14 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ፣ ሜሪላንድ እና ቨርጂኒያ (ዲ.ኤም.ቪ) የሚገኙ የወላይታ ብሔር ተወላጆች፣ የብሔሩ አሮጌው ዓመት መሸኛ እና የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ የሆነውን የዘመን መለወጫ ‘ጊፋታ’ በዓል ከሦስት ሺህ በላይ ተሳታፊዎች እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በቨርጂኒያ ግዛት በደማቅ ሁኔታ አከበሩ።
በበዓሉ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የወላይታ የመጨረሻ ንጉሥ የሆኑት የንጉሥ ጦና አራተኛ ትውልድ ወ/ሮ ሪብቃ ደስታ ፍሰሃ (ሮቤ ጦና)፣ ጊፋታ ከጊዜ አቆጣጠርነቱ ባሻገር የወላይታ ሕዝብ የስልጣኔ መነሻ፣ የአንድነት፣ የመሰባሰብ እና የፍቅር ተምሳሌት በመሆኑ የተለየ ክብር እና ሞገስ እንደሚሰጠው ገልጸዋል። የአባቶችን ታላቅነት እና አይበገሬነት ለትውልድ ማስተላለፍ የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን ያሳሰቡት ወ/ሮ ሪብቃ፤ ከ36 ዓመታት በፊት በፖለቲካ ጥገኝነት በሰሜን አሜሪካ ቆይተው ያረፉት አባታቸው ፊታውራሪ ደስታ ፍሰሃ፣ ይህንን ታላቅ የሕዝብ ስብስብ እና ፍቅር ቢያዩ ምን ያህል ደስ ባላቸው ነበር ሲሉ ሳግ እየተናነቃቸው በስሜት ተናግረዋል።
የዘንድሮውን በዓል ለየት ካደረጉት ሁነቶች መካከል በወጣት ኢንጂነር ሳምሶን ራማቶ የተዘጋጀው የወላይታ ብሔር ዲጂታል የዘመን አቆጣጠር (Gifaataa Digital Calendar) ይፋ መደረጉ ነው። ወጣቱ የብሔሩን የዘመን ቀመር ወደ ዲጂታል ሥርዓት ለማሸጋገር ላደረገው የላቀ ጥረት ከታዳሚው ከፍተኛ አድናቆት እና ምስጋና የተቸረው ሲሆን፣ ተጠቃሚዎች ይህንን የዘመን አቆጣጠር በጎግል ክሮም (Google Chrome) መፈለጊያ ላይ "Wolaita. netlify .app" ብለው በመጻፍ ማግኘት እንደሚችሉ በዕለቱ ተገልጿል።
ዝግጅቱ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች እንዲሁም አዝናኝ እና ቁምነገር አዘል ባህላዊ ጭውውቶች የቀረቡበት ነበር። ታዳሚው ልዩ ልዩ ባህላዊ ምግቦችን (የጥሬ ሥጋ ቁርጥ በዳታ አዋዜ፣ ቆጭቆጮ፣ ቡላ እና የመሳሰሉትን) እየተመገበ በዓሉን ያከበረ ሲሆን፣ የዕለቱ መርሃ ግብር በሴቶች የ‘ኩላ ኩርቹቼ’ እና በወንዶች የ‘ባልሄሌሌ’ ባህላዊ ጨዋታዎች በድምቀት ተጠናቋል።
ይህ የዘንድሮው የጊፋታ በዓል፣ ትውፊቱ ከባህላዊ አልባሳቱ (ዱንጉዛ ሀዲያ)፣ ምግቡ እና አጨዋወቱ ጋር በመሆን እ.ኤ.አ. በ2025 በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ተቋም (UNESCO) በማይዳሰሱ የዓለም ባህላዊ ቅርሶች (Intangible Cultural Heritage of Humanity) ዝርዝር ውስጥ ከተመዘገበ በኋላ የተከበረ የመጀመሪያው በዓል በመሆኑ ታሪካዊ ፋይዳው የጎላ ሆኗል።
(ዘገባው ለዘ-ሐበሻ - በሙሉቀን ገብሬ ላንካ ከዲ.ኤም.ቪ ወላይታ ኮሚዩኒቲ የተጠናቀረ ነው)

17 days ago
የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል “ጊፋታ” ድምቀት የሆነው "ሹሃ ዎጋ"
******************
በዩኔስኮ በማይዳሰስ ቅርስነት ተምዝግቦ የዓለም ቅርስ የሆነው የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል በብሔሩ ዘንድ እጅግ የተለየ ትኩረት የሚሰጥ የብሔሩ መገለጫ ነው።
ለበዓሉ ከዓመት እስከ ዓመት የእርድ በሬ መግዣና የእናቶች የቅቤ ቁጠባን የመሳሰሉ ዝግጅቶች የሚደረጉ ሲሆን፣ በዓሉ ሲቃረብ ግን ሳምንታት እና ቀናቶች የየራሳቸው ስያሜ አሏቸው።
