል ድርጅቱ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት ሩብ ክፍለ ዘመን (25 ዓመታት) በህጻናት ጥበቃ፣ በቤተሰብ መልሶ ማቋቋም እንዲሁም በሴት የቤት መሪዎች ኢኮኖሚያዊ አቅም ማጎልበት ረገድ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ገልጿል።
በመጪው ነሐሴ ወር የሚከበረውን የ25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓልን አስመልክቶ የድርጅቱን የህጻናት መቀበል አቅም በብዙ እጥፍ የሚያሳድግ የአዲስ ህንጻ ግንባታ የማስጀመሪያ መርሃ ግብርም አብሮ እንደሚከናወን ተገልጿል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #ስለእናትየበጎአድራጎትድርጅት

በኦሮሚያ ክልል በባለፈው ዓመት የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ከወጪ ማዳን ተችሏል
******************
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ የ2018/19 ክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ ግብር በይፋ ተጀምሯል።
መርሐ ግብሩን ያስጀመሩት የክልሉ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ሳዳት ነሻ ናቸው፡፡
አቶ ሳዳት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዜጎች በአብሮነት እና በአንድነት በመቆም የማኅበረሰቡን ችግሮች የሚፈቱበትና የወገን አለኝታነትን የሚያሳይ የኢትዮጵያውያን የቆየ ባህልና እሴት መሆኑን ገልጸዋል።
በኦሮሚያ ክልል ባለፈው ዓመት በተሠራው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የመንግሥትና የሕዝብ ገንዘብ ከወጪ ማዳን መቻሉንም አስታውሰዋል።
የምስራቅ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አባቦ ዋቆ በበኩላቸው፣ በዞኑ ባለፈው ዓመት 154 ትምህርት ቤቶችና 2 ሺህ የአቅመ ደካሞች ቤቶች መታደሳቸውንና ሌሎች ዘርፈ ብዙ የበጎ አድራጎት ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
ዘንድሮም መርሐ ግብሩ ሙሉውን ማኅበረሰብ ባካተተ መልኩ በበለጠ ትኩረትና ዝግጅት እንደሚተገበር ተናግረዋል።
በምሥራቅ ሸዋ ወለንጪቲ ከተማ በተጀመረው በዚህ መርሐ ግብር፣ ለወላድ እናቶች የደም ልገሳ፣ ለአካል ጉዳተኞች የዊልቸር ድጋፍ፣ የምግብ እና የዘይት አቅርቦት፣ የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ እንዲሁም ተጨማሪ የትምህርት ቤት ክፍሎች ግንባታ ሥራዎች መጀመራቸው ተመላክቷል።
በአሊ ደደፎ
#ethiopia #ebc #ebcdotstream #welfare

#fastmereja I የዘንድሮው የአለም የአፍሪካ ህጻናት ቀን “በአፍሪካ ለሚገኙ ደህንነቱና ንፅህናው የተጠበቀ አካባቢ ለሁሉም ህፃናት" በሚል አህጉራዊ መሪ ቃል በአዲስ አበባ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።
“ስለ እናት” የበጎ አድራጎት ድርጅት (SECO) በዓሉን ምክንያት በማድረግ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ አቅመ-ደካማ ወላጆችን ለመደገፍና ህጻናትን ከትምህርት ማቋረጥ ለመታደግ ያለመ የ1,500 ህጻናት የክረምት የትምህርት ቁሳቁስ ማሰባሰብ ንቅናቄ በይፋ መጀመሩን አስታውቋል።
የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ አብዱ እንደገለፁት፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ማግኘት፣ ጤናማና ንጹህ አካባቢ መፍጠር እንዲሁም መሰረታዊ የንጽህና ቁሳቁሶችን ማቅረብ ችሮታ ሳይሆን የማንኛውም ህጻን መሰረታዊ ሰብአዊ መብት መሆኑን አብራርተዋል።
አሁንም በአህጉሪቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህጻናት በውሃ ወለድ በሽታዎች እየተጠቁና ሴት ህጻናት ደግሞ በቂ የንፅህና መጠበቂያ ባለመኖሩ ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እየቀሩ መሆናቸውን የጠቀሱት ዋና ስራ አስኪያጁ፣ ማህበረሰቡ፣ መንግስታዊ አካላትና አለምአቀፍ አጋሮች ለWASH (የንጹህ ውሃ እና ንፅህና) ተደራሽነት መስፋፋት በጋራ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።
ድርጅቱ አሁን ላይ በአገሪቱ ካለው የኑሮ ውድነት አንጻር በርካታ አቅመ-ደካማ ወላጆች ለልጆቻቸው መሰረታዊ የትምህርት ቁሳቁሶችን ማሟላት ብርቱ ፈተና እንደሆነባቸው ገልጿል።
ይህንን ክፍተት ለመሙላትም በመጪው አዲስ የትምህርት ዘመን የኢኮኖሚ አቅም ማነስ የትምህርት እክል ሊሆንባቸው የሚችሉ 1,500 እና ከዚያ በላይ የሚሆኑ ህጻናትን በደብተር፣ በቦርሳና በሌሎች የትምህርት ቁሳቁሶች ለመደገፍ ዘመቻ መጀመሩን አስታውቆ፣ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ በጎ አድራጊዎች በቁሳቁስም ሆነ በገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቋል።
