በኦሮሚያ ክልል በባለፈው ዓመት የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ከወጪ ማዳን ተችሏል
******************
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ የ2018/19 ክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ ግብር በይፋ ተጀምሯል።
መርሐ ግብሩን ያስጀመሩት የክልሉ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ሳዳት ነሻ ናቸው፡፡
አቶ ሳዳት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዜጎች በአብሮነት እና በአንድነት በመቆም የማኅበረሰቡን ችግሮች የሚፈቱበትና የወገን አለኝታነትን የሚያሳይ የኢትዮጵያውያን የቆየ ባህልና እሴት መሆኑን ገልጸዋል።
በኦሮሚያ ክልል ባለፈው ዓመት በተሠራው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የመንግሥትና የሕዝብ ገንዘብ ከወጪ ማዳን መቻሉንም አስታውሰዋል።
የምስራቅ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አባቦ ዋቆ በበኩላቸው፣ በዞኑ ባለፈው ዓመት 154 ትምህርት ቤቶችና 2 ሺህ የአቅመ ደካሞች ቤቶች መታደሳቸውንና ሌሎች ዘርፈ ብዙ የበጎ አድራጎት ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
ዘንድሮም መርሐ ግብሩ ሙሉውን ማኅበረሰብ ባካተተ መልኩ በበለጠ ትኩረትና ዝግጅት እንደሚተገበር ተናግረዋል።
በምሥራቅ ሸዋ ወለንጪቲ ከተማ በተጀመረው በዚህ መርሐ ግብር፣ ለወላድ እናቶች የደም ልገሳ፣ ለአካል ጉዳተኞች የዊልቸር ድጋፍ፣ የምግብ እና የዘይት አቅርቦት፣ የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ እንዲሁም ተጨማሪ የትምህርት ቤት ክፍሎች ግንባታ ሥራዎች መጀመራቸው ተመላክቷል።
በአሊ ደደፎ
#ethiopia #ebc #ebcdotstream #welfare

1 month ago