በገበያዎች "ሀረ-ሀይቆ፣ ቦቦዳ እና ጎሻ" ቀናት "ኮሴታ ሐሙሳ፣ ሱልዓ አርባ፣ ባጭራ ቄራ እና ሹሃ ዎጋ" የሚባሉ የበዓሉ መዳረሻዎች ናቸው። የቀናቱ ስያሜ ከበዓሉ ማግስት "ታማ ሰኞ" ጀምሮ እስከ "ጎሏዋ እጌታ" ወደሚባልበት የበዓሉ ለቀጣይ ዓመት መልካም ምኞት ቀን ይቀጥላሉ።
በዚህ መሠረት ዛሬ በወላይታ ብሔር ዘንድ ቀኑ የዕርድ እሁድ" ሹሃ ዎጋ" በመባል ይጠራል። የዕርድ እሁድ አባቶች በ"Amuwaa" (በቡድን) አንድ ላይ ሆነው ከወራት በፊት ለእርድ የሚሆን በሬ ገዝተው ከቡድኑ አባላት በአንዱ ቤት የተቀለበው በሬ የሚታረድበት የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ቀን ነው።
የዕርድ በሬው በእሸት፣ በቆሎ፣ ስኳር ድንች እና በሌሎች እህልና ስራስሮች አባለቱ በየተራ እያዋጡ ይቀለባል። በሬ የሚታረደው "በአሙዋ" አባላት ውስጥ በሬ ሲቀለብ የቆየው አባወራ ደጅ ሲሆን፣ አባላት በዕርድ ቀን ጠዋት ተሰብስበው ከእርድ አስቀድመው በቦታው ባህላዊ ምግቦችን ይበላሉ፣ መጠጦችንም ይጠጣሉ።
በእርድ ቦታ ከስጋ ዓይነቶች የተወሰነ ወስደው የቡድኑ አባላት የአብሮነት መገለጫ ብለው በቦታው ይቋደሳሉ። የየራሳቸው ቅርጫ ከተከፋፈሉ በኋላ በእርጥብ ቆዳ ለሚቀጥለው ዓመት ጊፋታ በዓል የዕርድ በሬ መግዣ ተቀማጭ ገንዘብ ማስቀመጥ ይጀምራሉ።
ዕጣ ጥለው የተከፋፈሉትን ስጋ ወደየቤታቸው ከወሰዱ በኋላ እናቶች ቆጮ፣ ቂጣና ዳጣ በርበሬ በማዘጋጀት ሥጋውን የቤተሰቡ አባለት በጋራ በኮባ ቅጠል በመሬት ዘርግፈው ለማዕዱ ፈጣሪን በማመስገን በደስታ የበዓሉ ድግስ በጋራ ይበላሉ።
የዘንድሮ ጊፋታ በዩኔስኮ የተመዘገበበት የመጀመሪያ ዓመት በዓል በመሆኑ በወላይታ ሶዶ ከተማ በተለዬ ድምቀት “የትውልድ ቅርስን እንጠብቅ፣ የጊፋታን ውርስ እናስቀጥል” በሚል መሪ ቃል በአደባባይ እየተከበረ ይገኛል።
በትዕግስቱ ቡቼ
#ethiopia #ebc #gifata #yoogifata #wolaita #ethiopianculture

ዮ…ዮ… ጊፋታ!
የወላይታ ዘመን መለወጫ በዓል — ከትውፊት ወደ ዓለም የተሻገረ የአንድነት ቅርስ
ዮ…ዮ… ጊፋታ!
ዮ…ዮ…!
#ethiopia | እንኳን ለወላይታ ሕዝብ የዘመን መለወጫ በዓል ጊፋታ በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!
በደቡባዊ ኢትዮጵያ የሚገኘው የወላይታ ምድር በተፈጥሮ ውበቷ፣ በጥንታዊ ታሪኳ፣ በልዩ ቋንቋዋ እና በሕያው ባህሏ የምትታወቅ ናት። ከእነዚህ የባህል ሀብቶቿ መካከል ጊፋታ ልዩ ስፍራ ይይዛል።
ጊፋታ የወላይታ ሕዝብ የአዲስ ዓመት በዓል ሲሆን፣ የአሮጌውን ዓመት ተሰናብቶ አዲሱን ዓመት በተስፋ፣ በደስታ፣ በምስጋና እና በአብሮነት የሚቀበሉበት ታላቅ የባህል ወቅት ነው። UNESCO እንደሚገልጸው ጊፋታ በወላይታ ማኅበረሰብ በመስከረም አጋማሽ እስከ ጥቅምት መጀመሪያ ባለው ወቅት የሚከበር የአዲስ ዓመት በዓል ነው።
ጊፋታ — ከአሮጌው ወደ አዲሱ
የጊፋታ ትልቁ መልዕክት የዘመን መለወጥ ብቻ አይደለም። በውስጡ የተያዙት የሰላም፣ የዕርቅ፣ የመከባበር፣ የመረዳዳት፣ የቤተሰብ አንድነት እና የትውልድ ትስስር እሴቶች ናቸው።
በበዓሉ ዋዜማ ሰዎች ቤታቸውንና አካባቢያቸውን ያጸዳሉ፤ ከሩቅ የሚኖሩ የቤተሰብ አባላትም ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ። ከዚህ በላይ በሰዎች መካከል የነበሩ ግጭቶችና አለመግባባቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የሚደረግበት ወቅት ነው። UNESCO ይህንን እርቅና ሰላማዊ መፍትሔ ከጊፋታ ዋና የማኅበራዊ እሴቶች አንዱ አድርጎ ይጠቅሰዋል።
ስለዚህ ጊፋታ አሮጌውን ዓመት በአሮጌ ቂምና ጥላቻ ሳይሆን፣ በይቅርታና በእርቅ ለመሰናበት እና አዲሱን ዘመን በንጹሕ ልብ ለመቀበል የሚጠራ ትውፊት ነው።
የጨረቃ ዑደትና የወላይታ የጊዜ ቀመር
ጊፋታ ከዘመን መለወጥ ጋር ብቻ የሚያያዝ በዓል አይደለም። የወላይታ የጊዜ አቆጣጠር እና የሰማይ አካላት ምልከታ ከበዓሉ የተያያዙ ጥንታዊ እውቀቶች ናቸው።
