4 days ago
የአዋሽ ኮምቦልቻ ሀራ ገብያ የባቡር መስመር ሥራ ጀምረናል
➡ https://youtu.be/e0pZ-1LU_...
#awash #haragebya #kombolacha #train #pmabiyahmed
16 days ago
ተጨባጭ ውጤት ያመጣው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የግሉን ዘርፍ ማዕከል ያደረገ ሥርዓት ለመገንባት የተነደፈ ሪፎርም ነው።
ማሻሻያው የኢኮኖሚውን መዋቅራዊ ችግሮችን በመቅረፍ ዘላቂ ዕድገትን ለማረጋገጥ ያለመ ሲሆን፤ ዋና ዓላማው የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባቶችን በማስተካከል የወጪ ንግድን በማሳደግ ዘላቂ ብልጽግናን ማረጋገጥ ነው።
የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ካካተታቸው ቁልፍ ጉዳዮች መካከል ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚወጣባቸውን ምርቶች በሀገር ውስጥ በማምረት መተካት ነው፡፡
በዚህም ለሀገር በቀል አምራች ኢንዱስትሪዎች ትኩረት በመስጠትና ድጋፍ በማድረግ ትልቅ አቅም እየፈጠረ ይገኛል፡፡
አምራች ኢንዱስትሪዎች በሚያመርቱት ተኪ ምርት ከሀገር ውስጥ ፍጆታ አልፈው ወደ ውጪ በመላክ የውጭ ምንዛሬ ገቢን ከፍ በማድረግ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን በማጎልበት ላይ ናቸው።
የኢንዱስትሪው ዘርፍ ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስቀረትና አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር ሀገራዊ ኢኮኖሚውን በመቀየር ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
በተከናወኑ ዓበይት የማሻሻያ ስራዎች አጠቃላይ የማኑፋክቸሪንግ አቅም ከነበረበት 47 በመቶ ወደ 67 በመቶ አድጓል፡፡
ከነባሮቹ የሐዋሳ፣ ኮምቦልቻ እና መቐለ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በተጨማሪ በርካታ ፓርኮች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁ ሲሆን፤ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትም ወደ ዘርፉ እንዲገባ ተደርጓል።
በተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ለውጦች መታየት የጀመሩ ሲሆን፤ በዚህም ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት ዕቅዱ በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ እየሆነ መጥቷል፡፡
እንደ ሲሚንቶ፣ ብረት እና ሴራሚክ የመሳሰሉ የግንባታ ምርቶች በስፋት በሀገር ውስጥ መመረት መጀመራቸው በሀገር ውስጥ ተኪ ምርቶች ብቻ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬን ማዳን ተችሏል።
ዘርፉ ራሱን ከማሳደጉ ጎን ለጎን በርካታ አዳዲስ ጥቃቅን፣ መካከለኛ እንዲሁም ከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በማፍራትና በማጠናከር ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጥሯል፡፡
ለኢንደስትሪው ዘርፍ በተሰጠው ትኩረት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪ የሚደረግባቸው ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት ኢኮኖሚው ላይ ያለውን ጫና እየቀነሰ ይገኛል፡፡
ሀገሪቱ በኢኮኖሚው ዘርፍ የምታከናውናቸው ማሻሻያዎች ከተረጂነት ወጥታ በራሷ ምርቶች የምትተማመንና ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ማዕከል እንድትሆን ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡
በመልካም ፈቃዱ

23 days ago
አዲሱ መንበረ ጵጵስና በብፁዓን አበው ቡራኬ ተመረቀ
#ethiopia | የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ያስገነባው አዲሱ መንበረ ጵጵስና በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬና ጸሎት በድምቀት ተመርቋል።
በሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም በተከናወነው በዚህ የምረቃ መርሐ ግብር ላይ መንበረ ጵጵስናው በብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ፣ በብፁዕ አቡነ ቄርሎስና በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ቡራኬ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ አባታዊ መልእክት ያስተላለፉት የሰሜን ወሎ የደቡብ ወሎና በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ኬሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ፤ ቀደም ሲል አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው መንበረ ጵጵስና በ1940ዎቹ የተገነባ ጥንታዊ መሆኑን አስታውሰዋል።
ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ቀደም ሲል የሰሜን ወሎ፣ የዋግኸምራ፣ የአፋርና የኬሚሴ አህጉረ ስብከትን አካቶ ያስተዳድር የነበረና በርካታ ጥንታውያን ገዳማት፣ አድባራትና የመንፈሳዊ ትምህርት ተቋማት መገኛ በመሆኑ ታሪኩን የሚመጥን ዘመናዊ መንበረ ጵጵስና ለመገንባት ዕቅድ መኖሩን ጠቁመዋል።
አሁን የተሠራው መጠነኛ መንበረ ጵጵስናም ዋናው ሕንጻ እስኪገነባ ድረስ አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ በአባቶች እንዲባረክ የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ብፁዕነታቸው አያይዘውም፣ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ ዘመኑን የዋጀ መንበረ ጵጵስና ሳይኖራቸው ለ34 ዓመታት በታሪክ የሚዘከሩ ታላላቅ ሥራዎችን ማከናወናቸውን በማውሳት በሁለቱ አረጋውያን አባቶች ጸሎትና ምክር ታግዘው የአካባቢውን ታሪክ ለማሳወቅና ክብሩን ለመመለስ እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል።
በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት መረጃ መሠረት በ470 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው የዚህ መንበረ ጵጵስና ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳቱ በተጨማሪ የሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ አንድነት ገዳም አበምኔት፣ የደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች አብያተ ክህነት ሥራ አስኪያጆች፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎችና የታላላቅ ጉባኤ ቤት መምህራን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከናውኗል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

1 month ago
ውሻዉን ያልገደለ ግለሰብ በ50,000 ብር እና በእስራት እንዲቀጣ ታወጀ !
በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሆሳና ከተማ እያንዳንዱ ግለሰብ በቤቱ ያለዉን ዉሻ አውጥቶ እንዲገድል በታወጀው መሰረት ዉሻ ያላቸው ግለሰቦች ....
ዉሻቸውን ገመድ በማጥለቅ በቀንጨት ላይ በማንጠልጠል ዉሾችን እያነቁ እየገደሉ መሆኑን በትናንትናው ዕለት ግዮን ማለዳ ዘግቦ ነበር።
በሆሳእና ከተማ ከሰሞኑ በውሻ ምክንያት በሽታ ተከስቷል የተባለ ሲሆን ይህ የውሻ ግድያ ዘመቻ የተጀመረው አንድ ውሻ የ13 አመት ልጅ ነክሳው ከሞተ በኋላ መሆኑን ታውቋል።
ቪዲዮዎች Ghion Maleda የቴሌግራም ቻናል እንደምታዩት የራሳቸው ባለቤት ያላቸውና ክትባት የተሰጣቸው ውሾችን ጨምሮ በእጅግ አሰቃቂ ሁኔታ በመንጋ ውሾችን እያስጮሁ ዛፍ ላይ በማ- ነቅ የገደሏቸው ።
በኮምቦልቻ ከተማ የእብድ ውሻ በሽታ (Rabies) ከባድ የሕዝብ ጤና ስጋት መሆኑን ሪፖርቶች ቢወጡም መሰል ከሰባዊነት ያፈነገጠ ተግባር በፍጹም አልተደረገም ነበር ።
በሆሳና ከተማ በጣም የሚያሳስበው፣ አንዳንድ ሕፃናት በእነዚህ ድርጊቶች ውስጥ ተሳትፈዋል በቪዲዮዎች ተመልክተናል ።ጉዳዩ የእንስሳት ደህንነት ብቻ ሳይሆን ለሚቀጥለው ትውልድ ምን ዓይነት እሴቶችን እያስተላለፍን እንዳለን የሚያስጠይቅ ነው። ርኅራኄ ይማራል፤ ጭካኔም እንዲሁ ይማራል።
የእብድ ውሻ በሽታ (Rabies) ከባድ የሕዝብ ጤና ጉዳይ ነው፣ መቆጣጠር ያስፈልጋል። ሆኖም የሳይንስ ማስረጃዎች እንደሚያሳዩት ችግሩን በዘላቂነት የሚቀንሱት...
ሰብዓዊና ውጤታማ መንገዶች እንደ የጅምላ ክትባት፣ የውሾች ማምከን፣ ለሕዝብ ግንዛቤ መስጠት እና ኃላፊነት ያለው የእንስሳት አስተዳደር ናቸው፤ ጭካኔ እና ግፍ ግን መፍትሔ አይደሉም።via Ghion maleda
Seledadotio

2 months ago
የሟቾች ቁጥር 31 ደረሰ🕯🕯
በተከሰተው የመኪና አደጋ የሟቾች ቁጥር 31 መድረሱን የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
ዛሬ ጠዋት በደሴ እና ኮምቦልቻ መካከል ሐረጎ በተባለ ሥፍራ በደረሰ የመኪና አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉን መዘገባችን ይታወሰል።
አሁን ደግሞ የሟቾች ቁጥር መጨመሩን ፖሊስ አስታውቋል። የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ እንደገለጸው በአደጋው ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች 31 ደርሷል።
አደጋው የደረሰው በተለምዶ ከደሴ ወደ ኮምቦልቻ በሚወስደው ሐረጎ "S" መንገድ መታጠፊያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከንጋቱ 12:00 መኾኑን የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ጌታቸው ሙህዬ ተናግረዋል።
ተሽከርካሪው ከ100 ሜትር በላይ ርዝመት ያለው ገደል ውስጥ በመግባቱ ሹፌሩን ጨምሮ የ31 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ33 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱንም ኮማንደር ጌታቸው ለአሚኮ ገልጸዋል።
ተሽከርካሪው 64 ሰዎችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ እንደነበር ያነሱት ኮማንደር ጌታቸው ተጎጅዎች በደሴ እና በኮምቦልቻ ሆስፒታሎች ሕክምና እየተደረገላቸው እንደኾነም አንስተዋል።
የአደጋው መንስኤም እየተጣራ መኾኑን አስታውቀዋል።
ለተጎጅ ቤተሰቦችም መጽናናትን እንመኛለን።

ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ።
ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ በደረሰ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታውቋል።
አደጋው የደረሰው ከደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች መካከል በሚገኘው የሐረጎ መንገድ ላይ ነው።
ዛሬ ሰኔ 08/10/18ዓ.ም ማለዳ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ የሕዝብ አውቶቡስ በተለምዶ ሐረጎ እየተባለ በሚጠራው መንገድ ላይ በደረሠበት አደጋ እስካሁን የ28 ሰው ሕይወት ሲያልፍ በርካቶች ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባተቸዋል።
የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው በግምት100 ሜትር ጥልቀት ወዳለው ገደል ገብቶ ነው አደጋው የደረሠው። በሕይወት የተረፉትን ወደ ሕክምና ቦታ ለማድረስ አሁንም ርብርብ እየተደረገ መኾኑን የገለጸው ፓሊስ የአደጋውን ምክንያት በመጣራት ላይ መኾኑን አስታውቋል።
አሚኮ

Sponsored by
Surafel
2 months ago
አሳዛኝ ዜና‼️
ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ዛሬ ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ማለዳ ላይ በደረሰበት አሰቃቂ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።
አደጋው የደረሰው ከደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች መካከል በሚገኘው የሐረጎ መንገድ ላይ ሲሆን፣ አውቶቡሱ በግምት 100 ሜትር ጥልቀት ወዳለው ገደል መግባቱ ታውቋል።
በአደጋው በርካታ ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፣ በሕይወት የተረፉትን ወደ ሕክምና ተቋማት ለማድረስ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።

በደሴ እና በኮምቦልቻ መካከል
በትራፊክ አደጋ የ28 ሕይወት ተቀጠፈ
#ethiopia | ከደሴ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ በደረሰ ከባድ የትራፊክ አደጋ የ28 ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ ገለጸ።
አደጋው የተከሰተው በደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች መካከል ልዩ ስሙ ሐረጎ በሚባለው አካባቢ መሆኑ ታውቋል።
ዛሬ ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ማለዳ ላይ ሲጓዝ የነበረው ይህ አውቶቡስ መንገዱን ስቶ በግምት 100 ሜትር ጥልቀት ወዳለው ገደል በመግባቱ የ28 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሊያልፍ ችሏል።
በተጨማሪም በጉዞው ላይ በነበሩ ሌሎች በርካታ ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በአሁኑ ወቅት ከአደጋው የተረፉትን ተጎጂዎች በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋማት ለማድረስ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ የገለጸው ፖሊስ፣ አደጋው የተከሰተበትን ትክክለኛ መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን አስታውቋል።
ሳሙኤል ኪሮስ
አሚኮ
#የጎዳናአደጋ #የትራፊክአደጋ #ደሴ #ኮምቦልቻ #አሚኮ #የአደጋመረጃ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

