ሁሌ ቅርጫ የዲጂታል ቅርጫ አገልግሎት ሥራ ጀመረ
ሁሌ ቅርጫ የተባለ የቅርጫ አገልግሎትን በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ አሠራር ተግባር ላይ መዋሉን የሁሌ ቅርጫ የሥራ መሪ አቶ ቶማስ መለሰ አስታውቀዋል። ከኢትዮ ቴሌኮምም ጋር ይህን ሥራ ለመሥራት የሥራ ውል ስምምነት ተፈራርመዋል።
በኢትዮ ቴሌኮም በኩል የዘመን ገበያ ኦፕሬሽን ማኔጀር አቶ ቸርነት ሰኢድ የውል ስምምነቱ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩ ሲሆን በቴሌብር በዘመን ገበያ አማካይነት ግብይቱ እንደሚከናወን ታውቋል።
ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ የተዘጋጀው ይህ አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ የትንሣኤ በዓል አስመልክቶ ለተገልጋዮች ክፍት ይሆናል ተብሏል።
አፓርትመንት እንዲሁም የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ የሚኖሩ ሰዎች፣ ቅርጫ ለማግኘት እንደሚቸገሩ ያስታወሱት አቶ ቶማስ፣ አገልግሎቱ አንድም ይህን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አስረድተዋል። በተጨማሪም፣ ሰዉ በኑሮ ሩጫ መካከል ሆኖ ጊዜ እያጠረው ከመሆኑ አንጻር፣ ቅርጫ የሚገቡ ሰዎችን ማፈላለግና ማሰባሰብ፣ በሬ ለመግዛት ገበያ ማቅናት እንዲሁም አራጆችን መፈለግ አስቸጋሪ መሆኑን አንስተዋል። ሁሌ ቅርጫ ይህን ሁሉ ድካም በማስቀረት ለኅብረተሰቡ ትልቅ ጠቀሜታ የሚሰጥ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ከዚህም ባሻገር ከእርድ የሚተርፉ እንደ በሬ ቆዳ፣ ጭንቅላት እና የመሳሰሉት፣ ፅዱና ንፁህ በሆነች ከተማ ላይ በየአካባቢው መጣሉ ለነዋሪዎች ጤንነት እክል እንደሚሆን አንስተዋል። ሁሌ ቅርጫም ይህን በማስቀረት ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
ከሃገር ውጭ የሚኖሩ ሰዎችም ያለምንም ውጣ ውረድ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው የቅርጫ ሥጋ የሚገዙበት መልካም አጋጣሚ መሆኑን አቶ ቶማስ አስረድተዋል።
ዋጋውን በተመለከተ ቅናሽ ያለው ሲሆን፣ ከመደበኛ ግብይት በተሻለ ደንበኞች የመረጡትን በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት የሚችሉበት ነው። በኢትዮ ቴሌኮም የዘመን ገበያ አገልግሎት በኩልም፣ ደንበኞች በኢትዮ ቴሌኮም ክፍያ ከፈፀሙ በኃላ በየቤታቸው የሚደርስበት የዴሊቨሪ አገልግሎት መኖሩንም ታውቋል። ሁሌ ቅርጫ ከሸጠው ላይ 2 % አቅም ለሌላቸው የበዓል ድጋፍ እንደሚያውልም ታውቋል።
'ሁሌ ቅርጫ' ላለፉት ዓመታት ጥራቱን እና ደረጃውን የጠበቀ፣ ደኅንነቱም የተረጋገጠ ስጋን ለውጭ ገበያ ሲልክ ቆይቷል። አሁን ላይ ይህን ተመሳሳይ አገልግሎት ለሀገር ውስጥ ገበያ መስጠት ጀምሯል።
አቶ ቶማስ እንደገለጹት፣ ይህ ግብይት አሁን በዓሉን በማስመልከት ይጀመር እንጂ በአዘቦት ቀናትም የሚቀጥል ነው። ከዓመት ዓመት የበግ እና የፍየል እርድን ጨምሮ፣ ለተለያየ ኹነትም ሰብሰብ ብለው ቅርጫ ለፈለጉም አገልግሎቱ ተደራሽ እንደሚሆን አሳውቀዋል።
ቅርጫ የሚለው ባህል እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ቀለል ባለና ደኅንነቱ እና ደረጃው በተጠበቀ መንገድ አገልግሎትን መስጠት የሁሌ ቅርጫ ዓላማ መሆኑንም አቶ ቶማስ ተናግረዋል።

2 months ago