የወላይታ ዞን አስተዳደር የባህል መረጃ እንደሚያሳየው የወላይታ የቀን መቁጠሪያ ከጨረቃና ከፀሐይ ዑደት ጋር የሚያያዝ ሲሆን፣ ጊፋታም የዘመን መለወጫ በዓል ነው።
ቤተሰብ ወደ ቤት፣ ልብ ወደ ልብ
ጊፋታ በወላይታ ማኅበረሰብ ውስጥ የመመለስ በዓልም ነው። በየአቅጣጫው የተበተኑ የቤተሰብ አባላት ወደ ትውልድ ቀዬአቸው ይመለሳሉ። ዘመድ ከዘመድ፣ ጎረቤት ከጎረቤት ይገናኛል።
በዚህም በዓሉ የቤተሰብ ግንኙነትን ከማደስ ባለፈ የማኅበረሰቡን የጋራ መኖር የሚያጠናክር ማኅበራዊ ሥርዓት ሆኖ ይታያል። UNESCO በጊፋታ ውስጥ የአዛውንቶች ሚናን እና እውቀቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ መተላለፉን በተለይ ያጎላል።
እርቅ — ከጊፋታ ዋና መልዕክቶች አንዱ
አዲስ ዓመትን በአዲስ ልብ መቀበል፤ የድሮ ጥላቻን ከኋላ መተው፤ በቂም የተራራቁ ሰዎችን ማቀራረብ — እነዚህ የጊፋታ ጥልቅ ማኅበራዊ መልዕክቶች ናቸው።
በበዓሉ ዋዜማ ግጭቶችን በሰላም መፍታት የበዓሉ ዋና የዝግጅት አካል መሆኑን UNESCO ይገልጻል።
ይህም ጊፋታን ከአንድ የዘመን መለወጫ በዓል በላይ ያደርገዋል፤ ማኅበራዊ ትስስርን የሚያድስ የሕይወት ፍልስፍና ያደርገዋል።
የምግብ፣ የመጠጥ፣ የዜማና የውዝዋዜ ድምቀት
የጊፋታ ዋና ቀን ሲደርስ ቤተሰቦች ይሰበሰባሉ። ባህላዊ ምግቦች ይዘጋጃሉ፤ የበዓሉ ልዩ የምግብና የመጠጥ ሥርዓቶች ይከናወናሉ። UNESCO በዋናው የበዓል ቀን ቤተሰቦች በመሰባሰብ ሥጋና የአካባቢውን መጠጥ በመካፈል ከአዛውንት በረከት እንደሚቀበሉ ይገልጻል።
በሌሊትም ማኅበረሰቡ በእሳት ዙሪያ በመሰባሰብ ሥርዓታዊ ዝግጅቶችን፣ ዜማንና ውዝዋዜን ያከናውናል።
የባህላዊ አልባሳት ውበት፣ የጨዋታና የውዝዋዜ ትርኢቶች፣ የባህላዊ ዜማዎች ድምጽ እና የበዓሉ የማኅበረሰብ ስብሰባ ወላይታን በእጅጉ ያደምቃሉ።
የጊፋታ የቁጠባ ጥበብ
ጊፋታ በደስታ እና በውዝዋዜ ብቻ የሚያልፍ በዓል አይደለም። በውስጡ የቤተሰብ ኢኮኖሚን የሚያጠናክሩ የቁጠባና የመረዳዳት ባህሎችም ይገኛሉ።
የጊፋታ ዝግጅት በቤተሰብ ደረጃ ከቀደም ብሎ ስለሚጀመር ሰዎች ለበዓሉ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን አስቀድመው ያዘጋጃሉ። ይህ ባህል በዓሉን ከማክበር ባለፈ የቤተሰብ የኢኮኖሚ ዕቅድን እና የመረዳዳት ባህልን ያጠናክራል።
ለትውልድ የሚተላለፍ ቅርስ
ጊፋታ የአንድ ትውልድ ብቻ በዓል አይደለም። አዛውንት የሚያስተላልፉት፣ ወጣቶች የሚማሩት፣ ልጆች የሚመለከቱትና በቀጣዩ ዘመን የሚያስቀጥሉት ሕያው ባህላዊ ትውፊት ነው።
UNESCO በጊፋታ የአዛውንቶች ሚና፣ የትምህርት ተቋማትና የቅርስ ክለቦች ተሳትፎ፣ የምርምር መድረኮችና የባህል ቦታዎችን መጠበቅ የበዓሉን ቀጣይነት ከሚያጠናክሩ ሥራዎች መካከል እንደሆኑ ይጠቅሳል።
2025 — ወደ UNESCO የዓለም መድረክ
በጊፋታ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ የተከፈተው በ2025 ነው። የUNESCO የማይዳሰስ የባህል ቅርስ መንግሥታት ኮሚቴ በኒው ዴልሂ በተካሄደው 20ኛ ስብሰባ ጊፋታን በRepresentative List of the Intangible Cultural Heritage of Humanity ላይ አስመዝግቧል።
ይህ ማለት ጊፋታ የሚከበረው በወላይታ ሕዝብ ዘንድ ብቻ ሳይሆን፣ በUNESCO የሰው ልጅ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ ተወካይ ዝርዝር ውስጥ የተካተተ ሕያው ባህላዊ እሴት መሆኑን ያሳያል።
ኢትዮጵያ አሁን በUNESCO የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ ዝርዝሮች ላይ ሰባት የተመዘገቡ እሴቶች አሏት፤ ጊፋታም በ2025 የተጨመረው አዲሱ አካል ነው።
የዓለም ቅርስ መሆን ለወላይታ ምን ይሰጣል?
