1 month ago
"ከተፈጥሮ ጥበቃ ዶላር ማግኘት እንደሚቻል ማሳያ የሆነው የሁምቦ የደን ካርበን ፕሮጀክት"
********************
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንጹሕ ልማት ሥርዓት ተመዝግቦ የሚገኘውና በአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው የወላይታ ሁምቦ የደን ካርበን ፕሮጀክት፣ በተራቆቱ ተራሮች ላይ አዲስ ሕይወት በመዝራት የአየር ንብረት መዛባትን መከላከል እንደሚቻል ትልቅ ማሳያ እየሆነ ይገኛል።
ይህ ብቻ ሳይሆን፣ ከተፈጥሮ ጥበቃ ተጨባጭ የውጭ ምንዛሬ (ዶላር) ማግኘት እንደሚቻልም በተግባር ያሳየው ይህ ፕሮጀክት፤ በአፍሪካ አንደኛ፣ በዓለም ደግሞ ንጹሕ የደን ልማት ዘዴ ተጠቃሽ ፕሮጀክት ሆኖ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በይፋ ተመዝግቧል።
በወላይታ ዞን በ2 ሺህ 728 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ፕሮጀክት፣ ቀደም ሲል ጠፍተው የነበሩ ከ70 በላይ የአገር በቀል የዛፍ ዝርያዎች ተመልሰው እንዲያንሰራሩ ያደረገ ነው።
የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል ረገድም ይህ ፕሮጀክት በዓመት በአማካይ ወደ 29 ሺህ 343 ሜትሪክ ቶን በላይ የካርቦን ዳይኦክሳይድ ጋዝ ከከባቢ አየር ውስጥ እንደሚያስወግድ ይታመናል።
በዛፎች ዕድገት እና በአየር ንብረት መለዋወጥ ውጤቶች ላይ በመመስረት ትክክለኛው የሚወገደው የካርቦን መጠን ከዓመት ዓመት ሊለያይ ቢችልም፤ 29 ሺህ343 ቶን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንጹሕ ልማት ዘዴ ምዝገባ ላይ የተቀመጠ ይፋዊ አማካይ ስሌት በመሆኑ፣ ለአለም አቀፉ የአየር ንብረት መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
ይህ ስኬት ሊመዘገብ የቻለው “በአርሶ አደር የሚመራ የተፈጥሮ ደን መልሶ ማልማት የተባለውን ሳይንሳዊና ባህላዊ ጥበብ በማቀናጀት ደኑን በተደራጀ መልኩ በመንከባከብ ነው። በዚህም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንጹሕ ልማት ዘዴ መስፈርቶችን በአግባቡ በማሟላቱ በአህጉሪቱ ቀዳሚው ተጠቃሽ ፕሮጀክት ሊሆን ችሏል።
ደኑን ከመጠበቅ ባሻገር ለአካባቢው ማኅበረሰብ ዘላቂ የገቢ ምንጭ መፍጠር የቻለው ይህ ፕሮጀክት፤ በአሁኑ ወቅት 7 የደን ልማትና ጥበቃ የኅብረት ሥራ ማኅበራት በአንድ ዩኒየን ሥር ተደራጅተው ደኑን በባለቤትነት እየጠበቁት ይገኛል።
እነዚህ ማኅበራት በዓለም አቀፉ የበጎ አድራጎት ድርጅት "ዎርልድ ቪዥን" ድጋፍና አስተባባሪነት፣ የካርበን ፕሮጀክት ክሬዲትን ለዓለም ባንክ በመሸጥ በየዓመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ዶላር ገቢ እያገኙ ነው። ይህም ለአካባቢው ነዋሪዎች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የጤና መሻሻልን ለማምጣት ትልቅ አቅም ፈጥሯል።
የሁምቦ ፕሮጀክት ያሳየው ተጨባጭ ስኬት ኢትዮጵያ በረጅም ጊዜ ዕቅዷ በ2050 ዓ.ም የተለያዩ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከያ ስትራቴጂዎችን በመተግበር፣ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን የበካይ ጋዝ ወይም የካርበን ልቀት ፍጹም ዜሮ ለማድረግ ለጀመረችው አገራዊ ጉዞ ትልቅ ማሳያና አቅም የሚሆን ነው።
አሁን ላይ ይህ ስኬት ተስፋፍቶ በወላይታ ዞን ዳሞታ ተራራን ፕሮጀክት ጨምሮ በ9 ወረዳዎች ከ22,000 ሄክታር በላይ መሬት በካርበን ፕሮጀክት እየለማ የሚገኝ ሲሆን፤ 48 የደን ማኅበራት እና 3 የደን ዩኒዮኖች በዚሁ አረንጓዴና ትርፋማ ፕሮጀክት ላይ በንቅናቄ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በትዕግስቱ ቡቼ
#ebc #humbocarbonproject #wolaita #climateaction #greeneconomy

Comments