9 days ago
«ግራንድ ኢሬቻ ቦክስ ምሽት» መስከረም 22 ይካሄዳል
#fastmereja I በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም የሚካሄደው «ግራንድ ኢሬቻ ቦክስ ምሽት» የቦክስ ውድድር በመጪው መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም ምሽት እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታወቁ። ይህን ታሪካዊ ስፖርታዊ ዝግጅት በአፍሮ ኮ ትሬዲንግ እና ኤችኬ ኤንተርቴይንመንት ከአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት እንደሆነ ተገልጿል።
በዚሁ የስፖርት ምሽት ሰባት የወንዶች እና አንድ የሴቶች ውድድርን ጨምሮ በአጠቃላይ ስምንት የቦክስ ፍልሚያዎች ይካሄዳሉ። በውድድሩ ላይ የሚሳተፉት ተወዳዳሪዎች ከ48 እስከ 64 ኪሎ ግራም ክብደት ባላቸው የውድድር መደቦች የሚፋለሙ ሲሆን፣ ለዚህ ትልቅ ውድድር ላለፉት ዘጠኝ ወራት ያህል ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸውን በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ተገልጿል። #ኹነት

1 month ago
6ኛው “Arki Homes Expo" ከ20 በላይ የሪል እስቴት አልሚዎችን በማሰባሰብ ሊካሄድ ነው!
#fastmereja :- በአዲሱ ዓመትና በመስቀል በዓል ምክንያት ወደ ሀገራቸው የሚገቡ ዳያስፖራዎችን እና የሀገር ውስጥ ቤት ፈላጊዎችን ማዕከል ያደረገው 6ኛው "Arki Homes Expo” ከመስከረም 8 እስከ 10 ቀን 2019 ዓ.ም በጊዮን ሆቴል ሊካሄድ መሆኑ በዛሬዉ እለት በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።
“በአዲስ ዓመት አዲስ ቤት” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ይህ ኤክስፖ፣ ከ20 በላይ ታዋቂ፣ ታማኝ እና በግንባታ ጥራታቸው የሚታወቁ የሪል እስቴት አልሚዎችን በአንድ መድረክ የሚያሰባስብ መሆኑ ተገልጿል።
ዝግጅቱ ቤት የመግዛት እቅድ ያላቸው ወገኖች ከብዙ አማራጮች መካከል መርጠው በቂ መረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ እንዲወስኑ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተመልክቷል።
የዝግጅቱ ተሳታፊ የሆኑት ቴምር ሪል እስቴት፣ ሜሪት ፕሮፐርቲስ እና ጃንቦሮ ሪል እስቴት ከአዘጋጆቹ ጋር በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች በከፍተኛ ጥራትና ፍጥነት የገነቧቸውን የመኖሪያ ቤቶችና ሱቆች በልዩ የበዓል ቅናሽና አመቺ የክፍያ አማራጮች ማዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።
ከዚህ ቀደም በሚሊኒየም አዳራሽና በስካይላይት ሆቴል ይዘጋጁ የነበሩትን ኤክስፖዎች በማስፋፋት፣ ዘንድሮ በጊዮን ሆቴል ቤተሰቦች ከልጆቻቸው ጋር መጥተው እየተዝናኑ የሚገበዩበት ሰፊ የመጫወቻና የመዝናኛ ስፍራ መዘጋጀቱ ተገልጿል።
የኤክስፖው ዋና ዓላማ ገዥዎችንና አልሚዎችን በቀጥታ ማገናኘት፣ ለአልሚዎች የገበያ ዕድል መፍጠር እንዲሁም ህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የቤት ባለቤት እንዲሆን ማስቻል መሆኑን አዘጋጆቹ ገልጸው፤ ቤት ፈላጊዎች ኤክስፖውን ሳይጎበኙ የግዢ ውሳኔ እንዳይወስኑ ጥሪ አቅርበዋል።
#ኹነት

በጥርስ ሕክምና የላቀ አፈጻጸም ላላቸው ተቋማትና ባለሙያዎች እውቅና ሊሰጥ ነው!
#fastmereja I በጥርስ ሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የሕክምና ተቋማትና ባለሙያዎች እውቅና ለመስጠት የተዘጋጀ አዲስ የሽልማት መርሃ-ግብር በዛሬዉ እለት በሳፋየር አዲስ ሆቴል በተሰጠ መግለጫ ይፋ ተደርጓል።
መርሃ-ግብሩ በአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን (AAFDA) እና በሮባ መልቲ ሚድያና ኢቬንትስ ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን፣ ትግበራው በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት 2019 ዓ.ም እንደሚከናወን ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ሙሉእመቤት ታደሰ እንደገለጹት፤ መርሃ-ግብሩ በህግ ከተሰጣቸው ቁጥጥርና ፈቃድ የመስጠት ኃላፊነት ባሻገር፣ ጥራታቸውን ጠብቀው የሚሰሩ የጤና ተቋማትን በማበረታታት ለአገልግሎት ተቀባዩ ማህበረሰብ የተሻለ የጤና ዋስትና ለመስጠት ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።
አክለውም፣ መርሃ-ግብሩ የጥርስ ሕክምና ማዕከላትን አቅም በመገንባት፣ የልምድና የዕውቀት ሽግግር በመፍጠር እንዲሁም የሀገሪቱን የሕክምና ቱሪዝም (Medical Tourism) በማሳደግ አዲስ አበባን በአፍሪካ የጥርስ ሕክምና ማዕከል ለማድረግ ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል።
አሸናፊዎች የሚለዩባቸው ዋና ዋና የምዘና መስፈርቶች፦የባለስልጣኑ ሙያዊ ምዘና (70%)፦ በኢትዮጵያ ስታንዳርድ ኤጀንሲ መስፈርት መሰረት ተመዝነው 75% እና ከዚያ በላይ ያገኙ ተቋማት የሚካተቱ ሲሆን ሌላኛዉ
የሕዝብና የደንበኞች ድምፅ (30%)፦ አገልግሎት በሚያገኙ ደንበኞች የቀጥታ ድምፅ (Vote) እንደሚወሰንም ነዉ የተገለፀዉ።
በአጠቃላይ በ15 የሙያ ዘርፎች እውቅና የሚሰጥ ሲሆን፤ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ በኢንፌክሽን ቁጥጥር፣ ለህጻናትና ለአካል ጉዳተኞች ምቹ አካባቢ በመፍጠር፣ በኮስሞቲክ ሕክምና፣ በላቦራቶሪ ብቃት ፣በማህበረሰብ ግንዛቤ ማሳደግ እንዲሁም በሌሎችም ዘርፎች የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው ተቋማትና ባለሙያዎች የሚሸለሙ ይሆናል።
ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው ይህ የእውቅና መርሃ-ግብር በየዓመቱ ደረጃውን ጠብቆ የሚቀጥል ሲሆን፣ የውድድሩን ሂደትና መረጃዎች ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ይፋዊ ድህረገጽ እና የማህበራዊ ሚዲያ ቻናሎች መከፈታቸው ተገልጿል።

ዩጎ ሲቲ ቸርች ቦሌ አጥቢያ ላይ ትልቅ የአምልኮ ፕሮግራም ሊካሄድ ነው!
#fastmereja I ሙዚቀኛውና የአምልኮ ፕሮግራም አዘጋጁ ዮሐንስ ዋጋሪ ከአሜሪካና ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የአምልኮ መድረኮች ቆይታ በኋላ፣ በኢትዮጵያ ታላቅ የአምልኮ ፕሮግራም ለማዘጋጀት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን በዛሬዉ እለት በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደተገለጸው፣ ይህ ፕሮግራም ከአንጋፋና ከአዳዲስ ዘማሪዎች ጋር በመቀናጀት የተዘጋጀ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም የወንጌል ስርጭትን ማስፋፋትና አምልኮን ማቅረብ መሆኑ ተገልጿል።
ዮሐንስ ዋጋሪ ቀደም ሲል በአሜሪካ 18 ስቴቶች እንዲሁም በአውስትራሊያና በሌሎች ሀገራት ተመሳሳይ ፕሮግራሞችን ሲያዘጋጅ የቆየ ሲሆን እድሉ የሌላቸውን አዳዲስ ዘማሪዎችና ባለጸጋዎችን በነፃ በስቱዲዮ በማስተናገድና በመደገፍ ይታወቃል።
ይህ የአምልኮ መድረክ በከፍተኛ ጥራትና የላቀ ዝግጅት (Excellence) የሚቀርብ ሲሆን፣ የቃሉን አገልግሎት የሚያካፍሉ አገልጋዮችም አብረው እንደሚሳተፉም ነዉ የተገለፀዉ።
የዜማ ዮሐንስ ፕሮጀክት (Zema Yohannes Project) ከተጀመረ ከ10 ዓመታት በላይ እንሆነዉ የተገለፀ ሲሆን በወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጎ አዳዲስ ዘማሪዎችን እንደሚያበራታ እና የወንጌል ስርጭት ስራዎችን እንደሚሰራ ገልጿል።

"አዲሱ የዓለም ስርዓት" መፅሐፍ ተመረቀ
#fastmereja I በኪንግ ታደለ ድሪባ የተደረሰዉና የአዕምሮ እንዲሁም የፍልስፍና ውጤት የሆነው "አዲሱ የዓለም ስርዓት" የተሰኘው አዲስ መፅሐፍ እሁድ ነሐሴ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በኩሪፍቱ ሪዞርት ተመርቋል።
ይህ መፅሐፍ በዋናነት በዓለም ላይ የህዝቦች እኩልነት፣ ፍትህና ወንድማማችነት በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲሰፍን ከተፈለገ ዓለም በአንድ መንግስት፣ በአንድ ንጉስ እና በአንድ የገንዘብ ኖት ብቻ መመራት አለባት የሚለውን የፍልስፍና ሐሳብ መነሻ ያደረገ ነው ተብሏል። ጽሁፉ "ይህ አስተሳሰብ በምን መልኩ ወደ ተግባር ሊለወጥ ይችላል?" ለሚሉ ጥያቄዎች ሰፊ ምላሽ ለመስጠት ያለመ ሲሆን፣ ጉዳዩን ከኢኮኖሚ፣ ከመልከዓ ምድር፣ ከተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም፣ ከአካባቢ ጥበቃ፣ ከሐይማኖት፣ ከባህልና ከአጠቃላይ ማህበራዊ ጉዳዮች በስፋት ዳስሶ እንደሚያቀርብ ነው የተነገረው።
መፅሐፉ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ለማድረግ ሲባል በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች ተዘጋጅቶ ለንባብ የበቃ ሲሆን፣ በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙ ተጋባዥ እንግዶችና የዘርፉ ባለሙያዎች የመፅሐፉን ፍልስፍናዊ ይዘትና የቀረቡትን አማራጭ ሀሳቦች በተመለከተ ዳሰሳ እና ውይይት አድርገዋል።