የUNESCO ምዝገባ ለጊፋታ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ከመስጠት ባለፈ የቅርሱን ጥበቃና ትውልድ-ተሻጋሪ ቀጣይነት ማጠናከር እንደ ዋና አላማ ያለው ነው።
ይህ ዕውቅና ወላይታን በባህላዊ ቱሪዝም ዘርፍ ይበልጥ ለማስተዋወቅ፣ የአካባቢውን ባህላዊ ፈጠራዎች ለዓለም ለማቅረብ እና በቅርስ ላይ የተመሠረተ የጎብኚ ልምድ ለማሳደግ እድል ይፈጥራል።
የወላይታ ዞን እና የደቡብ ኢትዮጵያ ቱሪዝም ቢሮም ጊፋታን ከወላይታ ሌሎች የተፈጥሮ፣ የታሪክና የባህል መስህቦች ጋር በማጣመር የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እየሠሩ፤ እየታተሩ ናቸው።
ጊፋታን ከበዓል በላይ ማየት
ጊፋታ ሲከበር ወደ ወላይታ መጓዝ ማለት አንድ ቀን የሚከበር በዓልን ብቻ መመልከት አይደለም።
የዳሞታ ተራራን፣ የአጆራ ፏፏቴን፣ የኤግዘር ድልድይን እና ሌሎች የወላይታ የተፈጥሮና የታሪክ መስህቦችን ከባህላዊ ልምዱ ጋር ማየት ይቻላል። የደቡብ ኢትዮጵያ ቱሪዝም ቢሮ እነዚህን መዳረሻዎች ከጊፋታ ጋር የሚያያዙ የጎብኚ ልምዶች አድርጎ ይዘረዝራል።
ስለዚህ ወደ ወላይታ ሂዱ።
በጊፋታ ወቅት ባህሉን ይመልከቱ፤ የወላይታን ሙዚቃ ይስሙ፤ የባህላዊ ውዝዋዜውን ይመልከቱ፤ ከሕዝቡ ጋር ይገናኙ፤ የበዓሉን የእርቅና የአብሮነት መልዕክት ይረዱ።
ከዚያም የወላይታን ተፈጥሮ፣ ታሪክና ሕያው ባህል ለመረዳት ዓመቱን ሙሉ መመለስ ይቻላል።
ጊፋታ — የወላይታ ኩራት፣ የኢትዮጵያ ቅርስ፣ የዓለም ሕያው ባህል
ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፈው ጊፋታ የወላይታ ሕዝብ የዘመን መለወጫ በዓል ብቻ አይደለም።
የተራራቁን የሚያቀራርብ፣
የተጣሉትን የሚያስታርቅ፣
የተረሳውን የሚያስታውስ፣
ቤተሰብን የሚያሰባስብ፣
ትውልድን ከትውልድ የሚያገናኝ፣
ያለፈውን በይቅርታ ተሻግሮ የወደፊቱን በተስፋ ለመቀበል የሚያስችል ሕያው የባህል ቅርስ ነው።
ዮ…ዮ… ጊፋታ!
ዮ…ዮ… ወላይታ!
እንኳን ለጊፋታ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን!
ሀሹ ቆሬናን ሻኬናን ኡባካ ሳሮ ጋቴስ!
የጊፋታ በዓል የሰላም፣ የዕርቅ፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የአብሮነትና የተስፋ ይሁንልን!
