Logo
FIDEL POST NEWS
የ1,000 ሊትር ጉድ፦ በኮምቦልቻ የተደረገው ድንገተኛ የነዳጅ ቁጥጥር ምን አሳየ?

​በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ህገ-ወጥ የነዳጅ ዝውውርን ለመግታት በተደረገ የተቀናጀ ክትትል፣ 12 የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ።

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከተሽከርካሪዎቹ የፋብሪካ ስሪት ውጭ እስከ 1,000 ሊትር ተጨማሪ ነዳጅ መያዝ የሚችሉ "ሳልቫቶዎችን" በህገ-ወጥ መንገድ አስገጥመው በመገኘታቸው ነው ሲል አስተዳደሩ ገልፇል።

​የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮናስ መላኩ እንደገለጹት፣ ከነዳጅ ታንከሮቹ በተጨማሪ በገንዘብ ጥቅማጥቅም የነዳጅ ወረፋ ለማስቀደም የሞከሩ ተራ አስከባሪዎችና አሽከርካሪዎችም በፖሊስ ተይዘዋል።

የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ጌታቸው ሙህየ፣ በኬላዎችና በነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚደረገው ጥብቅ ቁጥጥር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.