በሌላ በኩል ድርጅቱ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት ሩብ ክፍለ ዘመን (25 ዓመታት) በህጻናት ጥበቃ፣ በቤተሰብ መልሶ ማቋቋም እንዲሁም በሴት የቤት መሪዎች ኢኮኖሚያዊ አቅም ማጎልበት ረገድ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ገልጿል።
በመጪው ነሐሴ ወር የሚከበረውን የ25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓልን አስመልክቶ የድርጅቱን የህጻናት መቀበል አቅም በብዙ እጥፍ የሚያሳድግ የአዲስ ህንጻ ግንባታ የማስጀመሪያ መርሃ ግብርም አብሮ እንደሚከናወን ተገልጿል።
#ማህበራዊ

"ከተፈጥሮ ጥበቃ ዶላር ማግኘት እንደሚቻል ማሳያ የሆነው የሁምቦ የደን ካርበን ፕሮጀክት"
********************
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንጹሕ ልማት ሥርዓት ተመዝግቦ የሚገኘውና በአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው የወላይታ ሁምቦ የደን ካርበን ፕሮጀክት፣ በተራቆቱ ተራሮች ላይ አዲስ ሕይወት በመዝራት የአየር ንብረት መዛባትን መከላከል እንደሚቻል ትልቅ ማሳያ እየሆነ ይገኛል።
ይህ ብቻ ሳይሆን፣ ከተፈጥሮ ጥበቃ ተጨባጭ የውጭ ምንዛሬ (ዶላር) ማግኘት እንደሚቻልም በተግባር ያሳየው ይህ ፕሮጀክት፤ በአፍሪካ አንደኛ፣ በዓለም ደግሞ ንጹሕ የደን ልማት ዘዴ ተጠቃሽ ፕሮጀክት ሆኖ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በይፋ ተመዝግቧል።
በወላይታ ዞን በ2 ሺህ 728 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ፕሮጀክት፣ ቀደም ሲል ጠፍተው የነበሩ ከ70 በላይ የአገር በቀል የዛፍ ዝርያዎች ተመልሰው እንዲያንሰራሩ ያደረገ ነው።
የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል ረገድም ይህ ፕሮጀክት በዓመት በአማካይ ወደ 29 ሺህ 343 ሜትሪክ ቶን በላይ የካርቦን ዳይኦክሳይድ ጋዝ ከከባቢ አየር ውስጥ እንደሚያስወግድ ይታመናል።
በዛፎች ዕድገት እና በአየር ንብረት መለዋወጥ ውጤቶች ላይ በመመስረት ትክክለኛው የሚወገደው የካርቦን መጠን ከዓመት ዓመት ሊለያይ ቢችልም፤ 29 ሺህ343 ቶን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንጹሕ ልማት ዘዴ ምዝገባ ላይ የተቀመጠ ይፋዊ አማካይ ስሌት በመሆኑ፣ ለአለም አቀፉ የአየር ንብረት መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
ይህ ስኬት ሊመዘገብ የቻለው “በአርሶ አደር የሚመራ የተፈጥሮ ደን መልሶ ማልማት የተባለውን ሳይንሳዊና ባህላዊ ጥበብ በማቀናጀት ደኑን በተደራጀ መልኩ በመንከባከብ ነው። በዚህም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንጹሕ ልማት ዘዴ መስፈርቶችን በአግባቡ በማሟላቱ በአህጉሪቱ ቀዳሚው ተጠቃሽ ፕሮጀክት ሊሆን ችሏል።
ደኑን ከመጠበቅ ባሻገር ለአካባቢው ማኅበረሰብ ዘላቂ የገቢ ምንጭ መፍጠር የቻለው ይህ ፕሮጀክት፤ በአሁኑ ወቅት 7 የደን ልማትና ጥበቃ የኅብረት ሥራ ማኅበራት በአንድ ዩኒየን ሥር ተደራጅተው ደኑን በባለቤትነት እየጠበቁት ይገኛል።
እነዚህ ማኅበራት በዓለም አቀፉ የበጎ አድራጎት ድርጅት "ዎርልድ ቪዥን" ድጋፍና አስተባባሪነት፣ የካርበን ፕሮጀክት ክሬዲትን ለዓለም ባንክ በመሸጥ በየዓመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ዶላር ገቢ እያገኙ ነው። ይህም ለአካባቢው ነዋሪዎች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የጤና መሻሻልን ለማምጣት ትልቅ አቅም ፈጥሯል።
የሁምቦ ፕሮጀክት ያሳየው ተጨባጭ ስኬት ኢትዮጵያ በረጅም ጊዜ ዕቅዷ በ2050 ዓ.ም የተለያዩ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከያ ስትራቴጂዎችን በመተግበር፣ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን የበካይ ጋዝ ወይም የካርበን ልቀት ፍጹም ዜሮ ለማድረግ ለጀመረችው አገራዊ ጉዞ ትልቅ ማሳያና አቅም የሚሆን ነው።
አሁን ላይ ይህ ስኬት ተስፋፍቶ በወላይታ ዞን ዳሞታ ተራራን ፕሮጀክት ጨምሮ በ9 ወረዳዎች ከ22,000 ሄክታር በላይ መሬት በካርበን ፕሮጀክት እየለማ የሚገኝ ሲሆን፤ 48 የደን ማኅበራት እና 3 የደን ዩኒዮኖች በዚሁ አረንጓዴና ትርፋማ ፕሮጀክት ላይ በንቅናቄ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በትዕግስቱ ቡቼ
#ebc #humbocarbonproject #wolaita #climateaction #greeneconomy

ለነፃ የልብ ሕክምና ተዘጋጁ!