2 months ago
የምንመካከረው በብሔራዊ መግባባት አገርን ለማጽናት እንጂ የቡድን የበላይነትን ለማንበርና ሌላ አዲስ የእርስ በእርስ ጦርነት ለማዋለድ አይደለም!
በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ዙሪያ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ የአቋም መግለጫ
ኢትዮጵያ ሀገራችን እያለፈችበት ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመፍታት በምክክር ብሔራዊ መግባባት በመፍጠር አገር ልትጸና ይገባል በሚል ጽኑ እምነት ፓርቲያችን የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል። በአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምሥረታው፣ በኮሚሽነሮች አመራረጥና በኮሚሽኑ የአሠራር ሂደት፣ የአካታችነት ችግሮች፣ እየተካሄዱ ያሉ ጦርነቶች በሚያሳድሩት አሉታዊ ተጽዕኖና መሰል አስቻይ ባልሆኑ ሁኔታዎች ላይ ጠንካራ ሀሳቦችንና የመፍትሔ ጥቆማዎችን ፓርቲያችን ሲያቀርብ መቆየቱም ይታወቃል። ፓርቲያችን በምክክሩ ሂደት እና ከምክክሩ አስቀድሞ ስኬታማ ምክክር ለማካሄድ ሊተገበሩ ይገባቸዋል ብሎ የሚያምንባቸውን ሃሳቦችና ቅድመ ሁኔታዎች በግልጽ አስቀምጦ ያለመታከት ሲያሳስብ የቆየ ቢሆንም ሰሚ ጆሮ በመጥፋቱ አገር ባለችበት ሁኔታ ወደ ምክክር እንድትገባ ተደርጓል። እናት ፓርቲ ይህን በትክክለኛው ጎዳና ተጉዞ በስኬታማ መልኩ ሊጠናቀቅ ቢችል የአገራችን መፃኢ ጉዞ ላይ ትልቅ ምዕራፍ ሊከፍት የሚችልን ሂደት ቅድመ ሁኔታዎች ስላልተሟሉ በማለት በቸልታ ሊመለከተው ያልፈለገ ሲሆን ይልቁን ሂደቱ ውስጥ በማሳተፍ ትክክለኛነቱን ካረጋገጠ ለአገር የሚበጁ ሀሳቦችን በማንሳት ለመሞገት ብሎም በተመካካሪዎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ በማድረግ በጎ ተጽዕኖ መፍጠርን በማሰብ በምክክሩ እየተሳተፈ ይገኛል።
አገር የገባችበት ችግር ከምንጊዜውም ይልቅ በተወሳሰበበት ሁኔታ ውስጥ የምክክሩ ሂደት ከነችግሮቹ እያነከሰ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ ምክክር ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እየተሸጋገረ ያለ ቢሆንም በሂደቱ የጎሉ ችግሮች እየተስተዋሉበት ይገኛል። ለአብነትም በወረዳ ደረጃ ተደረጉ ከተባሉ ምክክሮች ጀምሮ የምክክር ተሳታፊዎች የገዥው ፓርቲ አባላት እና የሥርዓቱ ደጋፊዎች መሆናቸው ሲገለጽ የነበረ ሲሆን በአገር አቀፍ ደረጃ እየተደረገ ባለው በዚህ ምክክርም አብላጫውን ቁጥር የሚይዙ ተሳታፊዎች የገዥው ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች መሆናቸውን መረዳት ችለናል። በምክክሩ ሂደት ድምጾች እንዳይሰሙ መገደብ፣ የአካታችነት ችግሮች፣ የተሳታፊዎች ምርጫና ምደባ፣ የፍትሓዊነት፣ የገለልተኝነት፣ የግልጽነት ማነስ፣ በጸጥታ አካላት ታጅቦ መወያየት፣ የውይይት ተሳትፎውን ለማጥበብ ከውስጥና ከውጭ የሚደረጉ ጫናና ወከባዎች፣ የምክክሩ አጠቃላይ ወለል ወይም ቀይ መሥመር ያለመኖር እና የመሳሰሉ ጉልህ ችግሮች የተስተዋሉበትን እውነታ ታዝበናል።
ምክክሩ ኢትዮጵያን ለማጽናት ሳይሆን እንዳለፈው ጊዜ ስሑት ትርክትና ሕገ መንግሥታዊ መሠረት ያለው የጨቋኝ ተጨቋኝ ትርክት ብሎም ሁሉ ለእኔ ብቻ ፍላጎት በአጠቃላይ ኢትዮጵያን አንደ ሀገር እና ዋና መገለጫ ጌጦቿን ኹሉ ለድርድር ያቀረበ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። በዚኽም የምክክሩን ፍትሓዊነትና ቅቡልነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ሆኖ አግኝተነዋል። ይኽ ደግሞ ፓርቲያችንና ሌሎች ተሳታፊዎች ከሂደቱ ራሳቸውን እንዲያገሉ እያስገደደ ይገኛል።
ምክክር የቅንጦት ጊዜ ኹነት ሳይኾን የቀውስ ጊዜ መፍትሔ ማመንጫ ውጥን ነው። ቀዳሚው ዘርና ጎሳ ላይ የተመሠረተው ፌዴራሊዝም ሀገራችንን ሊያጠፋት ከጫፍ ደርሶ እያለ ይህን ያፈጠጠ አደጋ ሊያስቀር ወይም ሊያለዝብ የሚችል መፍትሔ ይጠበቅ የነበረ ቢሆንም ምልክቱ እንኳ አለመታየቱ እጅግ የሚያስቆጭ ነው። እንዲያውም ገና ምክክሩ ሳይጠናቀቅ አንዳንድ ክልሎችን በስም ተጠርተው ሌላ ክልል ለማዋለድ ምክረ ሀሳብ ሲነሳ ብቻ በደስታ ይጨበጨባል፤ ሌላው ደግሞ ማን ነክቶን እያለ በማን አለብኝነት መግለጫ ይሰጣል። ይህም በዘርና በጎሳ ላይ የተመሠረተ ፖለቲካ ለሀገር አንድነትና ሕልውና ሥጋት መሆኑን አንዱ ማሳያ ነበር። በሌላ በኩል ይህ ምክክር እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ወቅት ቢያንስ ሦስት ክልሎች ላይ ጦርነቶች እየተካሄዱ ነው፤ ሌላውም መጣሁ እያለ ነው። የርስ በርስ ጦርነቱን ጉዳይ ብልጽግናን ጨምሮ ሁሉም ተዋጊ ኃይሎች ወደ ድርድር እንዲመጡ እውነተኛ፣ ጥልቅ ውይይትና ደፋር ምክረ ሀሳብ ይፈልግ የነበረ ቢሆንም ሂደቱ ግን እከከኝ ልከክህ ሆኖ የአንድን ወገን ጥቅምና ፍላጎት ለማስጠበቅ ቀድሞ የተወሰነን ውሳኔ በሀገራዊ ምክክር ስም ቅቡልነት እንዲኖረው ለማድረግ እየተከናወነ ነው። የታሪክና የትርክት መፋለሶች በናኙበት በዚህ ዘመን ቢያንስ እውነት አፈላላጊ ቡድኖችን አዋቅሮ ግማሽ መንገድ እንኳን ማቀራረብ ይገባ ነበር።
እነዚኽንና መሰል አንኳር ጉዳዮች እንጂ የኢትዮጵያ መሪ (ከፕሮቶኮል አንጻር ነው አመክንዮው) ጠቅላይ ሚንስትር ሳይሆን ፕሬዝዳንት መኾን ነው ያለበት ላይ አልነበረም የችግሮቹ ቋጠሮ ያለው። ዙሪያ ዙሪያዋን ሲሏት የነበረችውን አዲስ አበባ በወከባ ብዛት ለአንድ ቡድን ሆ ብሎ ለማሳቀፍና አዲስ የፀብ ግንባር ለመቀስቀስም አልነበረም ለምክክር የተቀመጥነው፡፡ ድሬዳዋ ከየት ወገን ትሑን የሚለው ሀገር ሊያፈርስ ደርሶም አልነበረም በሚሊዮን የሚቆጠር የሀገር ሀብት አባክነን ለምክክር የተቀመጥነው፡፡ በዓለም በልዩነት የምንታወቅበት ዘመን አቆጣጠር አሥሮ ይዞንም አልነበረም ምክክር ያስፈለገን፡፡ በአጠቃላይ የተጠቀሱና መሰል የተስተዋሉ ሳንካዎች ምክክሩ ከታለመለት ዓላማና በሀገሪቱ ያለውን ችግር ከሥሩ ከመፍታት ይልቅ ጠግኖ ለማስቀጠል፣ ለይምሰል የተደረገ፣ የአገዛዝ እና ቡድን(ኖች) ጠባብ ጊዜያዊ ፍላጎት ለማሳካት በሚመስል ሁኔታ እየተከናወነ እንዳለ ይሰማናል። በዚህም በመሠረታዊ የሀገር ሕልውና ጉዳዮች በዋናነት የርስ በርስ ጦርነትን በማስቆም፣ የዘርና ጎሳ ፌዴራሊዝምን ማስቀረት/ማለዘብ እንደ ዋና ግብ መያዝና መሰል የተጋረጡ ፈተናዎች በአግባቡ ተረድቶ እልባት የሚበጅበትን አቅጣጫ ሊያስቀምጥ ያልቻለ ሀገራዊ ምክክር ከመነሻው እንደከሸፈ ለመረዳት ነቢይ መሆን አይጠይቅም።
እናት ፓርቲ ከዚህ በመለስ ባሉ የምክክር አጀንዳዎች እና በምክክር ስም ተላለፉ በሚባሉ ስምምነቶች ላይ ፊርማውን የማያሰፍር መሆኑን ሕዝባችን እንዲያውቅ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡ በዚህም፤
1. ገዥው ፓርቲ በሀገራዊ ምክክሩ ስም ለማሳካት ከሚፈለግ ማንኛውም ፍላጎትና ሀገርን አስይዞ ከሚደረግ የፖለቲካ ቁማር እንዲታቀብ እናሳስባለን።
2. ተመካካሪዎች ለጊዜያዊ ጥቅምና የፖለቲካ ውሳኔዎች ሽፋን ከመስጠት እና በታሪክ ተወቃሽ ከሚያደርጉ ድርጊቶች በመቆጠብ ለሀገርና ለሕዝብ መቆምን በቀረችው አጭር ጊዜም ቢሆን በድፍረት እንዲያሳዩ በአክብሮት እንጠይቃለን።
3. ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀገራዊ ምክክሩ የጥቂት አካላትን ፍላጎት ማስፈጸሚያና ለአዲስ ቁርሾ የሚያዘጋጅ እንዳይሆን ሂደቱን በንቃትና በትኩረት እንዲከታተል እናሳስባለን።
ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!
እናት ፓርቲ
ነሐሴ ፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) እናት ፓርቲ በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለውን ሀገራዊ የምክክር ሂደት በተመለከተ ጥብቅ አቋሙን አንጸባርቋል። ፓርቲው ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ የምክክር መድረኩ አገርን በብሔራዊ መግባባት ከማጽናት ይልቅ የቡድን የበላይነትን ለማንበር እና አዲስ የእርስ በእርስ ጦርነት ለማስነሳት ታልሞ እየተሠራበት መሆኑን ገልጿል። በመሆኑም ከዚህ የምክክር መድረክ በሚወጡ ማናቸውም ስምምነቶች ላይ ፊርማውን እንደማያኖር አስታውቋል።
እናት ፓርቲ በመግለጫው እንዳብራራው ገና ከጅምሩ በኮሚሽነሮች አመራረጥ፣ በአካታችነት እና በወቅቱ በነበሩ ጦርነቶች ዙሪያ ስጋቱን ሲገልጽ ቢቆይም ሰሚ በማጣቱ ሀገሪቱ ወደ ምክክር እንድትገባ ተደርጓል። ፓርቲው ሂደቱን በውስጥ ሆኖ ለማረም እና በጎ ተጽዕኖ ለመፍጠር በማሰብ ተሳትፎ ሲያደርግ መቆየቱን ያስታወሰው መግለጫው፣ ይሁን እንጂ ከወረዳ ጀምሮ እስከ አገር አቀፍ ደረጃ ባለው የምክክር መድረክ አብላጫውን ቁጥር የያዙት የገዥው ፓርቲ አባላት እና የሥርዓቱ ደጋፊዎች መሆናቸውን ታዝቤያለሁ ብሏል።
በተጨማሪም በሂደቱ ድምጾች እንዳይሰሙ መገደባቸው የገለልተኝነት እና የግልጽነት ማነስ፣ በጸጥታ አካላት ታጅቦ መወያየት፣ እንዲሁም የተሳትፎ አድማስን ለማጥበብ ከውስጥ እና ከውጭ የሚደረጉ ወከባዎች የምክክሩን ፍትሐዊነት እና ቅቡልነት ክፉኛ ጥያቄ ውስጥ እንደከተቱት ፓርቲው አስገንዝቧል።
እንደ እናት ፓርቲ እምነት፣ ሀገራዊ ምክክር የቀውስ ጊዜ መፍትሔ ማመንጫ እንጂ የቅንጦት ኹነት አይደለም። በአሁኑ ወቅት ቢያንስ በሦስት ክልሎች ውስጥ ጦርነቶች እየተካሄዱ ባለበት እና ዘርን መሠረት ያደረገ ፌዴራሊዝም ሀገሪቱን አደጋ ላይ በጣለበት ሁኔታ፣ ምክክሩ እነዚህን የህልውና አደጋዎች ለማስቆም አልሞከረም። ከዚህ ይልቅ የችግሩን ሥር በማድበስበስ፣ ፖለቲካዊ ቁማሮች ላይ ማተኮሩን ፓርቲው ተችቷል።
ለአብነትም የሀገሪቱን መሪ ከጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ፕሬዝዳንትነት የመቀየር ጉዳይ፣ አዲስ አበባን ለአንድ ቡድን አሳልፎ ለመስጠት የሚደረግ ወከባ፣ የድሬዳዋ ዕጣ ፈንታ እና የዘመን አቆጣጠርን የመሳሰሉ ርዕሰ ጉዳዮች የሀገሪቱን ወቅታዊ ቀውስ የማይፈቱ እና አዲስ የጸብ ግንባር የሚከፍቱ መሆናቸውን በመግለጫው ተብራርቷል።
እናት ፓርቲ እነዚህ መሰረታዊ ሄደቶች ካልተስተካከሉ በስተቀር ከዚህ በመለስ ባሉ አጀንዳዎች ዙሪያ በሚደረጉ ስምምነቶች ላይ ፊርማውን እንደማያኖር አሳውቋል።
ገዥው ፓርቲ በሀገራዊ ምክክሩ ስም ሀገርን አስይዞ ከሚሠራው የፖለቲካ ቁማር እንዲታቀብ ያሳሰበው ፓርቲው፣ ተመካካሪዎችም ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሽፋን ከመሆን ተቆጥበው ለሀገር እና ለሕዝብ መቆምን በድፍረት እንዲያሳዩ ጠይቋል። በመጨረሻም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ይህ ሀገራዊ ምክክር የጥቂት አካላት ፍላጎት ማስፈጸሚያ እና ለአዲስ ቁርሾ መነሻ እንዳይሆን ሂደቱን በንቃት እና በትኩረት እንዲከታተለው እናት ፓርቲ ጥሪውን አስተላልፏል።

