“ኢትዮ ሆም-ኤክስፖ 2026” በለንደን ከተማ ሊካሄድ ነዉ!
#fastmereja I በዩናይትድ ኪንግደም ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው አስተማማኝ የቤት ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችል “ኢትዮ ሆም-ኤክስፖ 2026" የተሰኘ ታላቅ የሪል ስቴት ኤክስፖ በለንደን ከተማ እንደሚካሄድ በዛሬዉ እለት ተገለፀ።
በለንደን የሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ፣ ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት፣ ከኢትዮጵያ ሪልስቴት አልሚዎች ማህበር፣ ከአዲስ አበባ ንግድ ምክርቤት እና ኤድማርቬንቸርስ ከተባለ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተቋም ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
ኤክስፖው ከግንቦት 15 እስከ 17 ቀን 2018 (May 23-25, 2026) ለሶሰት ተከታታይ ቀናት በለንደን ከተማ የሚካሄድ ሲሆን ከ3000 በላይ ተሳታፊዎች እንደሚኖሩም ነዉ የተገለፀዉ።
ይህ ኤክስፖ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ቤት የማፍራት ህልማቸውን እውን እንዲያደርጉ፣ በአልሚዎችና በተጠቃሚዎች መካከል ያለውን መተማመን ማሳደግና አስተማማኝ የግብይት ሥርዓት ማስተዋወቅ የተዘጋጀ መሆኑ ተጠቁሟል።
የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት በኤክስፖው የሚሳተፉ አልሚዎችን በግንባታ አፈፃፀማቸው፣ በጥራትና በሰነድ ህጋዊነት የመለየትና የማጣራት ስራ በመስራት የዲያስፖራውን ስጋት ለመቅረፍ እንደሚሰራ የኤድማር ቬንቸር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፋሲካ አብዛ ገልፀዋል።
ኤክስፖዉ በዘርፉ ስላሉ አዳዲስ ፖሊሲዎችና የቤት ግዢ አማራጮች ከመንግስትና ከግል ተቋማት ጋር የመረጃ ልውውጥና የፓናል ውይይቶች የሚደረጉ ሲሆን የንግድ ባንኮች ለዲያስፖራው ማህበረሰብ የሚሆኑ ልዩ የፋይናንስ ድጋፎችንና የቤት ባለቤት የሚያደርጉ የብድር አማራጮችን ለተሳታፊዎች እንደሚያስተዋዉቁም ነዉ የተገለፀዉ።
በዛሬዉ እለት በተከናወነ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አዘጋጁ ኤድማር ቬንቸር እና አዲስ ቻምበር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን የፌርማ ስነ-ስርአት አከናዉነዋል።
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍፁም አረጋን ጨምሮ የኢትዮጵያ ሪልስቴት አልሚዎች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አለማየሁ ከተማ፣ የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ ወልደገብርኤል እንዲሁም የኤድማር ቬንቸርስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፋሲካ አብዛ ተገኝተዋል።
#ኹነት

4 months ago