* ከ54 በላይ የልብ ሕክምና ባለሙያዎች ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው
#ethiopia | «ኸርት አታክ ኢትዮጵያ» የበጎ አድራጎት ድርጅት ከ54 በላይ የልብ ሕክምና በጎ ፈቃደኛ ባለሙያዎችን ያቀፈ የሕክምና ቡድን በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከ200 በላይ ነፃ የልብ ሕክምናና የቀዶ ሕክምና አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ አስታውቋል።
ድርጅቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የሕክምና ቡድኑ ከህንድ፣ ካናዳ፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ሩዋንዳ እና ቦትስዋና የተውጣጡ የልብ ስፔሻሊስት ሐኪሞች፣ ነርሶችና ሌሎች የጤና ባለሙያዎችን ያካተተ መሆኑን ገልጿል።
የድርጅቱ መስራች ዶ/ር ኦብሴ መርዕድ እንዳሉት፣ በዚህ አምስተኛ የሕክምና ዘመቻ ከ200 በላይ የልብ ቀዶ ሕክምናዎችና ሌሎች የካርዲዮሎጂ ፕሮሲጀሮች ይከናወናሉ።
አገልግሎቱም በኮሪያ ሆስፒታል፣ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል እና በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ይሰጣል።
«ኸርት አታክ ኢትዮጵያ» ከዚህ ቀደም ባከናወናቸው አራት የነፃ የሕክምና ዘመቻዎች ወደ 480 የሚጠጉ የልብ ቀዶ ሕክምናዎችን በነፃ ማከናወኑን ገልጾ፣ በቀጣይም ተመሳሳይ ድጋፎችን እንደሚያስቀጥል አስታውቋል።
ድርጅቱ በመጨረሻም ነፃ የልብ ሕክምና ለማግኘት የሚፈልጉ ዜጎች ለቀጣይ እሁድ እንዲዘጋጁ ጥሪ አቅርቧል።
ሆኖም የሕክምና አገልግሎቱ በአብዛኛው በተዘጋጁ የልብ ሕክምና ማዕከላት ቀድሞ ክትትል ላይ ከነበሩ እና በስፔሻሊስት ሐኪሞች ከተለዩ ታካሚዎች መካከል እንደሚሰጥም ገልጿል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ኸርትአታክኢትዮጵያ #የልብህክምናበኢትዮጵያ #ጥቁርአንበሳሆስፒታል #ጌጡተመስገንሚዲያናኮሙኒኬሽንስ #getutemesgenmediacommunications

“ኸርት አታክ ኢትዮጵያ' ከ200 በላይ ለሚሆኑ የልብ ሕሙማን ነጻ ሕክምና ሊሰጥ ነው!
#fastmereja I «ኸርት አታክ ኢትዮጵያ» (Heart Attack Ethiopia) የተሰኘው የበጎ አድራጎት ድርጅት፣ 5ኛው ዙር ዘመቻው ከ200 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ውስብስብና ነጻ የልብ ሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን በዛሬዉ እለት በሰጡት መግለጫ አስታዉቋል።
ለዚህ በጎ ተግባር ከ55 በላይ ዓለም አቀፍ የልብ ህክምና ስፔሻሊስቶችን የያዘውና በዶክተር ተስፋዬ ተሊላ የሚመራው የህክምና ቡድን የፊታችን ቅዳሜ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተገልጿል።
የዘንድሮው 5ኛ ዙር ዘመቻ ከተመሠረተ ጀምሮ ትልቁ ሲሆን፣ ሕክምናው በጥቁር አንበሳ፣በቅዱስ ጳውሎስ ፣ በካርዲያክ ሴንተር እና ዘንድሮ አዲስ በተጨመረው በኮሪያ ሆስፒታል በአጠቃላይ በ4 ማዕከላት ውስጥ እንደሚደረግ ተገልጿል።
ይህን ህክምና የሚሰጡ ባለሙያዎች ከካናዳ፣ ሕንድ፣ አሜሪካ፣ ሩዋንዳ እና ቦትስዋናን ጨምሮ ከ6 አገራት የተውጣጡ ከ55 በላይ የበጎ ፈቃደኛ የልብ ሐኪሞች፣ ሰርጅኖችና ነርሶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ህክምናዉን እንደሚሰጡ ነዉ የተገለፀዉ።
ድርጅቱ ህክምናውን በነጻ የሚሰጥ ሲሆን፣ ህሙማንን የመለየቱ ስራ እና የወረፋ ሂደት ግን በአገር ውስጥ ሆስፒታሎች አሰራር አማካኝነት በውስጥ የሚለይ መሆኑን አስረድተዋል።
የዘመቻው ዓላማ ጊዜያዊ ሕክምና መስጠት ብቻ ሳይሆን በሀገር ውስጥ ዘላቂ አቅም መገንባት ሲሆን ለዚህም ስድስት የሀገር ውስጥ ባለሙያዎች ለከፍተኛ ስልጠና ወደ ሕንድ የሚላኩ ሲሆን፣ በሐምሌ 11 በሚካሄደው የጋላ ዲነር መርሐ-ግብር ላይ የሕክምና ማዕከል ግንባታ ዕቅድ (Hub-and-Spoke Plan) ይፋ እንደሚደረግ ነዉ የተገለፀዉ።
ድርጅቱ ለጤና ሚኒስቴር፣ የሕክምና ቁሳቁሶችን በነጻ ላጓጓዘው የኢትዮጵያ አየር መንገድና ለባለሙያዎች ምስጋና ያቀረበ ሲሆን፣ ይህንን ሰብአዊ ሥራ ለማገዝ እያንዳንዱ አካል ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።
በዶክተር ኦብስኔት መርዕድ እና በዶክተር ተስፋዬ ተሊላ የተመሠረተው ተቋም ላለፉት ሁለት ዓመታት ከስድስት ወራት በላይ በነጻ ሕክምና ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ ባለፉት አራት ዙሮች ብቻ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ ወጪ በመሸፈን የ461 ሰዎችን ሕይወት መታደግ ችሏል።
#ጤና

በቴሌብር እንደጋገፍ!
