3 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የፔፕ ጋርዲዮላን ቦታ በመተካት የማንቸስተር ሲቲው አዲስ አሰልጣኝ የሆኑት ኤንዞ ማሬስካ የመጀመሪያ ፈተናቸውን በሆንግ ኮንግ አድርገዋል። ቡድናቸው ከጣሊያኑ ሀያል ክለብ ኢንተር ሚላን ጋር ባደረገው አጓጊ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ 1 ለ 1 ከተለያየ በኋላ፣ በፍጹም ቅጣት ምት ሽንፈትን አስተናግዷል። ማሬስካ በሲቲ ቤት ህልም የሚመስል ጅምር አድርገው ነበር፤ ገና በ14ኛው ደቂቃ ላይ ዲቪን ሙባማ ከቅርብ ርቀት ባስቆጠራት ግብ ሲቲዎች ቀዳሚ መሆን ችለው ነበር። ነገር ግን ደስታቸው ብዙም አልቆየም፤ ከስድስት ደቂቃዎች በኋላ ቤንጃሚን ፓቫርድ ለኢንተር ሚላን የአቻነቷን ግብ አስቆጠረ። በሁለተኛው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች የማሸነፊያ ግብ ለማግኘት ጥረት ቢያደርጉም ሳይሳካላቸው ቀርቷል። ጨዋታው ወደ ፍጹም ቅጣት ምት ሲያመራ ማንቸስተር ሲቲዎች የመጀመሪያዎቹን ሶስት ምቶች በማባከናቸው ዋጋ የከፈሉ ሲሆን፣ ማቲዮ ላቬሊ ለኢንተር ሚላን የማሸነፊያዋን ኳስ መረብ ላይ አሳርፏል።
የማንቸስተር ሲቲ ተጫዋቾች የሜዳ ላይ አቋም ምን ይመስል ነበር?
በቋሚ አሰላለፍ የገቡትን ስንመለከት ጂያንሉዊጂ ዶናሩማ (5) ሙሉውን 90 ደቂቃ ተጫውቷል። ጥሩ ኳስ አድኗል፣ ነገር ግን አልፎ አልፎ መደናገጦች ነበሩበት። ስህተት ሰርቶ ለተጋጣሚ ኳስ ቢሰጥም እድለኛ ሆኖ ግብ አልተቆጠረበትም።
ሪኮ ሉዊስ (7) በሁለተኛው አጋማሽ ወደ አማካይ ስፍራ ሲመጣ ብቃቱ በእጅጉ ተሻሽሏል። ከሳጥን ውጪ ያገኘውን ኳስ አየር ላይ ያባከነ ሲሆን፣ ከቅርብ ርቀት ያገኛትን ኳስ በተሻለ መጠቀም ሲገባው ሳይጠቀምባት ቀርቷል።
የኡዝቤኪስታናዊው ተጫዋች አብዱኮዲር ኩሳኖቭ (6) አቋም ወጣ ገባ ነበር። አንቶዋን ሴሜንዮ ግብ ሊያስቆጥርበት የነበረውን አስደናቂ ኳስ ያቀበለ ሲሆን፣ ወሳኝ ኳስም አግዷል። ነገር ግን የቢጫ ካርድ ሰለባ ከመሆኑም በላይ በፍጹም ቅጣት ምት ኳስ አስመልሶበታል።
የጆስኮ ግቫርዲዮል (5) ደካማ የኳስ አወጣጡ ለኢንተር ሚላን ግብ መቆጠር ምክንያት ሆኗል። ካለፈው የውድድር ዘመን የእግር ስብራት ጉዳት በኋላ ገና እውነተኛ አቋሙን እያፈላለገ ይገኛል።
ስቴፈን ምፉኒ (6) በቋሚነት ከጀመሩት ሁለት ወጣቶች አንዱ ሲሆን በአንዲ ዲዩፍ በቀላሉ ቢታለፍም ኢንተሮች ወደ ግብነት ሳይቀይሩት ቀርተዋል።
ስለ ቀጣይ የዝውውር ቆይታው ጥርጣሬዎች ቢኖሩም ማቲዮ ኮቫቺች (6) በተጫወተበት 45 ደቂቃ ውስጥ በመሀል ሜዳ ላይ ንቁ እና ተንቀሳቃሽ እንቅስቃሴ አድርጓል።
ቲጃኒ ሬይንደርስ (6) በመጀመሪያው አጋማሽ መሬት ለመሬት የመታው ሙከራ በግብ ጠባቂው ቢዳንም፣ ከዚያ ውጪ ብዙም አልታየም።
አንቶዋን ሴሜንዮ (8) የኢንተርን ተከላካይ ዲዩፍን ክፉኛ ሲፈትን አምሽቷል። ጋናዊው ኮከብ የመጀመሪያዋን ግብ የፈጠረ ሲሆን፣ አስደናቂ የብቻ ጥረቱን አድርጎ ግብ ማስቆጠር ሲገባው በግብ ጠባቂው ተመልሶበታል።
ወደ ቶተንሃም ሊያመራ እንደሚችል ቢነገርም ሳቪንሆ (7) በዚህ ጨዋታ ግን እጅግ ማራኪ እንቅስቃሴ አሳይቷል። ከቀኝ መስመር አፈትልኮ ገብቶ ያሻማትን ኳስ የቡድን አጋሩ ሳይጠቀምባት ቀርቷል።
ፊል ፎደን (6) የቡድኑን አምበልነት ኃላፊነት ወስዶ የቅጣት ምቶችን ሲያሻማ ቢውልም፣ ያን ያህል አደገኛ የግብ እድሎችን አልፈጠረም። ባለፈው ዓመት በስቶክ ሲቲ በውሰት ያሳለፈው ዲቪን ሙባማ (7) አሁን ዋናውን ቡድን ለመቀላቀል አጋጣሚውን እየተጠቀመበት ይገኛል፤ ያስቆጠራትም ግብ ለዚህ ማሳያ ናት።
ከተቀያሪዎቹ መካከል ራያን አኢት-ኑሪ (5) ድንቅ ኳስ ከግራ መስመር ቢያሻማም ኒኮ ጎንዛሌዝ አላስቆጠረውም። በፍጹም ቅጣት ምት መለያው ላይም ኳሷን አየር ላይ አውጥቷታል። ቪክቶር ሬስ (7) እጅግ ድንቅ 45 ደቂቃ አሳልፏል። የጨዋታ ንባቡን በማሳየት ወሳኝ ኳስ በማቋረጥ የተጋጣሚን ግብ ያዳነ ሲሆን፣ የእሱ ሙከራም በግቡ አግዳሚ ተመልሶበታል። ማክስ አሌይን (6) ኳስ ሲይዝ በራስ መተማመን ይታይበታል። ባለፈው የውድድር ዘመን ሰባት ጊዜ ለዋናው ቡድን ተሰልፎ የነበረ ሲሆን፣ ዘንድሮም የተሻለ እድል ሊያገኝ ይችላል። ኒኮ ጎንዛሌዝ (6) ኳስ ይዞ ጥሩ መንቀሳቀስ የቻለ ሲሆን፣ ለግብ የቀረበች ሙከራም አድርጓል። ሆኖም በፍጹም ቅጣት ምቱ ላይ ስቶታል። የወጣቱ ተጫዋች ራያን ማክኢዱ (7) አቋም እጅግ አስደናቂ ነበር። ግብ ለማስቆጠር ሞክሮ የግቡ ቋሚ የመለሰበት ሲሆን ሌላ ሙከራውም በትንሹ ወጥቶበታል። ማሃማዱ ሳንጋሬ (6) ተቀይሮ ከገባ በኋላ ኳስ እምብዛም አላገኘም። ክላውዲዮ ኤቼቬሪ (7) የማሸነፊያ ግብ ሊያስቆጥር ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም ተመልሶበታል። በፍጹም ቅጣት ምቱ ያሳየው ደፋር የ‘ፓኔንካ’ አጨራረስ ነጥቡን ከፍ አድርጎለታል። ካደን ብሬዝዌት (6) ባገኘው ጥቂት የጨዋታ ጊዜ ጥሩ ትጋት አሳይቷል።
ያልተሰለፉ ተቀያሪዎች ጃክ ዊንት፣ ማክስ ቻቦት፣ ጀረሚ ሞንጋ፣ ፍሎይድ ሳምባ፣ ጄይደን ሄስኪ፣ ማቲ ሄንደርሰን-ሆል እና ዛቪዬር ፓርከር ነበሩ።

4 days ago
ማንቸስተር ዩናይትድ፣ አርሰናል እና ቶተንሃም በዝውውር መስኮቱ ትኩረት ስቧል፦ የብሩኖ ጊማራኤስ፣ ሊዊስ ኦል እና ክርስቲያን ሮሜሮ አዳዲስ መረጃዎች
በአውሮፓ የእግር ኳስ የዝውውር መስኮት ታላላቅ ክለቦች ስብስባቸውን ለማጠናከር በሚያደርጉት እንቅስቃሴ በርካታ ትኩረት ሳቢ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ።
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አርሰናል የኒውካስል ዩናይትድ አማካኝና አጋዥ ብሩኖ ጊማራኤስን ለማስፈረም የሚያደርገውን ንግግር አፋጥኗል። እንደ ዘ ታይምስ (The Times)፣ ዘ ሳን (The Sun) እና ኢኤስፒኤን (ESPN) ዘገባዎች ከሆነ፤ አርሰናል ተጨማሪ ክፍያዎችን (add-ons) ጨምሮ 80 ሚሊዮን ፓውንድ በሚጠጋ ሂሳብ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ከጫፍ ደርሷል። በተለይም አሰልጣኝ ኤዲ ሃው ከኒውካስል ለመልቀቃቸው ተከትሎ አርሰናል ተጫዋቹን ለማስፈረም ያለው እምነት ከፍ ማለቱ ተጠቁሟል።
በሌላ በኩል ማንቸስተር ዩናይትድ የኒውካስሉን የግራ መስመር ተከላካይ ሊዊስ ኦልን በዝውውር አማራጭነት እየተመለከተው ይገኛል። በተመሳሳይ የዩናይትዱ አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ ወደ ጣሊያኑ ክለብ ሮማ የመዛወር ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌለው ታውቋል።
በተጨማሪም ከአሰልጣኝ አንጌ ፖስቴኮግሉ ስብስብ ቶተንሃም ጋር በተያያዘ የስፓኒሹ አትሌቲኮ ማድሪድ የአርጀንቲናውን ማዕከላዊ ተከላካይ ክርስቲያን ሮሜሮን ለማስፈረም ያለውን ፍላጎት ዳግም ያቀጣጠለው ሲሆን፤ የፖርቱጋሉ ፖርቶ ደግሞ የቶተንሃሙን የግራ መስመር ተከላካይ ሶውዛን ለማስፈረም ፍላጎት ማሳየቱ ተገልጿል።