"አምራች ኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ የልብ ምት ነው " አሕመዲን ሙሐመድ ( ዶ.ር)
"ኢትዮጵያ ታምርት" ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር "ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት" በሚል መሪ መልዕክት በኮምቦልቻ ከተማ ዛሬ ግንቦት 30 2018 ተካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ ከባለሃብቶች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ የተገኙ ባለሃብቶች የግብዓት፣ የኀይል አቅርቦት እና የመሠረተ ልማት ዝርጋታ እንዲሟላ ጠይቀዋል። የክልሉን ኢንቨስትመንት ለማሳደግ ሰላምን ማረጋገጥ እንደሚገባም ተናግረዋል።
ክልሉ ተወዳዳሪ እንዲኾን ከተፈለገ ሰላምን ማረጋገጥ እና ለኢንዱስትሪ ማነቆ የኾኑ ችግሮችን መፍታት ይገባል ነው ያሉት። የማስፋፊያ ቦታዎችን ማመቻቸት እንደሚገባም ገልጸዋል። የፋይናንስ ተቋማት ለባለሃብቶች የብድር አቅርቦት እንዲያመቻቹም ጠይቀዋል።
የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ የክልሉ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ባለሃብቶች የሚያነሷቸውን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት በትኩረት እየሠራ መኾኑንም ተናግረዋል።
ችግሮች እንዲፈቱ ተደጋጋሚ ውይይቶች እየተደረጉ እና አቅጣጫዎች እየተቀመጡ መኾናቸውንም ገልጸዋል። የፋይናንስ ተቋማት የብድር አቅርቦት እንዲያመቻቹ ውይይት መደረጉንም አንስተዋል። ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ እንደሚፈቱም ገልጸዋል።
በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢኮኖሚ መዋቅር ለውጥ ማምጣቱን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ችግሮችን እየፈታ፣ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ምርት እንዲጨምር ያደረገ ነው ብለዋል።
"አምራች ኢንዱስትሪው የኢኮኖሚው የልብ ምት ነው" ያሉት አስተባባሪው የልብ ምት የኾነውን ዘርፍ በቅንጅት ማሳደግ ይገባል ነው ያሉት። አምራች ኢንዱስትሪው ያለበትን ማነቆ እየፈቱ መሄድ እንደሚገባም አመላክተዋል።
የኀይል አቅርቦትን እና ሌሎች ችግሮችን መፍታት አለብን ነው ያሉት። ከተቋማት ጋር ያለን ቅንጅት ማጠናከር እንደሚያስፈልግም አንስተዋል። ለኢንዱስትሪ የሚመጥን የሰው ኀይል መገንባት እንደሚገባም አመላክተዋል። ባለሃብቶች ጥራቱን የጠበቀ ምርት እንዲያመርቱም አስገንዝበዋል። በተገቢው መንገድ በመሥራት ኢትዮጵያን ከኢኮኖሚ ጥገኝነት እንዲያላቅቁ እና በሁሉም መስክ ራሷን የቻለች እንድትኾን እንዲተጉም አሳስበዋል።

"ሀገር የተሟላ ሉዓላዊነት እና ነፃነት የሚኖራት በሁሉም መስክ ራስን መቻል ሲቻል ነው" - የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ
*******************
የአማራ ክልል "ኢትዮጵያ ታምርት" የንቅናቄ ማጠቃለያ መርሐ ግብር "ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት" በሚል መሪ መልዕክት በኮምቦልቻ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ ክልሉን ተወዳዳሪ እና ቀዳሚ ለማድረግ ሁሉም አካል በቅንጅት እና በትብብር ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ በራስ አቅም የማደግ፣ የራስን ምርት የማሳደግ እና የመጠቀም እንዲሁም ሀገርን በአንድነት የማበልጸግ እሳቤ የወለደው መሆኑን አቶ አረጋ ገልጸዋል።
"ሀገር የተሟላ ሉዓላዊነት እና ነፃነት የሚኖራት በሁሉም መስክ ራስን መቻል ሲቻል ነው" ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ በምርት ራሱን ያልቻለ ሀገር የሌሎች ሀገራት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ ጥገኛ መሆኑ እንደማይቀር አስገንዝበዋል።
ኢትዮጵያ በቀኝ ግዛት ያልተገዛች ሀገር ብትሆንም፣ የተሟላ ነፃነት እና ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ሕዝቡን ከድህነት እና ኋላቀርነት ማላቀቅ እንዲሁም በምርት ራስን መቻል የውዴታ ሳይሆን ግዴታ መሆኑን አብራርተዋል።
የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ዕድገት በከፍተኛ ደረጃ እየቀየረው መምጣቱን ገልጸው፣ ከዚህ ቀደም የነበሩ የኃይል፣ የፋይናንስ አቅርቦት እና ሌሎች ማነቆዎች በሂደት እየተፈቱ መምጣታቸውን ተናግረዋል።
በሀገር አቀፍም ሆነ በክልል ደረጃ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የማምረት አቅም ከበፊቱ በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉን ጠቁመው፣ አሁንም ግን ለአነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ዕድገት ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።
የክልሉ ኢንዱስትሪ በፀጥታ ችግር ውስጥ ማለፉን በማስታወስም፣ ኢንዱስትሪዎችን ማስፋፋት ራሱ የፀጥታ ችግሩን እንደሚፈታው ተናግረዋል።
"ኢኮኖሚው ያደገ ሀገር እና ሕዝብ ወደ ግጭት አይገባም" በማለትም የኢንዱስትሪው ዕድገት ለሰላም ያለውን አስተዋፅኦ አጉልተዋል።
ይህንንም መሠረት በማድረግ፣ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የክልሉ የ25 ዓመታት የአሻጋሪ ዕድገት እና የዘላቂ ልማት ዕቅድ ቁልፍ የትኩረት አቅጣጫ መደረጉን ገልጸዋል።
የፀጥታ ችግር ሳይበግራቸው በክልሉ በመሥራት ለውጤት የበቁ ባለሀብቶችን አመስግነዋል።
"የኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ የክልሉን ጸጋ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ባለሀብቶች ለማስተዋወቅ፣ የገበያ ትሥሥር ለመፍጠር እና የመንግሥት እና የባለሀብቱን ቅርርብ ለማሻሻል ዓይነተኛ ሚና መጫወቱን አብራርተዋል።
የክልሉ መንግሥት አዳዲስም ሆነ ነባር ባለሀብቶችን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን በማረጋገጥ፣ ሌሎች ባለሀብቶችም ወደ ሥራ እንዲገቡ ጥሪ ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል።
#ethiopia #ebc #madeinethiopia #industry

ንቅናቄው ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ የሚደረግ የኢኮኖሚ ትግል ምዕራፍ ነው - አቶ አረጋ ከበደ
በአዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ የሚደረግ የኢኮኖሚ ትግል ምዕራፍ ነው አሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር በኮምቦልቻ ከተማ እየተካሄደ ነው።
አቶ አረጋ ከበደ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ የሌሎች ሀገራት ጥገኛ የሆነ ኢኮኖሚ የገነባ ሀገር ሉዓላዊነቱ የተረጋገጠ ነው ሊባል አይችልም።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የራስን አቅም በመጠቀም የራስን ምርት ማምረት በሚል መርሕ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ገልጸው ÷ ንቅናቄው ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ የሚደረግ የኢኮኖሚ ትግል ምዕራፍ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
ከዚህ ቀደም የነበረውን ፍጆታን ብቻ መሰረት ያደረገ ኢኮኖሚ በመቀየር አሁን ላይ ሀገሪቱ በራሷ ልጆችና ግብዓት የራሷን ምርት በማምረት እንድትጠቀም ንቅናቄው ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አንስተዋል።
ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ላይ እየተሰራ ያለው ሥራ አበረታች ነው፤ ይሁን እንጂ የኢኮኖሚ ፍትሐዊነትንና የብዙዎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በመካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ልማት ላይ ልዩ ትኩረት መስጠት ይገባል ብለዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በበኩላቸው÷ በክልሉ እየተመረቱ ያሉ ምርቶች በዋናነት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን የሚተኩና ወደ ውጭ ገበያ የሚላኩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
የክልሉን ሁለገብ አቅም በመጠቀም በሁሉም ዘርፍ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የማምረት ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
በክልሉ የኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ባለፉት ዓመታት ትልቅ ለውጥ ቢመዘገብም የኃይል አቅርቦት፣ የመሰረተ ልማት ችግር እና የፋይናንስ እጥረት አሁንም የዘርፉ ተግዳሮቶች መሆነው መቀጠላቸው በመድረኩ ተመላክቷል።
በአለባቸው አባተ

"ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉአላዊነት " በሚል መሪ ቃል ክልላዊ የኢትዮጵያ ታምርት ማጠቃለያ መርሐ ግብር ነገ በኮምቦልቻ ከተማ ይካሄዳል።
ኮምቦልቻ: ግንቦት 29/2018 ዓ.ም (ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ)
የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የኢትዮጵያ ታምርት ክልላዊ የማጠቃለያ መድረክ ነገ ግንቦት 30/2018 ዓ.ም በኢንዱስትሪ መንደሯ ኮምቦልቻ ከተማ ያካሂዳል። የማጠቃለያ መርሐ ግብሩም "ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት" በሚል መሪ መልዕክት ነው የሚካሄደው።
የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኀላፊ አቶ ተፈሪ ታረቀኝ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በክልሉ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ላይ የነበሩ ችግሮችን እየፈታ መምጣቱን ገልጸዋል።
የማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ከመካሄዱ አስቀድሞ 159 የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄዎች በየደረጃው ሲካሄድ መቆየታቸውን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ማምረት አለባት ያሉት ምክትል ቢሮ ኀላፊው ማምረት የሕልውና እና የሉዓላዊነት ጉዳይ መኾኑን ነው የገለጹት። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለአማራ ክልል በርካታ ትሩፋቶች እያመጣ ነው ብለዋል።
ንቅናቄው የክልሉን ጸጋዎች በማስተዋወቅ አዳዲስ ባለሀብቶች ወደ ክልሉ እንዲመጡ ማድረጉን ተናግረዋል። በበጀት አመቱ ባለፉት ወራት 414 ቢሊዮን ብር ሀብት ያስመዘገቡ 3 ሺህ 518 ባለሀብቶች ወደ ክልሉ መጥተው የኢንቨስትመንት ፈቃድ ማውጣታቸውን አስታውቀዋል።
880 ባለሀብቶች ደግሞ ፕሮጄክቶችን አቅርበው ማስገምገማቸውን ገልጸዋል። 158 መካከለኛ እና ከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች በአዲስ ወደ ምርት መግባታቸውንም አንስተዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በክልሉ አምራች እንዱስትሪው እንዲያድግ እያደረገ መኾኑን ነው የገለጹት።
በክልላዊ ማጠቃለያ መርሐ ግብሩ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ለኤክስፖ ምርቶቻቸውን እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራቾች ምርታቸውን እንዲያስተዋውቁ፣ የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ እና ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ የሚያደርግ ነው ብለዋል።
በማጠቃለያ ኤክስፖው 145 አምራች ኢንዱስትሪዎች እንደሚሳተፉም አንስተዋል።
በመርሐ ግብሩ በባለፉት ዓመታት ውጤታማ ለነበሩ አምራች ባለሀብቶች ዕውቅና እንደሚሰጥም ኃላፊዉ አመላክተዋል።
የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪዎችም ከነገ ጀምሮ ወደ ኤክስፖው እየገቡ ምርቶችን እንዲጎበኙ እና በኤክስፖው ላይ እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርበዋል።
የዚህ ዝግጅት የሚድያ ማስተባበር ሥራ በተወዳጅ ሚድያ የተከናወነ ነው።

ሀገራዊ ኃላፊነታችንን ለመወጣት ዝግጅታችንን አጠናቅቀናል - የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪዎች
************************
የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪዎች ሰኞ ዕለት በምርጫው በንቃት ለመሳተፍ እና የሚጠበቅባቸውን ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት የመጨረሻ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ተናገሩ።
ነዋሪዎቹ ለኢቲቪ በሰጡት ሀሳብ በዕለቱ የሚጠበቅባቸውን ታሪካዊ ግዴታ ለመወጣት ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
"አንዲት ድምፅ ትልቅ ዋጋ አላት" ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ የምርጫ ካርድ ከመውሰድ እና ሲካሄዱ የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክሮችን በንቃት ከመከታተል ጀምሮ በርካታ ዝግጅቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን ተናግረዋል።
ይህ የቅድመ-ምርጫ ክትትል ሂደትም የሚመርጡትን ተወካይ በሚገባ ለመለየት እና አማራጭ የፖሊሲ ሀሳቦችን ለማወቅ በከፍተኛ ሁኔታ እንደረዳቸው ጠቁመዋል።
ነገ ሰኞ ማለዳ በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምፃቸውን እንደሚሰጡ ያረጋገጡት የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪዎች፤ መላው ሕዝብ በምርጫው በንቃት በመሳተፍ ሀገራዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ እንደሚገባ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በአባዲ ወይናይ
#yourvoicematters

