በሐዋሳ ከተማ ታላቅ የጎዳና ላይ ሩጫ ሊካሄድ ነው!
#fastmereja “አብረን እንሩጥ፣ ለሐዋሳ ከፍታ'' በሚል መሪ ቃል ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ የሚካሄድ ታላቅ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ መዘጋጀቱ በዛሬዉ እለት በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።
ይህ በዓይነቱ ለየት ያለ ስፖርታዊ ኩነት የሚዘጋጀው ለስድስት አስርት ዓመታት በታማኝነት ሲያገለግል በቆየውና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለቤትነት በሚተዳደረው ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና በታዋቂው አትሌት ገዝሀኝ አበራ ትብብር መሆኑ ተገልጿል።
በዝግጅቱ ላይ ከ15 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ ታዋቂ አትሌቶች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እንዲሁም የሐዋሳ ከተማና የአካባቢው ነዋሪዎች የሩጫው አካል እንደሚሆኑ ታውቋል።
ውድድሩን በአሸናፊነት ለሚያጠናቅቁ ሯጮችም ከፍተኛ የገንዘብ እና የሜዳሊያ ሽልማት እንደሚበረከት አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
የዝግጅቱ ዋና ዓላማዎች የማህበረሰቡን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ባህል ማሳደግ፤በከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ያለውን ማህበራዊ ትስስር፣ ሰላምና አብሮነት ማጠናከር፤የሐዋሳን የቱሪዝም ዘርፍ ማነቃቃት እንዲሁም የከተማዋን ገጽታ መገንባት መሆኑ ነዉ የተገለፀዉ።
ኮሜርሻል ኖሚኒስ በቀጣይም ከታዋቂው አትሌት ገዝሀኝ አበራ ጋር በመሆን መሰል የጎዳና ላይ ሩጫዎችን በተመረጡ የሀገሪቱ ከተሞች ለማካሄድ እቅድ እንዳለው ገልጿል።
#ስፖርት #ኹነት

4 months ago