1 month ago
ማይክል ካሪክ - የኦልድ ትራፎርድ የልብ ትርታ፣ በታላላቅ ኮከቦች ጥላ ስር ተደብቆ የኖረ ድንቅ ጥበበኛ
***********************
ስለ እርሱ ሲታሰብ አምስት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችና የሻምፒዮንስ ሊጉ ድል ትዝ ሊሉን ይችላሉ። ነገር ግን እውነተኛው ማይክል ካሪክ የተገነባው በብዙዎች ዘንድ በማይታወቁ፣ ልብ በሚነኩና አስገራሚ በሆኑ ድብቅ ታሪኮች ውስጥ ነው።
ዛሬ የምናውቀው ካሪክ በኳስ ቁጥጥሩና አርቆ አሳቢነቱ የሚታወቅ የአማካይ ስፍራ ኮከብ ነው። ነገር ግን ወደ ዌስትሃም አካዳሚ በ15 ዓመቱ ሲቀላቀል ሕልሙ ሌላ ነበር፤ ያኔ የፊት መስመር አጥቂ ነበር።
ካሪክ ያደገው እንደ አላን ሺረር እና ፒተር ቤርድስሌይ ያሉ ታላላቅ ሰዎችን ባፈራው ታዋቂው የዎልሰንድ ቦይስ አካዳሚ ውስጥ ነው። የኒውካስል ዩናይትድ ደጋፊ የነበረ ቢሆንም፣ በ15 ዓመቱ ኒውካስልን ትቶ ወደ ዌስትሃም ዩናይትድ አቀና።
በ15 ዓመቱ ወደ ዌስትሃም አካዳሚ ሲቀላቀል የመስመር አጥቂ ነበር። በአንድ ጨዋታ ላይ ግን የመሃል አማካይ በመጥፋቱ በአጋጣሚ ቦታው ተቀይሮ የክፍለ ዘመኑ ብልህ አማካይ ሊሆን አጋጣሚው ተፈጠረ።
ካሪክ በቦታው መጀመሪያ ባይደሰትም ያለ እንቢታ ተጫወተ። ይህ አጋጣሚ ግን የእግር ኳስን ታሪኩን ቀየረች፤ አጥቂው ካሪክ ቀርቶ፣ የአውሮፓን መድረክ የሚገዛው ብልሁ አማካይ ተወለደ።
የካሪክ የጉርምስና ዕድሜ ደግሞ ሌላ አስገራሚ ፈተናን ይዞ መጣ። 17 ዓመቱ ላይ በአንድ ጊዜ 8 ኢንች ያህል ቁመት ጨመረ። በወቅቱ የነበረው ቀጭን ሰውነቱ ከቁመቱ ጋር ባለመመጣጠኑ ሜዳ ላይ መሮጥ እስኪያቅተው ተቸግሮ እንደነበር የቀድሞ አሰልጣኙ ሃሪ ሬድናፕ ያስታውሳሉ።
ብዙዎች የወደፊት መንገዱን ተስፋ ሲያጡበት፣ እርሱ ግን በትጋትና በጽናት ሰውነቱን ገነባ፤ በመጨረሻም ከሪዮ ፈርዲናንድ እና ፍራንክ ላምፓርድ ጋር የዌስትሃም ወርቃማ ትውልድ አካል ሆነ።
ካሪክ ገና በወጣትነቱ ጨዋታን የማንበብ ብቃቱ ድንቅ ነበር። ከዌስትሃም፣ ስዊንደን፣ በርሚንግሃም እና ቶተንሃም በኋላ በ2006 ታላቁን ማንችስተር ዩናይትድን ሲቀላቀል፣ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በሮይ ኪን መልቀቅ የዛለውን የመሃል ሜዳ የሚያክምላቸውን የፈጠራ ሰው አገኙ።
በእንግሊዝ እግር ኳስ ታሪክ ስቲቨን ጄራርድ እና ፍራንክ ላምፓርድ በችሎታ እንደማይደረስባቸው የመሀል ሜዳ ጣኦታት ይታዩ ነበር። ነገር ግን ታላቁ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ልብ ውስጥ የነበረው እውነተኛው ንጉሥ ካሪክ ብቻ ነበር።
ፈርጉሰን በግል ማስታወሻቸው ላይ “...ላምፓርድና ጄራርድ ታላላቅ ስብዕና የነበራቸው ተጫዋቾች ናቸው፤ እውነተኛ ምርጥ ተጫዋቾች ግን አልነበሩም ፤ ካሪክ ግን የእግር ኳስ አዕምሮ ነበረው። የእንግሊዝ ሚዲያዎች ስለ እነርሱ አብዝተው በማወደስ ሲጮሁ፣ ካሪክ ግን በትህትናውና በአይናፋርነቱ ምክንያት በነርሱ ጥላ ስር ተደብቆ ተበደለ።” ሲሉ ነበር እንጋፋው አሰልጣኝ በብዕራችው ከትበው ስለካሪክ የመሰከሩት።
ማይክል ካሪክ ዛሬም ቢሆን ያው ነው - ዝምተኛ፣ አስተዋይና ልባም። የዩናይትድን ታላቅ ስም ለመታደግ በዋና አሰልጣኝነት ተሰይሟል። ትናንት በዝምታ ሜዳውን እንደገዛው ሁሉ፣ ዛሬም በዚያው ጥንቁቅ አዕምሮው የታላቁን ክለብ ታሪክ ለመጻፍ እየተዘጋጀ ነው።
ካሪክ እ.አ.አ በ2006 ከቶተንሃም ማንቸስተር ዩናይትድን ከተቀላቀለ በኋላ በ12 ወርቃማ ዓመታት 5 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን፣ የሻምፒዮንስ ሊግን እና የኤፍኤ ካፕን ጨምሮ በርካታ የክብር አክሊሎችን ደፍቷል።
ሆኖም ግን እንደ ፖል ስኮልስ ፣ ጄራርድ እና ላምፓርድ ባሉ ደማቅ ስሞች ጥላ ስር ተደብቆ አሳልፏል። ነገር ግን ሳይታይ የሚደምቅ የቡድኑ የጀርባ አጥንት ነበር።
በኦልድ ትራፎርድ የነበረው ስፍራ ከብዙ ተጫዋቾች የተለየ ነበር። ግቦችን ብዙ አያስቆጥርም፣ አስደናቂ ትርዒቶችንም አያሳይም፤ ነገር ግን ጨዋታው በእርሱ እግር ይጀምር፣ በእርሱም አዕምሮ ይመራ ነበር።
ከተጫዋችነት በኋላ በሞሪንሆ እና ሶልሻየር ስር በረዳትነት የሰራው ካሪክ በ2021 ለአጭር ጊዜ ዩናይትድን በጊዜያዊነት መርቶ ጥሩ ውጤት አሳይቷል።
በመቀጠል ሚድልስብሮን በዋና አሰልጣኝነት ይዞ አስደናቂ ጊዜ ካሳለፈ በኋላ፣ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሩበን አሞሪም ስር የተንኮታኮተውን ማንችስተር ዩናይትድን ለመታደግ በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ኦልትራፎርድ ሲደርስ ብዙዎች እምነት አልጣሉበትም ነበር።
ነገር ግን ዝምተኛው ካሪክ ፤ ትናንት በዝምታ ሜዳውን እንደገዛው ሁሉ፣ ታላቁን ክለብ ከመውረድ ውርደት ታድጎ ለሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ አበቃው።
ማይክል ካሪክ በተጫዋችነት ዘመኑ በማንቸስተር ዩናይትድ የቡድን አጋሮቹ "ሃቮክ" በሚል ቅጽል ስም ይጠሩት ነበር። ይህ ስም የመጣው በወቅቱ ተጫዋቾቹ በፒኤስፒ (PSP) ላይ "SOCOM US Navy SEALs: Fireteam Bravo" የተሰኘውን ታክቲካዊና ስውር የጦርነት ጨዋታ(ኮምፒዩተር ጌም) በጋራ ሲጫወቱ ከነበራቸው ትውስታ ነው።
ዌይን ሩኒ እንደተናገረው ይህ ጨዋታና የካሪክ መሪነት ቡድኑን አንድ ላይ ለማሰባሰብ ትልቅ ሚና ነበረው። ካሪክ በጨዋታው ላይ ብቻ ሳይሆን በሜዳው ላይም ያንን ስውር እና ጥንቁቅ ታክቲክ የሚተገብር መሪ ነበር።
ካሪክ ብዙ ጊዜ በሚያወሩ ኮከቦች መካከል በዝምታ የበራ ኮከብ ነበር። የጨዋታውን ስልተ-ምት በአንድ ንክኪ የሚቀይር፣ የቡድኑን ልብ በጸጥታ የሚያስመታ ረቂቅ የሙዚቃ መሪ።
እሱን የሚለየው ያሸነፋቸው ዋንጫዎች ብቻ አይደሉም፤ ያለ ጩኸት ታሪክ መፍጠር የቻለ ሰው መሆኑ ነው። አንዳንድ ኮከቦች በብርሃን ይደምቃሉ፤ ካሪክ ግን በዝምታው ታላቅ ሆነ።
ለዚህም ነው ዛሬም በኦልድ ትራፎርድ ታሪክ ውስጥ ከማይረሱ ስሞች አንዱ ሆኖ የሚጠራው፤ እየመጡ ያሉትን ብሩህ የአሰልጣኝነት ዘመናቱንም ያስናፈቀው።
በአዲስ የሺዋስ
Ethiopian Broadcasting Corporation EBC-መዝናኛ EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት #football

2 months ago
ሻምፒዮኑ አርሰናል ከሻምፒዮንሺፑ አሸናፊ ኮቬንትሪ ሲቲ …
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2026/27 የውድድር ዘመን የጨዋታ መርሐ ግብር በትናንትናው ዕለት ይፋ መደረጉ ይታወቃል፡፡
በዚህም የወቅቱ የሊጉ ሻምፒዮን አርሰናል ከሻምፒዮንሺፑ አሸናፊ ኮቬንትሪ ሲቲ ጋር በሜዳው ኢምሬትስ የሊጉን የመክፈቻ ጨዋታ ያደርጋል፡፡
ኮቬንትሪ ሲቲ ለመጨረሻ ጊዜ በአንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የተሳተፈው በ2000/01 የውድድር ዓመት እንደነበር ይታወሳል፡፡
በዚያ የውድድር ዓመት በሊጉ ካደረጋቸው 38 ጨዋታዎች 34 ነጥብ በመሰብሰብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወደ ሻምፒዮንሺፕ ለመውረድ ተገዷል፡፡
ክለቡ በአሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ እየተመራ ከዓመታት በኋላ በአስደናቂ ብቃት
ለ2026/27 የውድድር ዘመን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ማደጉ ይታወሳል፡፡
የ2026/27 የውድድር ዓመት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታ የፕሪሚየር ሊጉና የሻምፒዮንሺፑ አሸናፊ ቡድኖች በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀምራል፡፡
አርሰናል በ3ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር በሜዳው ቼልሲን የሚያስተናግድበት የለንደን ደርቢ ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡
አርሰናል በ9ኛ ሳምንት ከሊቨርፑል፣ በ12ኛ ሳምንት ከማንቼስተር ሲቲ፣ በ14ኛ ሳምንት ከቶተንሃም ሆትስፐር እንዲሁም በ16ኛ ሳምንት ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር ይገናኛል፡፡
ከአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ጋር በመለያየት አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካን በኃላፊነት የሾመው ማንችስተር ሲቲ በሜዳው ከቦርንማውዝ ጋር የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል፡፡
አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በማንቼስተር ሲቲ ቤት ከዚህ ቀደም በምክትል አሰልጣኝነት የሰሩ ሲሆን፥ በአዲሱ የውድድር ዓመት በዋና አሰልጣኝነት የሚያደርጉት ጉዞ ይጠበቃል፡፡
ማንቼስተር ሲቲ ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር በ4ኛ ሳምንት እንዲሁም ከሊቨርፑል ጋር በ6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ይገናኛል።
በአሰልጣኝ ማይክል ካሪክ የሚመራው ማንቼስተር ዩናይትድ በበኩሉ ከአዲስ አዳጊው ሃል ሲቲ ጋር በመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታው ይገናኛል፡፡
ማንቼስተር ዩናይትድ ከአሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ቅጥር በኋላ በመሻሻል የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ቦታን በማግኘት የውድድር ዓመቱን ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡
ከ4ኛ ሳምንት የማንቼስተር ደርቢ ጨዋታ በኋላ በ9ኛ ሳምንት ከቼልሲ፣ በ11ኛ ሳምንት ከሊቨርፑል እንዲሁም በ16ኛ ሳምንት ደግሞ ከወቅቱ የሊጉ ሻምፒዮን አርሰናል ጋር ይገናኛል፡፡
አንዶኒ ኢራዮላን በኋላፊነት የሾመው ሊቨርፑል ከኒውካስል ዩናይትድ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
ሊቨርፑል በ6ኛ ሳምንት ከማንቼስተር ሲቲ፣ በ9ኛ ሳምንት ከአርሰናል፣ በ11ኛ ሳምንት ከማንቼስተር ዩናይትድ እንዲሁም በ12ኛ ሳምንት ደግሞ በመርሲሳይድ ደርቢ ከኤቨርተን ይፋለማል፡፡
ከአውሮፓ ውድድሮች ውጪ ሆኖ የውድድር ዓመቱን ያጠናቀቀው ቼልሲ በመጀመሪያ ሳምንት ከፉልሃም ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
ቼልሲ አዲሱን የውድድር ዓመት በአሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ እየተመራ የሚጀምር ይሆናል፡፡
በመርሐ ግብሩ መሰረት አዲሱ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም የሚጀመር ይሆናል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ

ቮዚኒያ : የኬፕቨርዴው ግብ ጠባቂ
#ethiopia | በዓለም ዋንጫ መድረክ ኬፕቨርዴ ከኃያሏ ስፔን ጋር ነጥብ እንድትጋራ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከተው ግብ ጠባቂው ቮዚኒያ በአሁኑ ወቅት ሰፊ አድናቆትን እያገኘ ይገኛል።
ይህ ድንቅ ብቃቱ ማኅበራዊ ገጹ ላይም ትልቅ ተፅዕኖ የፈጠረ ሲሆን ከጨዋታው በኋላ የኢንስታግራም ተከታዮቹ ቁጥር ከ56 ሺህ ተነስቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ 3 ሚሊዮን አድጓል።
ዕድሜው 40 ዓመት የሞላው ይህ ግብ ጠባቂ በዓለም ዋንጫ ታሪክ ውስጥ ጨዋታ በማድረግ ሁለተኛው በእድሜ አንጋፋ ተጨዋች በመሆን አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል።
ከእርሱ ቀድሞ የሚገኘው በ45 ዓመቱ ሜዳ ውስጥ የገባው ግብፃዊው ግብ ጠባቂ ኢሳም ኤል ሀዳሪ ብቻ ነው።
ትክክለኛ ስሙ ጆሲማር ሆሴ ኤቮራ ዲያስ ቢሆንም በይበልጥ የሚታወቀው ግን ቮዚኒያ በሚለው የቅፅል ስሙ ነው።
ጆሲማር የሚለውን ስም ያወጣለት አባቱ ሲሆን በ1986 የዓለም ዋንጫ ወቅት አባቱ በወታደራዊ አገልግሎት ላይ እያለ ብራዚላዊው ተጫዋች ጆሲማር ባሳየው አስደናቂ ብቃት ተማርኮ አዲስ የተወለደ ልጁን በእርሱ ስም ሰይሞታል።
ቮዚኒያ የሚለው የቅፅል ስሙ ደግሞ በፖርቹጋልኛ ቋንቋ አያቴ ማለት ነው። ይህን ስም ሊያገኝ የቻለው ከአያቱ ጋር ስላደገ እና በጣም ይቀራረብ ስለነበር ነው። በልጅነቱ ሰፈር ውስጥ ኳስ ሲጫወት በተጎዳ ቁጥር በቀጥታ ወደ አያቱ ይሮጥ ስለነበር የሰፈሩ ልጆች ይህንን ስም አውጥተውለታል።
ይህ አንጋፋ ግብ ጠባቂ በዕለቱ ለምን እንደአለቀሰ ሲያስረዳ ከአያቱ ጋር እንዳደገ ገልጾ እርሷ በቅርብ ዓመት ማለፏንና እናቱ ደግሞ በቪዛ ምክንያት እንዲሁም ከፍተኛ የገንዘብ ማስያዣ በመጠየቋ ወደ ስፍራው ልትመጣ ስላልቻለች መሆኑን በሀዘን ተናግሯል።
ቢረፍድም ለሀገሩ ታሪክ የሰራው ቮዚኒያ በደስታ ዕንባ ታጥቧል። በአትላንታ ስታዲየም የስፔን የፊት መስመር አጥቂዎች ወደ ግብ በደረሱባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ በፖርቹጋል ሁለተኛ ዲቪዚዮን ለቻቬስ ክለብ የሚጫወተው ይህ ባለተሰጥኦ ግብ ጠባቂ እንደ ብረት የጠነከረ ግንብ በመሆን ወደ መረብ የተመቱ ኳሶችን በሚገርም ብቃት መልሷል።
በተለይም ፌራን ቶሬስ እና አሜሪክ ላፖርቴ ያደረጓቸውን ተደጋጋሚ እና አደገኛ ሙከራዎች ማክሸፍ የቻለ ሲሆን ቶሬስ ያገኘውን ወርቃማ የግብ ዕድል በቮዚኒያ ጫና ምክንያት አግድም ብረት ላይ መትቶታል።
በጨዋታው ማጠናቀቂያ ላይ ሚኬል ኦያርዛባል የሞከረውን ኳስ ደግሞ ሮቤርቶ ሎፔስ ባደረገው አስደናቂ መከላከል ሊያድን ችሏል።
ስፔን በጨዋታው በአጠቃላይ 27 የግብ ሙከራዎችን ያደረገች ቢሆንም ኢላማውን የጠበቀው ግን ሰባቱ ብቻ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ የኒኮ ዊሊያምስ በቋሚነት አለመሰለፍ የስፔንን የማጥቃት ጥንካሬ በእጅጉ ቀንሶታል ተብሏል።
የቀድሞው የቶተንሃም አሰልጣኝ አንጅ ፖስቴኮግሉ በእንግሊዙ አይቲቪ ስፖርት በሰጡት ትንታኔ ይህ የእግር ኳስ ውበትና ታላቅነት ነው ካሉ በኋላ የኬፕ ቨርዴ ተጫዋቾች በውስጣቸው የነበረው ወኔና ተነሳሽነት እጅግ አስደናቂ ነበር ብለዋል።
ጨዋታው ሲጠናቀቅም አንጋፋው ግብ ጠባቂ ቮዚኒያ በቡድን አጋሮቹ ታቅፎ የደስታ ዕንባውን ሲያብስ ታይቷል።
ስፔን እ.አ.አ በ2010 የዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ በስዊዘርላንድ ብትሸነፍም በመጨረሻ ዋንጫውን ማንሳቷ ለዘንድሮው ጉዞዋ እንደ ተስፋ የሚቆጠር ታሪካዊ ማስታወሻ ሲሆን ኬፕ ቨርዴ ግን ከጋና የ2006 ጉዞ በኋላ ወደ ቀጣዩ ዙር የምታልፍ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር የመሆን ዕድሏን በከፍተኛ ደረጃ አሳድጋለች።
#football #worldcup #capeverde #spain #sportsnews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ኬፕ ቨርዴ ከስፔን ጋር ያለ ጎል አቻ በመለያየት ታሪክ ሰራች
#ethiopia | በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ እስካሁን ከተመዘገቡት ኩነቶች ሁሉ እጅግ አስገራሚና ታላቅ የተባለው ታሪክ በአትላንታ ሜዳ ላይ ተከስቷል።
በዓለማችን በቆዳ ስፋቷ በሦስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው አነስተኛዋ አገር እና በፊፋ የደረጃ ሰንጠረዥ 67ኛ ላይ የምትገኘው ኬፕ ቨርዴ የአውሮፓ ሻምፒዮንና በዓለም እግር ኳስ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘውን ጠንካራዋን ስፔንን ያለ ምንም ጎል 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት በመግታት ነጥብ ማስጣል ችላለች።
የእግር ኳስ ተንታኞችና ብዙኃኑ ተመልካቾች ይህ ጨዋታ ለስፔን ብሔራዊ ቡድን ቀላል የግብ ማግቢያ ልምምድ እንደሚሆን ቅድመ ግምት ሰጥተው የነበረ ቢሆንም በሜዳ ላይ የታየው እውነታ ግን የዓለም ዋንጫ ሁልጊዜም አስቀድሞ ለመተንበይ አስቸጋሪ መሆኑን ዳግም አስመስክሯል።
የስፔን ተጫዋቾች በጨዋታው ላይ ለረጅም ሰዓታት ኳስን ተቆጣጥረው ቢጫወቱም የኬፕ ቨርዴን የተከላካይ መስመር ሰብረው ለመግባት ግን በእጅጉ ተፈትነዋል።
የስፔን የፊት መስመር አጥቂዎች ወደ ግብ በደረሱባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ በፖርቹጋል ሁለተኛ ዲቪዚዮን ለቻቬስ ክለብ የሚጫወተው የ40 ዓመቱ አንጋፋ የኬፕ ቨርዴ ግብ ጠባቂ ቮዚንሃ እንደ ብረት የጠነከረ ግንብ ሆኖ አግዷቸዋል።
ይህ ግብ ጠባቂ ፌራን ቶሬስ እና አሜሪክ ላፖርቴ ያደረጓቸውን ተደጋጋሚና አደገኛ ሙከራዎች በሚያስደንቅ ብቃት አድኗል።
ቶሬስ በጨዋታው ያገኘውን ወርቃማ የግብ ዕድል በቮዚንሃ ጫና ምክንያት አግድም ብረት ሲመታበት በጨዋታው ማጠናቀቂያ ላይ ሚኬል ኦያርዛባል የሞከረውን ኳስ ደግሞ ሮቤርቶ ሎፔስ ባደረገው አስደናቂ መከላከል ሊከሽፍ ችሏል።
ስፔን በጨዋታው በአጠቃላይ 27 የግብ ሙከራዎችን ያደረገች ቢሆንም ኢላማውን የጠበቀው ግን ሰባቱ ብቻ ነበር።
የአሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላ ፉየንቴ ስብስብ የጨዋታውን አካሄድ ለመቀየር በማሰብ ከጉዳት ገና ያገገመውን የባርሴሎናውን ታዳጊ ላሚን ያማልን በሁለተኛው አጋማሽ ቀይረው ቢያስገቡም የያማል መግባት ስታዲየሙን ከማሞቅ ባለፈ ከስምንት ሳምንታት የጉዳት እረፍት በኋላ የተመለሰ በመሆኑ የስፔንን የማጥቃት ድክመት ሙሉ በሙሉ ሊፈታ አልቻለም።
ከዚህም በተጨማሪ የኒኮ ዊሊያምስ በቋሚነት አለመሰለፍ የስፔንን የማጥቃት ጥንካሬ በእጅጉ ቀንሶት ታይቷል።
የስፔኑ ታዋቂ ጋዜጣ ማርካ ሁኔታውን ሲገልጽ በአትላንታ ድንገተኛ አደጋ ተከሰተ ስፔን መጫወቻ መንገድና መፍትሔ አጥታ ተቸገረች በማለት በትችት ጽፏል።
በሌላ በኩል የቀድሞው የቶተንሃም አሰልጣኝ አንጅ ፖስቴኮግሉ በእንግሊዙ አይቲቪ ስፖርት በሰጡት ትንታኔ ይህ የእግር ኳስ ውበትና ታላቅነት ነው የኬፕ ቨርዴ ተጫዋቾች በውስጣቸው የነበራቸው ወኔና ተነሳሽነት እጅግ አስደናቂ ነበር። አሁን የዚህች ትንንሽ አገር ዜጎች በማንነታቸው በኩራት ይናገራሉ መላው ዓለምም አውቆላቸዋል በማለት አወድሰዋል።
የመጨረሻው ዳኛ ፊሽካ ሲነፋ የኬፕ ቨርዴ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች የዓለም ዋንጫውን በራሱ ያሸነፉ ያህል ስታዲየሙን በደስታ ድምፅ አናውጠውታል።
አንጋፋው ግብ ጠባቂ ቮዚንሃ በቡድን አጋሮቹ ታቅፎ የደስታ ዕንባውን ሲያብስ ታይቷል።
ስፔን እ.አ.አ በ2010 የዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ በስዊዘርላንድ ብትሸነፍም በመጨረሻ ዋንጫውን ማንሳቷ ለዘንድሮው ጉዞዋ እንደ ተስፋ የሚቆጠር ታሪካዊ ማስታወሻ ሲሆን ኬፕ ቨርዴ ግን ከጋና የ2006 ጉዞ በኋላ ወደ ቀጣዩ ዙር የምታልፍ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት አገር የመሆን ዕድሏን በከፍተኛ ደረጃ አሳድጋለች።
#የዓለምዋንጫ #ኬፕቨርዴ #ስፔን #እግርኳስ #ስፖርት #አፍሪካ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Sponsored by
Surafel
2 months ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) በዓለም ዋንጫው ሀያሏን ስፔን ያለምንም ግብ (0-0) አቻ ያሰረችው ኬፕ ቨርዴ በፈጠረችው ታሪካዊ ክስተት የዓለምን ትኩረት መሳቧን ቀጥላለች። ይህን አስገራሚ ውጤት ተከትሎ፣ የቀድሞው የቶተንሃም እና የአውስትራሊያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አንጅ ፖስቴኮግሉ ለተጫዋቾቹ ያላቸውን ጥልቅ አድናቆት ገልጸዋል።
አሰልጣኙ በእንግሊዙ አይቲቪ (ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ በሰጡት ትንታኔ "የስፖርት እና በተለይም የእግር ኳስ ታላቅነት ያለው በቁጥር በማይሰሉ እና በዓይን በማይታዩ ስሜቶች ውስጥ ነው" ብለዋል። "ዛሬ የኬፕ ቨርዴ ተጫዋቾች በምንም ተአምር እጅ ላለመስጠት በውስጣቸው የነበራቸው ወኔ እጅግ አስገራሚ ነበር" በማለት የቡድኑን የልብ ጥንካሬ አወድሰዋል።
በእግር ኳስ ትንታኔ ውስጥ የሚታየውን ክፍተት ሲያብራሩም "እኛ ጨዋታዎችን በወረቀት ላይ ስንተነትን ስፔን በቀላሉ ታሸንፋለች ብለን መደምደማችን አይቀርም፤ ነገር ግን እነዚያ የኬፕ ቨርዴ ተጫዋቾች በልባቸው ውስጥ ያዘሉትን ጥልቅ ስሜት እና ወኔ ከግምት ውስጥ አናስገባም" ብለዋል።
ፖስቴኮግሉ የዚህን የአቻ ውጤት ትርጉም ከሜዳ ውጪ ሲገልጹ "አሁን የዚህች አነስተኛ ሀገር ዜጎች 'እኛ ከኬፕ ቨርዴ ነን' ብለው በኩራት የሚናገሩበት ጊዜ ላይ ደርሰዋል፤ ከዛሬ ጀምሮ መላው ዓለም ማንነታቸውን አውቆላቸዋል" በማለት ታሪካዊቷ ምሽት ለሀገሪቱ ያመጣችውን ትልቅ የገጽታ ግንባታ መስክረዋል።