የቴሌብር መርጃ መድረክ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ቀላል፣ ፈጣንና ግልጽ ያደርጋል።
የተቸገሩትን ለመደገፍና የበጎ አድራጎት ማኅበራትን ለማገዝ የደግነት እጅዎን መዘርጋት አሁን በሞባይልዎ ቀላል ሆኗል። የቴሌብር መተግበሪያዎን በመክፈት የበጎ አድራጎት መድረኩን ይጎብኙ፤ በጥቂት ቅጽበቶች በልበ ሙሉነት ይላኩ፤ የብዙዎችን ሕይወት በጋራ እንቀይር!
ቴሌብር ሱፐርአፕን
https://bit.ly/telebirr_Su... ጭነን ስንደጋገፍ እንዲህ ነን!
#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን #ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን #ስንጭን_እንዲህ_ነን #ስናስጀምር_እንዲህ_ነን
የቴሌብር መርጃ መድረክ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ቀላል፣ ፈጣንና ግልጽ ያደርጋል።
የተቸገሩትን ለመደገፍና የበጎ አድራጎት ማኅበራትን ለማገዝ የደግነት እጅዎን መዘርጋት አሁን በሞባይልዎ ቀላል ሆኗል። የቴሌብር መተግበሪያዎን በመክፈት የበጎ አድራጎት መድረኩን ይጎብኙ፤ በጥቂት ቅጽበቶች በልበ ሙሉነት ይላኩ፤ የብዙዎችን ሕይወት በጋራ እንቀይር!
ቴሌብር ሱፐርአፕን
https://bit.ly/telebirr_Su... ጭነን ስንደጋገፍ እንዲህ ነን!
#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን #ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን #ስንጭን_እንዲህ_ነን #ስናስጀምር_እንዲህ_ነን
2 months ago
በኪነጥበብ የታጀበ ደግነት🙏
ኮሜዲያን አስረስ በቀለ (ቼሪ) የመጽሐፉን ገቢ ሙሉ ለሙሉ ለበጎ አድራጎት አበረከተ
የሕፃናት መጻሕፍት ደራሲና የልጆች ፕሮግራም አዘጋጅ በመሆን፣ በተለይም “ቼሪ” የተሰኘውን ተወዳጅ የልጆች ካራክተር (ገጸ-ባህሪ) በመፍጠር በሕፃናት መዝናኛና ትምህርት ዘርፍ ጉልህ አሻራ ያሳረፈው ታዋቂው ኮሜዲያን አስረስ በቀለ፣ በድጋሚ የደግነት ተምሳሌትነቱን አሳይቷል።
ሰሞኑን በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ካስመረቃቸው ሁለት አዳዲስ የሕፃናት መጻሕፍት መካከል የመጀመሪያውን መጽሐፍ ሽያጭ ገቢ ሙሉ ለሙሉ ለሙዳይ በጎ አድራጎት ድርጅት በስጦታ አበርክቷል።
ከ15 በላይ የልጆች ተረት መጻሕፍትን ለንባብ ያበቃው ደራሲ አስረስ በቀለ፣ ለሕፃናት ሥነ-ጽሑፍ ባበረከተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ እ.ኤ.አ በ2022 በተካሄደው Ethiopia Reads Children’s Reading Summit ላይ እውቅና የተቸረው አንጋፋ ባለሙያ ነው።
ይህ የሰሞኑን ስጦታውም ጥበብን ከሕዝብ ወገንተኝነት ጋር አጣምሮ የመጓዙ ማረጋገጫ ሆኗል።
ይህንን ታላቅ የበጎ አድራጎት ስጦታ የተቀበለው የሙዳይ በጎ አድራጎት ድርጅት፣ ለረጅም ዓመታት በችግር ውስጥ ያሉ ሕፃናትን፣ እናቶችንና አረጋውያንን በመደገፍና ተስፋ በመሆን የሚታወቅ ተቋም ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 2 አድራሻውን አድርጎ ሰብአዊ አገልግሎቱን በስፋት እየሰጠ ይገኛል።
የድርጅቱ መሥራች ወይዘሮ ሙዳይ ምትኩ የተደረገላቸውን ድጋፍ አስመልክተው ባስተላለፉት ልባዊ መልእክት፦
"አስረስ በቀለ (ቼሪ) የምንግዜም የልብ አጋራችንና ታማኝ ደጋፊያችን ነው። ዛሬም ይህንን የመጽሐፉን ገቢ ሙሉ ለሙሉ ለእኛ በማበርከት ያደረገልንን ታላቅ በጎ ተግባር ስንመለከት ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን።"
በማለት አክለውም ለመላው የሀገራችንን ሕዝብ ጥሪ አቅርበዋል፦
"ሁሌም ከጎናችን የማትለዩ ደጋግ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤ ይህንን ጠቃሚ የሕፃናት መጽሐፍ በመግዛት፣ በአንድ በኩል የልጆቻችሁን የዕውቀት አድማስ እንድታሰፉ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የሽያጩን ገቢ በቀጥታ ለሙዳይ በማዋል አቅመ-ደካሞችንና ሕፃናትን እንድትደግፉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።"
ይህንን መጽሐፍ በመግዛት የዕውቀትና የቸርነት አጋር እንሁን!

