(ዘ-ሐበሻ ዜና) እናት ፓርቲ በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለውን ሀገራዊ የምክክር ሂደት በተመለከተ ጥብቅ አቋሙን አንጸባርቋል። ፓርቲው ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ የምክክር መድረኩ አገርን በብሔራዊ መግባባት ከማጽናት ይልቅ የቡድን የበላይነትን ለማንበር እና አዲስ የእርስ በእርስ ጦርነት ለማስነሳት ታልሞ እየተሠራበት መሆኑን ገልጿል። በመሆኑም ከዚህ የምክክር መድረክ በሚወጡ ማናቸውም ስምምነቶች ላይ ፊርማውን እንደማያኖር አስታውቋል።
እናት ፓርቲ በመግለጫው እንዳብራራው ገና ከጅምሩ በኮሚሽነሮች አመራረጥ፣ በአካታችነት እና በወቅቱ በነበሩ ጦርነቶች ዙሪያ ስጋቱን ሲገልጽ ቢቆይም ሰሚ በማጣቱ ሀገሪቱ ወደ ምክክር እንድትገባ ተደርጓል። ፓርቲው ሂደቱን በውስጥ ሆኖ ለማረም እና በጎ ተጽዕኖ ለመፍጠር በማሰብ ተሳትፎ ሲያደርግ መቆየቱን ያስታወሰው መግለጫው፣ ይሁን እንጂ ከወረዳ ጀምሮ እስከ አገር አቀፍ ደረጃ ባለው የምክክር መድረክ አብላጫውን ቁጥር የያዙት የገዥው ፓርቲ አባላት እና የሥርዓቱ ደጋፊዎች መሆናቸውን ታዝቤያለሁ ብሏል።
በተጨማሪም በሂደቱ ድምጾች እንዳይሰሙ መገደባቸው የገለልተኝነት እና የግልጽነት ማነስ፣ በጸጥታ አካላት ታጅቦ መወያየት፣ እንዲሁም የተሳትፎ አድማስን ለማጥበብ ከውስጥ እና ከውጭ የሚደረጉ ወከባዎች የምክክሩን ፍትሐዊነት እና ቅቡልነት ክፉኛ ጥያቄ ውስጥ እንደከተቱት ፓርቲው አስገንዝቧል።
እንደ እናት ፓርቲ እምነት፣ ሀገራዊ ምክክር የቀውስ ጊዜ መፍትሔ ማመንጫ እንጂ የቅንጦት ኹነት አይደለም። በአሁኑ ወቅት ቢያንስ በሦስት ክልሎች ውስጥ ጦርነቶች እየተካሄዱ ባለበት እና ዘርን መሠረት ያደረገ ፌዴራሊዝም ሀገሪቱን አደጋ ላይ በጣለበት ሁኔታ፣ ምክክሩ እነዚህን የህልውና አደጋዎች ለማስቆም አልሞከረም። ከዚህ ይልቅ የችግሩን ሥር በማድበስበስ፣ ፖለቲካዊ ቁማሮች ላይ ማተኮሩን ፓርቲው ተችቷል።
ለአብነትም የሀገሪቱን መሪ ከጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ፕሬዝዳንትነት የመቀየር ጉዳይ፣ አዲስ አበባን ለአንድ ቡድን አሳልፎ ለመስጠት የሚደረግ ወከባ፣ የድሬዳዋ ዕጣ ፈንታ እና የዘመን አቆጣጠርን የመሳሰሉ ርዕሰ ጉዳዮች የሀገሪቱን ወቅታዊ ቀውስ የማይፈቱ እና አዲስ የጸብ ግንባር የሚከፍቱ መሆናቸውን በመግለጫው ተብራርቷል።
እናት ፓርቲ እነዚህ መሰረታዊ ሄደቶች ካልተስተካከሉ በስተቀር ከዚህ በመለስ ባሉ አጀንዳዎች ዙሪያ በሚደረጉ ስምምነቶች ላይ ፊርማውን እንደማያኖር አሳውቋል።
ገዥው ፓርቲ በሀገራዊ ምክክሩ ስም ሀገርን አስይዞ ከሚሠራው የፖለቲካ ቁማር እንዲታቀብ ያሳሰበው ፓርቲው፣ ተመካካሪዎችም ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሽፋን ከመሆን ተቆጥበው ለሀገር እና ለሕዝብ መቆምን በድፍረት እንዲያሳዩ ጠይቋል። በመጨረሻም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ይህ ሀገራዊ ምክክር የጥቂት አካላት ፍላጎት ማስፈጸሚያ እና ለአዲስ ቁርሾ መነሻ እንዳይሆን ሂደቱን በንቃት እና በትኩረት እንዲከታተለው እናት ፓርቲ ጥሪውን አስተላልፏል።

2 months ago