ሻምፒዮኑ አርሰናል ሲያሸንፍ፣ ዌስትሀም ወረደ ቶተንሀም ተረፈ
ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የዘለቀው የመድፈኞቹ የዋንጫ ጥማት ዛሬ በደመቀ ሁኔታ ተቋጭቷል።
አርሰናል በ38ኛው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታው ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሊጉን የክብር አክሊል ይረከባል።
በመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ገብርኤል ጀሱስ ያስቆጠራት ግብ የድሉን መንገድ የጠረገች ሲሆን፤ ቡድኑ እስከ ጨዋታው ፍጻሜ ድረስ ብቃቱን በማስመስከር የለንደን ጎዳናዎችን በደስታ እና በእልልታ እንዲሞሉ አድርጓል።
በሌሎች የዛሬው የመጨረሻ ሳምንት መርሃ ግብሮች ማንቸስተር ሲቲ በአስቶን ቪላ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ሲሸነፍ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ ብራይተንን 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ረቷል።
ዌስትሃም ሊድስን በ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ቢያሸንፍም ወደታችኛው ሊግ ወርዷል።
ቶተንሃም ኤቨርተንን 1 ለ 0 አሸንፎ በሊጉ መቆየት ችሏል።
በሌላ በኩል ሊቨርፑል ከብሬንትፎርድ ጋር 1 ለ 1፣ ፉልሃም ኒውካስትልን 2 ለ 0፣ ሰንደርላንድ ቼልሲን 2 ለ 1 በማሸነፍ ያልተጠበቀ ውጤት አስመዝግቧል።
በርንሌይ ከዎልቭስ እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት ከቦርንማውዝ ጋር 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት የውድድር ዘመኑን አጠናቀዋል።
Seledadotio

መድፉ ተተኮሰ
#ethiopia | የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ፍጻሜ አርሰናል በድል ሲያጠናቅቅ ቶተንሃም በሊጉ መትረፉን አረጋግጧል ማንችስተር ሲቲ ደግሞ ሽንፈት አስተናግዷል
የ2025/26 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን ዛሬ በአንድ ሰዓት በተደረጉ አስር ጨዋታዎች ፍጻሜውን አግኝቷል።
ከ22 ዓመታት ረጅም ጥበቃ በኋላ የሊጉን ዘውድ የደፋው አርሰናል ወደ ክሪስታል ፓላስ ሜዳ በመጓዝ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
ለመድፈኞቹ የማሸነፊያ ግቦቹን ያስቆጠሩት ጋብርኤል ጄሱስ እና ኖኒ ማዱኤኬ ሲሆኑ ክለቡ የዓመቱን ጉዞ በ85 ነጥብ በበላይነት አጠናቋል።
ወደ ታችኛው ክፍል የመውረድ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ የነበረው ቶተንሃም ሆትስፐርስ ኤቨርተንን 1 ለ 0 በማሸነፍ በሊጉ መቆየቱን አረጋግጧል።
ለለንደኑ ክለብ ወሳኟን የህልውና ግብ ያስቆጠረው ጆአኦ ፓልሂንሃ ነው። በሌላ በኩል ላለመውረድ ሲፋለም የነበረው ዌስትሃም ዩናይትድ ሊድስ ዩናይትድን 3 ለ 0 ቢያሸንፍም ከውድድር መውረዱን ሊያስቀር አልቻለም።
ክለቡ ከቶተንሃም በሁለት ነጥብ በማነሱ ምክንያት በርንሌይ እና ዎልቭስን ተከትሎ ወደ ቻምፒየንሺፕ ወርዷል።
ከማንችስተር ሲቲ ጋር ለመለያየት የወሰነው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በመጨረሻው የሊግ ጨዋታው በአስቶንቪላ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ሽንፈት ገጥሞታል።
ታዋቂ ተጫዋቾቹን ሞሐመድ ሳላህ እና አንዲ ሮበርትሰንን በክብር ያሰናበተው ሊቨርፑል ከብሬንትፎርድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በአቻ ውጤት አጠናቋል።
ለአሰልጣኝ ማይክል ካሪክ የአንድ ዓመት ተጨማሪ ውል ያበረከተው ማንችስተር ዩናይትድ ብራይተንን ከሜዳው ውጪ 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል።
በዚህ ጨዋታ ላይ አንድ ግብ አስቆጥሮ ለሌላው ደግሞ አመቻችቶ ያቀበለው ብሩኖ ፈርናንዴዝ አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል። ፖርቹጋላዊው አማካይ በአንድ የውድድር ዓመት ውስጥ 21 ግብ የሆኑ ኳሶችን በማመቻቸት ቀዳሚው ተጫዋች መሆን ችሏል።
ወደ ሊጉ በቅርቡ ያደገው ሰንደርላንድ ቼልሲን 2 ለ 1 በማሸነፍ በቀጣዩ ዓመት በአውሮፓ መድረክ ላይ የመሳተፍ መብቱን አግኝቷል።
በተያያዙ ዜናዎች ፉልሃም ኒውካስትል ዩናይትድን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ ኖቲንግሃም ፎረስት ከቦርንማውዝ ጋር 1 ለ 1 ተለያይቷል።
ቀድመው መውረዳቸውን ያረጋገጡት በርንሌይ እና ዎልቭስ ያደረጉት ጨዋታም በተመሳሳይ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።
#የእንግሊዝፕሪምየርሊግ #አርሰናል #ቶተንሃም #ማንችስተርሲቲ #ማንችስተርዩናይትድ #ሊቨርፑል #እግርኳስ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ዌስትሃም ዩናይትድ ከ14 ዓመታት በኋላ ከፕሪሚየር ሊጉ ወረደ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዌስትሃም ዩናይትድ ከ14 ዓመታት በኋላ ወልቭስ እና በርንሌይን ተከትሎ ከፕሪሚየር ሊጉ ወርዷል።
በፈረንጆቹ 2012/13 የውድድር ዓመት ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደገው የለንደኑ ክለብ ወደ ሻምፒዮንሺፕ ተሰናብቷል።
በውድድር ዓመቱ አብዛኛውን ጊዜ ከሊጉ ላለመውረድ ሲጫወት የነበረው ቶተንሃም በሊጉ መቆየቱን አረጋግጧል።
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዌስትሃም ዩናይትድ ከ14 ዓመታት በኋላ ወልቭስ እና በርንሌይን ተከትሎ ከፕሪሚየር ሊጉ ወርዷል።
በፈረንጆቹ 2012/13 የውድድር ዓመት ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደገው የለንደኑ ክለብ ወደ ሻምፒዮንሺፕ ተሰናብቷል።
በውድድር ዓመቱ አብዛኛውን ጊዜ ከሊጉ ላለመውረድ ሲጫወት የነበረው ቶተንሃም በሊጉ መቆየቱን አረጋግጧል።
Sponsored by
Surafel
2 months ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ታሪክ ከባህር ማዶ መጥቶ እንደ ግብጹ "የአባይ ውሃ ዘመዳችን" መሀመድ ሳላህ የጎል መረብን ያንቀጠቀጠ የለም፤ 193 የማይታመኑ ጎሎች! ታሪኩ የሚጀምረው ነሐሴ 12 ቀን 2017 ነው። ሊቨርፑል ዋትፎርድን ሲገጥም፣ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ አዲስ ፈራሚውን «ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንኳን በደህና መጣህ!» በሚል አጭርና ግልጽ መልዕክት ወደ ሜዳ ሰደዱት። ያኔ የተጠነሰሰው አስፈሪው የሳላህ፣ ማኔ እና ፊርሚኖ የአጥቂ መስመር ጥምረት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላን ጭምር «ያናውጡኛል፣ አደገኞች ናቸው» እስኪል ድረስ ዓለምን ጉድ አሰኝቷል።
ሳላህ እና ማኔ የቅርብ ጓደኛሞች ባይሆኑም፣ በመካከላቸው የነበረው ጤናማ ውድድር እና ፊርሚኖ በሁለቱ መሀል የሚነሳውን እሳት በማጥፋት የተጫወተው ሚና፣ የሊቨርፑልን የድል ጉዞ የጀርባ አጥንት ሆኗል። የቡድኑ አጋሮቹ «ለእግር ኳስ የተፈጠረ» ብለው የሚመሰክሩለት ሳላህ፣ በምሳሌነት የሚመራ [ይላል] እና ለዝርዝር ነገሮች ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ ጽኑ ተዋጊ ነው። ዋትፎርድን 5 ለ 0 ባሸነፉበት ጨዋታ ላይ፣ ጨዋታው እንደተጠናቀቀ ግብ ጠባቂውን ቤን ፎስተርን «ፍጹም ቅጣት ምት ቢሆን ኖሮ ወደየትኛው አቅጣጫ ትዘል ነበር?» ብሎ መጠየቁ ለስራው ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።
በአንፊልድ ቆይታው አንዳንዴ ተስፋ መቁረጥ እና ቁጣ ታይቶበት ያውቃል። ባለፈው ታህሳስ ከዋና አሰልጣኙ አርኔ ስሎት ጋር የነበረው አለመግባባት አሁን ላለው ስንብት መነሻ ሆኗል። ይህ የውድድር ዘመን ለሊቨርፑል ስብስብ እጅግ ከባድ የነበረ ሲሆን፣ የቡድን አጋሩ ዲዮጎ ጆታ ህይወት ማለፍ ሳላህን ክፉኛ ጎድቶታል። «ከእረፍት በኋላ ወደ ሊቨርፑል መመለስ እንደዚህ ያስፈራኛል ብዬ አስቤ አውቅም» ሲል ሀዘኑን ገልጾ፣ በአንፊልድ ፊት እምባውን በማፍሰስ ሰብዓዊነቱን አሳይቷል።
በሜዳ ላይ ግን ሳላህ ከተፈጥሮ በላይ ነበር። በአንፊልድ የመጀመሪያ የውድድር ዘመኑ 58 የጎል ተሳትፎዎችን (በየ 71 ደቂቃው አንድ ጎል ላይ ተሳትፎ) በማድረግ ሜሲ እና ሮናልዶ ካሉበት ደረጃ ደርሷል። ማድሪድ ላይ ቶተንሃምን አሸንፈው የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ሲያነሱ፣ በጉዲሰን ፓርክ ኤቨርተን ላይ የፑስካስ አዋርድ ያሸነፈባትን ጎል ሲያገባ፣ እና በኦልድ ትራፎርድ ማንችስተር ዩናይትድ ላይ ያሳየው ጀብዱ... ትዝታዎቹ ማለቂያ የላቸውም። የሲቲው አይሜሪክ ላፖርት ጭምር «ሳላህ በእኛ ላይ ሁልጊዜ እሳት ይተፋ ነበር፤ ለመከላከል ከገጠሙኝ ከባድ ተጫዋቾች አንዱ ነው» በማለት ይመሰክራል።
ሸሚዙን አውልቆ ደስታውን ሲገልጽም ሆነ በሱጁድ ፈጣሪውን ሲያመሰግን፣ የሳላህ ምስሎች መቼም አይረሱም። የቀድሞው አምበል ስቲቨን ጀራርድ «ቁጥሮቹ፣ ዋንጫዎቹ እና የገነባው ባህል የራሳቸው ታሪክ ይናገራሉ። መሀመድ ሳላህ በሁላችንም ዘንድ የተወደደ የክለቡ እውነተኛ ጀግና ነው» ሲል አወድሶታል። ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድም ለክለቡ ያላቸውን ዋጋ ሲገልጽ ሳላህን እና ጀራርድን በእኩልነት አንደኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧቸዋል።
የ2024-25 የውድድር ዘመን ሊቨርፑል 20ኛውን የሊግ ዋንጫ ሲያነሳ፣ ሳላህ ከፍተኛ ጎል እና አሲስት በማድረግ በእንግሊዝ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ደማቅ አሻራ አሳርፏል። አሁን ግን ሁሉም ነገር ፍጻሜ አለው። ከግብጽ የናይል ዴልታ የተነሳው የዚህ ድንቅ ተዋጊ ጉዞ፣ በሜርሲሳይድ አንፊልድ ላይ የማይረሳ ታሪክ ጽፎ ወደሚቀጥለው ምዕራፍ ተሸጋግሯል። የርገን ክሎፕ እንዳሉት፣ «ሲመጣ ሰዎች ምን እንደሚያስቡ ሳይሆን፣ ሲሄድ ምን እንደሚያስቡ ማወቁ ነው ትልቁ ነገር»። መሀመድ ሳላህ... ለአንፊልድ ትክክለኛው ተዋጊ፣ በትክክለኛው ጊዜ የመጣው ጀግና!