ሰላም! እንደምን አደራችሁ?
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሀገር ግንባታ ምሰሶ...
በኢትዮጵያ ከሚከናወኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እሴቶች ውስጥ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አንዱ ነው፡፡የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አብሮነትን፣ መተሳሰብ እና መረዳዳትን ከማጎልበቱ ባለፈ የሕሊና እርካታ የሚገኝበት መልካም ተግባር ነው፡፡
በኢትዮጵያ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከተለመደው የዕለት ተዕለት መረዳዳት ባለፈ ሀገር በቀል አቅምን የሚያንቀሳቅስ ትልቅ ብሔራዊ ንቅናቄ እየሆነ መጥቷል፡፡
ይህ ንቅናቄ የሕዝብ ለሕዝብ መተሳሰብን የሚያጠናክር፣ የሀገር አንድነትን የሚያጸና እና የወጣቱን ቁርጠኝነት በተግባር የሚያሳይ ዋነኛ መድረክ ሲሆን ÷ በዚህም በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች ወገናቸውን የሚያገለግሉበት መንገድ መፍጠር ተችሏል።
ዜጎች የአቅመ ደካሞችን ቤት መጠገን እና መገንባት፣ ደም መለገስ፣ በችግኝ ተከላ መሳተፍን ጨምሮ ከ14 በላይ በሚሆኑ የአገልግሎት ዘርፎች በመሳተፍ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ባሕል አድርገው እያሳደጉ ይገኛሉ።
እነዚህ ተግባራት በማሕበረሰቡ ውስጥ ያሉትን ክፍተቶች በመሙላት ረገድ የማይተካ ሚና አላቸው፤ ይህ አገልግሎት የመንግሥትን የልማት ሸክም ከመቀነስ ባለፈ ጥልቅ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን የሚያጠናክር ነው።
ወጣቶች ከሚኖሩበት አካባቢ እንዲሁም ከዚያ አልፈው በሌሎች አካባቢ ጭምር የተለያየ ቋንቋ እና ባህል ካላቸው ማሕበረሰቦች ጋር በጋራ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመስጠት በሕብረሰተቡ መካከል ጠንካራ የመተሳሰብ ድልድይ እንዲገነቡ አስችሏቸዋል።
በአስቸጋሪ የክረምት ወራት የአንዱ ችግር የሌላውም ህመም መሆኑን በመረዳት እርስ በርስ መደጋገፍ የዘመናት አብሮነትን በማደስ ኢትዮጵያዊነትን በጽኑ መሠረት ላይ የሚያቆም ተግባር ሲሆን÷ መተሳሰብ፣ ክፉ ቀናትን በጋራ የማለፍ ባህልን በማዳበር የሀገርን ሰላምና አንድነት በላቀ ደረጃ ያጠናክረዋል።
አሁን ላይ ወጣቱ ትውልድ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የሚያሳየው ከፍተኛ ተነሳሽነት፣ ስለ ሀገሩ የሚያስብና ኃላፊነት የሚሰማው ዜጋ እየተፈጠረ መሆኑን ማረጋገጫ ነው።
ወጣቶች እውቀታቸውን፣ ጉልበታቸውንና ጊዜያቸውን ያለምንም ክፍያ ለሀገራቸው በመስጠት፣ የነገዋን የበለጸገች ኢትዮጵያን በገዛ እጃቸው በመገንባት ለሀገር ዕድገት ያላቸውን ቀዳሚ ተዋናይነት ሚና እየተወጡ ይገኛሉ።
ይህ ንቅናቄ ማሕበራዊ ውበት ብቻ ሳይሆን፣ የሀገርን ኢኮኖሚያዊ ጫና በከፍተኛ ደረጃ ማቃለል የቻለ ነው ፤ዜጎች በሚሰጡት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ብቻ ከመንግሥት እና ከሕብረተሰቡ ሊወጣ የነበረን በቢሊየን የሚቆጠር ሀብት ማዳን ተችሏል።
በኢትዮጵያ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የሚታየው የዜጎች ከፍተኛ ተነሳሽነት በተለይም ወጣቱ ትውልድ የነገዋን የበለጸገች ኢትዮጵያን በገዛ እጁ የሚቀርጽ መሆኑን የሚያሳይ ነው ፤በጎ ፈቃድ ብሔራዊ አንድነትን በማጥበቅ እና ሕዝብን ከሕዝብ በማስተሳሰር ረገድ የሚጫወተው ሚና በቀላሉ የሚገመት አይደለም።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ጎሮ ወረዳ ያሳለፍነው ሰኔ11 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ማስጀመራቸው ይታወሳል፡፡
በዚህ ወቅትም ሀገራችንን በጋራ ማንሳት የምንችለው አንዳችን ለሌላችን እጃችንን ስንዘረጋ ብቻ ነው፡፡ የክረምቱ ወቅት ሲደርስ፣ እኛም ለወገኖቻችን የምንዘረጋው የደግነት እጅ አብሮ ይጀግናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በተያዘው ክረምት ወጣቶች ዕውቀታቸውንና ጉልበታቸውን፤ ባለሃብቶች ደግሞ ሃብታቸውን በማዋጣት የዐቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት በመገንባት፣ ማዕድ በማጋራት፣ በደም ልገሳ፣ በአረንጓዴ ዐሻራና በሌሎች በጎ ሥራዎች መሳተፍ ይጠበቅባዋል፡፡
