Logo
Getu Temesgen
በደሴ እና በኮምቦልቻ መካከል
በትራፊክ አደጋ የ28 ሕይወት ተቀጠፈ
#ethiopia | ከደሴ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ በደረሰ ከባድ የትራፊክ አደጋ የ28 ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ ገለጸ።

አደጋው የተከሰተው በደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች መካከል ልዩ ስሙ ሐረጎ በሚባለው አካባቢ መሆኑ ታውቋል።

ዛሬ ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ማለዳ ላይ ሲጓዝ የነበረው ይህ አውቶቡስ መንገዱን ስቶ በግምት 100 ሜትር ጥልቀት ወዳለው ገደል በመግባቱ የ28 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሊያልፍ ችሏል።

በተጨማሪም በጉዞው ላይ በነበሩ ሌሎች በርካታ ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በአሁኑ ወቅት ከአደጋው የተረፉትን ተጎጂዎች በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋማት ለማድረስ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ የገለጸው ፖሊስ፣ አደጋው የተከሰተበትን ትክክለኛ መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን አስታውቋል።

ሳሙኤል ኪሮስ
አሚኮ
#የጎዳናአደጋ #የትራፊክአደጋ #ደሴ #ኮምቦልቻ #አሚኮ #የአደጋመረጃ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.