Logo
FastMereja
የአእምሮ እድገት ውስንነት ቀንን አስመልክቶ የተዘጋጀዉ ስፖርታዊ ውድድር በይፋ ተከፈተ!

​#fastmereja | 11ኛው የዓለም የዳውን ሲንድሮም ቀን በኢትዮጵያ “ብቸኝነትን በአንድነት እንመክት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀዉ ስፖርታዊ ዉድድር በዛሬዉ እለት በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በይፋ ተከፍቷል።

​በዛሬዉ የመክፈቻ ስነ-ስርአት ላይ የኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ዴኤታ አቶ መኪዩ መሀመድ እንዲሁም የስፔሻል ኦሎምፒክ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ግዛቸዉ ግርማን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች በተገኙበት ነዉ የተከናወነዉ።

ስፔሻል ኦሊምፒክስ ኢትዮጵያ ከ“ፍቅር የኢትዮጵያ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ብሔራዊ ማኅበር” ጋር በመተባበር የተዘጋጀዉ ይህ ሀገር አቀፍ ጨዋታ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።

​ዉድድሩ ሁሉንም የኦሎምፒክ ስፖርት ዓይነቶች ያካተተ ሲሆን፣ ውድድሩም የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸውን ተወዳዳሪዎች ባማከለ ልዩ የስፖርት ሕግ መሠረት እየተከናወነ ይገኛል።

የፍቅር ኢትዮጵያ ማህበር የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸውን ልጆች አስተምሮና አሰልጥኖ በማኅበሩ ውስጥ የሥራ ቅጥር እንዲያገኙ በማድረግ ጭምር አርአያነት ያለው ሥራ እያከናወነ ይገኛል።

​በአሁኑ ወቅት በአፍሪካና በኢትዮጵያ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ወገኖች ላይ የሚደርሰው መገለልና መድልዎ ከፍተኛ በመሆኑ፣ እንዲህ ያሉ ስፖርታዊ መድረኮች ግንዛቤን ለመፍጠርና ብቸኝነትን ለመቀነስ ትልቅ ፋይዳ አላቸው።

በዛሬዉ የመክፈቻ መርሀ-ግብር ላይ ደራሲ፣ዳይሬክተር እንዲሁም ፕሮዲዉሰር የሆነችዉን የራስወርቅ ግርማ የስፔሻል ኦሎምፒክ በጎ ፍቃድ አምባሳደር ሆና ተሾማለች።
#ኹነት #ስፖርት

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.