ወሎ ፓራዳይዝ ሪልስቴት በወሎዋ ኮምቦልቻ ከተማ ግዙፍ የሪልስቴት ግንባታን አስጀመረ
#fastmereja I 50 ሽህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፈውና በወሎ ፓራዳይዝ ሪልስቴት የሚገነባው የመኖሪያ መንደር 400 ካሬ ሜትር ላይ ከሚያርፈው G+1 ሌግዠሪ ቪላ ጀምሮ G+4 እና G+6 አፓርትመንቶችን ያካተተ ነው፡፡
የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መሀመድአሚን የሱፍ በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ኮምቦልቻ በፍጥነት እያደገች የምትገኝና የሰው ፍሰቱና ብዛቱ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ወሎ ፓራዳይዝ ሪልስቴት የመኖሪያ ቤት ፍላጎትን ለማሟላት ከፍተኛ ድርሻ ያለው መሆኑን ጠቁመው ቃሉን አክብሮ ስራውን እንደሚያከናውን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
ወሎ ፓራዳይዝ ሪልስቴት ግዙፍ የሆነውንና የተለያዩ መንደሮች የተካተቱበትን ግንባታ ለማከናወን ከ50 በላይ ቋሚ ሰራተኞችን ቀጥሮ፣ የተደራጀ ቢሮ ገንብቶና ማሽነሪዎችን አስገብቶ ስራ የጀመረ ካምፓኒ መሆኑን የካምፓኒው ባለቤትና CEO ሱለይማን አራጋው ተናግረዋል፡፡
ወሎ ፓራዳይዝ ሪልስቴት ጥራታቸውን የጠበቁና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዘው የተገነቡ ቤቶችን ፍላጎቱ ላላቸው ሁሉ የሚያቀርብ ሲሆን በተለይ ከሀገራቸው ወጥተው በተለያዩ አለማት የሚገኙ ያካባቢው ተወላጆች የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡
የሪልስቴት ካምፓኒው ለወደፊት እድገቱ ሲል ቃሉን ማክበር ዋነኛ መገለጫው መሆኑ የተገለጸ ሲሆን አካባቢውን ያማከለ የዋጋ ተመን እንዳለው በስነ-ስርዓቱ ላይ ተነግሯል፡፡ በቦታው ላይ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ባለሃብቶች ተገኝተዋል፡፡
ወሎ ፓራዳይዝ ሪልስቴት
የህልም ቤትዎን እንገባለን

የኮምቦልቻው «ሐበሻ ቁርጥ ክትፎና ላውንጅ» በአዲስ አበባ ተከፈተ
#fastmereja I በወሎ ኮምቦልቻ ከተማ በምግብና መዝናኛ ዘርፍ ከፍተኛ ስም ያተረፈው «ሐበሻ ቁርጥ ክትፎና ላውንጅ»፣ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት በአዲስ አበባ ከተማ ላምበረት ማዕድን ሚኒስቴር አካባቢ አዲስ ቅርንጫፉን በትላንትናው ዕለት በይፋ አስመርቋል። ተቋሙ በዋና ከተማዋ ባለው ከፍተኛ የቢዝነስ እንቅስቃሴ ውስጥ የራሱን ድርሻ ለመያዝ ወደ ገበያው የገባ ሲሆን፣ «ሐበሻ ላውንጅ» ለ150 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፍጠሩን የድርጅቱ ባለቤት አቶ ሐበሻ ተፈራ ገልጸዋል።
ይህ አዲስ የንግድ ተቋም በከተማዋ ያለውን የምግብና የመዝናኛ ዘርፍ ፍላጎት መነሻ በማድረግ ሰፊ ካፒታል የወጣበት ሲሆን፣ ከግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 18 ቀን ድረስ ለተከታታይ አራት ቀናት የሚቆይ የማስተዋወቂያና የምረቃ ሥነ-ሥርዓት እያካሄደ ይገኛል። ተቋሙ በዋናነት የሠንጋና የፍየል ሙክት ቁርጥ፣ ክትፎ እና ልዩ ልዩ ባህላዊና ዘመናዊ ምግቦችን ጥራታቸውን ጠብቆ በማቅረብ የገበያ ተወዳዳሪነቱን ለማረጋገጥ ማቀዱን ከአስተዳደሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የንግድ ድርጅቱ ከመደበኛ የምግብና የመጠጥ አገልግሎት ባሻገር፣ የገበያ መሠረቱን ለማስፋትና ተጨማሪ ገቢ ለማመንጨት አዲስ የስትራቴጂ አቅጣጫ መከተሉን አስታውቋል። በዚህም መሠረት ሰፊ ልምድ ባካበቱ ባለሙያዎች አማካኝነት ለሠርግ፣ ለልደት እንዲሁም ለተለያዩ ማኅበራዊ ድግሶች የሚሆን ልዩ የኬተሪንግ (የምግብ ዝግጅት) አገልግሎት በስፋት ወደ መስጠት መሸጋገሩ ታውቋል። ይህ ዓይነቱ አደረጃጀት ተቋሙ በዘርፉ ካሉ አንጋፋ ተወዳዳሪዎች ጋር የሚያደርገውን የገበያ ፉክክር እንደሚያጠናክረው የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይገምታሉ።
አዲሱ የ«ሐበሻ ቁርጥ ክትፎና ላውንጅ» ቅርንጫፍ በስትራቴጂካዊ የንግድ ቀጠና ላይ ያረፈ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ ላምበረት መናኸሪያን አለፍ ብሎ ወደ ወሰን በሚወስደው ዋና መስመር፣ ማዕድን ሚኒስቴር መብራቱን እንደተሻገሩ በስተግራ በኩል ይገኛል። ተቋሙ በአሁኑ ወቅት የምረቃውን ሳምንት ምክንያት በማድረግ ለደንበኞቹ ልዩ የዋጋና የአገልግሎት ማበረታቻዎችን እያቀረበ ይገኛል።

3 months ago
የድምጻዊት ማዲቱ ወዳይን ህይወት ለመታደግ የእርዳታ ጥሪ ቀረበ
#ethiopia | እሽክም በሚለው ስራዋ የምትታወቀው ድምጻዊት ማዲቱ ወዳይ ከኮምቦልቻ ወደ ወልድያ በመጓዝ ላይ እያለች ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም በደረሰባት ድንገተኛ የመኪና አደጋ ለከፍተኛ ህክምና አዲስ አበባ መግባቷ ይታወቃል።
በአሁኑ ወቅት በድሪም የአጥንት የአደጋዎችና የአከርካሪ ህክምና ማዕከል የምትገኝ ሲሆን በተደረገላት የህክምና ምርመራ በግራ እጇ ላይ የሶስት ቦታ ስብራት በአከርካሪ አጥንቷና በሳምባዋ ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባት ታውቋል።
ባለሙያዎች ጉዳቱን ለመጠገን አስቸኳይ ቀዶ ህክምና እንደሚያስፈልጋት የገለጹ ሲሆን ለህክምናውና ለተከታታይ ክትትል እስከ ሁለት ሚሊየን ብር እንደሚያስፈልግ ተረጋግጧል።
በመሆኑም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን እንዲሁም የጥበብ አፍቃሪዎችና አድናቂዎቿ ከጎኗ እንድትቆሙ ጥሪ ቀርቧል።
እርዳታ ማድረግ የምትፈልጉ ወገኖች ከጎኗ ሆኖ እያስታመማት በሚገኘው
ባለቤቷ ወርቅነህ አበበ ተሰማ ስም በተከፈተው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት
1000088015097
ገቢ በማድረግ አልያም
በስልክ ቁጥር
+251911095021
በመደወል ድጋፋችሁን እንድታደርሱ ተጠይቋል።
#madituwoday #helpmaditu #woldia #ethiopianartist #medicalappeal #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ተወዳጇ የጥበብ ፈርጧን እናሳክማት
ድምጻዊት ማዲቱ ወዳይ ( እሽክም) በስራ ምክንያት ከኮምቦልቻ ወደ መኖሪያ ቤቷ ወልድያ እየተጓዘች እንዳለ በ26/08/2018 ዓ.ም አመሻሽ ወልድያ ለመግባት ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ሲቀሩ እየተጓዘችበት የነበረው መኪና ሞላ-ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ከመድረሳችን በፊት የተሰበረ ድልድይ ውስጥ በመግባቱ ድንገተኛ የመኪና አደጋ ደርሶባት ለከፍተኛ ህክምና አዲስ አበባ መሄዷም ይታወቃል።
በአሁኑ ሰአት ድምጻዊት ማዲቱ ወዳይ ለከፍተኛ ህክምና ሜክሲኮ ከአፍሪካ ህብረት ፊትለፊት በሚገኘው ድሪም የአጥንት የአደጋዎችና የአከርካሪ ህክምና ማዕከል ትገኛለች።
የተደረገላት የራጅ፣ ሲቲስካንና ኤም አር አይ ምርመራ ውጤት እንደሚያሳየው ግራ እጇ 3 ቦታ ላይ የአጥንት ስብራት ያለው ሲሆን ጀርባዋ (አከርካሪዋ) ከነርቭ ጋ በተያያዘ ጉዳት ደርሶባታል ፡፡
በተጨማሪም ሳምባዋም ላይ ችግር በመኖሩ ሁሉንም ችግሮች ለመፍታት ቀዶ ህክምና እንደሚያስፈልጋት በባለሞያዎች ተነግሯቸዋል።
በመላው አለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን አድናቂዎቿ በምን እናግዛት የሚለውን ጥያቄ ፈጥነን ለማሳወቅ ለህክምናው የሚያስፈለገው ጠቅላላ ብር እስኪታወቅ ድረስ እየጠበቅን ስለነበር እገዛው ዘግይቶ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ህክምናዋ ተጀምሮ እስክታገግም ድረስ እስከ ብር 2,000,000 ( ሁለት ሚሊየን ብር) እንደሚያስፈልግ ታውቋል ።
በመሆኑም በመላው አለም ያላችሁ ወዳጆቿ፣ አድናቂዎቿና የጥበብ አፍቃሪያን በሙሉ ገቢው አሁን ላይ ከጎኗ ሆኖ እያስታመማት በሚገኘው ባለቤቷ_ወርቅነህ_አበበ_ተሰማ ንግድ ባንክ አካውንት እንደሚሰበሰብ እና ሁሉም ሰው በይፋ እንዲያግዛት ወደ እናንተ መጥተናል፡፡
በሞያችሁም ሆነ በገንዘባችሁ ልታግዟት ያሰባችሁ የጥበብ ባለሞያዎች፣ በመላው አለም የምትገኙ ቲክቶከሮች ትልልቅ የሚድያ ገጽ ያላችሁ ወንድም እህቶች በመላው አለም የምትገኙ ወዳጆቿ አድናቂዎቿ በፍጥነት እንድትታከም በቻላችሁት ሁሉ እናግዛት ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ወርቅነህ አበበ ተሰማ (ባለቤቷ)
ንግድ ባንክ 1000088015097
ስልክ +251911095021
+251918252448

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች የሚኖሩ አርሶ አደሮች እና ነዋሪዎች በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና በታጣቂ ቡድኖች መሀል ተተኩሰው ከፍተኛ የህልውና ስጋት ውስጥ መውደቃቸውን ዋዜማ ራድዮ ያወጣችው አዲስ ዘገባ አጋልጧል። ዋነኛ የግብርና በተለይም የበቆሎ እርሻ ወቅት በሆነው አሁን ሰዓት፣ ገበሬው ማሳውን በማረስ ፋንታ የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላን (አፈሳን) በመሸሽ ወደ ጫካ እና ከተሞች ተሰዶ ለመደበቅ ተገዷል። ይህ ክስተት በክልሉ ያለውን የጸጥታ መደፍረስ ከማሳየቱም በላይ፣ በቀጣይ ሊከሰት የሚችለውን አደገኛ የምግብ ዋስትና ቀውስ በግልጽ የሚያመላክት ክሪቲካል ማሳያ ነው።
የግዳጅ ምልመላው ምንም ዓይነት የሰብዓዊ መብትም ሆነ የጤና ሁኔታን ከግምት ውስጥ ያላስገባ መሆኑ የችግሩን ጥልቀት ያሳያል። ነዋሪዎች ከቤት ለቤት ፍተሻ፣ ከገበያ፣ ከሃይማኖት ስፍራዎች ብሎም ከሀዘንና ደስታ ስነ-ስርዓቶች ላይ ሳይቀር እየታፈሱ ለግዳጅ ስልጠና ይወሰዳሉ። ለምሳሌ የሚጥል በሽታ ያለባቸው እና የዘወትር ህክምና የሚፈልጉ ዜጎች እንኳ ሳይቀሩ ታፍሰው መወሰዳቸው እና የህክምና ማስረጃቸው ተቀባይነት ማጣቱ የስርዓቱን ኢ-ፍትሃዊነት ያጋልጣል። በምስራቅ ወለጋ ጊዳ አያና እና ኪረሙ፣ እንዲሁም በሆሮ ጉዱሩ አቤ ዶንጎሮ፣ ጉሎ እና ሀባቦ ጉዱሩ ወረዳዎች መንግስት "ጋቸና ሲርና" (የስርዓት ጥበቃ) በሚል ሰበብ አርሶ አደሩን የአጭር ጊዜ የሚሊሻ ስልጠና እንዲወስድ ማስገደዱ ህዝቡን ወደ አላስፈላጊ ጦርነት እየማገደው ይገኛል።
ከዚህም በከፋ መልኩ ነዋሪው በሁለት ጥይት መሀል ተቀርቅሯል። በአንድ በኩል መንግስት "ታጣቂዎችን ትደግፋላችሁ" በሚል ሲያፍሳቸው፣ በሌላ በኩል ደግሞ የኦሮሞ ነፃነት ጦር (ኦነጦ) ታጣቂዎች "ለመንግስት መረጃ ታቀብላላችሁ" በማለት ጥቃት ይሰነዝሩባቸዋል። በተለይም በጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ የኦነጦ ታጣቂዎች "ፋ ኖን መዋጋት አለባችሁ" በሚል አርሶ አደሮችን በግዳጅ ወደ ጫካ መውሰዳቸው እና በዚህም ምክንያት አስራ ስድስት አርሶ አደሮች ህይወታቸው ማለፉ ቀውሱ ምን ያህል ደም አፋሳሽ ደረጃ ላይ መድረሱን ያረጋግጣል።
ከመደበኛው የጸጥታ መዋቅር ውጪ ያሉ ኢ-መደበኛ እና ህገ-ወጥ ተግባር ላይ የተሰማሩ ቡድኖች መበራከታቸው አካባቢውን የከፋ የህግ አልባነት ቀጠና አድርጎታል። በአባይ ጮመን፣ ጂማ ራሬ፣ ጂማ ገነት፣ ሱሉለ ፊንጫ እና ኮምቦልቻ ወረዳዎች የሚኖሩ አርሶ አደሮች ከሁለት ወራት በላይ ቤታቸውን ጥለው በጫካ ለመደበቅ ተገደዋል። የኦሮሚያ ክልል መንግስት እና የብልጽግና ፓርቲ ቃል አቀባዮች ስለዚህ አሳሳቢ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና የጸጥታ ቀውስ ምላሽ ከመስጠት መቆጠባቸው፣ መንግስት ለዜጎቹ ደህንነት ያለውን ኃላፊነት ከመሸሽም ባለፈ የዜጎችን ስቃይ እውቅና ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኑን ያሳያል።

ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
የጉምሩክ ኮሚሽን ከሚያዚያ 11 እስከ ሚያዚያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 386.2 ሚሊዮን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 14.5 ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ 400.7 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል አዳዲስ እና ልባሽ ጨርቆች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግብርና ምርቶች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ የተለያዩ ማዕድናት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡
በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ጅግጅጋ ፣ አዲስ አበባ ኤርፖርት፣ እና ኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ በቅደም ተከተላቸውም 126 ሚሊዮን፣ 95 ሚሊዮን እና 44 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣በፌደራል ፖሊስ፣በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣በጥቆማ እና በበረራ የተያዙ ሲሆን የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 26 ተጠርጣሪዎች እና 10 ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ጉምሩክ ኮሚሽን

5 months ago
የ1,000 ሊትር ጉድ፦ በኮምቦልቻ የተደረገው ድንገተኛ የነዳጅ ቁጥጥር ምን አሳየ?
በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ህገ-ወጥ የነዳጅ ዝውውርን ለመግታት በተደረገ የተቀናጀ ክትትል፣ 12 የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ።
ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከተሽከርካሪዎቹ የፋብሪካ ስሪት ውጭ እስከ 1,000 ሊትር ተጨማሪ ነዳጅ መያዝ የሚችሉ "ሳልቫቶዎችን" በህገ-ወጥ መንገድ አስገጥመው በመገኘታቸው ነው ሲል አስተዳደሩ ገልፇል።
የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮናስ መላኩ እንደገለጹት፣ ከነዳጅ ታንከሮቹ በተጨማሪ በገንዘብ ጥቅማጥቅም የነዳጅ ወረፋ ለማስቀደም የሞከሩ ተራ አስከባሪዎችና አሽከርካሪዎችም በፖሊስ ተይዘዋል።
የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ጌታቸው ሙህየ፣ በኬላዎችና በነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚደረገው ጥብቅ ቁጥጥር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

"አሰብ የአባቴ የዘላለም ቁጭት፣ የእኔም የታሪክ ውርስ ነው!” - የኢቢሲዋ ጋዜጠኛ እውነተኛ ታሪክ
#ethiopia | አሰብ ሲነሳ ለብዙዎች የካርታ ላይ መስመር ወይም የፖለቲካ መነጋገሪያ ሊሆን ይችላል፤ ለእኔ ግን የደም ስሬ፣ የልጅነት ትውስታዬና የአባቴ የዕድሜ ልክ ናፍቆት ነው።
አባቴ ፈንታው አደም በአሰብ ነጋዴ ሰፈር ስሙ ገዝፎ የሚነሳ፣ በንግዱና በሥራ ወዳድነቱ የሚታወቅ ብርቱ ሰው ነበር። አሰብ ለእሱ መኖሪያ ብቻ ሳትሆን ማንነቱ፣ ሀብቱና ክብሩም ነበረች።
የ1983 ዓ.ም የመለያየት ንፋስ ሲነፍስ ወንድሞቼና እህቶቼ በጅቡቲ በኩል ተሰደዱ፤ አባቴ ግን "ሀገሬን ጥዬ አልወጣም" ብሎ እስከ መጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ ከአሰብ ጋር ግብግብ ገጠመ። በ1986 ወይም 87 አካባቢ አሰብን ለቆ የወጣው የመጨረሻው ተፈናቃይ እሱ ነበር።
ከአሰብ ቢወጣም ልቡ ግን እዛው ቀርቷል። ኮምቦልቻ ካምፕ ውስጥ ተጠልሎ ሳለ እንኳ በረሃውና የለመደው የንግድ ግርግር እየመጣ ሲቀሰቅሰው "የአሰብ ተፈናቃይ" የሚለውን ስም ሊለምደው አልቻለም። ናፍቆቱ ሲበዛበት ለአሰብ ቅርብ ወደሆነችው ዲቺኦቶ (በአፋር ክልል በአሁኑ የኤሊዳር ወረዳ ውስጥ የምትገኘ የንግድ ቦታ ነች) ተመልሶ መነገድ ጀመረ፤ ሁሌም ግን ከጓደኞቹ ጋር ቁጭታቸው አንድ ነበር "አሰብ ተመልሰን ሄደን የድሮ ሕይወታችንን በኖርን" የሚል፡፡
አባቴ በ2007 ዓ.ም አላህ ይርሃመውና ከዚህ ዓለም ሲለይ፣ ያንን ትልቅ ተስፋና ቁጭት በእኔ እጅ አስቀምጦ አልፏል። ዛሬ እኔ ጋር የአባቴ ንብረት የሆኑ የቤትና የንግድ ቦታዎች ሕጋዊ ካርታዎችና ሰነዶች አሉ። "ይሄ የእኛ ነው" እያለ ያሳየን የነበረው ያ የንግድ ቦታና የመኖሪያ ቤት ዛሬም በዓይነ ሕሊናዬ ይርመሰመሳል።
አሁን የወደብና የአሰብ ጉዳይ ሲነሳ "የአባቴ ምኞት በእኔ ዘመን እውን ይሆን ይሆን?" የሚለው ጥያቄ በውስጤ በኃይል ይጮኻል።
አሰብ ለኮምቦልቻ፣ ለባቲና ለአካባቢው ሕዝብ የሕልውና መሠረት፣ የንግድ መፍለቂያና የትልቅ ተስፋ ምድር ነበረች። እኔ የአባቴን ታሪክ የምሸከም፣ ሰነዱን የያዝኩ ሕጋዊ ወራሹ ነኝ።
ያ የቁጭት ታሪክ ተቀይሮ፣ አባቴ በሕይወት እያለ ያላየውን ያንን የወደብ ብርሃን እኔ ሄጄ የማየውና ለእናንተም በደስታ የምነግራችሁ ቀን ቅርብ እንደሆነ አምናለሁ። የታሪክ ፍትህ የአባቴንና የሺዎችን ቁጭት የሚያብስበት ጊዜ ይመጣል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #assab #history #identity #ኢትዮጵያ #አሰብ #የወደብጉዳይ #ቁጭት #ትውስታ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ101 ሚሊዮን ብር የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
ድጋፉ የተደረገው ለአምስት የመንግስት ሆስፒታሎች መሆኑ ተነግሯል።
በኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ አማካኝነት የቀረበው ይህ ድጋፍ፣ በኡስታዝ አቡበከር አህመድ አስተባባሪነት ከሙስሊም ኤይድ አሜሪካ የተገኘ ነው።
በርክክብ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ድጋፉ የረመዳን ወርን የመተሳሰብ እሴት የሚያንፀባርቅ መሆኑን ገልጸዋል።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሰሃረላ አብዱላሂ በበኩላቸው ድጋፉ ለጤና ተቋማቱ ትልቅ አቅም እንደሚሆን በመጥቀስ ምስጋና አቅርበዋል።
ድጋፉ የተደረገላቸው ሆስፒታሎች አቦምሳ፣ ኮምቦልቻ፣ ጭናክሰን፣ ጉንችሬ እና ቋንጤ ይገኙበታል።

ባዕድ ነገር የተቀላቀለበት በመመረት ላይ ያለ ማር መሰል ምርት ከሶስት አምራች ተጠርጣሪዎች ጋር መያዛቸውን የአቢሻ አገር ክፍለ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ሁሴን መብራት ተናገሩ ‼️
ባዕድ ነገር የተቀላቀለበት ማር መሰል ምርት ሲያመርቱ እጅ ከፍንጅ የተያዙት 1ኛ አሰን መሃመድ ከማል አድራሻ ኮምቦልቻ አቢሻ አገር ክፍለ ከተማ ሁርባ ቀበሌ 2ኛ አባተ ሽፈራው አማረ አድራሻ ምዕራብ ጎጃም እንጅባራ ከተማ 3ኛ ወርቅነህ ምህረት አይኔ አድራሻ ምስራቅ ጎጃም መርጥለማሪያም ከተማ የሆነ ሶስት ተጠርጣሪ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውለው ምርመራ መጀመራቸውን የጣቢያው አዛዥ ኢንስፔክተር ሁሴን መብራት ገልጸዋል
ኢንስፔክተር ሁሴን አያይዘው ማር መሰል ምርቱን የሚያመርቱበት የተለያዩ ኬሚካሎችን መያዛቸውን ገልጸው ተጠርጣሪዎቹን ለማያዝ ማህበረሰቡ ላደረገላቸው ትብብር አመሰግነዋል
ኮምቦልቻ ፖሊስ መምሪያ
seledadotio

6 months ago
አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት፦ በማር ስም የሚሸጥ "መርዝ" በቁጥጥር ስር ዋለ!
በኮምቦልቻ ከተማ የተደረሰበት ዘግናኝ የሀሰተኛ ማር ዝግጅት!
በንጹህ ማር ስም ባዕድ ነገሮችን በመቀላቀል የህዝባችንን ጤና አደጋ ላይ የሚጥሉ ግለሰቦች እኩይ ተግባር አሁንም ቀጥሏል።
በኮምቦልቻ ከተማ ፖሊስ የተደረሰበት መረጃ ማንኛውንም ሸማች ክፉኛ የሚያስደነግጥ ነው።
ድርጊቱ የተፈጸመው በኮምቦልቻ ከተማ፣ ቦርከና ክፍለ ከተማ፣ ቁጠባ ቀበሌ (ልዩ ስሙ አዲስ አለም ሰፈር) ሲሆን፤ አንድ ግለሰብ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የሀሰተኛ ማር ፋብሪካ ዘርግቶ ሲሰራ እጅ ከፈንጅ ተይዟል።
ለዝግጅቱ ጥቅም ላይ የዋሉ አስደንጋጭ ግብዓቶች፦
ፖሊስ በቁጥጥር ስር ባዋላቸው መረጃዎች መሰረት፣
"ማሩ" የሚዘጋጀው ከሚከተሉት ባዕድ ነገሮች ነው፦
* ጀሶ (Plaster of Paris) : ለክብደትና ማሩ እንዲረጋ ለማድረግ
* ስኳር — ለማጣፈጫ
የክፍለ ከተማው ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ክፍል ኃላፊ ም/ኢንስፔክተር አንዋር ሰይድ እንደገለጹት፤ ግለሰቡ እነዚህን አደገኛ ግብዓቶች በመጠቀም ማር መሰል ውህድ ሲያዘጋጅ በህዝብ ጥቆማ ተደርሶበታል።
በአሁኑ ሰዓት ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት ይገኛል።
ለህብረተሰቡ የቀረበ ጥሪ፦
1. በየመንገዱ የሚዞሩ ነጋዴዎችን ይጠንቀቁ፦ በትንንሽ ባልዲዎች እየዞሩ "ንጹህ ማር ነው" የሚሉትን ከመግዛት ይቆጠቡ።
2. ጀሶና ኬሚካሎች የተቀላቀሉበት ማር ለከፍተኛ የኩላሊት፣ የጨጓራና የውስጥ አካላት ህመም እንደሚዳርግ ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ።
3. ይህንን መረጃ ለወዳጅ ዘመድዎ Share በማድረግ ከጥፋት ይታደጓቸው።
Via ፦ የኮምቦልቻ ፖሊስ መምሪያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኮምቦልቻ ገቡ
#ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ወሎ ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በኮምቦልቻ አባቶችና እናቶች ምርቃት የታከለበት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
#pmoethiopia