በጅማ ዞን ለሚካሄደው የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ የተለያዩ እንግዶች ጅማ ገቡ!
በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ሰቃ ወረዳ በቡዬ ቀጨማ ቀበሌ ነገ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄደውና ለመላው ኢትዮጵያውያን ጥሪ የቀረበበት የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ዝግጅት መጠጠናቀቁ ተገለጸ። በአገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር ከ800 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል በተያዘው ግብ መሠረት የሚከናወነው ይህ መርሃ-ግብር፤ አረንጓዴ አሻራን በማሳረፍ ረገድ የትውልድ ሀላፊነትን ለመወጣት ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።
ይህ ሀገር አቀፍ አቅጣጫን መሠረት ያደረገ ታላቅ መርሃ-ግብር በግሪን ዌቭ አሊያንስ ሀገር በቀል ግብረ-ሰናይ ድርጅት፣ ከኢፌድሪ ግብርና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዘጋጅነት የቀረበ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ አስፈላጊውን ቴክኒካል ድጋፍ በማድረግ ተሳትፏል።።
ለዝግጅቱ ስኬት በጅማ ከተማ የደረሱ ታዋቂ ግለሰቦች፣ አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ቲክቶክሮች እና የጥሪው ተጋባዦች በዞኑ እና በከተማ አስተዳደሩ፣ በአባ ገዳዎች፣ በሀደ ሲንቄዎች እንዲሁም በሀገር ሽማግሌዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ነገ በሚካሄደው በዚህ ታሪካዊ ኹነት ህብረተሰቡ በነቃ ሁኔታ እንዲሳተፍ አዘጋጆቹ ጥሪ አቅርበዋል።

“አደይ አዲስ ዓመት ታላቅ የንግድ ኤክስፖ እና ፌስቲቫል” ይፋ ሆነ
#fastmereja I የ2019 አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ በአዲስ ኮንቬንሽን ሴንተር ሊካሄድ የታቀደው “አደይ አዲስ ዓመት ታላቅ የንግድ ኤክስፖ እና ፌስቲቫል” ይፋ ተደርጓል። ኤክስፖው ከነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 05 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለ15 ቀናት እንደሚቆይ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
ይህ ታላቅ የንግድ እና የፌስቲቫል መድረክ በማስተር ፒስ ትሬዲንግ እና ራይት ኤቨንትስ ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን፣ አዘጋጆቹ ለሚዲያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት ዝግጅቱ ለስሚት እና ለአካባቢው ነዋሪዎች የገበያ አማራጮችን በቅርበት የሚያቀርብ ነው። በኤክስፖው ላይ ከ200 በላይ የሀገር ውስጥ አምራቾች፣ አስመጪዎች፣ የዕደ-ጥበብ ባለሙያዎች እና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ምርትና አገልግሎታቸውን በተፎካካሪ እና በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚያቀርቡ ተገልጿል።
ከንግድ እንቅስቃሴው ጎን ለጎን ፌስቲቫሉ በየቀኑ 15 አርቲስቶች የሚሳተፉበት የቀጥታ የሙዚቃ ኮንሰርት፣ የፋሽን ሾው፣ የህፃናት መጫወቻዎች እና የበጎ አድራጎት ስራዎችን ያካተተ እንደሚሆን ተጠቅሷል። በተጨማሪም የኪነ-ጥበብ መድረኮችን ጨምሮ የመጽሐፍት አውደ ርዕይ እና ሽያጭ ይካሄዳል።
በ15 ቀናቱ የፌስቲቫል ቆይታ ከ80,000 በላይ ጎብኚዎች እና ደንበኞች ይገበያያሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ አዘጋጆቹ ቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናቀው የኤግዚቢሽን ቦታዎችን በመሸጥ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