#gifaataa #wolaita #unesco #wolaitadunguzza #culturalheritage #visitwolaita #visitethiopia

21 days ago
የናፍቆት ማሳረጊያው የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ‘ጊፋታ’
*****************
በመስከረም ወር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ 'ጊፋታ' በዓል አንዱ ሲሆን፣ ጥልቅ ማህበራዊ፣ ሥነ-ልቦናዊ እና ሞራላዊ እሴቶችን በውስጡ አቅፎ የያዘ ነው፡፡
"ኪያዳ ኪያዳ ሞካ ታና ታዬ!" መጥቼልሻለሁ ወጥተሸ ተቀበይኝ እናቴ! የሚል ትርጉም ያለው የድምፃዊት ትዕግስት ወይሶ ሙዚቃ፤ ድምፅ የናፍቆት ነው፤ ዜማው የርቀት ነው፤ ጥሪው የልጅነት ትዝታን አዝሎ፣ የኑሮን ውጣ ውረድ ተቋቁሞ፣ ከወራት መለየት በኋላ ወደ እናት ጉያ የሚደረግን ጉዞን የሚያሳይ ነው።
መስከረም ጠባ ማለት ኑሮን ለማሸነፍ ሲል ከትውልድ ቀዬው ለራቀው ወጣት የልብ ትርታው የሚጨምርበት ወቅት ነው። ‘ጊፋታ’ የዘመን መለወጫ ብቻ ሳይሆን፣ የቤተሰብ መገናኛ ድልድይም ጭምር ነው።
ወጣቱ በአካል ተገኝቶ የናፈቀችውን እናቱን ሲስም፣ መከታ የሆነውን አባቱን ሲያቅፍ፣ በስስት የሚያያቸውን እህት ወንድሞቹን እና የልጅነት አብሮ አደግ ጓደኞቹን ሲያገኝ ደስታው እጥፍ ድርብ ይሆናል። ድምፃዊት ትዕግስት ወይሶ በዜማዋ እንዳንቆረቆረችው፣ የጊፋታ ወቅት 'ተናፋቂ' የሚሆነውም ለዚህ ነው።
የኑሮ ግዴታ ሆኖበት በአካል ወደ ቤተሰቡ መሄድ ላልቻለው ወጣት ጊፋታ የኃላፊነት መወጫ ነው። ካለበት ሆኖ፣ በላቡና በትጋቱ ካገኘው ገንዘብ ቀንሶ ለቤተሰቦቹ በመላክ በዓሉ ደምቆ እንዲውል ያደርጋል። ይህ ድርጊት በወላይታ ማህበረሰብ ውስጥ ያለውን ጠንካራ የቤተሰብ ትስስር እና መረዳዳት የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው።
በዓሉ ከመድረሱ በፊት ያለው የቅድመ ዝግጅት ድባብ ራሱን የቻለ አንድ በዓል ነው። እናቶችና ሴቶች ባህላዊ ምግቦችን ለማሰናዳት ይዘጋጃሉ። ሙቾ፣ ቆጮ፣ ቂጣ፣ ባጭራን የመሳሰሉ ባህላዊ ምግቦችን እና ጠረኑ የሚያውደውን ዳጣ ሲያዘጋጁ፤ እነዚህን ምግቦች ለማወራረድ ደግሞ 'ቦርዴ' የተሰኘው ባህላዊ መጠጥ ይጣላል።
የጊፋታ በዓል ትልቁ ዕሴት ደግሞ አብሮነትን ማጉላት ነው፡፡ ማህበረሰቡ ለበዓሉ የሚታረዱትን ከብቶች በጋራ ይገዛል፣ የሥጋ ማከፋፈሉ ሥራ በወንዶች በኩል በፍትሃዊነት ይከናወናል። ቤተሰብ እና ጎረቤት በአንድነት ተሰባስቦ በአንድ ማዕድ ይቋደሳል። ይህ ሥርዓት፣ በዘመናዊው ዓለም እየጠፋ የመጣውን 'አብሮነትን' እና 'ጉርብትናን' በተግባር ያሳያል።
ጊፋታ ትዝታ ቀስቃሽ እና ዘመድ አስታዋሽ ብቻ አይደለም፤ ዕርቅ አንጋሽም ነው። በወላይታ ባህል ማንም ሰው በልቡ ቂም ይዞ፣ ወንድሙን አስቀይሞ ወይም ከጎረቤቱ ጋር ተጣልቶ ጊፋታን አያከብርም።
አዲሱ ዓመት ሲመጣ የተጣላ ይታረቃል፤ የተቀያየመ ይቅርታ ይደራረጋል። ቂምና በቀልን በአሮጌው ዓመት ጥሎ፣ አዲሱን ዓመት በንፁህ ልብ መቀበል የሕዝቡን አንድነትና ሰላም የሚያስጠብቅ፣ የማህበራዊ ትስስር ዋልታ ነው። አባቶችም አዲሱን ዓመት አዲሱ ትውልድ በሰላም እንዲያልፈው ይመክራሉ፣ ይመርቃሉም።
የበዓሉ ሌላው ማሳረጊያ እና ድምቀት የ'ጉልያ' ወይም የችቦ ማብራት ሥርዓት ነው። ችቦ ሲበራ ተምሳሌታዊ ትርጉሙ ጥልቅ ነው። ማህበረሰቡ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሐዘን ወደ ደስታ፣ ከክረምት ጭቃ ወደ በጋው ፀዳል መሸጋገሩን ያበስራል።
በዚህ የብርሃን ጅማሮ ወቅት "ሃያያ ለኬ" የተሰኘው የጊፋታ ባህላዊ ዘፈን በወጣቶች እና በጎልማሶች አንደበት ይንቆረቆራል። ወጣቶች በየቤቱ እየዞሩ መልካም ምኞታቸውን በዘፈን ይገልጻሉ። ሁሉም በአንድ ድምፅ፡ "ሃሹ ላይታፔ ላይታ ሰሯን ጋቲስ!" (ከዓመት ወደ ዓመት እንኳን በሰላም አሸጋገረን) እያሉ ሀገርን በሰላም ላቆየው ፈጣሪ ምስጋና ያቀርባሉ።
ጊፋታ በቀን መቁጠሪያ ላይ ያለ አንድ ዕለት ብቻ አይደለም። ጊፋታ የወላይታ ሕዝብ ፍቅርን፣ ሰላምን፣ መተሳሰብን እና ኩራቱን ለትውልድ የሚያስተላልፍበት ትልቅ የህይወት መድረክ ነው።
ብርሃን ሲፈነጥቅ ጨለማ እንደሚገፈፈው ሁሉ ጊፋታ ሲመጣ ቂም ይረግፋል፤ ፍቅር ያብባል፤ አብሮነት ይፀናል።
በሲሳይ ደበበ
#ethiopia #ebc #gifata #wolaita #culturalheritage

2 months ago
ቶልሷ፦ ተወዳጁ የወላይታ ጥሬ ስጋ እና ማህበራዊ እሴት!
