10ኛው "ኢትዮ ኸልዝ" ዓለምአቀፍ አውደርዕይ እና ጉባኤ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው
#fastmereja I በአስርተ ዓመታት የጤናው ዘርፍ ጉዞ ታላቅ ስም ያተረፈው ኢትዮ ኸልዝ ዓለምአቀፍ አውደርዕይና ጉባኤ፣ ለ10ኛ ጊዜ ከመጋቢት 24 እስከ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር (AICC) እንደሚካሄድ ዛሬ መጋቢት 08 ቀን 2018 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።
ፕራና ኢቨንትስ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና ከአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (AHRI) ጋር በመተባበር ባዘጋጁት በዚህ መድረክ ላይ፣ ከ8 ሀገራት የተውጣጡ ከ90 በላይ ኩባንያዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ያቀርባሉ።
የዘንድሮው ኹነት 2ኛው የሀገር ውስጥ የሕክምና ግብዓት ምርትና ኢኖቬሽን ኤግዚቢሽን ጎን ለጎን የሚካሄድ ሲሆን፣ ዓላማውም የሀገር ውስጥ አምራቾችን አቅም ማሳየትና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መተካት ነው።
ከ20 በላይ ከሚሆኑ የሙያ ማኅበራት ጋር በመተባበር፣ ከ40 በላይ የሙያ ማጎልበቻ ስልጠናዎች ለጤና ባለሙያዎች ይሰጣሉ።
2ኛው ዓመታዊ ሳይንሳዊ ፎረም፣ የጤና አመራር ጉባኤ እና 3ኛው የዲጂታል ኸልዝ ሃካቶን በኹነቱ ውስጥ የተካተቱ አቢይ መድረኮች ናቸው።
ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ከባንግላዴሽ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ ሩሲያ፣ ቱርክ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ እና አሜሪካ የመጡ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ።
ይህ መድረክ በኢትዮጵያ የጤናው ዘርፍ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲፋጠን፣ የንግድ ትስስር እንዲጎለብትና የሕክምና አገልግሎት ጥራት እንዲሻሻል ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል። በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ባለሥልጣን (EFDA) እና በሌሎችም ተቋማት ሙሉ ዕውቅና የተሰጠው ይህ አውደርዕይ፣ የዘርፉ ተዋናዮች የሚገናኙበት ትልቁ ሀገራዊ መድረክ ነው።
#ኹነት

3 months ago