6ኛው “Arki Homes Expo" ከ20 በላይ የሪል እስቴት አልሚዎችን በማሰባሰብ ሊካሄድ ነው!
#fastmereja :- በአዲሱ ዓመትና በመስቀል በዓል ምክንያት ወደ ሀገራቸው የሚገቡ ዳያስፖራዎችን እና የሀገር ውስጥ ቤት ፈላጊዎችን ማዕከል ያደረገው 6ኛው "Arki Homes Expo” ከመስከረም 8 እስከ 10 ቀን 2019 ዓ.ም በጊዮን ሆቴል ሊካሄድ መሆኑ በዛሬዉ እለት በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።
“በአዲስ ዓመት አዲስ ቤት” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ይህ ኤክስፖ፣ ከ20 በላይ ታዋቂ፣ ታማኝ እና በግንባታ ጥራታቸው የሚታወቁ የሪል እስቴት አልሚዎችን በአንድ መድረክ የሚያሰባስብ መሆኑ ተገልጿል።
ዝግጅቱ ቤት የመግዛት እቅድ ያላቸው ወገኖች ከብዙ አማራጮች መካከል መርጠው በቂ መረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ እንዲወስኑ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተመልክቷል።
የዝግጅቱ ተሳታፊ የሆኑት ቴምር ሪል እስቴት፣ ሜሪት ፕሮፐርቲስ እና ጃንቦሮ ሪል እስቴት ከአዘጋጆቹ ጋር በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች በከፍተኛ ጥራትና ፍጥነት የገነቧቸውን የመኖሪያ ቤቶችና ሱቆች በልዩ የበዓል ቅናሽና አመቺ የክፍያ አማራጮች ማዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።
ከዚህ ቀደም በሚሊኒየም አዳራሽና በስካይላይት ሆቴል ይዘጋጁ የነበሩትን ኤክስፖዎች በማስፋፋት፣ ዘንድሮ በጊዮን ሆቴል ቤተሰቦች ከልጆቻቸው ጋር መጥተው እየተዝናኑ የሚገበዩበት ሰፊ የመጫወቻና የመዝናኛ ስፍራ መዘጋጀቱ ተገልጿል።
የኤክስፖው ዋና ዓላማ ገዥዎችንና አልሚዎችን በቀጥታ ማገናኘት፣ ለአልሚዎች የገበያ ዕድል መፍጠር እንዲሁም ህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የቤት ባለቤት እንዲሆን ማስቻል መሆኑን አዘጋጆቹ ገልጸው፤ ቤት ፈላጊዎች ኤክስፖውን ሳይጎበኙ የግዢ ውሳኔ እንዳይወስኑ ጥሪ አቅርበዋል።
#ኹነት

1 month ago