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ወሎ ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በኮምቦልቻ አባቶችና እናቶች ምርቃት የታከለበት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
#pmoethiopia
seledadotio
seledadotio
#pmoethiopia
seledadotio
seledadotio
7 months ago
ኢትዮጵያ የራሷን ጎግል ካርታ ይፋ አደረገች
በዓመቱ መጨረሻ 36 ከተሞች ላይ ተደራሽ ይደረጋል
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት በስምንት ከተሞች የዲጂታል አድራሻ ሥርዓትን መተግበሩን አስታወቀ።
በበጀት አመቱ አዳማ፣ ሐረር፣ ጅማ፣ ደብረ ብርሃን፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ኮምቦልቻና ቢሾፍቱ ከተሞች ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል አድራሻ ሥርዓት መግባታቸውን ተቋሙ አመልክቷል።
የዲጂታል አድራሻ ሥርዓትን እስከ ተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻ 36 ከተሞች ላይ ተደራሽ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል፡፡
የዲጂታል ኢትዮጵያን ግንባታ ለማፋጠን ቁልፍ ሚና የሚጫወተውን የዲጂታል አድራሻ ሥርዓት፤ የቤት ቁጥርን ከጂፒኤስእና ከዲጂታል ካርታ ጋር በማገናኘት ትክክለኛ መገኛን በቀላሉ ለማወቅ ያስችላል ተብሏል፡፡
አገልግሎቱ በድረገጽና በሞባይል መተግበሪያ የቀረበ ሲሆን፤ መረጃው በየጊዜው የሚሻሻል መሆኑም ተጠቁሟል።

በኢትዮጵያ 334 ተፈጥሯዊ ዋሻዎችን በጥናት የለየው ብቸኛው የዋሻ ተመራማሪ - ናስር አሕመድ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የመጀመሪያው፣ በአፍሪካ ደግሞ ሁለተኛው የዋሻ ተመራማሪ (Speleologist) የሆነው ኢትዮጵያዊው ናስር አሕመድ፤ እስካሁን ባደረገው ከፍተኛ ተጋድሎ የሚጠይቅ የምርምር ሥራ 334 ተፈጥሯዊ ዋሻዎችን በጥናት መለየቱን ገለጸ።
ተመራማሪው በዘርፉ ላበረከተው አስተዋጽኦ አህጉሪቱን ወክሎ በጀርመን ሀገር ዕውቅና እና ሽልማት ተሰጥቶታል።
ትምህርት እና ወደ ሀገር ቤት መመለስ
ተወልዶ ያደገው በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ የሆነው ናስር፤ የዋሻ ምርምር ትምህርቱን በፈረንሳይ፣ በጣሊያን እና በጀርመን ሀገራት ተከታትሏል።
በውጭ ዓለም የመኖር እና የመስራት ሰፊ ዕድል ቢኖረውም፤ "ሀገሬ በዚህ ሙያ እኔን ብቻ ስላላት፣ እንደ እኔ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ማፍራት አለብኝ" በሚል ወደ ሀገር ቤት ተመልሶ በኦሮሚያ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ በምርምር ሥራ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል።
የምርምር ውጤቶች እና ግኝቶች
ናስር እስካሁን ባደረገው ጥናት፡-
334 ተፈጥሯዊ ዋሻዎችን መለየት የቻለ ሲሆን፣ በ200ዎቹ ላይ "Caves in Oromia" የተሰኘ መጽሐፍ አሳትሟል።
ከጥንታዊው የኦሮሞ ሥልጣኔ ጋር የተያያዙ 133 የድንጋይ ላይ ጽሑፎችንና ስዕሎችን በዋሻዎች ውስጥ አግኝቷል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቀውን የሶፍ ዑመር ዋሻ አስመልክቶ ባለ 350 ገጽ መጽሐፍ አዘጋጅቶ ለምረቃ አድርሷል።
በሐረርጌ የሚገኘው እና በስሙ የተሰየመው "ናሲኦል" ዋሻ፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዓመታት ዕድሜ እንዳለው በታይዋን ዩኒቨርሲቲ ላቦራቶሪ ተረጋግጧል።
የሙያው አደገኛነት
የዋሻ ምርምር ከፍተኛ የአካል ብቃት እና ድፍረት የሚጠይቅ ሙያ ነው። ናስር እንዳብራራው፣ ወደ ዋሻዎች ለመግባት ከ60 እስከ 100 ሜትር ጥልቀት ያላቸውን ገደሎች በገመድ መውረድ የግድ ይላል።
በሂደቱ የኦክስጅን እጥረት፣ የድንጋይ መደርመስ እና እንደ ዘንዶ ያሉ አደገኛ አራዊት ማጋጠማቸው የተለመደ ነው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ በዘርፉ ከተሰማሩ ተመራማሪዎች መካከል 25 በመቶ የሚሆኑት ለሕይወት መጥፋት እንደሚጋለጡም ተመራማሪው ጠቁሟል።
የወደፊት ተስፋ እና ጥሪ
ዋሻዎች የሀገርን የጥንት የአየር ንብረት ሁኔታ ለማጥናት እና ለግብርና ምርምር ጠቃሚ መረጃዎችን የያዙ ናቸው።
በአሁኑ ወቅት የሶፍ ዑመር ዋሻ በዩኔስኮ (UNESCO) የዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ አስፈላጊው የጥናት ሰነድ በናስር እና በቡድኑ እየተዘጋጀ ይገኛል።
ተመራማሪው መንግሥት ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት የዋሻ ምርምር ተቋም እንዲያቋቁም እና ተተኪ ወጣቶችን ለማፍራት እንዲሰራ ጥሪ አቅርቧል።
"የሀገር ሀብትና ዕድገት በዋሻ ውስጥ ተደብቆ ይገኛል፤ ይህንን ሀብት ተንክባክቦ ለትውልድ ማስተላለፍ የሁላችንም ኃላፊነት ነው" ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

አንጋፋው የመድን ባለሙያ ሊመሰገኑ ነው
ዕዝራ እጅጉ(ተወዳጅ ሚድያ)
#ethiopia | የኢትዮጵያ መድን ድርጅትን በዋና ሥራ አስኪያጅነት የመሩት አንጋፋው የመድን ሰው አቶ አያሌው በዛብህ የምስጋና መርሀ ግብር ሊደረግላቸው ነው።
ሐሙስ ታህሳስ 16 2018 ዓ.ም በሒልተን ሆቴል በሚደረገው የምስጋና ክፍለ- ጊዜ ያሁንና የቀድሞ የመድን ባለሙያዎች ፣ የተመስጋኙ ቤተሰቦችና ወዳጆች እንደሚታደሙ ይጠበቃል።
ይህን መርሀ ግብር ለማዘጋጀች ራሱን የቻለ ኮሚቴ ተዋቅሮ ላለፉት 3 ወራት ሲንቀሳቀስ የቆየ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።
ተወዳጅ ሚድያ ያነጋገራቸውና ከኮሚቴ አባላት አንዱ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ፈንቴ ሲናገሩ፦"....አገር ውስጥና ውጭ አገር ሥልጠናዎችን እንድናገኝ ዕድል የፈጠሩልን ናቸው።አሁን በአገራችን ያለው የመድን አሠራር እርሳቸው መሠረት የጣሉበት ስለሆነ በብዙዎች የሚከበሩ ትልቅ ባለሙያ ናቸው።" ብለዋል።
አቶ አያሌው በዛብህ፣ በመድን ዘርፍ ያሳረፉት አሻራ ትልቅ በመሆኑ የቅርብ ወዳጆቻቸው ለማመስገን መነሳሳታቸውን ከሀሣቡ አመንጪዎች አንዱ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ፈንቴ ለተወዳጅ ሚድያ ተናግረዋል።
የእርሳቸው ተሞክሮ ለአዲሱ ትውልድ አስተማሪ ሆኖ በመገኘቱ አሁን ያሉት ወጣት የኢንሹራንስ ባለሙያዎች ልምድ ይቀስማሉ ብለን ይህን የምስጋና ቀን አዘጋጀን ይላሉ የተመስጋኙ የቅርብ ወዳጆች።
ይህን መርሀ -ግብር በማዘጋጀቱ በኩል ትልቁን ድርሻ የተወጡት የኮሚቴ አባላት አቶ ተስፋዬ ፈንቴ፣ወይዘሮ ጌጤነሽ ኃይለማሪያም፣አቶ ፀጋዬ ከምሲ፣አቶ መንበሩ ዲበኩሉ፣ወይዘሮ መሪማ መሐመድ፣አቶ ይሁን አመኑ ከካናዳ እና አቶ ተዘራ በልሁ ከአሜሪካ ናቸው።
በሒልተን በሚደረገው መርሀ -ግብር በአቶ አያሌው በዛብህ ላይ ትኩረቱን ያደረገ የ45 ደቂቃ ዘጋቢ ፊልም የሚቀርብ ሲሆን የዶክመንተሪውም አዘጋጅ ስንታየሁ ታዬ እንደሆነ ታውቋል።አቶ አያሌው በዛብህን ለማክበርም የካባ ማልበስ ሥነ ሥነሥርዓት ይኖራል ተብሏል።
ተመስጋኙ አቶ አያሌው የኢንሹራንሶችን ቅርንጫፍ በማብዛት የመድን ምንነት እንዲታወቅ ፣ ለሠራተኞች የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ ለመንግስት የሥራ ማረጋገጫ ሪፖርት እንዲቀርብ በማድረግ ብዙ ርቀት መጓዛቸውን በቅርብ የሚያውቋቸው ይናገሩላቸዋል።
በመዲናዋ አዲስ አበባ ብቻ ተወስነው የቀሩት የመድን ቅርንጫፎች በአቶ አያሌው የሥራ ዘመን ተደራሽነታቸዉ ሰፍቶ በጎንደር፣ ሀዋሳ፣ ጅማ፣ ናዝሬት፣ ድሬዳዋ፣ ነቀምት፣ ኮምቦልቻ እና ጅቡቲ ድረስ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አገልግሎት እንዲሰጥ አድርገዋል።
አቶ አያሌው በዛብህ ተወዳጅ ሚድያ ለሚያዘጋጀው መዝገበ አእምሮ የባንክና ኢንሹራንስ ኢንሳይክሎፒዲያ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ኢንሹራንስ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ቅርፅ ይዞ እንዲገኝ የተቻላቸውን ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