Sponsored by
Surafel
3 months ago
በሊንክድኢን ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ የኢትዮጵያ ባለሙያዎችና የይዘት ፈጣሪዎች ሊሸለሙ ነው
#fastmereja :-በኢትዮጵያ በሊንክድኢን (LinkedIn) መድረክ ላይ ንቁ ተሳትፎ ላላቸው የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች እና ባለሙያዎች እውቅና ለመስጠት የተቋቋመው "የሊንክድኢን ቼንጅሜከርስ አዋርድስ ኢትዮጵያ (LCAE)" የመጀመሪያውን የሽልማት ስነ-ስርዓት ሊያካሂድ መሆኑን በዛሬዉ እለት በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።
ይህ መርሃ ግብር የፊታችን ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም (August 1, 2026) በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ቲያትር አዳራሽ በደመቀ ሁኔታ ይካሄዳል።
በጉሩጂ ኤአር ኢትዮጵያ ከዥማ ሚዲያና ፕሮዳክሽን ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ የክብር ምሸት ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎችና የልማት አጋሮች የሚታደሙ ሲሆን፤ በህዝብ ጥቆማ፣ በድምፅ አሰጣጥ እና በባለሙያዎች ጥብቅ ግምገማ ያለፉ ድንቅ እጩዎች ሽልማት ይበረከትላቸዋል።
የጉሩጂ ኤአር ኢትዮጵያ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ያብስራ መካሻ እንደገለጹት፤ ሽልማቱ በሀገሪቱ የሙያ ስነ-ምህዳር ውስጥ የነበረውን ክፍተት ለመሙላትና ይዘታቸው ሌሎችን የሚያነቃቃና ትርጉም ያለው ሙያዊ ውይይት የሚፈጥሩ ሰዎችን ለማበረታታት ያለመ ነው፡፡
ይህ አገር አቀፍ ሽልማት በሳይንስና ቴክኖሎጂ (STEM)፣ በጤና፣ በስራ ፈጠራ፣ በአየር ንብረት እና በማርኬቲንግ ጨምሮ በ6 ዋና ዋና ምድቦች የተከፋፈለ ሲሆን፤ ከዲጂታል መድረክ ባሻገር በተጨባጭ ማህበረሰባዊ ተፅዕኖ የፈጠሩ ባለሙያዎችን ይሸልማል።
የሊንክድኢን ተፅእኖ ፈጣሪዎች ሽልማት ኢትዮጵያ (LCAE) በሀገሪቱ ሙያዊ እና ማህበራዊ መልክዓ-ምድር ላይ በተጨባጭ የሚለካ ተፅዕኖ እያሳደሩ ያሉ ግለሰቦችን እና ድርጅቶችን እውቅና የሚሰጥ የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ብሔራዊ፣ ሁለገብ ዘርፍ መድረክ ነው።

የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ያዘጋጀው ታላቅ የሥራ ትስስር (Job Fair) ተካሄደ
#fastmereja I የተፈሪ መኮንን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ምሩቃንን እና ሌሎች የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞችን በቀጥታ ከቀጣሪ ድርጅቶች ጋር ለማገናኘት ያለመ የመጀመሪያው የሥራ ትስስር (Job Fair) ዛሬ ሐምሌ 09 ቀን 2018 ዓ.ም. በታላቅ ድምቀት አካሂዷል።
የተፈሪ መኮንን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ተሾመ ፌይሳ ዋክቶሌ ለፋስት መረጃ በሰጡት ቃል እንደገለጹት፤ ይህ የሥራ አውደሪ የተዘጋጀው ቀጣሪ ኢንዱስትሪዎችንና ሥራ ፈላጊ ሰልጣኞችን በአንድ መድረክ በማገናኘት፣ ሁለቱም ወገኖች ተፈላጊ ሰራተኛና የሥራ ዕድል ፍለጋ የሚያባክኑትን ጊዜና እንግልት ለመቀነስ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ኮሌጁ ይህንን መድረክ በተቋም ደረጃ ሲያዘጋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም በሌሎች መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችና አማካሪዎች አማካኝነት ይዘጋጅ የነበረውን መርሃ ግብር ተቋሙ በባለቤትነት ተረክቦ ከተማ አቀፍ በሆነ መልኩ ማዘጋጀቱን አስረድተዋል።
በአውደሪው ላይ የኮሌጁ 967 መደበኛና የአጭር ጊዜ ሰልጣኞች ብቻ ሳይሆኑ፣ በአዲስ አበባ የሚገኙ 14ቱም ኮሌጆች ሰልጣኞቻቸውን ይዘው እንዲገኙ ጥሪ ተላልፎላቸዋል። ሰልጣኞቹ ከቀጣሪዎች ጋር ከመገናኘታቸው አስቀድሞ የሲቪ (CV) አጻጻፍ፣ የቃለ መጠይቅ ዝግጅት፣ አለባበስ እና የስራ ፈጠራ አስተሳሰብን በሚመለከት ሰፊ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል። ይህ ዝግጅት ምሩቃኑ በራስ የመተማመን ስሜት ኖሯቸው ወደ ሥራው ዓለም እንዲቀላቀሉ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግላቸው ታምኖበታል።
በዕለቱ በተካሄደው የሥራ አውደሪ ላይ ከሆቴል፣ ከኮንስትራክሽን፣ ከማኑፋክቸሪንግ፣ ከዘመናዊው የፈጠራ ግሪን ቴክኖሎጂ እና ከኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) ዘርፎች የተውጣጡ ከ35 በላይ ኢንዱስትሪዎች ተገኝተው የቅጥር ሂደቶችን ሲያከናውኑ ውለዋል። ከተለመደው የቅጥር ሁኔታ በተጨማሪ በኮሌጁ በቴክኖሎጂ (ICT) ዘርፍ የተደራጁና የሰው ሰራሽ አስተዋጽኦ (AI) መተግበሪያዎችን በመጠቀም ድረ-ገጾችንና የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን የሚሰሩ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች የራሳቸውን ማሳያ ጥግ ይዘው ስራዎቻቸውን ለእይታ አቅርበዋል።
ለአንድ ቀን ብቻ የሚቆየው ይህ የሥራ አውደሪ መርሃ ግብር፣ በቀጣይም በየዓመቱ ከምረቃ ሥነ-ሥርዓት አስቀድሞ በቋሚነትና በስፋት የሚዘጋጅ ዓመታዊ መርሃ ግብር ሆኖ እንደሚቀጥል ዋና ዲኑ አቶ ተሾመ ፌይሳ ጨምረው ገልጸዋል።

የ1 ሚሊዮን ብር ሽልማት የሚያስገኘው የቤላ ስፖርት የክረምት የፉትሳል ውድድር ቅዳሜ ይጀመራል
#fastmereja I የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከቤላ ስፖርት ትጥቅ አምራች ድርጅት ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁትና አሸናፊውን ቡድን የ1 ሚሊዮን ብር ባለቤት የሚያደርገው 2ኛው ዙር የቤላ ስፖርት የክረምት የፉትሳል ውድድር በሚመጣው ቅዳሜ በይፋ እንደሚጀመር በጋዜጣዊ መግለጫ ተገለጸ።
ከሐምሌ 11 እስከ ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በጨፌ ሜዳ ለአንድ ወር በሚቆየው በዚህ ውድድር ላይ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ፣ በከፍተኛ ሊግ እና በሱፐር ሊግ የሚሳተፉ ተጨዋቾች ይሳተፋሉ።
ሁለቱ አካላት ውድድሩን በጋራ ለማዘጋጀት የሚያስችል የሁለትዮሽ ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን፣ ዝግጅቱ ክለቦች አዲሱ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት አቋማቸውን ለመለካት ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥርላቸው ታውቋል። ውድድሩን አሸናፊ ለሚሆን ቡድን ከተዘጋጀው 1 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ሽልማት በተጨማሪ፣ ለውድድሩ ኮከብ ተጫዋች፣ ኮከብ ግብ አግቢ እና ኮከብ በረኛ እያንዳንዳቸው የ20 ሺህ ብር የክብር ሽልማት እንደሚሰጣቸው ተገልጿል። #ኹነት

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ100ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በታላቅ ድምቀት ሊያከብር ነው
#fastmereja I የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) የተመሰረተበትን 100ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አስመልክቶ ከሐምሌ 7/2018 ዓ.ም በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ የተለያዩ ዝግጅቶችን እያከናወነ እንደሚገኝ ተነግሯል። ኢንስቲትዩቱ የክፍለ ዘመኑን ጉዞ ለመዘከርና በጤናው ዘርፍ የተመዘገቡ አዳዲስ ምርምሮችን ለማቅረብ መዘጋጀቱን አስታውቋል።
የኢንስቲትዩቱ ይፋዊ መርሃ-ግብር እንደሚያሳየው፣ ዋናው በዓልና ሳይንሳዊ ጉባኤው ከሐምሌ 9 እስከ ሐምሌ 11/2018 ዓ.ም ባሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት በልዩ ሁኔታ ይካሄዳል። በዓሉ የኢንስቲትዩቱን የ100 ዓመታት ጉዞ የሚያሳዩ ፎቶግራፎችና ቪዲዮዎች፣ የምስጋናና የእውቅና አሰጣጥ ስነ-ስርዓቶች እንዲሁም በጤናው ዘርፍ ተስፋ ሰጪ በሆኑ አዳዲስ ግኝቶች ላይ ያተኮሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች የሚቀርቡበት መድረክ እንደሚሆን ተነግሯል።