የመንግሥት ተቋማትም በቁጠባ ከሚጠቀሙት ሀብታቸው በማዋጣት ይህንን የበጎ አድራጎት ልምድ የማስፋት እና ወደ ላቀ ባህል ደረጃ ለማሳደግ በትኩረት መስራት አለባቸው፡፡
ስለሆነም ይህንን መልካም ዕሴት ይበልጥ ተቋማዊ በሆነ መንገድ በማደራጀትና የወጣቱን ብሎም የባለሃብቱን ቁርጠኝነት በዘላቂነት በመደገፍ፣ የሀገሪቱን የነገ ጉዞ ብሩህ ማድረግ የሁሉም አካላት የጋራ ሃላፊነት ሊሆን ይገባል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እንዳሉት÷ እውነተኛ ብልጽግናም ሆነ የሀገር ግንባታ እውን የሚሆነው ትልቅ የሀገሪቱ ሃብት የሆኑት ከ130 ሚሊየን በላይ ዜጎች ጉልበታቸውን፣ ሃብታቸውንና እውቀታቸውን ደምረው መጠቀም ሲችሉ ነው፡፡

የክረምት በጎ ባህሎቻችንን ወደ ላቀ መገለጫነት እናሻግራለን - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የክረምት በጎ ባህሎቻችንን ወደ ላቀ መገለጫነት እናሻግራለን አለ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት።
አገልግሎቱ ጉዳዩን አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ ሙሉ መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል።
ኢትዮጵያውያን ባለፉት የለውጥ ዓመታት ክረምት በመጣ ቊጥር የምንከውናቸው ሁለት አንኳር ባህሎችን እየገነባን መጥተናል፤ ኢትዮጵያን አረንጓዴ ማልበስ እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት፡፡
ኢትዮጵያ የደን ሀብቷ እየተመናመነ፣ የዐፈር መሸርሸር እና ድርቅ ተጋላጭነቷ እየጨመረ መምጣቱን በመገንዘብ መንግሥት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን በሚሊዮን ችግኞች ተከላ በማብሰር ከጥቂት ዓመታት በፊት ጀምሯል፡፡
ኢትዮጵያውያንም ይህንን በጎ ጅምር እና የመዳረሻ ትልም በላቀ ደረጃ በመገንዘብና የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብሩን በተነሣሽነት በመተግበር ዓለምን ያስደመሙ ስኬቶችን አስመዝግበናል፡፡ በሂደቱ የምግብ፣ የደን እና የውበት ችግኞችን በመትከል ዐሻራችን እያኖርን ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበስ ባህላችንን በእጅጉ አጎልብተናል፡፡
በየዓመቱ በርካታ ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል የዓለም ሕዝብን ከአምስት እጥፍ የሚበልጥ ከ48 ቢሊዮን ላይ ችግኞች ተክለናል፤ በዚህም የኢትዮጵያን የደን ሽፋን ትርጒም ባለዉ መጠን አሳድገናል፤ ለምግብ ሉዓላዊነታችን መሠረት መጣል ጀምረናል፤ የፍራፍሬ የወጪ ንግዳችን አሳድገናል።
ከሁለት ዓመታት በፊት ይፋ በተደረገ የጥናት ውጤት መሠረት የደን ሽፋናችን እጅግ ከተመናመነበት በከፍተኛ ፍጥነት አገግሞ ወደ 23.6% አድጓል፡፡
በልዩ ኹኔታ የኢትዮጵያውያንን የተቀናጀ እና የተሰናሰነ ተነሣሽነት በሚጠይቁ የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሮችም የዓለምን ትኩረት በሳበ መልኩ ሚሊዮኖች በአንድ ጀምበር እየወጣን በመትከል የራሳችንን ክብረ ወሰን በራሳችን ደጋግመን እያሻሻልን መጥተናል፡፡
በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የተከልናቸው የምግብ፣ የደን እና የውበት ችግኞች የኢትዮጵያን ኹለንተና የሚቀይሩ፣ የምግብ ሉዓላዊነታችንን የሚያረጋግጡ፤ የአበባ እና ፍራፍሬ ወጪ ንግዳችንን ዕድገት እየለወጡ ያሉ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም ዐቅም ያጎለበቱ ናቸው፡፡
በመኾኑም ይህ ክረምት በመጣ ቊጥር በንቅናቄ የሚከናወን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ባህል የበለጠ እንዲጠናከርና እንዲጎለብት በትጋት መሥራታችንን እንቀጥላለን፤ ኢትዮጵያን አረንጓዴ በማልበስ ንጹሕ አየር ለዓለም እናበረክታለን፡፡ ዘንድሮም የራሳችንን ክብረ ወሰን በራሳችን የላቀ የሚሊዮኖች ተሳትፎ በማሻሻል ጭምር ከ8 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን እንተክላለን፡፡
የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትም ሌላኛዉ ዐዲስ እያደገ የመጣ ልምምዳችን ነው፡፡ ወጣቶች ዕውቀታቸዉን እና ከትምህርት የተረፈ ጊዜያቸውን፣ ባለሀብቶች ደግሞ ሀብታቸውን በማዋጣት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያሉ ዐቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት በመገንባት፣ ማዕድ በማጋራት እጅግ የተዋጣለት ልምምድ አዳብረዋል፡፡