#ethiopia | ጥሬ ስጋ በወላይታ ህዝብ ዘንድ የምግብ አይነት ብቻ ሳይሆን፤ ከማህበራዊ እሴት፣ ከበዓላትና ከከፍተኛ የእንግዳ አቀባበል ስነ-ስርዓት ጋር የተሳሰረ የጠበቀ ባህል ነው።
በወላይታ ባህል የታወቁ የጥሬ ስጋ አዘጋጃጀት አይነቶች፦
ቶልሷ (ቁርጥ ሥጋ)፦ የወላይታ አዲስ ዓመት (ግፋታ) ሲከበር በተለየ ሁኔታ ከተቀለበ ሰንጋ በሬ ተመርጦ የሚዘጋጅ፣ ከዋና ዋና የጮማ እና የቀይ ስጋ ክፍሎች የሚቀርብ ልዩ ቁርጥ ነው።
ሱልሷ፦ ምንም ጮማ ሳይቀላቀል ቀይ ስጋ ብቻ ተመርጦ በደቃቁ ከተከተፈ በኋላ ከነጠረ ቅቤ ጋር ተሰርቶ "ሞቂያ" በተሰኘ ባህላዊ ማንኪያ የሚበላ ነው። ይህ ምግብ በተለይም ለአባወራ እና ለክብር እንግዳ የሚቀርብ እጅግ ተወዳጅ ባህላዊ ምግብ ነው።
አሿ ጢጣ (ጥብስ)፦ ገና በእሳት ላይ ሲጠበስ ምራቅ የሚያስውጥ፣ ልዩ ጣዕም ያለውና በጥብስነቱ በእጅጉ የሚወደድ ነው።
የአቀራረብ ስነ-ስርዓት
ጥሬ ስጋ ብቻውን አይበላም!
በቅመማቅመም እና በቅቤ ከተለወሰው "ሳዎ ባምባሪያ" (ዳታ በርበሬ) ጋር ይጣቀሳል።
ከእንሴት ውጤት ቆጮ (ጎዴታ ኡንጫ) እና ከበቆሎ ቅጣ (ባዳላ ኦይታ) ጋር በመሶብ ዙሪያ አምሮ ይቀርባል።
ዳታው የሚቀርበው "ሻትያ" በተሰኘ ባህላዊ የሸክላ እቃ ላይ ተደርጎ ነው።
"እማታ ፓያ ኤሆ" (መልካም እንግዳ ያምጣልን!)
የወላይታ ሰው እንግዳ አሳቦ ስጋ መብላት ስለሚወድ ሁልጊዜ መልካም እንግዳ እንዲመጣ ይመኛል። ድንገት እግር ጥሎት ወደ ወላይታ የመጣ እንግዳ ጥሬ ስጋ በዳታ አጣቅሶ ሳይበላ አይመለስም—በላ ማለት ደግሞ ቤተኛ ሆኖ የመቅረት ዕድሉ ሰፊ ነው!
በሴፉ ሳሙኤል
#wolaita #ethiopianfood #culture #tolsuwa #sulsuwa #ethiopia #giphata #traditionalfood

3 months ago
"ከተፈጥሮ ጥበቃ ዶላር ማግኘት እንደሚቻል ማሳያ የሆነው የሁምቦ የደን ካርበን ፕሮጀክት"
********************
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንጹሕ ልማት ሥርዓት ተመዝግቦ የሚገኘውና በአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው የወላይታ ሁምቦ የደን ካርበን ፕሮጀክት፣ በተራቆቱ ተራሮች ላይ አዲስ ሕይወት በመዝራት የአየር ንብረት መዛባትን መከላከል እንደሚቻል ትልቅ ማሳያ እየሆነ ይገኛል።
ይህ ብቻ ሳይሆን፣ ከተፈጥሮ ጥበቃ ተጨባጭ የውጭ ምንዛሬ (ዶላር) ማግኘት እንደሚቻልም በተግባር ያሳየው ይህ ፕሮጀክት፤ በአፍሪካ አንደኛ፣ በዓለም ደግሞ ንጹሕ የደን ልማት ዘዴ ተጠቃሽ ፕሮጀክት ሆኖ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በይፋ ተመዝግቧል።
በወላይታ ዞን በ2 ሺህ 728 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ፕሮጀክት፣ ቀደም ሲል ጠፍተው የነበሩ ከ70 በላይ የአገር በቀል የዛፍ ዝርያዎች ተመልሰው እንዲያንሰራሩ ያደረገ ነው።
የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል ረገድም ይህ ፕሮጀክት በዓመት በአማካይ ወደ 29 ሺህ 343 ሜትሪክ ቶን በላይ የካርቦን ዳይኦክሳይድ ጋዝ ከከባቢ አየር ውስጥ እንደሚያስወግድ ይታመናል።
በዛፎች ዕድገት እና በአየር ንብረት መለዋወጥ ውጤቶች ላይ በመመስረት ትክክለኛው የሚወገደው የካርቦን መጠን ከዓመት ዓመት ሊለያይ ቢችልም፤ 29 ሺህ343 ቶን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንጹሕ ልማት ዘዴ ምዝገባ ላይ የተቀመጠ ይፋዊ አማካይ ስሌት በመሆኑ፣ ለአለም አቀፉ የአየር ንብረት መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
ይህ ስኬት ሊመዘገብ የቻለው “በአርሶ አደር የሚመራ የተፈጥሮ ደን መልሶ ማልማት የተባለውን ሳይንሳዊና ባህላዊ ጥበብ በማቀናጀት ደኑን በተደራጀ መልኩ በመንከባከብ ነው። በዚህም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንጹሕ ልማት ዘዴ መስፈርቶችን በአግባቡ በማሟላቱ በአህጉሪቱ ቀዳሚው ተጠቃሽ ፕሮጀክት ሊሆን ችሏል።