በኢትዮጵያ እና በጣሊያን መካከል ያለውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የዲዛይን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመው ከፍተኛ የቢዝነስ እና የዲዛይን ኹነት በኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም ሊካሄድ ዝግጅቱ ተጠናቋል።
📅 የሁነቱ መርሃ-ግብር
ቀን፦ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 2 ቀን 2018 ዓ.ም (እ.ኤ.አ ከጁላይ 7 እስከ 9 ቀን 2026
*ቦታ፦በአዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም
✨ በሁነቱ ላይ ምን ምን ይጠበቃል?
🛍️ ልዩ ኤግዚቢሽን እና የB2B ትስስር
ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የጣሊያን የቤት ዕቃዎች (Furniture)፣ የሥነ-ሕንጻ ብርሃን ቴክኖሎጂዎች፣ ሴራሚክስ እና እብነበረድ የሚቀርቡበት ሲሆን፤ የሁለቱን ሀገራት ኩባንያዎች በቀጥታ የሚያገናኝ የንግድ ትስስር መድረክ ተዘጋጅቷል።
🏗️ ሙያዊ ሴሚናሮች፦
በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባለው ‘Interni Magazine’ አወያይነት በዘላቂ የከተማ ልማት፣ በሃይል ቆጣቢ ህንፃዎች እና በኢትዮጵያ የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት እድሎች ዙሪያ የሀገር ውስጥ፣ የጣሊያንና የቀጣናው (ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ) ምሁራንና ጋዜጠኞች የሚሳተፉበት ውይይት ይደረጋል።
🎓 የዲዛይን ማስተር ክላስ እና ልዩ ውድድር፦
በታዋቂው አርክቴክት ዱቺዮ ግራሲ (Arch. Duccio Grassi) የሚመራ ልዩ የስልጠና መርሃ-ግብር የሚሰጥ ሲሆን፤ በታሪካዊው የመርካቶ የንግድ ቀጠና ላይ ያተኮረ የመርካቶ ከተማ መልሶ ማልማት ውድድር (Merkato Urban Regeneration Competition) በይፋ ይጀመራል።
🏛️ የMade in Italy” ታሪክ ትዕይንት
በአለም አቀፍ የ“Made in Italy” ቀን ምክንያት በማድረግ በጣሊያን የምርት መለያዎች ሙዚየም አማካኝነት ታዋቂ ብራንዶች ያለፉበትን የዲዛይን እድገት የሚያሳይ ልዩ ኤግዚቢሽን ለዕይታ ይቀርባል።
📌 ለተደራሲያን የቀረበ ማሳሰቢያ
ሁነቱ ለመጀመሪያዎቹ ቀናት ለባለሙያዎችና ለቢዝነስ ተቋማት (B2B) ብቻ ክፍት የሚሆን ሲሆን፤ በመጨረሻው ቀን ማለትም በሐምሌ 2 ቀን 2018 ዓ.ም (እ.ኤ.አ ጁላይ 9) ለማንኛውም ፍላጎት ላለው የህዝብ ክፍል እና ለዲዛይን አፍቃሪዎች ሙሉ በሙሉ ነፃ ሆኖ ክፍት ይደረጋል።
#italiansmart Living2026 #addisababa #ethiopia #italy #business #design #architecture #innovation
4 months ago
በኢትዮጵያ የስፖርት ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ ሊከፍት የሚችል የመጀመሪያው አገር አቀፍ የስፖርት ኤግዚቢሽን ሊካሄድ ነው
በኢትዮጵያ የስፖርት ዘርፍ ታሪክ አዲስ የኢንዱስትሪ ዕንቅስቃሴ ለመጀመር እና ስፖርትን ከመዝናኛነት ወደ ላቀ የኢኮኖሚ ምንጭነት ለማሸጋገር ያለመ ታላቅ አገር አቀፍ የስፖርት ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ።
ይህንን በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደውን ታላቅ ኹነት ያዘጋጁት አዱሊያን ማስታወቂያ እና ዳይመንድ ማርኬቲንግ ኤንድ ኮሚኒኬሽን ሲሆኑ፣ ዝግጅቱ የኢትዮጵያን ስፖርት ከባሕላዊ የሩጫ እና የእግር ኳስ ማዕቀፍ አውጥቶ ወደ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ የንግድ ትስስር እና የኢንዱስትሪ ምርታማነት የሚያሸጋግር የለውጥ ምዕራፍ እንደሚሆን አዘጋጆቹ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
ይህ አውደ ርዕይ እና አገራዊ መድረክ በርካታ ዘርፈ ብዙ ፋይዳዎችን ይዞ የሚቀርብ ሲሆን፣ የስፖርት ዕቃ አምራቾችን፣ አከፋፋዮችን፣ ስፖርተኞችን እና የስፖርት ማሕበራትን በአንድ መድረክ በማገናኘት የአገር ውስጥ ምርትን ማበረታታት እና የገበያ ትስስር መፍጠር፤ በዓለም ላይ ያሉ ዘመናዊ የስፖርት ስልጠና ቴክኖሎጂዎችን (Digital Sports Solutions)፣ የስፖርት ሕክምና፣ አመጋገብ እና ሳይንስ ላይ ያተኮሩ የውይይት መድረኮችን ለኢትዮጵያ ስፖርተኞችና አሰልጣኞች ማስተዋወቅ፤ ወጣቶች እና ቤተሰቦች በአካል ተገኝተው የተለያዩ የስፖርት አይነቶችን እንዲሞክሩ በማድረግ፣ በአካላዊ ብቃት፣ በእንቅስቃሴ እና በጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ላይ ሰፊ ግንዛቤ መፍጠር እንዲሁም የስፖርት ዝግጅቶችን በንግድ መልክ በማደራጀት ለሀገር ውስጥ አምራቾች ሰፊ እድል መስጠት፤ ይህም የውጭ ምንዛሪ ወጪን በመቀነስ የአገር ውስጥ አቅምን ለመገንባት እና ለዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽዖ ይኖረዋል።
### ለሀገር የሚሰጠው ስልታዊ ጠቀሜታ
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፖርቱ መስክ የጎላ ዝና ያላት ቢሆንም፣ ይህንን እውቅና ወደ ስፖርት ኢንዱስትሪ ለመቀየር የሚያስችል የተቀናጀ የንግድ እና የልውውጥ መድረክ ክፍተት እንደነበረበት ይነገራል። ዳይመንድ ማርኬቲንግ እና አዱሊያን ማስታወቂያ ይህንን ክፍተት በመሙላት የኢትዮጵያን ስፖርት ከ"ሞያ" ወደ "ኢንዱስትሪ" ለማሸጋገር አቅኚ የለውጥ ስራ መጀመራቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ዝግጅቱ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን (MDF-based) የኤግዚቢሽን ስታንዳርዶችን የሚጠቀም በመሆኑ፣ ለወደፊት በሀገሪቱ ለሚካሄዱ ስፖርታዊ ኹነቶች አዲስ የጥራት ደረጃ (Benchmark) ያስቀምጣል። ይህም ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፖርት አስተናጋጅነት (Sports Event Hub) እንድትታወቅ በማድረግ ረገድ ለስፖርት ዲፕሎማሲው ትልቅ አጋዥ እንደሚሆን ታምኖበታል።
ኩባንያዎቹ ከዚህ ቀደም መሰል ዝግጅቶችን የማካሄድ ልምድ እንዳላቸው የገለጹ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ ወጣቶች ማሕበር ጋር በመተባበር "የአመለካከት እና አስተሳሰብ ለውጥ ኤግዚቢሽን" እንዲሁም ከአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር በጃን ሜዳ "የባሕል እና ስፖርት ፌስቲቫል" በተሳካ ሁኔታ ማከናወናቸውን አስታውሰዋል።
ለተሳታፊዎች እና ለጎብኚዎች ደህንነት ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን፣ እያንዳንዱ የኤግዚቢሽን ቦታ (Zone) በዓለም አቀፍ የደሕንነት መመዘኛዎች መሰረት እንደሚዋቀር ተገልጿል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ ከፌዴሬሽኖች፣ ከጤና ባለሞያዎች እና ከሚመለከታቸው የደህንነት አካላት ጋር በቅርበት በመስራት ላይ መሆናቸውንና የህክምና እና የድንገተኛ አደጋ ዝግጅቶች በተሟላ ሁኔታ እንደሚቀርቡ አዘጋጆቹ አረጋግጠዋል።
ይህ አገር አቀፍ የስፖርት ኤግዚቢሽን የአንድ ጊዜ ክስተት ብቻ ሆኖ እንደማይቀረና ዋና ዓላማው በየዓመቱ የሚካሄድ ብሔራዊ የስፖርት ክብረ በዓል (Annual Sports Exhibition) ማድረግ መሆኑ ተገልጿል። የዘንድሮውን የመጀመሪያ ዝግጅት ስኬት እንደ ግብዓት በመጠቀም፣ በቀጣይ ዓመታት የክልል እና የዓለም አቀፍ ተሳታፊዎችን በማካተት ዝግጅቱን ይበልጥ ለማስፋት ታቅዷል።

ከ18 በላይ ሀገራት የሚሳተፉበት ዓለም አቀፍ የንግድ ኤግዚቢሽን ሊካሄድ ነው
በኢትዮጵያ የንግድና የኢንቨስትመንት ዕድገት ላይ ከፍተኛ አዎንታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቀው 8ኛው አግሮፉድ እና ፕላስትፕሪንትፓክ እንዲሁም 2ኛው የኢትዮጵያ የምግብና የኤክስፖርት የቡና ንግድ ትርዒት ጥምር ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ሊካሄድ ሙሉ ዝግጅቱ መጠናቀቁ ተገለጠ ።
ይህ በዓነቱ ግዙፍ የሆነው የኢንዱስትሪ መድረክ በአፍሪካ ፈጣን ዕድገት እያሳየች ባለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ከብራዚል፣ ቻይና፣ ጣሊያን፣ ጀርመን እና ፈረንሳይ ጨምሮ ከ18 በላይ ሀገራት የተውጣጡ በርካታ ዓለም አቀፍና ሀገር በቀል ኩባንያዎችን በአንድ ጣሪያ ስር የሚያገናኝ ልዩ ኹነት መሆኑ ተጠቁሟል ።
ዝግጅቱ በተለይም በምግብ፣ በግብርና፣ በቡና፣ በላስቲክና ማሸጊያ ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ አዳዲስ ፈጠራዎችንና የንግድ ትስስሮችን ይዞ እንደሚቀርብ የወጣው መርሃ-ግብር ያሳያል ።
ይህ ታላቅ ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን ከሰኔ 18 እስከ 20 ቀን 2018 ዓ.ም (June 25–27, 2026) በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ለሶስት ቀናት ተከፍቶ እንደሚቆይ ታውቋል ።