8 months ago
ከሎዛ ኹነቶች የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ
የተወደዳችኹ ኦርቶዶክሳውያን በያላችኹበት ሠላመ እግዚአብሔር ይብዛላቹ! ሰሞኑን በአንዳንድ እና ጥቂት ማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ግለሰቦች ዘንድ በተቀናጀ እና በተደራጀ መንገድ ሎዛ ኹነቶች አዘጋጅን - Loza Events organizer ን እና ከሎዛ ኹነቶች አዘጋጅ ጋራ አብረው ይሠራሉ የተባሉ ሚዲያዎችን፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን፣ ዩቱበሮችን እና ቲክቶከሮችን አስመልክቶ ያልተገባ መልክ በመስጠት የስም ማጥፋት ዘመቻ መክፈታቸውን ተመልክተናል።
እንዲህ ዓይነት የስም ማጥፋት ዘመቻ ባደረጉ አካላት ላይ በእጅጉ አዝነናል፤ አፍረናልም፡፡ እግዚአብሔር ወደ ልባቸው እንዲመልስቸው እንለምናለን፡፡ ነገር ግን እኒህ አካላት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ያለስማችን ስም በመስጠት በሐሰት የስም ማጥፋት ዘመቻ ስለዘመቱብን፣ ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን እና ኦርቶዶክሳውያት እውነታውን ማወቅ ስላለባቸው እና በጉዳዩ ዙሪያ ያለውን እውነታ አውቀው የራሳቸው ኅሊናዊ ፍርድ እንዲሰጡ ይህንን ወቅታዊ መግለጫ መስጠት አስፈልጓል፡፡
ስለዚህ የተወደዳችሁ ኦርቶዶክሳውያን እና ኦርቶዶክሳውያት! ‹‹ነገርን ከሥሩ ውኃን ከምንጩ›› እንዲሉ፡፡ እውነታውን በማኅበራዊ ሚዲያ በሚነዛ አሉባልታ መነዳት ሳይሆን እውነቱን ከምንጩ እንሆ፡፡
1. ሎዛ ኹነቶች ማን ነው?
ሎዛ ኹነቶች የቤተመንግሥትም
የቤተክህነትም ሕጋዊ ፈቃድ ያለው ተቋም ነው። በሀገራችን ብቻ ሳይኾን በቤተክርስቲያናችን ታሪክ የመጀመሪያው እና ፈር ቀዳጁ መንፈሳዊ እና ሳይንሳዊ በኾነ መንገድ ኹነቶች እያዘጋጀ ያለ በአጭር ጊዜ ስምና ዝናን ያተረፈ ድንቅ ተቋም ነው።
ተቋሙ የሚሠራው ኦርቶዶክሳዊ ኹነቶችን ነው። ከእርሱ በኋላም መንፈሳዊ ሠርጎችን የሚያዘጋጁ ተቋማት እንዲበዙ አርአያ የኾነ፤ ተዋሕዶ በልምድ ብቻ ሳይኾን በትምህርት በተደገፈ ቅጥ(pattern) አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ልጆች እና ተቋማት እንዳሏት ያሳየ ስንዱ እመቤት እንደኾነች በተግባር ያረጋገጠ እንዲኹም በር የከፈተ ተቋም ነው። በዚኽም እልፍ የምስጋናና እና የምስክር ወረቀቶችን አግኝቷል።
የሚሠጣቸው አገልግሎቶችም መንፈሳዊ ሠርጎችን ማዘጋጀት፣ የልደት መርሐግብሮችን፣ ጥምቀተ ክርስትናዎችን፣ የጋብቻ ክበረ በዓላትን፣ ምረቃቶችን፣ የሚዲያ ንቅናቄዎችን፣ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን፣ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብሮችን ያዘጋጃል። ያስተዳድራል። ይመራል። ያስተባብራል።
ዓላማውም ጊዜ፣ ጉልበት እና የቦታ ርቀት ፈተና የኾነባቸውን ግለሰቦችን እና ኮሚቴዎችን የሥራ ሸክም በመሸከም፤ ድካማቸውን በመድከም ኦርቶዶክሳዊ ኹነቶችን መንፈሳዊ እና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ማዘጋጀት ነው። ራእይው መንፈሳዊ ኹነቶች ቤተክርስቲያኗን በሚያውቁ፣ መንፈሳዊውንና ዘመናዊውን ትምህርት በቀሰሙ ልጆቿ የቤተክርስቲያኗን፣ ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት በጠበቀ ኹኔታ፣ ደረጃቸውን እና ከፍታቸውን ይዘው ከሌብነት፣ ከመጓተት እና ከብልሽት በጸዳ ፍኖት ኹነቶች ሲዘጋጁ ማዬት ነው።
ሎዛ ኹነቶች እንደ ተቋም እንደ መሪም በነፃ አገልግሎት የሰጠባቸው ተቋማት እና ግለሰቦች በጥቂቱ:-
1. የጎንደር ሐመረ ብርሃን ደብረ ምጥማቅ ማርያም ሕንፃ ቤተክርስቲያንን ለማስፈጸም ከጥር 23/2017 እሰከ ጥቅምት 03/2018 ለ 8 ወር ቀን እና ሌሊት ያለምንም ክፍያ አንዳንድ ጥቃቅን የቡድኑን ወጪዎች ጭምር ራሱ በመሸፈን ያስተባበረ፣ የመራ በራሱ ሚዲያም ለሦስት ቀናት በቀጥታ ሥርጭት ያስተላለፈ ድንቅ ተቋም ነው፤ በወቅቱ የሰጡትን ምስክርነትም ቪዲዮ ላይ ተመልከቱ። 100% የምንኮራበት አገልግሎታችን ነው።
2. ለራማ ኪዳነ ምሕረት ገዳም በሚሊኒዬም አዳራሽ የተዘጋጀውን መርሐግብር ከትኬት ሽያጭ ውጭ ያለውን ሥራ ያለምንም ክፍያ ሙሉ በሙሉ የማማከር እና የማስተባበር ሥራ ከመሥራት በተጨማሪ ዶክመንተሪ በነፃ የሠራ ተቋም ነው። ሌሎችንም በአጭር በአጭር ከዚኽ በታች ተቀምጠዋል፦
3.የመምህር በጽሐ ዓለሙ ጉባኤ ቤት የግዮን ሆቴል የቀጥታ ሥርጭት በነፃ አስተላልፏል እና የማስታወቂያዎችን ፕሮዳክሽን ያለምንም ክፍያ ሠርቷል፤
4. የጎንደር አዘዞ ሎዛ ማርያም ህዳር ጽዮን መርሐግብር እና አስተርእዮ ማርያም በሎዛ ማርያም (በነፃ መሥራት ብቻ ሳይኾን ገንዘብ ከራሱ ወጪ ያደርጋል)
5.2015 ያንን የመሰለ ከ300,000 ሰው በላይ የታደመበት ዝክረ አበው ለአዘዞ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ከኮሚቴዎቹ ጋር በመተባበር (ኢቨንቱን በነፃ መሥራት ብቻ ሳይኾን ገንዘብ ከራሱ ጭምር አውጥቶ ያስተባበረ ነው)
6. ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማዕከል ግንፍሌ ለሚያስገነባው ሕንፃ የተሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫ አስተባብሯል፤
7. ለታዕካ ነገሥት ባዕታ ለማርያም ገዳም ጋዜጣዊ መግለጫ አስተባብሯል
8. ስምከ ሕያው ዘኢይመውት በሚል መሪ ቃል ሚሊኒዬም አዳራሽ ለተዘጋጀው ጉባኤ የሚዲያ ካምፔን የማስተባበር ሥራ በነፃ ሠርቷል፤
9. ለቂልጦ ቅድስት ማርያም ገዳም በየዓመቱ ሰኔ ማርያም ወደ ቂልጦ ማርያም በሚል መሪ ቃል ሚዲያዎችም በነፃ ሎዛ ኢቨንትም በነፃ ለበርካታ አመታት አስተባብሯል፤ ለወደፊትም ያስተባብራል፤
10. ተአምረ ማርያም ከግዕዝ ወደ ኦሮምኛ በብፁዕ አቡነ ናትናኤል ተተርጉሞ በማኅበረ ቅዱሳን አሳታሚነት ለንባብ የበቃውን የምረቃ እና ጋዜጣዊ መግለጫ አገልግሎት በነፃ አስተባብሯል፤ አዘጋጅቷል።
11.ለአምቦ ኪዳነ ምሕረት የተዘጋጀውን የዶክመንተሪ፣ የማስታወቂያ፣ የእራት እና የቀጥታ ሥርጭት መርሐግብር አምቦ እና አዲስአበባ ላይ የማማከር እና የማስተባበር ሥራ ያለ መታከት ያለ ክፍያ በነፃ በመሥራቱ ምስጋና እና አድናቆት ተበርክቶለታል።
12. 2016 ሆሳዕናን በሆሳዕና የማማከር እና የማስተባበር ሥራ እንደ ሎዛ ኢቨንት መርሐግብሩን መርቷል። እንደ ሚዲያም የቀጥታ ሥርጭቱን በነፃ አስተላልፏል።
13. ጻድቃኔ ማርያም ስትመረቅ ያደረግነው እንቅልፍ የሌለውን ሥራ፤ የዶክመንተሪ፣ የማስታወቂያ፣ የቀጥታ ሥርጭት፣ የሚዲያ ዘመቻ ተቆጥሮ የማያልቀውን የመምራት እና የማስተባበር ሥራ እንደ ግልም እንደ ቡድንም ያለምንም ክፍያ ለደከምነው ድካም ከእግዚአብሔር ውጪ ማን ሊከፍለን ይችላል?
14.ለሰሜን ወሎ ሀገረስብከት በዚያ የመከራ ዘመን ለሰጠነው የማማከር፣ የማስተባበር እና የማሰልጠን ሥራ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስን ብቻ መጠየቅ ተገቢ ነው።
15. ለኮምቦልቻ ገብርኤል የገቢ ማሰባሰብ የቀጥታ ሥርጭት፣ የማታ ጉባኤ እና ሩጫ ሁለት እና ሦስት ቀን ለሰጠነው የሚዲያ ሽፉን እንኳን ገንዘብ ልንቀበል የተቀየረውን የአውሮፕላን ትኬት እንኳ እራሳችን እንደከፈልን ምስክራችን ቅ/ገብርኤል፣ ኮሚቴው እና መምህር ደረጀ ዘወይንዬ ናቸው፤
16. ለደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀውን ጋዜጣዊ መግለጫ ያስተባበረው ያለምንም ክፍያ ሎዛ ኢቨንት ነው፤
17. በለሳ የሚገኘውን ሙት አንሣ ማር ቅዱስ ሚካኤ አንድነት ገዳምን ከሰኔ 17/2017 ጀምሮ ለማስተዋወቅ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገውን ጉዞ፣ ጉባኤ፣ ዶክመንተሪ፣ ማስታወቂያ፣ ጋዜጣዊ መግለጫ በረሃ ለበረሃ እየዞረ በነፃ ያለምንም ክፍያ ያስተዋወቀው፣ የመራው፣ ያማከረው ሎዛ ኹነቶች ነው፤
18. የያያ ዘልደታን ልደት ምክንያት በማድረግ ቦሌ የተደረገውን የነዳያን ምግባ በነፃ ያስተባበረው የሞንታርቦ ወጪ የሸፈነው ሎዛ ኹነቶች ነው።
19. የግሸን ማርያም ኮሚቴዎች ቢሯችን መጥተው በጠየቁን ያስተባብሩልን ጥያቄ መሠረት የማማከር ሥራውን ያለምንም ክፍያ የሠራው ሎዛ ነው። በዚኽ የተደሰቱት ኮሚቴዎች የቢሮ ኪራይ አለባችሁ፤ የሠራተኞች ክፍያ አለባችኹ ክፍያ እንፈጽምላችሁ ምን ብለን እንደመለስንላቸው ኮሚቴዎቹ እነ ዲ/ን አንተነህ የደሴውን ልጂ ጠይቁ ይነግሯቹሃል።
20. በመልአከ መዊዕ ተስፋዬ መቆያ አባትነት የሚመራው የሜሪላንድ ጽርሐ ጽዮን መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያንና የምእራፈ ቅዱሳን ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳምን በተመለከተ በኤሊያና ሆቴል የተሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫ በነፃ ያለምንም ክፍያ አስተባብሯል። ከዚያ በኋላ የነበረውን አገልግሎት በተመለከተ የማማከር ሥራ ሠርቷል። ገንዘብ ከኪሳችን አውጥተናል። 1 ብር ግን አልጠየቅናቸውም።