3 months ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ለንደኑ ታላቅ ደርቢ በቼልሲ የ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል። በጨዋታው ላይ የቼልሲው ኤንዞ ፈርናንዴዝ ድንቅ ግብ ያስቆጠረ ሲሆን፣ ቶተንሃሞች በርካታ የግብ ዕድሎችን ሳይጠቀሙ ቀርተዋል። ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ክለቦች አሰልጣኞች ለስካይ ስፖርትስ አስተያየት ሰጥተዋል።
ከሽንፈቱ በኋላ የተናገሩት የቶተንሃሙ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዴ ዜርቢ፣ ቡድናቸው የተሻለ ተንቀሳቅሶ እንደነበር ገልጸዋል።
"በማቲስ ቴል አማካኝነት የመጀመሪያውን የግብ ዕድል ፈጥረን ነበር፤ ነገር ግን የቼልሲው ግብ ጠባቂ ሳንቼዝ አስደናቂ ብቃት አድኖታል። በመቀጠል ታላቅ ተጫዋች በሆነው በኤንዞ ፈርናንዴዝ አማካኝነት ግሩም ግብ ተቆጠረብን፤ በዚያች ግብ ላይ ከዚህ የተሻለ መከላከል እንችል ነበር። ሁለተኛውን ግብ እስክናስተናግድ ድረስ ግን በጨዋታው ውስጥ በጥሩ ሁኔታ ቆይተን ነበር። ሁለተኛውን ግብ ያስተናገድነው ሞኝነት በሞላበት ሁኔታ ኳስ በመንጠቃችን ነው፤ ነገር ግን ያ ግብ ከመቆጠሩ በፊት በሪሻርሊሰን አማካኝነት በጣም ትልቅ የግብ ዕድል ፈጥረን ነበር።"
አሰልጣኙ አክለውም፦ "በእኔ እምነት በጣም ጥሩ ጨዋታ ነው የተጫወትነው፤ ምንም እንኳን ብንሸነፍም። አሁን ግን ስለዚሁ ጨዋታ ብዙ የምናስብበት ጊዜ አይደለም። ትኩረታችንን ወደ ቀጣዩ ጨዋታ ማዞር አለብን። ቀጣዩን ጨዋታ በራሳችን ስታዲየም ከደጋፊዎቻችን ፊት ነው የምናደርገው። ባለን አቅም፣ በባህሪያችን፣ በኩራታችን እና በታላቅ ወኔ መጫወት ይኖርብናል። ዛሬ ባሳየነው ጥሩ ጨዋታ ምክንያት ለቀጣዩ ተስፋዬ ከፍተኛ ነው" ብለዋል።
የቼልሲው ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝ ካለም ማክፋርሌን በበኩላቸው፣ ቡድናቸው ካለበት የድካም ስሜት አንጻር ያስመዘገበው ድል ትልቅ መሆኑን ጠቅሰዋል።
"አንዳንድ ጊዜ ጨዋታው ማራኪ አልነበረም፤ ሜዳ ላይ የታየውም ይሄው ነበር። ነገር ግን በዚህ ቡድን ላይ ቀደም ሲል ጥያቄ ምልክት ይነሳበት የነበረውን ያንን ጠንካራ ፍላጎት እና ቁርጠኝነት ዛሬ ማሳየት ነበረብን። በጉልበትም ሆነ በጨዋታ ፍጥነት እነሱን ማሸነፍ እንደማንችል እናውቅ ነበር። ምክንያቱም ከተጫዋቾቻችን መካከል አንዳንዶቹ አሁንም ድረስ የዌምብሊው ጨዋታ ድካም እንዳልለቀቃቸው ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ በግልጽ ይታይ ነበር።"
ማክፋርሌን የቶተንሃምን የዕረፍት ጊዜ በመጥቀስ ሲናገሩ፦ "የእነሱ የመጨረሻ ጨዋታ መቼ እንደነበረ አላውቅም፤ ግን እንደ እኛ ቅዳሜ ዕለት እንዳልነበረ እርግጠኛ ነኝ። ስለዚህ የተሻለ ጉልበት ነበራቸው። የእኛ ልጆች ግን በዌምብሊው ጨዋታ ከአውሮፓ ምርጥ ከሚባሉ ቡድኖች አንዱ ጋር እልህ አስጨራሽ ትግል አድርገው የመጡ ናቸው። ዛሬ የሁለት ግቦች መሪነት አግኝተን በጥሩ ሁኔታ መከላከል ችለናል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በገዛ ደጋፊዎቻችን ፊት በበቂ ሁኔታ ማሸነፍ አልቻልንም ነበር፤ ስለዚህ ይህ ድል ትልቅ ነው" ሲሉ አብራርተዋል።

የዋንጫው ባለቤት ዛሬ ይታወቃል ወይስ…
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዘንድሮው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ባለቤት የሚሆነውን ክለብ ሊወስን የሚችለው የቦርንማውዝ እና ማንቼስተር ሲቲ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይደረጋል፡፡
ማንቼስተር ሲቲ የምሽቱን ጨዋታ አቻ ካጠናቀቀ ወይም ሽንፈት ካስተናገደ አርሰናል አንድ ጨዋታ እየቀረው የ2025/26 ሻምፒዮን መሆኑን ዛሬ ምሽት ያረጋግጣል፡፡
ማንቼስተር ሲቲ የዋንጫ ተስፋውን እስከ መጨረሻው ሳምንት ለማስቀጠል የምሽቱን ጨዋታ የማሸነፍ ግዴታ ውስጥ ገብቷል፡፡
በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከሲቲ ጋር እንደሚለያዩ የሚጠበቁት ፔፕ ጋርዲዮላ በምሽቱ ጨዋታ የሚጠቀሙት ቋሚ አሰላለፍ ይፋ ሆኗል፡፡
ጂያንሉጂ ዶናሩማ፣ ማቲያስ ኑኔዝ፣ ኩሳኖቭ፣ ማርክ ጉሂ፣ ኒኮ ኦ'ሬሊ፣ ሮድሪ፣ ኮቫቺች፣ በርናርዶ ሲልቫ፣ ሴሜንዮ፣ ዶኩ እና ሀላንድ በቋሚነት ወደ ሜዳ ይገባሉ፡፡
ባለሜዳው ክለብ በርንማውዝ ፔትሮቪች፣ ትሩፌርት፣ ሴኔሲ፣ ስኮት፣ ኢቫኒልሰን፣ አዳምስ፣ ስሚዝ፣ ታቨርኔር፣ ክሩፒ ጁኒየር፣ ሂል እና ራያንን በቋሚ አሰላለፍ ይጠቀማል፡፡
ጨዋታው ምሽት 3 ሰዓት ከ30 የሚጀመር ሲሆን፥ የ47 ዓመቱ አንቶኒ ቴይለር በመሃል ዳኝነት ይመሩታል፡፡
በሌላ ጨዋታ በለንደን ደርቢ ቼልሲ በሊጉ ለመቆየት 1 ነጥብ የሚፈልገውን ቶተንሃም ሆትስፐር ምሽት 4 ሰዓት ከ15 በስታምፎርድ ብሪጅ ያስተናግዳል፡፡

ኒውካስል ዌስትሃምን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ37ኛው ሳምንት እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኒውካስል ዩናይትድ ዌስትሃምን 3 ለ 1 አሸንፏል።
ከሰሜን ለንደኑ ቡድን ቶተንሃም ጋር እየተፎካከረ የሚገኘው ዌስትሃም በፕሪሚየር ሊጉ የመቆየት ዕድሉን ያጠበበ ሽንፈት በኒውካስል ዩናይትድ አስተናግዷል።
ዊሊያም ኦሱላ (ሁለት) እና ኒክ ዋልትማደ የኒውካስልን ግቦች ሲያስቆጥሩ፥ ታቲ ካስቴላኖስ የዌስትሃምን ብቸኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል።
በዚህ መሰረት ቶተንሃም ማክሰኞ ዕለት ከቼልሲ የሚያደርገውን ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለ ዌስትሃም ዩናይትድ መውረዱን የሚያረጋግጥ ይሆናል።
ቀደም ብለው በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ማንቼስተር ዩናይትድ ኖቲንግሃም ፎረስትን 3 ለ 2፣ ሰንደርላንድ እና ኤቨርተንን 3 ለ 1፣ ሊድስ ዩናይትድ ብራይተንን 1 ለ 0 አሸንፈዋል።
እንዲሁም ብሬንትፎርድ ከክሪስታል ፓላስ 2 ለ 2 እንዲሁም ወልቭስ ከፉልሃም 1 ለ 1 ተለያይተዋል።

ማንቼስተር ሲቲ ወይስ ቼልሲ - ተጠባቂው የፍጻሜ ጨዋታ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ሲቲን ከቼልሲ የሚያገናኘው የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ በዌምብሌይ ስታዲየም ይደረጋል፡፡
በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመራው ማንቼስተር ሲቲ በግማሽ ፍጻሜው ሳውዛምፕተንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜ መብቃቱ ይታወሳል፡፡
ማንቼስተር ሲቲ የዘንድሮውን ጨምሮ ያለፉትን አራት ተከታታይ ዓመታት በኤፍ ኤ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ መገኘት ችሏል፡፡
ሆኖም ካለፉት ሦስት የኤፍ ኤ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንዱን ብቻ ሲሆን፥ ለመጨረሻ ጊዜ የዋንጫው ባለቤት የሆነው በፈረንጆቹ 2023 ነበር፡፡
ማንቼስተር ሲቲ በታሪኩ ሰባት ጊዜ የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን ማሳካት የቻለ ሲሆን፥ ለስምንተኛ ጊዜ ሻምፒዮን ለመሆን የሚያደርገው ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
አስቀድሞ የካራባኦ ዋንጫን ያሳካው ሲቲ በዚህ የውድድር ዓመት 2ኛ ዋንጫውን ፍለጋ ወደ ሜዳ ይገባል፡፡
በውድድር ዓመቱ የሦስትዮሽ ዋንጫ የማሳካት እድል ያለው ማንቼስተር ሲቲ ጉዞውን አጠናክሮ ለመቀጠል ይፋለማል፡፡
እስካሁን አሸናፊው ባልተለየበት የሊጉ የዋንጫ ፉክክር ውስጥ የሚገኘው ማንቼስተር ሲቲ ይህንን ዋንጫ ማሳካት ከቻለ የሦስትዮሽ ዋንጫ ጉዞውን እንደሚያጠናክርለት ይታመናል፡፡
ተጋጣሚው ቼልሲ በበኩሉ በግማሽ ፍጻሜው ሊድስ ዩናይትድን በኢንዞ ፈርናንዴዝ ብቸኛ ግብ በመርታት ለፍጻሜ መድረሱ አይዘነጋም፡፡
በታሪኩ ስምንት ጊዜ የኤፍ ኤ ዋንጫን ማሳካት የቻለው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ለ9ኛ ጊዜ በመድረኩ ሻምፒዮን ለመሆን ይፋለማል፡፡
አሰልጣኞች ቢለዋውጥም መሻሻል ያልቻለው ቼልሲ የውድድር ዓመቱን ያለምንም ዋንጫ ላለማጠናቀቅ ብርቱ ፉክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ለመጨረሻ ጊዜ የኤፍ ኤ ዋንጫን ማሳካት የቻለው በፈረንጆቹ 2018 እንደነበር ይታወሳል፡፡
ከዚያ ወዲህ ቼልሲ በ2021 እና በ2022 የፍጻሜ ተፋላሚ መሆን ቢችልም ዋንጫውን ግን ማሳካት አልቻለም፡፡
በ1871/72 በጀመረው የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ዋንጫ ውድድር አርሰናል 14 ጊዜ የዋንጫው ባለቤት በመሆን ቀዳሚው ሲሆን፥ ማንቼስተር ዩናይትድ 13 ጊዜ በመድረኩ ሻምፒዮን በመሆን ይከተላል፡፡
የዛሬ የፍጻሜ ተፋላሚው ቼልሲ፣ ሊቨርፑል እና ቶተንሃም ሆትስፐር በተመሳሳይ ስምንት ጊዜ ሻምፒዮን ሆነዋል፡፡
ሌላኛው የምሽቱ የፍጻሜ ተፋላሚ ማንቼስተር ሲቲ እንዲሁም አስቶንቪላ በተመሳሳይ ሰባት ጊዜ የኤፍ ኤ ዋንጫን በማንሳት በርካታ ጊዜ ሻምፒዮን ከሆኑ ቡድኖች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
በዌምብሌይ ስታዲየም አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ የሚደረገውን ተጠባቂ የፍጻሜ ጨዋታ እንግሊዛዊው ዳኛ ዳረን ኢንግላንድ በመሐል ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል፡፡

