Logo
FIDEL POST NEWS
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ101 ሚሊዮን ብር የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ድጋፉ የተደረገው ለአምስት የመንግስት ሆስፒታሎች መሆኑ ተነግሯል።

በኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ አማካኝነት የቀረበው ይህ ድጋፍ፣ በኡስታዝ አቡበከር አህመድ አስተባባሪነት ከሙስሊም ኤይድ አሜሪካ የተገኘ ነው።

​በርክክብ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ድጋፉ የረመዳን ወርን የመተሳሰብ እሴት የሚያንፀባርቅ መሆኑን ገልጸዋል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሰሃረላ አብዱላሂ በበኩላቸው ድጋፉ ለጤና ተቋማቱ ትልቅ አቅም እንደሚሆን በመጥቀስ ምስጋና አቅርበዋል።

ድጋፉ የተደረገላቸው ሆስፒታሎች አቦምሳ፣ ኮምቦልቻ፣ ጭናክሰን፣ ጉንችሬ እና ቋንጤ ይገኙበታል።
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.