21. አዘዞ አየር ማረፊያ ሰሚው ሚካኤል ላይ የተሠራው የዶክመንተሪ አገልግሎት ሎዛ ኹነቶች በራሱ በነፃ የማስተባበር ሥራ ሠርቷል።
22.ክፍለ ሀገር ለሚገኘው የአቡነ ሐራ ገዳም የማማከር ሥራ በነፃ ሠርቷል።
23. ዘመን ተዋሕዶ ኤክስፖ ያለምንም ክፍያ ማርኮናል ኢቨንትስን በማገዝ የተሠራው።
24. ለአሐዱ ባንክ 2015 ከግንቦት 21 እሰከ ሰኔ21 /2015 ለተደረገው የሚዲያ ዘመቻ ያለምንም ክፍያ አንደ ወር ሙሉ በነፃ አስተባብሯል::
25. በእህታችን ዲዛይነር ሔቨን ጌታቸው የሚመራው ቤተ ሚካኤል ማኅበር 10ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ሲያከብር የማማከር እና የቀጥታ ሥርጭት መርሐግብር የሚዲያ ሽፋን እንደተቋም ያለምንም ክፍያ በነፃ አገልግሎት ሰጥቷል።
26. የጎጃም ጌራ መድኃኒት መድኃኔዓለም ገዳምን የማስታወቂያ ሥራ ለሎዛ ኹነቶች ድንቡሎ ሳይከፍሉ ያስተባበረላቸው እና የረዳቸው ሎዛ ነው።
27. ለአዲስአበባ ለሚገኘው ቅዱስ ሚናስ በየዓመቱ የሚዲያ የማስታወቂያ ሥራ ያለምንም ክፍያ የማስተባበሩን ሥራ የሚሠራው ሎዛ ነው።
28. የደብረ ዕንቁ ልደታን ኹነቱን ሳይኾን ዶክመንተሪውን እና የሦስት ቀኑን የቀጥታ ሥርጭት መርሐግብር በሚዲያው በነፃ የሠራው ሎዛ ነው።
29. የአቤኒን እና የባለቤቱን የቁርባን ሠርግ የቤተክርስቲያኑን እና የአዳራሽ ኹነቱን የsound፣ የሚዲያ ሽፋን በመስጠት በነፃ ያስተባበረው ሎዛ ነው፤
30. የአብራሃም ዘራጉኤልን ሠርግ የsound እና የሚዲያ ሽፋን በመስጠት ኹነቱን በነፃ ያስተባበረው እና ያማከረው ሎዛ ነው።
እነዚኽን ኹሉ በነፃ ሢሠሩ ድካማቸው እና ዋጋቸው ጠፍቶን ሳይኾን ዋጋችን በሰማይ ስለኾነ ነው። እነዚኽን ሁሉ ኹነቶች በነፃ እንደ ተቋም ሥንሠራ ድንቡሎ ሳንቲም እገዛ ያደረገልን ከደጋፊዎቻችን ይኹን ከነቃፊዎቻችን መሐል እኔ አለሁ የሚል የለም። ሌሎች ኹነቶች ላይ ሠርተን በምናገኘው እንጂ። ለበጎ ሥራችን ሺልማት ባንጠብቅም ነቀፋን ግን ለሰከንድ አልጠበቅንም። ስለሁሉም ነገር እናመሰግናለን። አገልግሎታችን በብዙ እጥፍ ተደራጂቶ እንደሚቀጥል ቃል እንገባላችኋለን።
2. ሥራዎችን እና አገልግሎቶችን እንዴት ይቀበላል?
አንድን ተግባር ለማከናወን ሃሳብ ያላቸው ኮሚቴዎች እና ግለሰቦች በጊዜ እጥረት፣ በቦታ ርቀት፣ በልምድ ማነስ ምክንያት ኹነታቸው እክል ሳይገጥመው ማዘጋጀት ሲፈልጉ ወደ ተቋማችን ይመጣሉ። በዚህ መሠረት ይኽንን ተግባር አከናውኑልን ሲሉ የጉዳዩን ሕጋዊነት ካጠናን እና ከመረመርን በኋላ በድርጅታችን ውስጣዊ አሠራር መሠረት መክፈል የማይችሉትን ያለምንም ክፍያ በነፃ እንሠራላቸዋለን። በዚኽም በርካታ ኹነቶችንም በነፃ ሠርተናል። ለወደፊትም እንሠራለን። መክፈል የሚችሉ ግለሰቦች እና ተቋማት ደግሞ ይከፍላሉ። ለዚኽም ሕጋዊ ደብዳቤ እንዲጽፉ አድርገን ቆጥረው የሰጡንን ተግባራት በንጽሕና፣ በጥራት እና በፍጥነት ቆጥረን እናስረክባለን።
ድካማቸውን ደክመን ሸክማቸውን ተሸክመን እናገለግላቸዋለን። ለዚኽም እሰከ ዛሬ ያገለገልናቸው ግለሰቦች፣ ኮሚቴዎች፣ ማኅበራት፣ ገዳማት፣ አድባራት፣ ሀገረ ስብከቶች ምስክሮቻችን ናቸው። ስለኾነም ከደንበኞቻችን በርካታ የምስጋና እና የምስክር ወረቀቶች ተበርክተውልናል።
3. ክፍያን በተመለከተ
ሀ) . በፐርሰንት ወይም በኮሚሽን በፍፁም ሠርተን አናውቅም። ለወደፊትም አንሠራም። ይኽን የማናደርገው ወንጀልም ኃጢአትም ስለኾነ ሳይኾን ከተሐድሶ እንቅስቃሴ ቀጥሎ ለቤተክርስቲያን ቀጣዩ ፈተና ነው ብለን ስለምናምን ነው። በዚኽ ምክንያት እኛ ወደዚኽ አገልግሎት ከመግባታችን በፊት በኮሚሽን ወይም በፐርሰንት ሲሠሩ የነበሩ ግለሰቦችን እና ተቋማትን በማስተማር፣ በመገሰጽ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አድርገናል። 99 % ተሳክቶልናል። 1% የሚኾኑ በዚኽ አቋማችን ያኮረፉም የእኛን ጩኽት ቀምተው ቀን ጠብቀው ከውስጥ እና ከውጭ ተባብረው ዘመቻ ከፍተውብናል። እኛ ግን በዘመቻ የሚንበረከክ ተቋማዊ ውቅር ስሌለን አገልግሎታችንን በንጽሕና እንቀጥላለን።
ሎዛ ኹነቶችን በተመለከተ አንድም ግለሰብ አንድም ተቋም በፐርሰንት የሠራንበትን ማስረጃም መረጃም ማቅረብ አይችልም። በፍፁም፣ በፍፁም፣ በፍፁም። እንደ ግለሰብም እንደተቋምም እንደዚኽ ዐይነት ስብእና እንደሌለን ብዙዎቻችኹ ታውቃላችኹ። የማታውቁንም እንድትጠይቁ በእግዚአብሔር ስም አደራ እንላለን።
ለ.) የመንግሥት ግብር፣ የቢሮ ኪራይ፣ የሠራተኞች ደሞዝ እንዴት ትከፍላላችኹ? ብሎ አዝኖልን የጠየቀን የለም፤ ስንት ግዙፍ ሥራዎችን ገንዘብ ከኪሳችን ጭምር እያወጣን በነፃ ስንሠራ ያላዘኑ፤ ያልጠየቁ፤ ምን እንርዳችኹ? እንዴት አናግዛችኹ ብለው አጠገባችን ያልነበሩ፤ ለዲኮር እና መሰል ጉዳዮች በሚሊዬን ደረጃ ሲከፈል ኮሚቴ ኹነው በሚሠሩበት ቦታ ዝም ያሉ፤ ለቴሌቪዥን ጣቢያዎቻችን ለአንድ ደቂቃ ማስታወቂያ እና ለአንድ ዶክመንተሪ ስንት እንደሚከፈል የሚያውቁ መርጦ አልቃሾች እና ግለሰቦች ዘመቻ ሲከፈቱብን ግን ሳያመዛዝኑ ግራ ቀኝ ሳይጠይቁ ለመፍረድ እና ለመሳደብ ብሎም የሚሸማቀቅ የለም እንጂ ለማሸማቀቅ የቀደማቸው የለም።
ተቋማችን ግን ለግለሰቦች እና ለተቋማት የሚሰጠው አገልግሎት እና ሥራ በተቋሙ አሠራር መሠረት ተመጣጣኝ ክፍያ ያስከፍላል። መክፈል የቻሉ ይከፍላሉ። ምክንያቱም የቢሮ ኪራይ፣ የስቱዲይ ዕቃዎች ኪራይ፣ የሠራተኞች ደሞዝ እና ልዩ ልዩ ወጭዎችን የምንሸፍነው ከጠቅላይ ቤተክህነት በተመደብልን በጀት አይደለም።
የምትሠሩት ለሀገር እና ለቤተክርስቲያን ነው ብሎ መንግሥት በጀት አይመድብልንም። አንድም በጎ አድራጊም አንድ ብር ሰጥቶን አያውቅም። መክፈል ያልቻሉ ግለሰቦች እና ተቋማት ደግሞ በአሠራራችን መሠረት በነፃ ያለምንም ክፍያ አገልግሎት ይሰጣቸዋል። በዚኽም በርካታ ተቋማት እና ግለሰቦች ተጠቃሚ ኾነዋል። በነፃ ያለምንም ክፍያ የሠራንላቸው ግለሰቦችን እና ተቋማትን ዝርዝራቸው በመጨረሻ ተመልከቱ። በዕውነት ነገሩ በጣም ያሳዝናል።
የሰሞኑን የስም ማጥፋት ዘመቻ የትኩረት ነጥቦች
1).ሎዛ ኹነቶች አዘጋጅ በኮሚሺን ወይም በፐርሰንት እየሠራ ነው የሚል ነው። መልሳችን በፍፁም ውሸት ነው የሚል ነው። አልሠራንም ነው። ሠርተንም አናውቅም። አንሠራምም። ጭራሺ በፐርሰንት የሚሠሩ ግለሰቦች ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ አለን። ነገሩ ጩኽቴን ቀሙኝ ነው። ሠርተዋል የሚል ካለ ባለቤቱ ወጥቶ አዎ ከእኔ ጋር ሠርተዋል ይበል። ወሬ ሳይኾን የሚነበብ ማኅተም ፊርማ፣ ሕጋዊ ውል እና ስምምነት ይዞ ይምጣ። 100% የምንነግራችኹ፤ አንድም ተቋም አንድም ግለሰብ ከሎዛ ኹነቶች ጋር በፐርሰንት ወይም በኮሚሽን በፍፁም አሠርቻለኹ ብሎ አይመጣም። ምክንያቱም እንደዚኽ ዐይነት ሥራ መሥራት ተገቢ ነው ብለን ስለማናምንበት፤ አልሠራንም። ምስክሮቻችን እስከዛሬ አብረውን የሠሩ ግለሰቦች እና ተቋማት ናቸው
2. ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወረ ባለው ዶክመንት ጉዳይ፦
ሀ.) ዶክመንቱ ኹነቱ የተዘጋጀው ከህዳር 12 እሰከ ህዳር 26/2018 ይላል። ሎዛ ኹነቶች በዚኽ በተባለው ቀን በፍፁም ሐዋሳ ላይ ኹነቶችን አላዘጋጀም።
ለ). ዶክመንቱ እኛን ባይመለከተንም ሰዎች ልከውልን ተመልክተነዋል። በዚኽም እንደ አንድ ኦርቶዶክሳዊ እና እንደ አንድ ሕሊና ባላቸው ሰዎች እንደሚመራ ተቋም በጥንቃቄ ለማየት ሞክረናል። በመኾኑም በርካታ የሐሰት ውንጀላዎች ተካተውበታል።ብዙ ውሸቶችንም ይዟል።
ጥቂቶቹ
ሐ), ማነው ይኼ ደብር? ኹነቱን ማን ነው ያስተባበረለት? የውል ስምምነታቸው የትአለ? ስምምነቱስ ምን ይላል? ደብሩ በግልፅ መግለጫ ለምን አልሰጠም? ደብሩ ተበደልኩ ለምን አላለም? የተበደለውስ ምንድን ነው? የማይነበብ ማኅተም ለምን ማዘዋወር ተፈለገ? ምእመናን ነገሩ እየገባችኹ ነው? በሳል አእምሮ ያለው ይጠይቅ። በዝርዝር በስም ተጠቅሶ ለማን ምን ተከፈለ? ገንዘብ የተቀበሉበት ፊርማ ወዘተ አለ? ክፍያውስ የተፈጸመው ያለገለገሉበትን ነው ወይስ ያላገለገሉበትን? ያልሠሩበትን ነው ወይስ እንደተባለው ዘርፈው ነው? አስገድደው ነው? ኮሚቴው ፈቅዶ እና አምኖበት ነው ያደረገው? አምኖበት ካደረገው በኋላስ ለምን ሚዲያ ላይ ማሠራጨት አስፈለገ? እውነት ከኾነ ዶክመንቱን ሙሉውን ለምን አለቀቁትም። ለምን ቆረጧት? ሰው ይኼን እንዴት መጠየቅ ያቅተዋል? የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጫጫ ለምን እንዲኾን ተፈለገ ዓላማው ሌላ ስለኾነ ነው።
መ) ቲክቶከሮቹን ማጥቃት የፈለገ አካል መኖሩን ማሳያ የዘማርያን የሰባኪያን አበል የታለ? መርሐግብሩ የተካኼደው ያለዘማርያን ነው? ውሸት፤
ሠ) አምስት መቶ ምናምን ሺ ብር ምግብ እንዴት? ፍፁም ውሸት። እውነት እንኳን ቢኾን አገልጋዮቹ እዚህ ሆቴል ካልኾነ አንተኛም ብለው ነው? ውሸት። መጀመሪያውኑ ወጪ የሚቀንስ ምግብ፣ ወጪ የሚቀንስ ምኝታ ለምን አላዘጋጁም? አገልጋዮቹ እና ሚዲያዎቹ እዚህ አንተኛም። ይኽንን አንበላም እንደማይሉ የታወቀ ጉዳይ ነው። ምክንያቱም አገልግሎቱ ሐዋሳ ብቻ አይደለም። ብዙ ቦታወች ተሰጧል። የጎላ ድስት ወጥ በልተው፣ ሰ/ት/ቤት አዳራሽ ተኝተው ጥንቅቅ ያለ መርሐግብር አዘጋጅተዋል።
