Logo
FastMereja
በጅማ ዞን ለሚካሄደው የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ የተለያዩ እንግዶች ጅማ ገቡ!

በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ሰቃ ወረዳ በቡዬ ቀጨማ ቀበሌ ነገ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄደውና ለመላው ኢትዮጵያውያን ጥሪ የቀረበበት የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ዝግጅት መጠጠናቀቁ ተገለጸ። በአገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር ከ800 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል በተያዘው ግብ መሠረት የሚከናወነው ይህ መርሃ-ግብር፤ አረንጓዴ አሻራን በማሳረፍ ረገድ የትውልድ ሀላፊነትን ለመወጣት ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።

ይህ ሀገር አቀፍ አቅጣጫን መሠረት ያደረገ ታላቅ መርሃ-ግብር በግሪን ዌቭ አሊያንስ ሀገር በቀል ግብረ-ሰናይ ድርጅት፣ ከኢፌድሪ ግብርና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዘጋጅነት የቀረበ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ አስፈላጊውን ቴክኒካል ድጋፍ በማድረግ ተሳትፏል።።

ለዝግጅቱ ስኬት በጅማ ከተማ የደረሱ ታዋቂ ግለሰቦች፣ አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ቲክቶክሮች እና የጥሪው ተጋባዦች በዞኑ እና በከተማ አስተዳደሩ፣ በአባ ገዳዎች፣ በሀደ ሲንቄዎች እንዲሁም በሀገር ሽማግሌዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ነገ በሚካሄደው በዚህ ታሪካዊ ኹነት ህብረተሰቡ በነቃ ሁኔታ እንዲሳተፍ አዘጋጆቹ ጥሪ አቅርበዋል።

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.