ደኑን ከመጠበቅ ባሻገር ለአካባቢው ማኅበረሰብ ዘላቂ የገቢ ምንጭ መፍጠር የቻለው ይህ ፕሮጀክት፤ በአሁኑ ወቅት 7 የደን ልማትና ጥበቃ የኅብረት ሥራ ማኅበራት በአንድ ዩኒየን ሥር ተደራጅተው ደኑን በባለቤትነት እየጠበቁት ይገኛል።
እነዚህ ማኅበራት በዓለም አቀፉ የበጎ አድራጎት ድርጅት "ዎርልድ ቪዥን" ድጋፍና አስተባባሪነት፣ የካርበን ፕሮጀክት ክሬዲትን ለዓለም ባንክ በመሸጥ በየዓመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ዶላር ገቢ እያገኙ ነው። ይህም ለአካባቢው ነዋሪዎች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የጤና መሻሻልን ለማምጣት ትልቅ አቅም ፈጥሯል።
የሁምቦ ፕሮጀክት ያሳየው ተጨባጭ ስኬት ኢትዮጵያ በረጅም ጊዜ ዕቅዷ በ2050 ዓ.ም የተለያዩ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከያ ስትራቴጂዎችን በመተግበር፣ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን የበካይ ጋዝ ወይም የካርበን ልቀት ፍጹም ዜሮ ለማድረግ ለጀመረችው አገራዊ ጉዞ ትልቅ ማሳያና አቅም የሚሆን ነው።
አሁን ላይ ይህ ስኬት ተስፋፍቶ በወላይታ ዞን ዳሞታ ተራራን ፕሮጀክት ጨምሮ በ9 ወረዳዎች ከ22,000 ሄክታር በላይ መሬት በካርበን ፕሮጀክት እየለማ የሚገኝ ሲሆን፤ 48 የደን ማኅበራት እና 3 የደን ዩኒዮኖች በዚሁ አረንጓዴና ትርፋማ ፕሮጀክት ላይ በንቅናቄ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በትዕግስቱ ቡቼ
#ebc #humbocarbonproject #wolaita #climateaction #greeneconomy

4 months ago
በአሰቃቂ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ
#ethiopia | ከአልቾ ውሪሮ ወረዳ 18 ተጓዦችን አሳፍሮ በጠረጋ ከተማ በኩል ወደ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ አንድ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሰዓታት በፊት ከመስመር ውጭ በመውጣት ወደ ገደል ወድቋል።
በዚህ አሰቃቂ አደጋም በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል።
በደረሰው አደጋ ምክንያት እናቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶችና አባቶችን ያካተቱ 11 ተጓዦች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን፣ ከአሽከርካሪ ጋር ሌላ ሁለት ሰዎች በድምሩ ሦስት ግለሰቦች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶ የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።
በአንጻሩ ሁለት ህጻናትን ጨምሮ አራት ተጓዦች ከአደጋው ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው በሰላም ለመትረፍ ችለዋል።
የአልቾ ውሪሮ ወረዳ አስተዳደር በአደጋው ህይወታቸውን ያጡትን ወገኖች አስክሬን ከቡታጀራ ሆስፒታል ወደ ወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በማጓጓዝ ለቤተሰቦቻቸው የማስረከብ ስራ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
በተመሳሳይ ሁኔታ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች በቡታጀራ እና በወራቤ ሆስፒታሎች ተገቢውን የህክምና ክትትል እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ይገኛል።
#trafficaccident #roadsafe #ethiopianews #wolaita #butajira #worabe #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Sponsored by
Surafel
8 months ago
የወላይታ ሶዶ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ በይፋ ተጀመረ!
