Logo
FastMereja
በኢትዮጵያ የሕክምና ዘርፍ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ሚና ላይ ያተኮረው 62ኛው የኢሕማ ዓመታዊ ጉባኤ በሂልተን ሆቴል ተከፈተ

​#fastmereja I የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር (ኢሕማ) "የሰው ሠራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) በሕክምና ትምህርት፣ በጤና አገልግሎት አሰጣጥ እና በምርምር ዘርፍ ያለውን ሚና ማሳደግ" በሚል መሪ ቃል 62ኛ ዓመታዊ ጉባኤውንና ዓለም አቀፍ የጤና ኤግዚቢሽኑን ዛሬ በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል በይፋ ጀምሯል።

​በመክፈቻው ላይ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰሃረላ አብዱላሂን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የሕክምና ስፔሻሊስቶች ተገኝተዋል። ጉባኤው በዋናነት ቴክኖሎጂን በመጠቀም የኢትዮጵያን የሕክምና ጥራትና ተደራሽነት ማዘመን በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ያተኮረ ምክክር እያካሄደ ይገኛል።

​የዘንድሮው መሪ ቃል በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ እምብዛም ያልተለመደውን የAI ቴክኖሎጂን ለምርምርና ለታካሚዎች ፈጣን ሕክምና እንዴት ማዋል እንደሚቻል አዳዲስ አቅጣጫዎችን የሚያመላክት መሆኑ ተገልጿል። በተጓዳኝ እየተካሄደ ባለው ኤግዚቢሽን ላይም ከቴክኖሎጂው ጋር የተያያዙ የሕክምና መሣሪያዎችና ዲጂታል መፍትሔዎች ለጉብኝት ቀርበዋል።

በዛሬው መርሃ ግብር ላይ የኢሕማ አዋርድ ላይ ተካሂዷል።
#ኹነት

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.