Logo
FastMereja
ወሎ ፓራዳይዝ ሪልስቴት በወሎዋ ኮምቦልቻ ከተማ ግዙፍ የሪልስቴት ግንባታን አስጀመረ
#fastmereja I 50 ሽህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፈውና በወሎ ፓራዳይዝ ሪልስቴት የሚገነባው የመኖሪያ መንደር 400 ካሬ ሜትር ላይ ከሚያርፈው G+1 ሌግዠሪ ቪላ ጀምሮ G+4 እና G+6 አፓርትመንቶችን ያካተተ ነው፡፡

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መሀመድአሚን የሱፍ በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ኮምቦልቻ በፍጥነት እያደገች የምትገኝና የሰው ፍሰቱና ብዛቱ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ወሎ ፓራዳይዝ ሪልስቴት የመኖሪያ ቤት ፍላጎትን ለማሟላት ከፍተኛ ድርሻ ያለው መሆኑን ጠቁመው ቃሉን አክብሮ ስራውን እንደሚያከናውን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

ወሎ ፓራዳይዝ ሪልስቴት ግዙፍ የሆነውንና የተለያዩ መንደሮች የተካተቱበትን ግንባታ ለማከናወን ከ50 በላይ ቋሚ ሰራተኞችን ቀጥሮ፣ የተደራጀ ቢሮ ገንብቶና ማሽነሪዎችን አስገብቶ ስራ የጀመረ ካምፓኒ መሆኑን የካምፓኒው ባለቤትና CEO ሱለይማን አራጋው ተናግረዋል፡፡

ወሎ ፓራዳይዝ ሪልስቴት ጥራታቸውን የጠበቁና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዘው የተገነቡ ቤቶችን ፍላጎቱ ላላቸው ሁሉ የሚያቀርብ ሲሆን በተለይ ከሀገራቸው ወጥተው በተለያዩ አለማት የሚገኙ ያካባቢው ተወላጆች የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡

የሪልስቴት ካምፓኒው ለወደፊት እድገቱ ሲል ቃሉን ማክበር ዋነኛ መገለጫው መሆኑ የተገለጸ ሲሆን አካባቢውን ያማከለ የዋጋ ተመን እንዳለው በስነ-ስርዓቱ ላይ ተነግሯል፡፡ በቦታው ላይ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ባለሃብቶች ተገኝተዋል፡፡

ወሎ ፓራዳይዝ ሪልስቴት
የህልም ቤትዎን እንገባለን

27 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.