የፓን አፍሪካ ሮቦቲክስ ሻምፒዮንሺፕ በአዲስ አበባ በድምቀት ተጀመረ
#fastmereja I አዲስ አበባ
በቴክኖሎጂ የታነጸ ትውልድ ለመፍጠር ያለመው የፓን አፍሪካ ሮቦቲክስ ሻምፒዮንሺፕ ውድድር "እኔ ችግር ፈቺ ነኝ" በሚል መሪ ቃል ዛሬ በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም በይፋ ተጀምሯል። የኢትዮ ሮቦቲክስ የትምህርትና ስልጠና ማዕከል ባዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች በሮቦቲክስ፣ በኮዲንግ እና በዲዛይኒንግ ዘርፎች የፈጠራ ብቃታቸውን እንደሚያሳዩ ታውቋል።
በመክፈቻው ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ፣ መንግስት ለወጣቶች የፈጠራ ስራ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠሩንና መሰል ውድድሮች ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስጠራት ያላቸውን ሚና ገልጸዋል። የኢትዮ ሮቦቲክስ መስራች አቶ ሰናይክረም መኮንን በበኩላቸው፣ መጪው ዘመን ድህነትና በሽታ በቴክኖሎጂ የሚሸነፉበት መሆኑን በመጥቀስ ታዳጊዎች ለችግር ፈቺነት እንዲተጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ባለፉት 15 ዓመታት ወጣቶችን በዓለም አቀፍ መድረኮች ሲያሳትፍ የቆየው ኢትዮ ሮቦቲክስ፣ የዘንድሮው የፓን አፍሪካ ውድድር ተማሪዎች ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነታቸውን የሚያጎለብቱበት ወሳኝ ድልድይ እንደሚሆን ይጠበቃል። ድርጅቱ ከዚህ ቀደም በቻይና፣ ካናዳና አሜሪካ በሚካሄዱ ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያን በመወከል ስኬታማ ተሳትፎ ማድረጉ ይታወሳል።
#ኹነት

4 months ago