በሊጉ የዋንጫ ፉክክር ውስጥ ለመቆየትና ላለመውረድ የሚደረጉ ተጠባቂ የሊጉ ጨዋታዎች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ36ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ በሚደረጉ አምስት ጨዋታዎች መደረግ ይጀምራል፡፡
ቀን 8 ሰዓት 30 ላይ ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ሮድ ቼልሲን የሚያስተናግድበት መርሐ ግብር የዕለቱ ቀዳሚ ጨዋታ ነው፡፡
ሁለቱም ቡድኖች በአውሮፓ መድረክ የሚያሳትፋቸውን ውጤት ይዘው የውድድር ዓመቱን ለማጠናቀቅ እየተፋለሙ ይገኛል፡፡
በሊጉ ከሦስት ተከታታይ ድል በኋላ በሳምንቱ መጨረሻ በማንቼስተር ዩናይትድ ሽንፈት ያስተናገደው ሊቨርፑል ወደ ድል ለመመለስ ወደ ሜዳ ይገባል፡፡
ያለፉትን ስድስት ተከታታይ ጨዋታዎች በሊጉ የተሸነፈው ቼልሲ ወደ ድል ለመምጣት የሚያደርገው ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
ቼልሲ በዛሬው ጨዋታ በሊቨርፑል የሚሸነፍ ከሆነ ከ74 ዓመታት በኋላ ሰባት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎችን የሚሸነፍ ይሆናል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች እርስበርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ሊቨርፑል በሦስቱ ሲያሸንፍ ቼልሲ በሁለቱ ድል አድርጓል፡፡
አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ ማንቼስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ከሰንደርላንድ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎውን ያረጋገጠው ማንቼስተር ዩናይትድ በሊጉ አራተኛ ተከታታይ ድሉን ለማሳካት ይፋለማል፡፡
ሰንደርላንድ በበኩሉ ከተከታታይ ሦስት ጨዋታዎች ድል አልባ ጉዞ በኋላ ወደ ድል ለመመለስ ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች እርስበርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ማንቼስተር ዩናይትድ አራቱን በማሸነፍ የበላይነቱን ሲይዝ ሰንደርላንድ በአንዱ ድል አድርጓል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት ፉልሃም ከቦርንማውዝ እንዲሁም ብራይተን ከወልቭስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ምሽት 1 ሰዓት 30 ላይ ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ኢትሃድ ከብሬንትፎርድ የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
በ35ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር ነጥብ የጣለው ማንቼስተር ሲቲ የዋንጫ ፉክክሩን ለማጠናከር ይፋለማል፡፡
ማንቼስተር ሲቲ የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ አርሰናል ነገ ምሽት ጨዋታውን እስከሚያደርግ ድረስ የነጥብ ልዩነቱን ወደ ሁለት ማጥበብ ይችላል፡፡
የሊጉ ጨዋታ ነገ ሲቀጥል የሊጉ መሪ አርሰናል ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ምሽት 12 ሰዓት 30 ላይ ከዌስትሃም ዩናይትድ ጋር ይጫወታል፡፡
የሊጉ መሪ አርሰናል መሪነቱን ለማጠናከር እና ዋንጫውን ለማንሳት የሚያደርገውን ጉዞ አጠናክሮ ለመቀጠል ይፋለማል፡፡
ተጋጣሚው ዌስትሃም ዩናይትድ በበኩሉ ላለመውረድ የሚያደርገው ብርቱ ፉክክር ተጠባቂ ነው፡፡
ኖቲንግሃም ፎረስት ከኒውካስል ዩናይትድ፣ ክሪስታል ፓላስ ከኤቨርተን እንዲሁም በርንሌይ ከአስቶንቪላ በዕለቱ በተመሳሳይ ሰዓት ቀን 10 ሰዓት ላይ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው፡፡
የ36ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር ሰኞ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ቶተንሃም ሆትስፐር ከሊድስ ዩናይትድ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጠናቀቃል፡፡
ሊጉን አርሰናል በ76 ነጥብ ሲመራ ማንቼስተር ሲቲ 71፣ ማንቼስተር ዩናይትድ 64 እንዲሁም ሊቨርፑል በ58 ነጥብ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
ኤርሊንግ ብራውት ሃላንድ በ25 ግቦች የሊጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ደረጃ ሲመራ ኢጎር ቲያጎ በ22 ግቦች ይከተላል፡፡

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌ ላይ አንዣብቦ የነበረው ጥቁር ደመና በድንገት ተገፎ፣ በቪላ ፓርክ ስታዲየም ብሩህ ተስፋ ፈንጥቋል። አዲሱ የቶተንሃም ሆትስፐር አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዴ ዘርቢ የጀመሩት "የነፍስ አድን ዘመቻ" ዛሬ ምሽት እጅግ አስደናቂ የሆነ ፍሬ አፍርቷል። ስፐርስ አስቶን ቪላን በገዛ ሜዳው ድባቅ በመምታት፣ ከወራጅ ቀጠናው ራሳቸውን ማላቀቅ የቻሉበትን ወሳኝ ድል ተቀዳጅተዋል።
ዌስትሃም ቅዳሜ ዕለት በብሬንትፎርድ መሸነፉ ለቶተንሃም የደረጃ መሻሻል በር ከፍቶላቸው ነበር። ስፐርስ ደግሞ ይህንን ወርቃማ ዕድል በዝምታ አላሳለፉትም። ምንም እንኳን ቁልፍ አጥቂዎቻቸው ሻቪ ሲሞንስ እና ዶሚኒክ ሶላንኬ በጉዳት ባይሰለፉም፣ በሜዳው ላይ የታየው መንፈስ ግን እጅግ አስፈሪ ነበር።
ጨዋታው እንደተጀመረ በ12ኛው ደቂቃ ላይ ኮኖር ጋላገር ከአትሌቲኮ ማድሪድ ወደ ለንደን ከተዛወረ በኋላ የመጀመሪያውን ግብ ከመረብ አሳረፈ። ከ20 ያርድ ርቀት ላይ በለሰለሰ አጨራረስ ያስቆጠራት ግብ ስፐርስን ቀድመው እንዲመሩ አደረገቻቸው። በ25ኛው ደቂቃ ላይ ደግሞ ብራዚላዊው አጥቂ ሪቻርሊሰን ከማቲያስ ቴል የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ በመገጨት የቪላውን ግብ ጠባቂ ኤሚ ማርቲኔዝን አሳፍሮ የዩናይትድን መሪነት ወደ ሁለት አሳደገ። ሪቻርሊሰን በስታዲየሙ የነበረውን ጥብቅ መከላከያ ሲያናውጥ፣ አማካዮቹ ፓልሂንሃ እና ሮድሪጎ ቤንታንኩር ደግሞ የሜዳውን መሃል በብረት አጥር አጥረውት ነበር።
ለአስቶን ቪላው አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ ግን ምሽቱ የውሳኔ ስህተት የታየበት ነበር። በዩሮፓ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ያለባቸውን ጨዋታ ታሳቢ በማድረግ፣ በቋሚ ስብስባቸው ላይ ሰባት ለውጦችን ማድረጋቸው ቡድኑን ለሽንፈት ዳርጎታል። የቪላ ደጋፊዎች በቡድናቸው ደካማ አፈፃፀም ተበሳጭተው በመጀመሪያው አጋማሽ ማጠቃለያ ላይ በፉጭት ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ተደምጠዋል።
ምንም እንኳን በጨዋታው መጠናቀቂያ ላይ ኤሚ ቡዌንዲያ አንዲት ግብ ቢያስቆጥርም፣ ለቪላው ተስፋ ግን "ከረፋዱ በኋላ የመጣ ዝናብ" ሆኖባቸዋል። ቶተንሃም በዴ ዘርቢ ስር በራስ መተማመናቸው ተመልሶ፣ በቪላ ደጋፊዎች ጩኸት ታጅበው የድል ዋንጫቸውን ጨብጠዋል።
ይህ ድል ቶተንሃምን ከዌስትሃም በአንድ ነጥብ ልቆ እንዲቀመጥ ያደረገ ሲሆን፣ ለዴ ዘርቢም በክለቡ ቋሚ የኮንትራት ጥያቄ እንዲቀርብላቸው ትልቅ ግፊት ፈጥሯል። ስፐርስ በቀጣይ ሰኞ ግንቦት 3 (May 11) ሌላኛው ወሳኝ ጨዋታቸውን ከሊድስ ዩናይትድ ጋር የሚያደርጉ ይሆናል። አስቶን ቪላ በበኩሉ የፊታችን ሐሙስ በዩሮፓ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ መልስ ጨዋታ ኖቲንግሃም ፎረስትን የሚያስተናግድ ይሆናል።

ማንችስተር ዩናይትድ ከ ሊቨርፑል
************
በ35ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፣ ዛሬ 11 ሰዓት ከ30 ላይ ማንችስተር ዩናይትድ እና ሊቨርፑል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። ትላንት በተደረገው ጨዋታ ብራይተን በኒውካስትል ዩናይትድ መሸነፉን ተከትሎ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎውን ያረጋገጠው ማንችስተር ዩናይትድ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎውን ለማረጋገጥ ከሚታገለው ሊቨርፑል ይጫወታል፡፡
ከዩናይትድ በሦስት ነጥብ ዝቅ ብሎ በ58 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው የመርሲሳይዱ ክለብ፣ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎውን በይፋ የሚያረጋግጥ ይሆናል። ዩናይትድ ከሊቨርፑል ጋር በተገናኘባቸው ያለፉት 19 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው ሦስቱን ብቻ ሲሆን፣ በኦልድ ትራፎርድ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎችም በሦስቱ ተሸንፏል፡፡
ማይክል ካሪክ ሩብን አሞሪምን ተክቶ ወደ ኦልድ ትራፎርድ ከመጣ በኋላ፣ እንደ እሱ ብዙ ነጥብ የሰበሰበ አሰልጣኝ በሊጉ የለም። ለዛሬው ጨዋታ ማቲያስ ኩኛ ከጉዳቱ በማገገሙ ሊሰለፍ ይችላል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ሉክ ሾውም በተመሳሳይ ወደ ሜዳ ሊመለስ ይችላል። ሆኖም ማቲያስ ዴሊክት ልምምድ ቢጀምርም በዛሬው ስብስብ ውስጥ እንዳልተካተተ ማይክል ካሪክ አረጋግጠዋል።
በሊቨርፑል በኩል በርካታ የጉዳት ያሉ ሲሆን ግብ ጠባቂዎቹ አሊሰን ቤከር እና ጆርጂ ማማርዳሽቪል በጉዳት ከቡድኑ ውጭ በመሆናቸው፣ ሦስተኛው ግብ ጠባቂ ፍሬዲ ውድማን በቋሚነት የሚሰለፍ ይሆናል። በተጨማሪም ሞሃመድ ሳላህ፣ ሁጎ ኢኪቲኬ እና ኮኖር ብራድሊ በጉዳት ምክንያት ከዛሬው ስብስብ ውጭ ናቸው። ሁለቱ ክለቦች ዛሬ ለ244ኛ ጊዜ ይገናኛሉ፡፡
በሊጉ ለመቆየት እየታገለ የሚገኘው ቶተንሀም ሆትስፐር ምሽት 3 ሰዓት ላይ ከሜዳው ውጭ ከአስቶን ቪላ ጋር ይጫወታል። በ34 ነጥብ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው የሰሜን ለንደኑ ክለብ፣ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎን ለማግኘት ከሚታገለው አስቶን ቪላ ሌላ ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል።
ዌስትሃም ትላንት በብሬንትፎርድ መሸነፉን ተከትሎ፣ ቶተንሃም ዛሬ ካሸነፈ ከወራጅ ቀጠናው የመውጣት ዕድል ይኖረዋል። ሆኖም ስፐርስ ዛሬም እንደ ሞሃመድ ኩዱስ፣ ቤን ዴቪስ፣ ቪካሪዮ እና ክርስቲያን ሮሜሮ ያሉ ወሳኝ ተጫዋቾችን በጉዳት ምክንያት የማይጠቀም ይሆናል። በተጨማሪም 10 ሰዓት ላይ ቦርንማውዝ ከክሪስታል ፓላስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በአንተነህ ሲሳይ
#ethiopiabroadcastingcorporation #epl #manchesterunited #liverpool