ረ). ወጪ ለማጋነን የተቀሰጡ ወጪዎች አሉ ለምን? ለምሳሌ ቁጥር 2 ለመወንጀል ከመጣደፋቸው የተነሣ በትክክል እንኳ መደመር አልቻሉም።
3. ዶክመንቱ እኛን የማይመለከተን ኾኖ ሳለ የሎዛ ኹነቶችን ስም በዚኽ መጠን ማጥፋት ለምን አስፈለገ? ዘመቻውን ያስጀመሩት አካላት እነማን ናቸው? ዓላማቸውስ ምንድን ነው? የሚለውን መመረመር ያስፈልጋል።
ሀ). የመጀመሪያዎቹ በፍፁም ቅንነት ለቤተክርስቲያን ያሰቡ መስሏቸው የተንጋደደ መረጃ ሰምተው ዘመቻውን የተቀላቀሉ ናቸው። ለእናንተ መልሳችን ሕሊና የሚባል ነገር አለ አጣሩ። ነግ በኔ በሉ። ሰው የዘራውን ነው የሚያጭደው። ቢያንስ ጉዳዩን ከኹለቱም ወገን ስሙ። ከዚያም መፍረድ የሚያስችል መንፈሳዊነት፣ ሞራል እና ስነልቡና ካላችኹ ፍረዱ። ሕጋዊ መረጃ እና ማስረጃ ሳትይዙ የግለሰብ ስም እና የተቋም ስም ከሚያጠፉ ሰዎች ጋር አትተባበሩ። ቆም ብላችኹ ጠይቁ። ቢያንስ ከሳሽ ሳይኖር ተካሣሽ ላይ አትፍረዱ። አሁን እየኾነ ያለው ሕጋዊ ከሳሺ እና ወቃሺ ሳይኖር አሯሯጮች መኾን አይገባንም።
ለ.) የአእላፋትን ዝማሬ ቲክቶከሮቹ ይደግፋሉ የሚል ነው። ስለዚኽ በሏቸው ነው። ቲክቶከሮቹን የሚያስተባብረው ደግሞ ሎዛ ኹነቶች ነው። እርሱንም በሉት
ሐ. እንደነዚኽ ዐይነት መርሐግብር ለምን አልተሳተፍንም የሚል ውስጣዊ ቅናት ያንገበገባቸው ናቸው። እንዚህ አካላት ደግሞ ያልተጋበዙት የኮሚቴዎቹ ምርጫ ስላልኾኑ። በቦታ ርቀት። ስልክ ስለማያነሱ። በብዙ ምክንያት ሳይጋበዙ የቀሩ። ነገሩ ትክክል ስለኾነ ስላልኾ ሳይኾነ እነሱ ስለሌሉበት። እነሱ ስላልጀመሩት። እነሱ ቡራኬ ስላልሰጡበት ነው።
መ). ወቅታዊ አጀንዳ ለማስቀየር። ይኽ ጉዳይ በሚነሣበት ወቅት ምን ዐይነት አጀንዳ ይናፈስ ነበር የሚለውን መፈተሽ ተገቢ ነው።
ሠ.) ምእመናን አገልጋዮችን፣ ኦርቶዶክሳዊ ዩቱበሮቹን፣ ቲክቶከሮቹን፣ ፊስቡከሮችን እና የኪነጥበብ ባለሙያውችን እንዲጠሉ፤ እንዲጠራጠሩ። አይይ ምን ሰው አለ? በማስባል ፈተና ውስጥ በማስገባት ለክህደት ጉዞ ማመቻቸት ነው፤
ረ). ዝናን፣ ዕይታን እና ገንዘብን ናፋቂነት ነው። ስም ያላቸውን ሰዎች ያለበቂ ምክንያት ያለ ሕጋዊ መረጃ እና ማስረጃ ፎሎወር እና ሰበስክራይበር ለመጨመር ትኩረት ለመሳብ ስም ያላቸው ሰዎች ማወረድ ትናንት የነበረ። ዛሬም እየኾነ ያለ። ለወደፊትም የሚቀጥል እኩይ ተግባር ነው። ለእነዚኽ አካላት መልሳችን የሚኾነው፤ ውሾች ይጮኻሉ፤ ግመሎችም ይኼዳሉ ነው::
በሙገሳ ብዛት የሚቀጥል አገልግሎት የለንም። በተራ ስም ማጥፋት የሚገታ ሥራ አይኖረንም። እኛ ሠናይ ዓላማ አለን። ዓላማችን ደግሞ ያለፈተና እንደማይሳካም ጠንቅቀን ስለምናውቅ ጉዟችን ወደፊት ነው።
ሰ.) አንዳንድ ተመሣሣይ ሥራ እና አገልግሎት የሚሠጡ አካላት ተቋማችን እያገኘ ባለው ስም እና ዝና ምክንያት ደስተኞች እንዳልኾኑ እናውቃለን። ኾኖም መጠላለፉ አይጠቅምም። ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ሥራህን ሥራ እንዳሉት ኹላችን በሥራችን እንገለጥ ነው መልሳችን።
ሸ. ) የሰይጣን ሥራ ነው፤ ምክንያቱም እየሠራነው ያለው መንፈሳዊ አገልግሎት እና ሥራ ነው። መንፈሳዊ ሥራ ደግሞ ያለፈተና አይሠራም። ፈተና ከሌለውም ቅድመ እግዚአብሔር አልደረሰም ይላሉ አበው። ይኽንን ፈተና በብዙ መልኩ ለምደነዋል። ደግሞም በድል አቁሞናል። ዐቢያተ ክርስቲያናት እየታነፁ ነው፤ አብነት ት/ቤቶች እየተገነቡ ነው፤ ወንጌል እየተስፋፋ ነው። ዝማሬው እየቀለጠ ነው። በዚኽ ያልተበሳጨ ሰይጣን በምን ይበሳጭ? እንዲያውም ይኽ ፈተና መምጣቱን እግዚአብሔር አገልግሎታችን እንደተቀበለልን እንቆጥረዋለን።
ቀ.) እንደሚታወቀው በርካታ ገዳማት፣ አድባራት፣ አብነት ት/ቤቶች ፣ ማኅበራት፣ ሰ/ት/ቤቶች፣ የነዳያን መርጃ ተቋማት፣ ግለሰቦች ይኽንን አገልግሎት ይፈልጉታል። በዚኽ አገልግሎትም ወንጌል ስለሚስፋፋ፣ ድኾች ስለሚረዱ፣ አድባራት እና ገዳማት ስለሚታነፁ፤ ይኽ እንቅስቃሴ እና አገልግሎት ደግሞ አንዳንድ የቅባት፣ የተሐድሶ አራማጆችን ያስቆጣል። አስቆጥቷል። የመናበባቸው ምስጢርም ይኼው ነው። ስለዚኽ ጥያቄው በእነሱ ስም ማጥፋት ዘመቻ አገልግሎቱን እና ሥራውን እናቁመው ወይስ እንቀጥለው ነው? ጉዳዩ፤ አናቆምም ነው መልሳችን።
4. ለሚያገለግሉን ግለሰቦች እና ተቋማት ደም ወዝ መክፈል ነውር ነው ወይ? ክፍያ መፈጸም ኃጢአት ነው ወይ?
የሚችል እና ሌላ መተዳደሪያ ያለው በነፃ ያገልግል። የማይችል ግን ራሱን እና ቤተሰቡን የሚያስተዳድርበት ዋጋው ሊከፈለው ይገባል። ቤተክርስቲያን ያስተማረችንም ይኽው ነው። ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ጳጳሳቱ፣ መነኮሳቱ፣ ካህናቱ፣መምህራኑ፣ ዘማርያኑ፣ ወዘተረፈ በምን የሚተዳደሩ ይመስላችኋል? ከአንዳንድ ቦታወችና አባቶች ውጪ ምእመናን በሚሰጡት ገንዘብ ነው። ከመንግሥት ቀጥሎ ሚሊየኖችን ቀጥራ ደሞዝ ከፍላ የምታሠራ ለብዙዎች የሥጋም የነፍስም መጠጥና ምግብ የኢ/ኦ/ተ/ቤ ን ናት። ዘዳግም 25፡4 "እህል የማያበራየውን በሬ አፉን አትሠር " ተብሎ ተጽፏል። ቅዱስ ጳውሎስም "እግዘብሔርን ስለበሬዎች ይገድዋልን?"1ኛ ቆሮ 9፥9 ፤ ስለአገልጋዩ ነው ወዳጄ። ቀጥሎ ጳውሎስ "ለሠራተኛ ደሞዙ ይገባዋል" ይላል። ሠራተኛ ይዝረፍ አይልም። ይስረቅ አይልም።
ለሠራተኛ ዋጋው ይገባዋል ነው ያለው። እኛ ሠርቀው የሚበሉትን እንጂ ሠርተው የሚበሉትን አንቃወምም። ሠርቀዋል ካላችኹ ማስረጃ አምጡ። ነገር ግን ማስረጃ የላችኹም። ስም ማጥፋት ብቻ ከኾነ ግን በሥጋም በነፍስም ከተጠያቂነት አናመልጥም።
5. ቲክቶከሮችን እና ዩቱበሮችን በተመለከተ
አንድ ዓለማዊ ቲክቶከር ለአንድ ማስታወቂያ ስንት ነው የሚከፈለው? አንድ ዶክመንተሪ ለመሥራት በዓለማውያን ስንት ይጠየቃል? በራሳችን ሰዎች ላይ ምን ያህል ጨካኝ እንደኾንን የገባን ለኦርቶዶክሳውያን ለቲክቶከር እና ዩቱበር ለምን ይከፈላል? ብለን የስም ማጥፋት ዘመቻውን ስናሟሙቀው ያየነው ዕለት ነው። ሠርቀዋል? ውሸት። መረጃ የለም። ዘርፈዋል? ውሸት መረጃ የለም።
ተከፍሏቸው በንጽሕና ሠርተው ከኾነ ምንድን ነው ኅጢአቱ? ቤተክርስቲያኑ
ሢሠራ፣ ቀለሙ ሲቀባ፣ አጥሩ ሲታጠር ይኽን የሠሩት ሰዎች የሌላ ዕምነት ተከታዮች ናቸው? በብዛት አይደሉም። ኦርቶዶክሳውያን ተቋራጮች፣ መሐንዲሶች፣ ግንበኞች፣ ቀለም ቀቢዎች፣ ኤሌክትሪሻኖች ናቸው።
ለእነዚኽ ሁሉ ከፍለን አሠርተን፤ ለዩቱበር እና ለቲክቶከር ሲኾን ለምን ተበሳጨን ብለን ስንጠይቅ መልሱ ጨካኞች ስለኾንን ነው። እነሱም የቤት ኪራይ አለባቸው። እነሱም የቢሮ ኪራይ አለባቸው። እነሱም የካሜራ ማን ደሞዝ አለባቸው። እነሱም ኮ ሰው ናቸው እንደኛ ይበላሉ ይጠጣሉ። እነሱም የሞባይል ካርድ ይፈልጋሉ። እነሱም በክንፋቸው አይበሩም ትራንስፖርት ይፈልጋሉ። እንደ ዓለማውያኑ ቲክቶከሮች አንበሳ እና አበባ እየተሰጣቸውአይደለም የሚገለግሉት የሚታሠሩት የኛዎቹ ቲክቶከሮች፣ የሚሰደዱት ኦርቶዶክሳውያን ቲክቶከሮች፣ ከመናፍቅ እና ከተሐድሶ ጋር አንገት ለአንገት የሚተናነቁት መንፈሳዊ ቲክቶከሮች፤ ምን አድርጉ ነው የምንላቸው? ለምን የሁለት ዓለም ስደተኞች እናደርጋቸዋለን?
ሠርቶ የሚበላን መደገፍ፤ ሠርቆ የሚበላን መንቀፍ ተገቢ ነው። ስለመስረቃቸው አንድ ማስረጃ የለም። ካለ እንኳን ግለሰቡን መጠየቅ እንጂ በስመ ቲክቶከር ሁሉንም መጨፍጨፍ ተገቢ አይደለም። ክርስትናም አይደለም።
በመጨረሻ የእኛን ንጽሕና እና የተቋማችን የአገልግሎት ተደራሽነት የምታውቁ ሥራችን ለሁሉ ይደረስ ዘንድ ጸልዩልን። የማታውቁን ጠይቁ። እያወቃችኹ በክፋት እና በምቀኝነት ለተነሣችኹብን የምንላችኹ ሶሻል ሚዲያ ፍርድ ቤት አይደለም። መረጃ እና ማስረጃ ይዛችኹ ክሠሡን። ያኔ ውርደታችኹን ትከናነባላችኹ። ደስ የሚለው አትከሥሡንም። ምክንያቱም ወሬ እንጂ ፍሬ የላችኹም። ምክንያቱም መረጃ እንጂ ማስረጃ የላችኹም። ምክንያቱም ሠርቆ መብላት እንጃ ሠርቶ መብላት ወንጀል ስላልኾነ። ምክንያቱም አገልግሎ መቀበል መጽሐፍ ቅዱሳዊ እንጂ ኃጢአት ስላልኾነ። እናም ክሠሡን። ያኔ የእናንተ ትክክለኝነት ይታያል።
በቀጣይም በሀገር ውስጥ ተቀምጠው ስማችንን ጠቅሰው የተቋማችንን ስም እና ክብር ያጎደፉትን ግለሰቦች በሕግ የምንጠይቅ ይኾናል። ከሀገር ውጭ ያሉትን በተመለከተ ዋነኛ ተዋናዮች እንደኾኑ እናውቃለን። እዚህ ያሉትም ስደቡልን አዋርዱልን እያሉ የሚልኩትም ውጪ ላሉት ነው። እነሱም በቅርበት እንደማይገኙ ቢከሠሡም ፍርዳቸው ሩቅ እንደኾነ ስለሚያውቁ ለእግዚአብሔር እናመለክታለን።
በቅርበት እኛንም ተቋማችንም የምታውቁ በተፈጠረው የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ሳትበገሩ እሰከ መጨረሻው በጸሎታችኹም በሃሳባችኹም አብራችኹን ለነበራችኹ ወዳጆቻችንን እና የአገልግሎት ተጠቃሚወቻችን ቀን አይታችኹ ስላልተሸራተታችኹ፤ ጩኽት ፈርታችኹ ስላልከዳችኹን እናመሰግናለን። ክርስትና ይኽ ነው። በሆሳዕና ዕለትም በዕለተ አርብም አብሮ መቆም። የሚያስከፍለውን ዋጋ ከፍሎ ነፃ መውጣት። እናመሰግናለን ።

Comments