6 months ago
ሁሌ ቅርጫ የዲጂታል ቅርጫ አገልግሎት ሥራ ጀመረ
ሁሌ ቅርጫ የተባለ የቅርጫ አገልግሎትን በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ አሠራር ተግባር ላይ መዋሉን የሁሌ ቅርጫ የሥራ መሪ አቶ ቶማስ መለሰ አስታውቀዋል። ከኢትዮ ቴሌኮምም ጋር ይህን ሥራ ለመሥራት የሥራ ውል ስምምነት ተፈራርመዋል።
በኢትዮ ቴሌኮም በኩል የዘመን ገበያ ኦፕሬሽን ማኔጀር አቶ ቸርነት ሰኢድ የውል ስምምነቱ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩ ሲሆን በቴሌብር በዘመን ገበያ አማካይነት ግብይቱ እንደሚከናወን ታውቋል።
ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ የተዘጋጀው ይህ አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ የትንሣኤ በዓል አስመልክቶ ለተገልጋዮች ክፍት ይሆናል ተብሏል።
አፓርትመንት እንዲሁም የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ የሚኖሩ ሰዎች፣ ቅርጫ ለማግኘት እንደሚቸገሩ ያስታወሱት አቶ ቶማስ፣ አገልግሎቱ አንድም ይህን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አስረድተዋል። በተጨማሪም፣ ሰዉ በኑሮ ሩጫ መካከል ሆኖ ጊዜ እያጠረው ከመሆኑ አንጻር፣ ቅርጫ የሚገቡ ሰዎችን ማፈላለግና ማሰባሰብ፣ በሬ ለመግዛት ገበያ ማቅናት እንዲሁም አራጆችን መፈለግ አስቸጋሪ መሆኑን አንስተዋል። ሁሌ ቅርጫ ይህን ሁሉ ድካም በማስቀረት ለኅብረተሰቡ ትልቅ ጠቀሜታ የሚሰጥ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ከዚህም ባሻገር ከእርድ የሚተርፉ እንደ በሬ ቆዳ፣ ጭንቅላት እና የመሳሰሉት፣ ፅዱና ንፁህ በሆነች ከተማ ላይ በየአካባቢው መጣሉ ለነዋሪዎች ጤንነት እክል እንደሚሆን አንስተዋል። ሁሌ ቅርጫም ይህን በማስቀረት ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
ከሃገር ውጭ የሚኖሩ ሰዎችም ያለምንም ውጣ ውረድ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው የቅርጫ ሥጋ የሚገዙበት መልካም አጋጣሚ መሆኑን አቶ ቶማስ አስረድተዋል።
ዋጋውን በተመለከተ ቅናሽ ያለው ሲሆን፣ ከመደበኛ ግብይት በተሻለ ደንበኞች የመረጡትን በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት የሚችሉበት ነው። በኢትዮ ቴሌኮም የዘመን ገበያ አገልግሎት በኩልም፣ ደንበኞች በኢትዮ ቴሌኮም ክፍያ ከፈፀሙ በኃላ በየቤታቸው የሚደርስበት የዴሊቨሪ አገልግሎት መኖሩንም ታውቋል። ሁሌ ቅርጫ ከሸጠው ላይ 2 % አቅም ለሌላቸው የበዓል ድጋፍ እንደሚያውልም ታውቋል።
'ሁሌ ቅርጫ' ላለፉት ዓመታት ጥራቱን እና ደረጃውን የጠበቀ፣ ደኅንነቱም የተረጋገጠ ስጋን ለውጭ ገበያ ሲልክ ቆይቷል። አሁን ላይ ይህን ተመሳሳይ አገልግሎት ለሀገር ውስጥ ገበያ መስጠት ጀምሯል።
አቶ ቶማስ እንደገለጹት፣ ይህ ግብይት አሁን በዓሉን በማስመልከት ይጀመር እንጂ በአዘቦት ቀናትም የሚቀጥል ነው። ከዓመት ዓመት የበግ እና የፍየል እርድን ጨምሮ፣ ለተለያየ ኹነትም ሰብሰብ ብለው ቅርጫ ለፈለጉም አገልግሎቱ ተደራሽ እንደሚሆን አሳውቀዋል።
ቅርጫ የሚለው ባህል እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ቀለል ባለና ደኅንነቱ እና ደረጃው በተጠበቀ መንገድ አገልግሎትን መስጠት የሁሌ ቅርጫ ዓላማ መሆኑንም አቶ ቶማስ ተናግረዋል።

የፓን አፍሪካ ሮቦቲክስ ሻምፒዮንሺፕ በአዲስ አበባ በድምቀት ተጀመረ
#fastmereja I አዲስ አበባ
በቴክኖሎጂ የታነጸ ትውልድ ለመፍጠር ያለመው የፓን አፍሪካ ሮቦቲክስ ሻምፒዮንሺፕ ውድድር "እኔ ችግር ፈቺ ነኝ" በሚል መሪ ቃል ዛሬ በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም በይፋ ተጀምሯል። የኢትዮ ሮቦቲክስ የትምህርትና ስልጠና ማዕከል ባዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች በሮቦቲክስ፣ በኮዲንግ እና በዲዛይኒንግ ዘርፎች የፈጠራ ብቃታቸውን እንደሚያሳዩ ታውቋል።
በመክፈቻው ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ፣ መንግስት ለወጣቶች የፈጠራ ስራ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠሩንና መሰል ውድድሮች ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስጠራት ያላቸውን ሚና ገልጸዋል። የኢትዮ ሮቦቲክስ መስራች አቶ ሰናይክረም መኮንን በበኩላቸው፣ መጪው ዘመን ድህነትና በሽታ በቴክኖሎጂ የሚሸነፉበት መሆኑን በመጥቀስ ታዳጊዎች ለችግር ፈቺነት እንዲተጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ባለፉት 15 ዓመታት ወጣቶችን በዓለም አቀፍ መድረኮች ሲያሳትፍ የቆየው ኢትዮ ሮቦቲክስ፣ የዘንድሮው የፓን አፍሪካ ውድድር ተማሪዎች ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነታቸውን የሚያጎለብቱበት ወሳኝ ድልድይ እንደሚሆን ይጠበቃል። ድርጅቱ ከዚህ ቀደም በቻይና፣ ካናዳና አሜሪካ በሚካሄዱ ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያን በመወከል ስኬታማ ተሳትፎ ማድረጉ ይታወሳል።

10ኛው የኢትዮ ኸልዝ ዓለምአቀፍ አውደ ርዕይና 2ኛው የሀገር ውስጥ የህክምና ግብዓት ምርት ኤግዚቢሽን በይፋ ተከፈተ
#fastmereja I 10ኛው የኢትዮ ኸልዝ ዓለምአቀፍ አውደ ርዕይና ጉባኤ እንዲሁም 2ኛው የሀገር ውስጥ የህክምና ግብዓት ምርትና ኢኖቬሽን ኤግዚቢሽን ዛሬ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር (AICC) በይፋ ተከፍቷል። በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ በአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (AHRI) እና በፕራና ኢቨንትስ ትብብር የተዘጋጀው ይህ ታላቅ ኹነት ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ ከ8 ሀገራት የተውጣጡ ከ90 በላይ ኩባንያዎች ምርትና አገልግሎታቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ።
በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ አውደ ርዕይ በጤናው ዘርፍ ያለውን የቴክኖሎጂ ፍላጎት ለመሙላትና የሀገር ውስጥ አምራቾችን አቅም ለማሳየት ያለመ መሆኑ ተገልጿል። የዘንድሮው መርሃ ግብር ከኤግዚቢሽኑ ባሻገር ከ40 በላይ የሙያ ማጎልበቻ (CPD) ስልጠናዎችን እና 3ኛው የዲጂታል ኸልዝ ሃካቶንን ያካተተ በመሆኑ ለባለሙያዎች ልዩ የዕውቀት መጋሪያ መድረክ ፈጥሯል።
ኢትዮጵያ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ ሩሲያ፣ ቱርክ፣ ባንግላዴሽ፣ ዩኤኢ እና አሜሪካ ሀገራት ተሳታፊ ሲሆኑ ከ20 በላይ የሙያ ማህበራት ጋር በመተባበር የሚከናወኑ ሳይንሳዊ ፎረሞች እና የንግድ ትስስር መድረኮች ተዘጋጅተዋል።
መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም

አዲስ አበባ አህጉራዊ የሪል ስቴት ጉባኤና ኤክስፖን ልታስተናግድ ነው!
#fastmereja I የኢትዮጵያ የሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር "አዲስ አፍሪካ ሪል እስቴት ኤክስፖ 2026" የተሰኘውን የመጀመሪያውን አህጉራዊ የኤግዚቢሽን መድረክ በመጪው ሚያዚያ ወር በአዲስ አበባ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።
ማህበሩ ከዶክሳ ኢቨንትስ ጋር በመተባበር ከሚያዚያ 15 እስከ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሙዚየም ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚያካሂደው ይህ ታላቅ ኩነት፤ የኤክስፖውን ያህል ትልቅ አገራዊ ፋይዳ ያላቸውን መርሀ-ግብሮችን የያዘ መሆኑንም ገልፀዋል።
በእለቱ ከሚከናወኑ መርሀ-ግብሮች የማህበሩ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ፣የአፍሪካ ሪል ስቴት ማህበር(AFRES) የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ጉባኤ እና አልሚዎች ያላቸዉን ያሏቸዉን ግብአቶች እና ፕሮጀክቶቿቸዉን ለህዝብ እና ለተሳታፊዎች የሚያሳዩባቸዉ መድረኮች መሆናቸዉ ተገልጿል።
የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ አለማየሁ ከተማ እንደገለፁት የኢትዮጵያ ሪል ስቴት ማህበር የአባላቱን መብት ከማስጠበቅ ባለፈ፣ ደንበኞች ጥራት ያለውና በውል በተገባው ጊዜ የሚረከቡትን ቤት እንዲያገኙ የሚያስችል የክትትልና የሙያ ስነ-ምግባር ደንብ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ገልጿል።
በኤግዚቢሽኑ ላይ የሚሳተፉት የማህበሩ አባል የሆኑ ህጋዊና እውቅና ያላቸው አልሚዎች ብቻ በመሆናቸው፣ ቤት ፈላጊው ማህበረሰብ ካልተገባ እንግልት እንዲጠበቅ እንደሚያደርገው ተመልክቷል።
ይህ መድረክ በተለይ የማህበሩ አባላት የሆኑ አልሚዎች የተለያዩ የቤትና የህንፃ ፕሮጀክቶቻቸውን ይዘው የሚቀርቡበት በመሆኑ፣ ቤትና የንግድ ቦታ ፈለጊ ማህበረሰብ አማራጮችን በአንድ ቦታ እንዲያገኝ ሰፊ ዕድል እንደሚፈጥር ታውቋል።
ከሪል ስቴት አልሚዎች በተጨማሪ የፋይናንስ ተቋማት፣ የኮንስትራክሽን ድርጅቶች እና ከዘርፉ ጋር ግንኙነት ያላቸው አካላት በዝግጅቱ ላይ የሚሳተፉ በመሆኑ ለዘርፉ እድገት ትልቅ አቅም ይፈጥራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ነዉ የተገለፀዉ።
በኤክስፖው ላይ የሚሳተፉ የውጭ አገር እንግዶችና ባለሀብቶች አዲስ አበባ በቅርቡ ያስገነባቻቸውን አዳዲስ የቱሪስት መስህቦችና የኮሪደር ልማቶችን እንዲጎበኙ ፕሮግራም መያዙ ተያይዞ ተገልጿል።
ይህም አገሪቱ ከኮንፈረንስ ቱሪዝም የምታገኘውን ተጠቃሚነት ለማሳደግና የአዲስ አበባን የዲፕሎማሲ ማዕከልነት ዳግም ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