አርሰናል ከተከታዩ ማንቼስተር ሲቲ በ6 ነጥብ ለመራቅ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ35ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርሰናል በሜዳው ኢምሬትስ ምሽት 1 ሰዓት 30 ላይ ፉልሃምን ያስተናግዳል፡፡
ሊጉን ከተከታዩ ማንቼስተር ሲቲ በሦስት ነጥብ ልዩነት እየመራ የሚገኘው አርሰናል ከዚህ በኋላ የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ለዋንጫው በሚያደርገው ጉዞ ውስጥ ወሳኝ ናቸው፡፡
የካራባኦ ካፕ ዋንጫ ያጣውና ከኤፍ ኤ ውድድር የተሰናበተው አርሰናል በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እና በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫውን ለማንሳት የሚያደርገው ጉዞ ይጠበቃል፡፡
በሊጉ ከተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች ሽንፈት በኋላ ባሳለፍነው ሳምንት ኒውካስል ዩናይትድን በማሸነፍ ወደ ድል የተመለሰው አርሰናል ተከታታይ ጨዋታ በሊጉ ድል ለማድረግ ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል፡፡
ተጋጣሚው ፉልሃም ከሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ድል አልባ ጉዞ በኋላ ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ድል የተመለሰ ሲሆን አሸናፊነቱን ለማስቀጠል ብርቱ ፉክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች አርሰናል በሁለቱ ሲያሸንፍ፥ ፉልሃም በአንዱ ድል አድርጎ በቀሪ ሁለት ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል፡፡
አርሰናል የዛሬ ምሽቱን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ ማንቼስተር ሲቲ ሰኞ ምሽት ጨዋታውን እስከሚያደርግ ድረስ የነጥብ ልዩነቱን ወደ ስድስት ከፍ ማድረግ ይችላል፡፡
መውረዱን አስቀድሞ ያረጋገጠው ወልቭስ ከሰንደርላንድ፣ ኒውካስል ዩናይትድ ከብራይተን እንዲሁም ብሬንትፎርድ ከዌስትሃም ዩናይትድ በተመሳሳይ አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ የሚደረጉ የዛሬ ጨዋታዎች ናቸው፡፡
ነገ የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል ማንቼስተር ዩናይትድ በሜዳው ኦልድትራፎርድ አመሻሽ 11 ሰዓት 30 ላይ ሊቨርፑልን ያስተናግዳል፡፡
ሁለቱም ቡድኖች የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ቦታን ለማግኘት እየተፋለሙ ይገኛሉ፡፡
ማንቼስተር ዩናይትድ የነገውን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ ቀሪ ጨዋታዎች እያሉት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎውን የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡
ባለሜዳው ቡድን ማንቼስተር ዩናይትድ በሊጉ ሦስተኛ ተከታታይ ድሉን ለማሳካት ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል፡፡
ሊቨርፑል በበኩሉ አራተኛ ተከታታይ ጨዋታውን ድል ለማድረግ የሚያደርገው ፍልሚያ ተጠባቂ ነው፡፡
ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ሊቨርፑል ሁለቱን ሲያሸንፍ ማንቼስተር ዩናይትድ በአንዱ ድል አድርጎ በቀሪ ሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል፡፡
በዕለቱ ቀን 10 ሰዓት ላይ ቦርንማውዝ ከክሪስታል ፓላስ እንዲሁም ምሽት 3 ሰዓት ላይ አስቶንቪላ ከቶተንሃም ሆትስፐር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
የ35ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሰኞ ምሽት በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጠናቀቃል፡፡
በዕለቱ ማንቼስተር ሲቲ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ከኤቨርተን ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡
የአርሰናልን ውጤት አይቶ የሚጫወተው ማንቼስተር ሲቲ ለዋንጫው የሚያደርገውን ፉክክር አጠናክሮ ለመቀጠል ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል፡፡
ከዚህ ጨዋታ አስቀድሞ ሰኞ ቀን 11 ሰዓት ቼልሲ ከሊጉ ላለመውረድ እየተፋለመ የሚገኘውን ኖቲንግሃም ፎረስት በስታምፎርድ ብሪጅ ያስተናግዳል፡፡

4 months ago
ወሳኙ የውድድር ምዕራፍ ላይ መደነቃቀፍ ጀምሯል
በኤፍሬም የማነ
#ethiopia | የፔፕ ጋርዲዮላ ማንቸስተር ሲቲ በምዕራብ ለንደን ቼልሲን በምቾት ረታ ። ሲቲ የመድፉ ዳግም የዋንጫ ውሰድልን ግብዣንም በክብር መቀበሉን የሊያም ሮዚነየር ቀዳዴ ሚስተር ቼልሲን 3ለ0 በገዛ ሜዳው አሸንፎ በፍጥነት አረጋገጠ ።
አንደኛ ሆኖ አንደኝነቱን ተጠራጥሮ ለለመደው ሁለተኝነት ጠንክሮ እየታታረ የሚገኘው አርሰናል ሰርቶ ሰርቶ ልፋቱን መና ማስቀረት ፀጋ በረከቱ ከመሰለው ደንጋጣው አሰልጣኙ ማይክ አርቴታ ጋር ዘንድሮም የክብር ሙሽራነቱን ዘንግቶ ለለመደው አጃቢ ሚዜነት ወሳኙ የውድድር ምዕራፍ ላይ መደነቃቀፍ ጀምራል ።
የመድፉ ከዋንጫ ፊት መሽኮርመምን በአግባቡ እየተጠቀመ የሚገኘው ሲቲም የተወው ዋንጫን መልሶ ካስታወሰው አርሰናል ለመፋጠጥ በፀና አቋም ከብሪጅ ታይቷል ። አሁን ጊዜ ተገልብጦ ለትሪብል ዋንጫ የሚጫወተው ማንቸስተር ሲቲም መስሏል ።
ከኳርዳፕል ወደ ትሪብል ! ከትሪብል ወደ ሁለት የተነነው የአርሰናል የዋንጫ ጉዞ ተስፋ አለቃ አርቴታን ይዞ አሁንም በእጅ ላይ የሚገኘው አንድ ታላቅ ዋንጫን በክብር ማጠናቀቁ ለመድፉ ደጋፊዎች እራሱ አጠራጣሪ መስሏል ።
ማንቸስተር ሲቲም የመድፉ መንሸራተትን በአግባቡ ለመጠቀም ያለ ጫና ቼልሲን በገዛ ሜዳው ዘርሮ የአርሰናል ዳግም ግብዣን በክብር እንደተቀበለ አረጋግጧል ። ኦሮየሊ ጉዊ እና ዶኩ የሲትዚንስ ጎሎች ባለቤት ሆነዋል ። የቼልሲው አሰልጣኝ ሊያም ሮዚነየር ቀዳዴም ከጨዋታ በፊት ይፎክራሉ ። ከጨዋታ በኋላ ፎጣ ጥለው ይዘረራሉ ። ይህ የሚስተር ቼልሲ አዲሱ ህይወት ሆኗል ።
ከብሪጅ ወጣቱ አሰልጣኝ ከመጡ የቀጠለ የሰሚያዎቹ ዝብርቅርቅ ህይወት ኤንዞ ማሬስካን መልሶ አስናፍቋል ። እንደ ወሬያቸው ውለው ማደር ያልቻሉት አሰልጣኝ ሊያም ሮዚኒየርም ከቼልሲ የቀደሙት አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ለምን እንደተባረሩ የተጨዋቾቻቸው የአደባባይ የለየለት ጥያቄ ጋር በቀደዳቸው ልክ መገኘት ተስኗቸው ቀጥለዋል ።
በsuper sunday ዶክተር ቶተንሃም ያው ዶክተር ቶተንሃም እንደሆነ ሰሚ ጠፋ እንጂ የተረጋገጠው ዕውነታ ነው ። አሰልጣኝ አበረረ ወይ ቀየረ እየዞረ ለተጋጣሚዎቹ እንደ ፍቱን መድሃኒት ውጤት ማከፋፈል ለዶክተር ቶተንሃም ኑሮው ነው ።
አዲሱ የፈረንጆቹ 2026 ከገባ አንስቶ ባለፉት 105 ቀናቶች አንድም ጨዋታ በሊጉ ያላሸነፈው ቶተንሃም የወራጅ ቀጠናው ቁልቁለቱንም እያፈጠነው ነው ። ተስፋ የተጣለበት የዶሮዋ አዳኝ እና የነገው ከፍታ ውጤት ቀያሽ እንደሚሆን ታምኖበት ሰሜን ለንደን የደረሰው አዲሱ አሰልጣኝ ሮቤሮቶ ዴዘርቢም በማይሆን ሰዐት ደፍሮ በተቀበለው ሃላፊነት ከስቴዲየም ኦፍ ላይት በሰንደርላንድ በሽንፈት ጀምሯል ።
ስፐርስም ሊጠናቀቅ በተቃረበው ገናና መድረክ የወራጅ ቀጠናው ዋና ሰብሳቢ እንደሆነ 6 ቀሪ ጨዋታዎች ብቻ በቀረው ሊግ 18ኛ ደረጃ ላይ በቀጭኑ መስመስር እንደቆመ አለ ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

"እኔ አሰልጣኝ እንጂ የጽዳት ሰራተኛ አይደለሁም" ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ
#ethiopia | የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ፣ ስለ 2026ቱ ዓለም ዋንጫ ዝግጅት እና ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ስለመመለስ ያላቸውን ፍላጎት በተመለከተ በሰጡ አስተያየት መነጋገሪያ ሆነዋል። አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ በተለይ "እኔ አሰልጣኝ እንጂ የጽዳት ሰራተኛ አይደለሁም" በማለት የሰጡት ምላሽ በብዙዎች ዘንድ ትኩረት ስቧል።
የ54 ዓመቱ ፖቸቲኖ እንደገለጹት፣ የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ለ2026ቱ ዓለም ዋንጫ ራሱን በከፍተኛ ሁኔታ እያዘጋጀ ይገኛል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ መላው የአሜሪካ ሕዝብ ከቡድኑ ትልቅ ውጤት እንደሚጠብቅ እንደሚገነዘቡም ተናግረዋል። አሰልጣኙ አክለውም ለብሔራዊ ቡድኑ የሚመጥኑ ተጫዋቾችን ለመምረጥ አሁንም በቂ ጊዜ እንዳለ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ፖቸቲኖ በአሜሪካ ያለውን ቆይታ ቢወዱትም፣ የለንደን እና የእንግሊዝ እግር ኳስ ክርክርና ፉክክር እጅግ እንደናፈቃቸው አልሸሸጉም። "ከዓለም ዋንጫው በኋላ ወደ ለንደን ብመለስ ደስ ይለኛል፤ እኔ አሰልጣኝ እንጂ የጽዳት ሰራተኛ አይደለሁም፣ ስለዚህ ነጻነቴን እፈልጋለሁ" በማለት የወደፊት እቅዳቸውን አመልክተዋል።
ፖቸቲኖ ከዓለም ዋንጫው በኋላ ወደ እንግሊዝ የመመለስ ፍላጎት እንዳላቸው መነገሩን ተከትሎ፣ የቀድሞ ክለባቸው ቶተንሃም በድጋሚ ሊቀጥራቸው እንደሚችል ጭምጭምታዎች እየተሰሙ ነው። በተለይም ቶተንሃም በሊጉ የመቆየት እድሉ ካልተመናመነ፣ አመራሮቹ አርጀንቲናዊውን አሰልጣኝ በድጋሚ ወደ ክለቡ ለመመለስ ፍላጎት እንዳላቸው እየተገለጸ ይገኛል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ብስራትኤፍ ኤም #pochettino #usmnt #worldcup2026 #premier League #tottenham #london #footballnews #mauriciopochettino

