Logo
FastMereja
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ100ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በታላቅ ድምቀት ሊያከብር ነው
#fastmereja I የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) የተመሰረተበትን 100ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አስመልክቶ ከሐምሌ 7/2018 ዓ.ም በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ የተለያዩ ዝግጅቶችን እያከናወነ እንደሚገኝ ተነግሯል። ኢንስቲትዩቱ የክፍለ ዘመኑን ጉዞ ለመዘከርና በጤናው ዘርፍ የተመዘገቡ አዳዲስ ምርምሮችን ለማቅረብ መዘጋጀቱን አስታውቋል።

የኢንስቲትዩቱ ይፋዊ መርሃ-ግብር እንደሚያሳየው፣ ዋናው በዓልና ሳይንሳዊ ጉባኤው ከሐምሌ 9 እስከ ሐምሌ 11/2018 ዓ.ም ባሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት በልዩ ሁኔታ ይካሄዳል። በዓሉ የኢንስቲትዩቱን የ100 ዓመታት ጉዞ የሚያሳዩ ፎቶግራፎችና ቪዲዮዎች፣ የምስጋናና የእውቅና አሰጣጥ ስነ-ስርዓቶች እንዲሁም በጤናው ዘርፍ ተስፋ ሰጪ በሆኑ አዳዲስ ግኝቶች ላይ ያተኮሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች የሚቀርቡበት መድረክ እንደሚሆን ተነግሯል።
#ኹነት

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.