Logo
FastMereja
“አደይ አዲስ ዓመት ታላቅ የንግድ ኤክስፖ እና ፌስቲቫል” ይፋ ሆነ

​#fastmereja I የ2019 አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ በአዲስ ኮንቬንሽን ሴንተር ሊካሄድ የታቀደው “አደይ አዲስ ዓመት ታላቅ የንግድ ኤክስፖ እና ፌስቲቫል” ይፋ ተደርጓል። ኤክስፖው ከነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 05 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለ15 ቀናት እንደሚቆይ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

​ይህ ታላቅ የንግድ እና የፌስቲቫል መድረክ በማስተር ፒስ ትሬዲንግ እና ራይት ኤቨንትስ ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን፣ አዘጋጆቹ ለሚዲያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት ዝግጅቱ ለስሚት እና ለአካባቢው ነዋሪዎች የገበያ አማራጮችን በቅርበት የሚያቀርብ ነው። በኤክስፖው ላይ ከ200 በላይ የሀገር ውስጥ አምራቾች፣ አስመጪዎች፣ የዕደ-ጥበብ ባለሙያዎች እና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ምርትና አገልግሎታቸውን በተፎካካሪ እና በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚያቀርቡ ተገልጿል።

​ከንግድ እንቅስቃሴው ጎን ለጎን ፌስቲቫሉ በየቀኑ 15 አርቲስቶች የሚሳተፉበት የቀጥታ የሙዚቃ ኮንሰርት፣ የፋሽን ሾው፣ የህፃናት መጫወቻዎች እና የበጎ አድራጎት ስራዎችን ያካተተ እንደሚሆን ተጠቅሷል። በተጨማሪም የኪነ-ጥበብ መድረኮችን ጨምሮ የመጽሐፍት አውደ ርዕይ እና ሽያጭ ይካሄዳል።

በ15 ቀናቱ የፌስቲቫል ቆይታ ከ80,000 በላይ ጎብኚዎች እና ደንበኞች ይገበያያሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ አዘጋጆቹ ቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናቀው የኤግዚቢሽን ቦታዎችን በመሸጥ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
#ኹነት

5 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.