“ኢትዮ ሆም-ኤክስፖ 2026” በለንደን ከተማ ሊካሄድ ነዉ!
#fastmereja I በዩናይትድ ኪንግደም ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው አስተማማኝ የቤት ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችል “ኢትዮ ሆም-ኤክስፖ 2026" የተሰኘ ታላቅ የሪል ስቴት ኤክስፖ በለንደን ከተማ እንደሚካሄድ በዛሬዉ እለት ተገለፀ።
በለንደን የሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ፣ ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት፣ ከኢትዮጵያ ሪልስቴት አልሚዎች ማህበር፣ ከአዲስ አበባ ንግድ ምክርቤት እና ኤድማርቬንቸርስ ከተባለ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተቋም ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
ኤክስፖው ከግንቦት 15 እስከ 17 ቀን 2018 (May 23-25, 2026) ለሶሰት ተከታታይ ቀናት በለንደን ከተማ የሚካሄድ ሲሆን ከ3000 በላይ ተሳታፊዎች እንደሚኖሩም ነዉ የተገለፀዉ።
ይህ ኤክስፖ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ቤት የማፍራት ህልማቸውን እውን እንዲያደርጉ፣ በአልሚዎችና በተጠቃሚዎች መካከል ያለውን መተማመን ማሳደግና አስተማማኝ የግብይት ሥርዓት ማስተዋወቅ የተዘጋጀ መሆኑ ተጠቁሟል።
የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት በኤክስፖው የሚሳተፉ አልሚዎችን በግንባታ አፈፃፀማቸው፣ በጥራትና በሰነድ ህጋዊነት የመለየትና የማጣራት ስራ በመስራት የዲያስፖራውን ስጋት ለመቅረፍ እንደሚሰራ የኤድማር ቬንቸር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፋሲካ አብዛ ገልፀዋል።
ኤክስፖዉ በዘርፉ ስላሉ አዳዲስ ፖሊሲዎችና የቤት ግዢ አማራጮች ከመንግስትና ከግል ተቋማት ጋር የመረጃ ልውውጥና የፓናል ውይይቶች የሚደረጉ ሲሆን የንግድ ባንኮች ለዲያስፖራው ማህበረሰብ የሚሆኑ ልዩ የፋይናንስ ድጋፎችንና የቤት ባለቤት የሚያደርጉ የብድር አማራጮችን ለተሳታፊዎች እንደሚያስተዋዉቁም ነዉ የተገለፀዉ።
በዛሬዉ እለት በተከናወነ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አዘጋጁ ኤድማር ቬንቸር እና አዲስ ቻምበር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን የፌርማ ስነ-ስርአት አከናዉነዋል።
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍፁም አረጋን ጨምሮ የኢትዮጵያ ሪልስቴት አልሚዎች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አለማየሁ ከተማ፣ የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ ወልደገብርኤል እንዲሁም የኤድማር ቬንቸርስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፋሲካ አብዛ ተገኝተዋል።

የፊቼ ጫምባላላ በዓል በአዲስ አበባ በልዩ ድምቀት ተከበረ!
#fastmereja I የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫና በዩኔስኮ (UNESCO) በማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የፊቼ ጫምባላላ በዓል በዛሬዉ እለት በወዳጅነት አደባባይ በድምቀት ተከበረ።
በዓሉ በመዲናዋ ለ7ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን ዋና ዓላማውም የሰላም፣ የእርቅና የአንድነት እሴቶችን ለሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ማጋራት እንደሆነ ተገልፆ በዓሉ ለሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን ለእንስሳትና ለተፈጥሮም ጭምር ሰላምን የሚመኝ ጥልቅ ባህላዊ ትርጉም ያለው መሆኑም ተመላክቷል።
ፊቼ ጨምበላላ ትልቅ የመንፈሳዊና የቁሳዊ ባህል እሴት የሚታይበት በዓል መሆኑን እና፤ የጨረቃንና የከዋክብትን ፈለግና ዑደት ለዘመናት የቀመረ ነባር ሀገር በቀል የእውቀት መገለጫ መሆኑን አስረድተዉ በበዓሉ ላይ የሚታየው የባህሎች መስተጋብርም ኢትዮጵያ የምታልማትን የጋራና ማንነት የሚያንፀባርቅ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስትርዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ ገልፀዋል።
በዓሉ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ መሪነትና ድጋፍ በየዓመቱ እየተከበረ የቆየ ሲሆን፣ አሁን ላይ ለከተማዋ ተጨማሪ ድምቀት የሚሰጥ ትልቅ ህዝባዊ ፌስቲቫል ለመሆን መብቃቱ ነዉ የተገለፀዉ።
በዛሬዉ እለት በተከናወነዉ መርሀ-ግብር ላይ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሲዳማ ማህበረሰብ አባቶች፣ አባ ገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች እንዲሁም በርካታ የሲዳማ ተወላጆች ታድመዋል።

በኢትዮጵያ የሕክምና ዘርፍ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ሚና ላይ ያተኮረው 62ኛው የኢሕማ ዓመታዊ ጉባኤ በሂልተን ሆቴል ተከፈተ
#fastmereja I የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር (ኢሕማ) "የሰው ሠራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) በሕክምና ትምህርት፣ በጤና አገልግሎት አሰጣጥ እና በምርምር ዘርፍ ያለውን ሚና ማሳደግ" በሚል መሪ ቃል 62ኛ ዓመታዊ ጉባኤውንና ዓለም አቀፍ የጤና ኤግዚቢሽኑን ዛሬ በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል በይፋ ጀምሯል።
በመክፈቻው ላይ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰሃረላ አብዱላሂን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የሕክምና ስፔሻሊስቶች ተገኝተዋል። ጉባኤው በዋናነት ቴክኖሎጂን በመጠቀም የኢትዮጵያን የሕክምና ጥራትና ተደራሽነት ማዘመን በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ያተኮረ ምክክር እያካሄደ ይገኛል።
የዘንድሮው መሪ ቃል በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ እምብዛም ያልተለመደውን የAI ቴክኖሎጂን ለምርምርና ለታካሚዎች ፈጣን ሕክምና እንዴት ማዋል እንደሚቻል አዳዲስ አቅጣጫዎችን የሚያመላክት መሆኑ ተገልጿል። በተጓዳኝ እየተካሄደ ባለው ኤግዚቢሽን ላይም ከቴክኖሎጂው ጋር የተያያዙ የሕክምና መሣሪያዎችና ዲጂታል መፍትሔዎች ለጉብኝት ቀርበዋል።
በዛሬው መርሃ ግብር ላይ የኢሕማ አዋርድ ላይ ተካሂዷል።

7 months ago
በሐዋሳ ከተማ ታላቅ የጎዳና ላይ ሩጫ ሊካሄድ ነው!
#fastmereja “አብረን እንሩጥ፣ ለሐዋሳ ከፍታ'' በሚል መሪ ቃል ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ የሚካሄድ ታላቅ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ መዘጋጀቱ በዛሬዉ እለት በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።
ይህ በዓይነቱ ለየት ያለ ስፖርታዊ ኩነት የሚዘጋጀው ለስድስት አስርት ዓመታት በታማኝነት ሲያገለግል በቆየውና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለቤትነት በሚተዳደረው ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና በታዋቂው አትሌት ገዝሀኝ አበራ ትብብር መሆኑ ተገልጿል።
በዝግጅቱ ላይ ከ15 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ ታዋቂ አትሌቶች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እንዲሁም የሐዋሳ ከተማና የአካባቢው ነዋሪዎች የሩጫው አካል እንደሚሆኑ ታውቋል።
ውድድሩን በአሸናፊነት ለሚያጠናቅቁ ሯጮችም ከፍተኛ የገንዘብ እና የሜዳሊያ ሽልማት እንደሚበረከት አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
የዝግጅቱ ዋና ዓላማዎች የማህበረሰቡን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ባህል ማሳደግ፤በከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ያለውን ማህበራዊ ትስስር፣ ሰላምና አብሮነት ማጠናከር፤የሐዋሳን የቱሪዝም ዘርፍ ማነቃቃት እንዲሁም የከተማዋን ገጽታ መገንባት መሆኑ ነዉ የተገለፀዉ።
ኮሜርሻል ኖሚኒስ በቀጣይም ከታዋቂው አትሌት ገዝሀኝ አበራ ጋር በመሆን መሰል የጎዳና ላይ ሩጫዎችን በተመረጡ የሀገሪቱ ከተሞች ለማካሄድ እቅድ እንዳለው ገልጿል።
#ስፖርት #ኹነት