5 months ago
የማይክል ካሪክ ማንቸስተር ዩናይትድ
ከውድቀት አረንቋ ወደ አውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ደጃፍ
#ethiopia | ማንቸስተር ዩናይትድ የቀድሞ ኮከቡን ማይክል ካሪክን በጊዚያዊ አሰልጣኝነት ካገኘ በኋላ፣ በውርደት ሽንፈት ተከናንቦ ከነበረበት ዝቅታ ወጥቶ በክብር የሚዋደቅ እና ውጤት የሚያስመዘግብ ቡድን ለመሆን በቅቷል። የካሪክ ዩናይትድ ተቸግሮም አይሸነፍም፤ በቀይ ካርድ ተጫዋች ተነጥቆም ቢሆን ለክለቡ ባጅ እስከመጨረሻው የሚፋለም ጠንካራ ስብስብ ሆኗል።
የበርንማውዝ ጨዋታ እና የካሪክ አሻራ
በቫይታሊቲ ስታዲየም ከበርንማውዝ ጋር የተደረገው አስቸጋሪ ጨዋታ የካሪክን ቡድን ጥንካሬ በድጋሚ ያሳየ ነበር።
ምንም እንኳ ዩናይትድ በግልጽ የተከለከለው ፔናሊቲ እና የሃሪ ማጉየር ቀይ ካርድ ፈተና ቢገጥመውም፣ በብሩኖ ፈርናንዴዝ መሪነት ጨዋታውን ሁለት አቻ በማጠናቀቅ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል። ካሪክ ከመጣ በኋላ ቡድኑ አንድ ጊዜ ብቻ በኒውካስትል መሸነፉ፣ አሰልጣኙ በአጭር ጊዜ ውስጥ የፈጠሩትን የውጤት ወጥነት ያሳያል።
ከደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ወደ 3ኛ ደረጃ
እንደ ሩበን አሞሪም ባሉ አሰልጣኞች የቀዘቀዘው የተጫዋቾች ፍላጎት ላይ ነፍስ የዘሩት ማይክል ካሪክ፣ በሦስት ወራት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ዩናይትድን በደረጃ ሰንጠረዡ 3ኛ ላይ እንዲቀመጥ አድርገዋል።
እንደ አስቶን ቪላ፣ ቼልሲ፣ ሊቨርፑል እና ኒውካስትል ያሉ ተፎካካሪዎችን በነጥብ በልጦ፣ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ዕድሉን በእራሱ እጅ እንዲያደርግ አስችለውታል።
የካሪክ ስኬት እና የቋሚ ኮንትራት ጥያቄ
ሲቲን፣ አርሰናልን እና ቶተንሃምን ተራ በተራ የረታው የካሪክ ስልጠና፣ ለቋሚ ኮንትራት የሚያበቃው ውጤታማ ጉዞ መሆኑን በተግባር አሳይቷል።
ምንም እንኳ የቀድሞ የቡድን አጋሮቻቸው ሳይቀሩ ጥርጣሬ ቢኖራቸውም፣ ካሪክ ግን የማንቸስተርን የድል አድባር DNA ጠንቅቆ በመረዳት ክለቡን ነጻ አውጥቷል። አሁን ዩናይትድ ከ32ኛ ሳምንት የሊድስ ጨዋታ በፊት ለ24 ቀናት የሚቆይ የእረፍት እና የዝግጅት ጊዜ ይኖረዋል።
የውጤት ማጠቃለያ፦
በርንማውዝ 2 - ማንቸስተር ዩናይትድ 2 (ከቫይታሊቲ ስታዲየም)
#getu #manchesterunited #michaelcarrick #mufc #premierleague #brunofernandes #championsleague #oldtrafford #ማንቸስተርዩናይትድ #ማይክልካሪክ #ብሩኖፈርናንዴዝ #ፕሪሚየርሊግ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

ባየርን ሙኒክ፣ ሊቨርፑል እና አትሌቲኮ ማድሪድ የሩብ ፍፃሜን ተቀላቀሉ
ትናንት ምሽት በተደረጉ የአውሮፓ ቻምፕየንስ ሊግ ጨዋታዎች ባየርን ሙኒክ አታላንታን 4 ለ 1 (በድምር ውጤት 10 ለ 2) በማሸነፍ በቀላሉ አልፏል።
ሃሪ ኬን ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር፣ ካርል እና ዲያዝ ቀሪዎቹን አክለዋል።
ሊቨርፑል በበኩሉ ጋላታሳራይን በአንፊልድ 4 ለ 0 በመርታት (በድምር 4 ለ 1) ተከታዩን ዙር ተቀላቅሏል።
ሳላህ፣ ሶቦስላይ፣ ኤኪቲኬ እና ግራቨንበርች የሊቨርፑልን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።
አትሌቲኮ ማድሪድ ምንም እንኳን በቶተንሃም 3 ለ 2 ቢሸነፍም፣ በመጀመሪያው ጨዋታ በነበረው 5 ለ 2 ሰፊ ውጤት ምክንያት በድምር 7 ለ 5 ማለፉን አረጋግጧል።
እነዚህ ሶስት ቡድኖች ባርሴሎና፣ ፒኤስጂ፣ ሪያል ማድሪድ፣ ስፖርቲንግ እና አርሰናልን በመቀላቀል ለታላቁ ፍልሚያ ተዘጋጅተዋል።

ሊቨርፑልና ቶተንሃም ባለቀ ሰዓት ነጥብ ተጋሩ
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በአንፊልድ ስታዲየም በተደረገው ተጠባቂ ጨዋታ ሊቨርፑልና ቶተንሃም 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያዩ።
ሊቨርፑል በ18ኛው ደቂቃ በሶቦስላይ አማካኝነት መሪ መሆን ቢችልም፣ እስከ መደበኛው ክፍለ ጊዜ ማጠናቀቂያ ድረስ ውጤቱን አስጠብቆ መቆየት አልቻለም።
በ90ኛው ደቂቃ ላይ ኮሎ ሙአኒ ያመቻቸለትን ኳስ ሪቻርሊሰን ከመረብ በማሳረፍ ለቶተንሃም ወሳኝ አቻ ነጥብ አስገኝቷል።
ውጤቱን ተከትሎ ሊቨርፑል በ49 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፣ ቶተንሃም በ30 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በቀጣይ ሳምንት ሊቨርፑል ብራይተንን ሲጎበኝ፣ ቶተንሃም ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ይጫወታል።

ሻምፒዮንስ ሊግ፡ ባየር ሙኒክ እና አትሌቲኮ ማድሪድ ለሩብ ፍጻሜ ተቃረቡ
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የ16ቱ ጥሎ ማለፍ መርሃ-ግብር ባየር ሙኒክ አታላንታን 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት በመርታት ለሩብ ፍጻሜው ተቃርቧል።
በጨዋታው ኦሊሴ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር፣ ስታኒሺች፣ ግናብሪ፣ ጃክሰን እና ሙሲያላ ቀሪዎቹን ግቦች አክለዋል።
በሌላ በኩል አትሌቲኮ ማድሪድ ቶተንሃምን 5 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የአልቫሬዝ ሁለት ግቦች እንዲሁም የሎሬንቴ፣ ግሪዝማን እና ሌ ኖርማንድ ጎሎች ለስፔኑ ክለብ ወሳኝ ድል አስገኝተዋል።
የቶተንሃም ግብ ጠባቂ ኪንስኪ የሰራቸው ስህተቶች ለቡድኑ ሽንፈት ምክንያት ሆነዋል።
ኒውካስትል እና ባርሴሎና ባደረጉት ትንቅንቅ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
ባርንስ ለኒውካስትል መሪነቱን ቢያስገኝም፣ በጭማሪ ሰዓት (96ኛው ደቂቃ) ላሚን ያማል በፍጹም ቅጣት ምት ባርሴሎናን ከሽንፈት ታድጓል።
ባየር እና አትሌቲኮ ለሚቀጥለው ዙር ሰፊ ዕድል ሲኖራቸው፣ የባርሴሎና እና ኒውካስትል እጣ ፈንታ በሁለተኛው ጨዋታ ይለያል።

የግዙፎች ፍልሚያ፦ ሪያል ማድሪድ ከማንቸስተር ሲቲ በድጋሚ ተገናኙ! ⚔️⚽
ዛሬ የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. በኒዮን ስዊዘርላንድ በወጣው የ2018ቱ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የ16ቱ ድልድል፣ መላው ዓለም በጉጉት የሚጠብቀው ፍልሚያ ይፋ ሆኗል።
"የአውሮፓ ነገስታቱ" ሪያል ማድሪዶች ካለፉት ዓመታት ባላንጣቸው ማንቸስተር ሲቲ ጋር በድጋሚ ተፋጠዋል።
የ16ቱ ድልድሎች፦
🔵 ማንቸስተር ሲቲ 🆚 ሪያል ማድሪድ (የዓመቱ ትልቅ ጨዋታ!)
🔴 አርሰናል 🆚 ባየር ሌቨርኩሰን (የአርቴታ እና ካስፐር ጁልማንድ ታክቲካዊ ጦርነት)
🔵 ፒኤስጂ 🆚 ቼልሲ (የድሮው ትውውቅ ተመለሰ)
🔴 ሊቨርፑል 🆚 ጋላታሳራይ
🔵 ባርሴሎና 🆚 ኒውካስል ዩናይትድ
⚪️ ቶተንሃም 🆚 አትሌቲኮ ማድሪድ
🔴 ባየርን ሙኒክ 🆚 አታላንታ
🟢 ስፖርቲንግ ሊዝበን 🆚 ቦዶ ግሊምፕት
📅 የጨዋታ ቀናት፦
የመጀመሪያ ጨዋታዎች መጋቢት 1 እና 2 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚከናወኑ ሲሆን፣ የመልስ ጨዋታዎች ደግሞ መጋቢት 8 እና 9 ቀን 2018 ዓ.ም. ይደረጋሉ።
seledadotio

አርሰናል ቶተንሃምን 4 ለ 1 አሸነፈ
በ27ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አርሰናል ቶተንሃም ሆትስፐርን 4 ለ 1 አሸንፏል
በመጀመርያው አጋማሽ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ወደ እረፍት ያመራው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በአርሰናል አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
seledadotio
seledadotio
በ27ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አርሰናል ቶተንሃም ሆትስፐርን 4 ለ 1 አሸንፏል
በመጀመርያው አጋማሽ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ወደ እረፍት ያመራው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በአርሰናል አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
seledadotio
seledadotio
5 months ago
ሰሜን ለንደን በመድፍ ተደበደበች፣ አርሰናል ቶተንሃምን 4 ለ 1 ረመረመ።
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እጅግ ተጠባቂ የነበረው የሰሜን ለንደን ደርቢ፣ በመድፈኞቹ ፍፁም የበላይነት ተጠናቋል። አርሰናል ቶተነሃምን በሜዳውና በደጋፊው ፊት 4 ለ 1 መርታት ችሏል።

"ከቶተንሃም ጋር መሸነፍ አይታሰብም" ዴክላን ራይስ
የአርሰናሉ አማካኝ ዴክላን ራይስ ከቶተንሃም ጋር ለሚደረገው ተጠባቂ ጨዋታ ቡድኑ ያለውን ቁርጠኝነት ገልጿል። ራይስ በተለይ ከቡድን አጋሩ ቡካዮ ሳካ የሰማውን ምክር በማስታወስ ለጨዋታው ያላቸውን ትኩረት ለ"ሰን ስፖርት" ተናግሯል።
"ሳካ 'እዚህ ክለብ ውስጥ ከስፐርስ ጋር የሚደረጉ የደርቢ ጨዋታዎችን መሸነፍ አትችልም' እንዳለኝ አስታውሳለሁ" በማለት የጨዋታውን ትልቅነት ገልጿል። ካለፈው ሳምንት የነጥብ መጣል በኋላ ይህ ጨዋታ ለደጋፊዎች፣ ለተጫዋቾችና ለክለቡ ሰራተኞች በሙሉ አቅም ምላሽ ለመስጠት ትክክለኛው አጋጣሚ መሆኑን ተናግሯል።
"ይህ ጨዋታ በፍጹም መሸነፍ የሌለብን ጨዋታ ነው" በማለት የደርቢውን ስሜትና ፉክክር አጽንኦት ሰጥቶታል።

Comments