#ethiopia | "የወላይታን ባህልና ታሪክ የያዘ፣ ከ40 እስከ 45 ሺህ ተመልካች የሚይዝ ግዙፍ ስታዲየም" በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የወላይታ ሶዶ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ ዛሬ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ በባህልና ስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ እና በወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ አማካኝነት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦለታል።
የስታዲየሙ ገፅታዎች:
✅ ደረጃ: የፊፋ (FIFA) እና የካፍ (CAF) ስታንዳርድን ያሟላ።
✅ አቅም: ከ40,000 እስከ 45,000 በላይ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም አለው።
✅ ዲዛይን: የወላይታን ህዝብ ታሪክ፣ ባህላዊ እሴቶች እና የአካባቢውን ገፅታ ያካተተ ነው።
✅ ይዞታ: በ51 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ይሆናል።
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፤ "ይህ ፕሮጀክት የህዝብ ነው፤ ከተባበርንና ካስተባበርን እውን ማድረግ ይቻላል" በማለት፤ የክልሉ መንግስት ለፕሮጀክቱ የሚሆን ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር እንደሚያዘጋጅ ገልጸዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ በበኩላቸው፤ "እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን!" በማለት መላው ህዝብ አሻራውን እንዲያሳርፍ ጥሪ አቅርበዋል።
ዎጌታ ኤፍ ኤም 96.6
#wolaita #stadium #construction #ethiopia
#wolaitasodo #internationalstadium #ethiopia #development #sports #southethiopia

9 months ago
"አንድ እንጀራ ለአንዲት እናት"
በጎ አድራጎት ማህበር የተፈናቀሉ እናቶችን ማዕድ አጋራ
• ከ200,000 ብር በላይ በሆነ ወጪ ድጋፍ ተደረገ
#ethiopia | "አንድ እንጀራ ለአንዲት እናት" በጎ አድራጎት ማህበር፤ በካዎ ኮይሻ ወረዳ በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ተፈናቅለው በአበላ አባያ ወረዳ ሰፍረው ለሚገኙ አቅመ ደካማ እናቶች እስከ መኖሪያ ስፍራቸው ድረስ በመጓዝ የምግብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
ማህበሩ ከ201,000 (ሁለት መቶ አንድ ሺህ) ብር በላይ ወጪ በማድረግ የገዛውን ዘይት እና ዱቄት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳደር ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ እና ሌሎች የዞኑ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በይፋ አስረክቧል።
የኃላፊዎች መልዕክት፡-
👤 ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ (የወላይታ ዞን ዋና አስተዳደር)፦
በዚህ በጎ ተግባር ላይ ለተሳተፉ አካላት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፤ "እንደዚህ ዓይነት በጎ ተግባራት በዞኑ ውስጥ በሚሰሩ ማህበራትና ግለሰቦች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የመንግስት ድጋፍና ክትትል አይለያቸውም" ብለዋል።
👤 ወጣት ስንታየሁ ሾላቶ (የማህበሩ ሰብሳቢ)፦
ማህበሩ ድንበር የሌለው እና ሰብዓዊነትን ብቻ መሠረት አድርጎ የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል። "ከትንሽ የበጎ ተግባራት ተነስቶ በሕዝቡ ዘንድ ተወዳጅነት እያተረፈ ወደዚህ ደረጃ ደርሷል" ያሉት ሰብሳቢው፤ በቀጣይም ከተለያዩ በጎ ፈቃደኞች ጋር በመተባበር ሰፊ እና ተጽእኖ ፈጣሪ ስራዎችን ለመስራት ማቀዳቸውን ተናግረዋል።
በጎነት ለራስ ነው!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#wolaita #charity #andenjeraleanditenat #humanity #abelaabaya #ethiopia

1 year ago
10 ሺህ ዜጎችን ተደራሽ የሚያደርገው ነጻ የሕክምና አገልግሎት
#ethiopia | በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ1 ሳምንት የሚቆይ የነጻ ሕክምና አገልግሎት እየተሰጠ ነው፡፡
ነጻ የሕክምና አገልግሎቱ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል ሲሆን ለ10 ሺህ ዜጎች ተደራሽ እንደሚሆን የሆስፒታሉ የጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ወኪል ወልዴ ገልጸዋል፡፡
ሆስፒታሉ ይህንን አገልግሎት ለመስጠት በተዘጋጀበት ወቅት ባለፈው ወር ድንገተኛ የእሳት አደጋ መከሰቱን ያስታወሱት ዶ/ር ወኪል ፤ በፈተናም ውስጥ ቢሆን ዕቅዱን ተግባራዊ ማድረግ መቻሉን ነው የተናገሩት።
በጎ ፈቃደነኛ ሐኪሞችን ጨምሮ መደበኛ ሐኪሞች ከሥራ ሰዓት ውጪ ይህንን ሥራ እንደሚደግፉም አስታውቀዋል።
አገልግሎቱን ከበጎ ፈቃደኛ ሀኪሞች ጋር በቅንጅት መስጠት መቻሉ የዘንድሮውን መርሐ-ግብር ለየት እንደሚያደርገውም ነው አክለው የገለጹት።
የራዲዮ ኢትዮጵያ ግብረሰናይ ድርጅት መስራች ዶ/ር ልሳነወርቅ ሆንሴቦ በበኩላቸው ይህ ሥራ 14ኛ የዘመቻ ተግባር መሆኑን ገልጸው፤ በአንድ ሳምንት ቆይታ ለ10 ሺህ ሰዎች ነጻ ምርመራና የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።
ስፔሻሊስቶችን ጨምሮ 15 የሕክምና ባለሙያዎች በነጻ አገልግሎቱ ተሳታፊ እንደሚሆኑም ጠቅሰዋል።
የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በሰጡት አስተያየት ሕክምናው ወጪ እና ጊዜ የሚቆጥብ ከመሆኑ ባሻገር፣ የጤና ሁኔታቸውን ለይተው እንዲያውቁ ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።
በተመስገን ተስፋዬ
#ebc #freemedicalservice #wolaita

Comments