170,000,000 ብር የእንጦጦ ኪዳነምሕረት የገቢ ማሰባሰቢያ
ሪከርድ በመስበር ተጠናቀቀ
ከመጋቢት 11 እሰ መጋቢት 12/2018 በእንጦጦ ኪዳነምሕረት አዳራሽ ሲከናወን የነበረው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር 170,000,000.000 /አንድ መቶ ሰባ ሚሊያን/ ብር በመሰብሰብ ተጠናቀቀ።
ከዚኽ ውስጥ 139,000,000.00 ሚሊዬን ብር የተረጋገጠ ሲሆን ቀሪው 31 ሚሊዬ ብር ደግሞ ቃል የተገባ ሲሆን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።
ይኽንን መሥሐግብር ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ መልአከ አሚን ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ ይርሳው የገዳሟ ዋና አበመኔት፣ ማኅበረ መነኮሳቱ፣ ማኅበረ መነኮሳቱ፣ መምህራን፣ ዘማርያን፣ ምእመናን በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሦስቱንም ሌሊት በንቃት ተሳትፈውበታል።
ቲክታከሮች፣ ዩቱበሮች እና የኪነጥበብ ባለሙያዎች ዶክመንተሪ፣ ማስታወቂያ፣ ቀጥታ ሥርጭት መርሐግብሩን በትሩፋት በማገልገላቸው ከገዳሟ አበው መነኮሳት ማስታወሻ እንዲኾናቸው መንበሯ ላይ ያለችውን የድንግል ማርያም ሥዕለ አድኅኖ እና ሠርተፍኬት በስጦታ ተበርክቶላቸዋል።
ይኽንን ኹነት ከኮሚቴው ጋር በመተባበር የማስተባበር እና የማማከር ተግባር ለአንድ ወር ያከናወነው ሎዛ ኹነቶች - Liza Events በትሩፋት በማገልገሉ መንበሯ ላይ ያለችውን የድንግል ማርያም ሥዕለ አድኅኖ፣ የወርቅ ካባ እና ሠርተፍኬት ከብፁዕ አቡነ መቃርዮስ እና ከገዳሙ አበመኔት እጅ በስጦታ ተበርክቶለታል።

የእንጦጦ ኪዳነምሕረት የገቢ ማሰባሰቢያ

10ኛው "ኢትዮ ኸልዝ" ዓለምአቀፍ አውደርዕይ እና ጉባኤ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው
#fastmereja I በአስርተ ዓመታት የጤናው ዘርፍ ጉዞ ታላቅ ስም ያተረፈው ኢትዮ ኸልዝ ዓለምአቀፍ አውደርዕይና ጉባኤ፣ ለ10ኛ ጊዜ ከመጋቢት 24 እስከ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር (AICC) እንደሚካሄድ ዛሬ መጋቢት 08 ቀን 2018 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።
ፕራና ኢቨንትስ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና ከአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (AHRI) ጋር በመተባበር ባዘጋጁት በዚህ መድረክ ላይ፣ ከ8 ሀገራት የተውጣጡ ከ90 በላይ ኩባንያዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ያቀርባሉ።
የዘንድሮው ኹነት 2ኛው የሀገር ውስጥ የሕክምና ግብዓት ምርትና ኢኖቬሽን ኤግዚቢሽን ጎን ለጎን የሚካሄድ ሲሆን፣ ዓላማውም የሀገር ውስጥ አምራቾችን አቅም ማሳየትና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መተካት ነው።
ከ20 በላይ ከሚሆኑ የሙያ ማኅበራት ጋር በመተባበር፣ ከ40 በላይ የሙያ ማጎልበቻ ስልጠናዎች ለጤና ባለሙያዎች ይሰጣሉ።
2ኛው ዓመታዊ ሳይንሳዊ ፎረም፣ የጤና አመራር ጉባኤ እና 3ኛው የዲጂታል ኸልዝ ሃካቶን በኹነቱ ውስጥ የተካተቱ አቢይ መድረኮች ናቸው።
ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ከባንግላዴሽ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ ሩሲያ፣ ቱርክ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ እና አሜሪካ የመጡ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ።
ይህ መድረክ በኢትዮጵያ የጤናው ዘርፍ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲፋጠን፣ የንግድ ትስስር እንዲጎለብትና የሕክምና አገልግሎት ጥራት እንዲሻሻል ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል። በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ባለሥልጣን (EFDA) እና በሌሎችም ተቋማት ሙሉ ዕውቅና የተሰጠው ይህ አውደርዕይ፣ የዘርፉ ተዋናዮች የሚገናኙበት ትልቁ ሀገራዊ መድረክ ነው።

የአእምሮ እድገት ውስንነት ቀንን አስመልክቶ የተዘጋጀዉ ስፖርታዊ ውድድር በይፋ ተከፈተ!
#fastmereja | 11ኛው የዓለም የዳውን ሲንድሮም ቀን በኢትዮጵያ “ብቸኝነትን በአንድነት እንመክት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀዉ ስፖርታዊ ዉድድር በዛሬዉ እለት በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በይፋ ተከፍቷል።
በዛሬዉ የመክፈቻ ስነ-ስርአት ላይ የኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ዴኤታ አቶ መኪዩ መሀመድ እንዲሁም የስፔሻል ኦሎምፒክ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ግዛቸዉ ግርማን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች በተገኙበት ነዉ የተከናወነዉ።
ስፔሻል ኦሊምፒክስ ኢትዮጵያ ከ“ፍቅር የኢትዮጵያ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ብሔራዊ ማኅበር” ጋር በመተባበር የተዘጋጀዉ ይህ ሀገር አቀፍ ጨዋታ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።
ዉድድሩ ሁሉንም የኦሎምፒክ ስፖርት ዓይነቶች ያካተተ ሲሆን፣ ውድድሩም የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸውን ተወዳዳሪዎች ባማከለ ልዩ የስፖርት ሕግ መሠረት እየተከናወነ ይገኛል።
የፍቅር ኢትዮጵያ ማህበር የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸውን ልጆች አስተምሮና አሰልጥኖ በማኅበሩ ውስጥ የሥራ ቅጥር እንዲያገኙ በማድረግ ጭምር አርአያነት ያለው ሥራ እያከናወነ ይገኛል።
በአሁኑ ወቅት በአፍሪካና በኢትዮጵያ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ወገኖች ላይ የሚደርሰው መገለልና መድልዎ ከፍተኛ በመሆኑ፣ እንዲህ ያሉ ስፖርታዊ መድረኮች ግንዛቤን ለመፍጠርና ብቸኝነትን ለመቀነስ ትልቅ ፋይዳ አላቸው።
በዛሬዉ የመክፈቻ መርሀ-ግብር ላይ ደራሲ፣ዳይሬክተር እንዲሁም ፕሮዲዉሰር የሆነችዉን የራስወርቅ ግርማ የስፔሻል ኦሎምፒክ በጎ ፍቃድ አምባሳደር ሆና ተሾማለች።
#ኹነት #ስፖርት

ሲቢኢ ኑር ኢድ ኤክስፖ 2018 በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል ተከፈተ!
#fastmereja I "ሲቢኢ ኑር ኢድ ኤክስፖ 2018" በታላቅ ድምቀት ዛሬ ተከፈተ! በNiembek Event Organization አዘጋጅነት የቀረበው ይህ ታላቅ የንግድ ትርኢት እና ባዛር በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል በይፋ ተከፍቷል። ኤክስፖው እስከ ኢድ ዋዜማ ድረስ ለተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል።
በኤክስፖው ላይ ተገኝተው ግብይት የሚፈጽሙ ጎብኚዎች በመግቢያ ቲኬታቸው ብቻ የታደሉ ሆነው ከተገኙ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) ተሸላሚ የሚሆኑበት ልዩ ዕድል ተዘጋጅቷል!
ልዩ ልዩ የቤት እና የቢሮ ቁሳቁሶች አልባሳት፣ ጫማዎች እና መዋቢያዎች ለየት ያሉ የበዓል ቅናሾች እና ስጦታዎች በኤክስፖ ይገኛል።

3ኛው ታላቁ የኢትዮ ኢድ ኤክስፖ በጊዮን ሆቴል በደመቀ ሁኔታ ተከፈተ!
#fastmereja I እምነትን፣ ባህልንና ንግድን በአንድ መድረክ የሚያገናኘው "3ኛው ታላቁ የኢትዮ ኢድ ኤክስፖ" በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል በይፋ ተከፈተ። በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ምሁራንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ባህልንና አንድነትን የሚያጠናክር መድረክ
የኤክስፖው አዘጋጆች በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት፤ የዝግጅቱ ዋና ዓላማ ኤግዚቢሽን ከማሳየት ባለፈ ቤተሰቦች፣ ሥራ ፈጣሪዎች፣ ሊቃውንትና ወጣቶች በአንድነትና በአነሳሽነት የሚሰባሰቡበት ብሔራዊ መድረክ መፍጠር ነው።
ኢትዮጵያ ያላትን የበለፀገ ባህልና የሰላማዊ አብሮ መኖር እሴት ማጠናከር እንዲሁም ለሀገር ውስጥ የንግድ ተቋማትና ለወጣት ባለተሰጥኦዎች ዕድል መፍጠር የኤክስፖው ዋነኛ ግብ መሆኑ ተጠቅሷል።
የአዛን ውድድር እና የበጎ አድራጎት ሥራዎች
የዘንድሮውን ኤክስፖ ልዩ የሚያደርጉ ሁለት ዋና ዋና ተነሳሽነቶች ይፋ ተደርገዋል፦
የመጀመርያው ሙአዚን ቢላል ኢብኑ ረባህ (ረ.ዐ) ያስጀመረውን የእኩልነትና የአንድነት ጥሪ ለማዘከርና ወጣቶች ከመንፈሳዊ ውበቱ ጋር እንዲገናኙ ለማድረግ የታለመ ውድድር መዘጋጀቱ ተገልጿል።
ኤክስፖው ማህበረሰባዊ አገልግሎትን ታሳቢ በማድረግ ከሚናሬት ኢንጂነሪንግና ከሌሎች አጋሮች ጋር በመተባበር፣ ከቲኬት ሽያጭ በሚገኝ ገቢና በሪል እስቴት ልገሳ ለችግረኞች ቤት የመገንባት የበጎ አድራጎት ዕቅድ ይፋ ሆኗል።
የአጋሮችና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ለዝግጅቱ መሳካት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ሂጅራ ባንክ፣ ሚናሬት ኢንጂነሪንግና ሌሎች ስፖንሰሮች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጋቸው በመክፈቻው ላይ ተጠቅሷል።
በመጨረሻም "ንግዶች የሚገናኙበትና ባህል የሚከበርበት ይሁን" በሚል ምርቃት ኤክስፖው በይፋ የተከፈተ ሲሆን፤ ነዋሪዎችና ጎብኝዎች በኤክስፖው ላይ በመገኘት የባህልና የንግድ ልውውጥ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
ይህ የኢድ ኤክስፖ እስከ ዋዜማው ድረስ እንደሚቆይም ነው የተገለፀው።

Comments