የመንግሥት ተቋማትም በቁጠባ ከሚጠቀሙት ሀብታቸው በማዋጣት ይህንን የበጎ አድራጎት ልምድ የማስፋት እና ወደ ላቀ ባህል ደረጃ የማሳደግ ኃላፊነትን እየተወጡ ይገኛሉ፡፡
በለውጡ ዓመታት በአዲስ አበባ እና በክልሎች የበርካታ ዐቅመ ደካሞች ቤት ታድሷል፤ በዐዲስ መልክ ተገንብቷል፤ ሕይወታቸዉ እንዲሻሻል ተደርጓል፡፡ በከተሞች የተጀመረዉ የኮሪደር ልማት ወደ ገጠር ተስፋፍቷል። ኢትዮጵያውያን ችግሮቻችንን ተጋግዞ የመፍታት ባህል እያዳበርን መጥተናል፡፡
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደየአካባቢያቸው በመሄድ እና በወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ታናናሾቻቸውን እያስተማሩ፣ እንደ ደም ልገሳ ያሉ ሕይወት አዳኝ ተግባራትን እያስተባበሩ፣ ዐቅመ ደካሞችን በማገዝ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው፡፡
በመኾኑም በየክረምቱ በበጎ ልምድነት እያሳደግናቸው የመጡ የአረንጓዴ ዐሻራ እና የበጎ ፈቃድ ሥራዎች የበለጠ ሀገራዊ መገለጫችንና ባህላችን እንዲኾኑ ዘንድሮም ካለፉት ዓመታት የላቀ ተሳትፎ የሚጠይቅ ዕቅድ ተዘጋጅቷል፤ ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል።
በተደመረ ዐቅማችን የኢትዮጵያን ዕቅድ በሚገባ ለማሳካት ቅድመ ዝግጅት ጨርሰን ወደ ትግበራ ገብተናል። ድላችንን በጋራ የምናበስርም ይኾናል።
የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአሜሪካዊው ፋንቱ ማንዶዬ ሞርጋን ፍሪማን በጎ ልብ
#ethiopia | በዓለም ዙሪያ በሚማርክ ድምፃቸው እና አስደናቂ የትወና ብቃታቸው የሚታወቁት አንጋፋው ተዋናይ ሞርጋን ፍሪማን፣ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት የሚተጉ ታዋቂ የሰብዓዊ መብትና የበጎ አድራጎት አምባሳደር መሆናቸው ይነገራል።
የሳቸው ዘርፈ ብዙ የበጎ አድራጎት ስራዎች በተለያዩ ቁልፍ ዘርፎች ላይ ያተኮሩ ሲሆን፣ ይህም በማህበረሰቡ ውስጥ አዎንታዊ ተጽዕኖ ለመፍጠር ያላቸውን ጥልቅ ፍላጎት የሚያንጸባርቅ ነው።
ከእነዚህም የጎላ አስተዋፅኦዎቻቸው መካከል በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የሚያደርጉት ድጋፍ በዋናነት ይጠቀሳል። አውዳሚ የሆኑ አውሎ ነፋሶች ባስከተሉት አደጋ የተረፉ ሰዎችን ለመደገፍ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሮችን በግንባር ቀደምትነት አስተባብረዋል።
በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ደረጃ በተፈጥሮ አደጋ ለሚጎዱ ሰዎች ፈጣን እርዳታ ለማድረግ "የግሬናዳ የዕርዳታ ፈንድን" የተሰኘ ኢኒሼቲቭ የነበራቸው ሲሆን፣ ይህ ተቋም አሁን ላይ “ፕላን ኢት ናው” ወደሚባል ዓለም አቀፍ ድርጅት ተሸጋግሯል።
ትምህርት የሌላኛው የበጎ አድራጎት ስራቸው የማዕዘን ድንጋይ ነው። እ.ኤ.አ. በ1991 በሚሲሲፒ ግዛት ውስጥ ለሚገኙ አቅመ ደካማ ታዳጊዎች የቅድመ መደበኛ ትምህርትን ለማስፋፋት ከልጃቸው ጋር በመሆን "የታላሃቺ ሪቨር ፋውንዴሽንን" መስርተዋል። ከዚህም ባሻገር፣ ለእንስሳት ደህንነት ልዩ ጥበቃ የሚያደርጉት ፍሪማን፤ እንደ 'ሚሲሲፒ የእንስሳት አድን ማህበር' ያሉ ድርጅቶችን በመደገፍ እና በእንስሳት ህክምና ኮሌጆች ውስጥ የጥናትና ምርምር ማዕከላትን በገንዘብ በማገዝ ላይ ይገኛሉ።
በእነዚህና መሰል ሰብዓዊ ተነሳሽነቶች፣ ሞርጋን ፍሪማን ተሰሚነታቸው እና ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸው ከፊልም ኢንዱስትሪው መድረክ እና ከካሜራ ዕይታ ውጭ ጭምር ነው።

🎁✨ ለምንወዳቸው ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ከቴሌብር ስጦታ በመግዛት እናበርክትላቸው!
በስጦታ:-
💰 የዲጂታል ሳንቲሞችን በቴሌብር መግዛት
🎉 ለጓደኞችና ለቤተሰብ ስጦታዎችን መላክና መቀበል (ከውጭ ሀገር መቀበል)
💵 የተቀበሉትን የዲጂታል ሳንቲሞች ወደ ገንዘብ መቀየር
🤝 የበጎ አድራጎትና የገቢ ማሰባሰቢያ በቀላሉ መክፈትና መደገፍ ይችላሉ።
በድረ-ገጽ https://web.sitota.et ፣ በቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/3S1hQqd ወይም በራሱ መተግበሪያ https://bit.ly/4lfevOH ያገኙታል!
#sitota #digitalgift #ethiotelecom #telebirr #telebirrsuperapp #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia

የካንሰር ታማሚ ህፃናትን ለመደገፍ ያለመ የጎዳና ሩጫና የደም ልገሳ ሊደረግ ነው
#ethiopia | የተስፋ አዲስ ልጆቻቸውን በካንሰር ያጡ ወላጆች እና በጎ ፈቃደኞች፣ ህክምናው ተደራሽ እንዲሆን በማሰብ ከዛሬ 14 ዓመት በፊት የጀመሩት የበጎ አድራጎት ነው። ዋናው ግቡም ልጆቻቸውን ለማሳከም በብዙ የህክምና ውጣ ውረድ ውስጥ ያለፉ ወላጆች፣ ሌሎችም ተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ያሉትን ለመርዳት በማሰብ ነው። ምንም አይነት ገቢ ወይም ሃብት ያልነበረው ይህ ተስፋ አዲስ፣ በትናንሽ ነገሮች ነበር ጅማሮውን ያደረገው ። ከዚያም ቀስ በቀስ በማደግ፣ አሁን ወደ ሰባት ሆስፒታሎች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
ታዲያ ይህን አገልገሎት ይበልጥ ለማስፋት ይረዳ ዘንድ ፣ "ተስፋ አዲስ" የበጎ አድራጎት ድርጅት ከአራራይ ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ እና የደም ልገሳ መርሐ ግብር አዘጋጅቷል።
የአራራይ ፕሮሞሽን ስራ አስኪያጅ ፣ ወጣት ክብሮም ሃብቱ (ጆን)፣ የካንሰር ታማሚ ህፃናት ህክምና ብዙ ደም እንደሚጠይቅ ገልፀው፣ ህብረተሰቡ ደም በመለገስ እና በሩጫው በመሳተፍ ለህፃናቱ ተስፋ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል። የፕሮግራሙ ብራንድ አምባሳደር የሆነው ቲክቶከር ቅዱስ አማኑኤልም፣ ተከታዮቹ በዚህ ቅዱስ ዓላማ ላይ ከጎኑ እንዲቆሙ እና ደም በመለገስ ለህፃናቱ እንዲደርሱ ጥሪውን አስተላልፏል።
የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫው አስተባባሪ እና የአራራይ ፕሮሞሽን ምክትል ስራስካያጅ፣ ወጣት መሃመድ ንጉስ እንደገለፀው፣ ሩጫው የሚካሄደው ሐምሌ 12 /2018 ዓ.ም ሲሆን መነሻው አትላስ አደባባይ ፤በውሃ ልማት አድርጎ መዳረሻውን አትላስ አደባባይ ያደርጋል።
ለሩጫው የሚሆኑ ቲሸርቶች በተስፋ አዲስ የካንሰር ህፃናት ድርጅት ይገኛሉ።
ለበለጠ መረጃ፡
መሐመድ፡ 0920875941
ጆን፡ 0914777751

#ትኩረት_ለገጠር_ቤተክርስቲያን
የገጠር አድባራትን እና ደብራትን ለመደገፍ የቀረበ ጥሪ
#ethiopia | በከምባታ ጠምባሮ እና ሀላባ ሀገረ ስብከት በጠምባሮ ልዩ ወረዳ የምትገኘው የጎፎሬ ደብረ መንክራት በአታ ለማርያም ቤተክርስቲያን በምዕመናን ሁለንተናዊ እገዛ የመሠረት ግንባታዋ ተጠናቋል።
ለቀጣዩ የዕድገት ምዕራፍ የዓምዶች እና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎችን ለማከናወን እንደ ፌሮ ብረት (ባለ 14፣ 10 እና 8)፣ አሸዋ፣ ጠጠር እና ሲሚንቶ ያሉ የግንባታ ቁሳቁሶች በአስቸኳይ ያስፈልጋሉ።
የተዋሕዶ ልጆች ልማዱን የበረከት ተሳትፎ በማድረግ የቅድስት በአታ ለማርያምን የሕንጻ ግንባታ ከፍጻሜ ለማድረስ የበኩላችሁን እንድትወጡ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም ጥሪ ቀርቧል።
የሕንጻ አሳሪ ኮሚቴው የባንክ አካውንቶች፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ 1000624326281
አቢሲኒያ ባንክ፦ 240587815
ዓባይ ባንክ፦ 362111107991610
አሐዱ ባንክ፦ 0081292811701
አዋሽ ባንክ፦ 013201006748101
ዳሽን ባንክ፦ 5640919295011
ለበለጠ መረጃ እና ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች 0933055802 ወይም 0911414852 መገናኘት ይችላሉ።
ድጋፍ ሲያደርጉ በጸሎት እንድናስብዎት የክርስትና ስምዎን መላክዎን አይርሱ።
እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና። (2ኛ ቆሮ. 9:7)
#ትኩረት_ለገጠር_ቤተክርስቲያን #ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ #በአታ_ለማርያም #የበጎ_አድራጎት #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
🌐 የፌስቡክ ገጽ፦ https://www.facebook.com/d...
"እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና።" (2ኛ ቆሮ. 9:7)

Comments