ሻምፒዮንስ ሊግ፡ ባየር ሙኒክ እና አትሌቲኮ ማድሪድ ለሩብ ፍጻሜ ተቃረቡ
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የ16ቱ ጥሎ ማለፍ መርሃ-ግብር ባየር ሙኒክ አታላንታን 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት በመርታት ለሩብ ፍጻሜው ተቃርቧል።
በጨዋታው ኦሊሴ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር፣ ስታኒሺች፣ ግናብሪ፣ ጃክሰን እና ሙሲያላ ቀሪዎቹን ግቦች አክለዋል።
በሌላ በኩል አትሌቲኮ ማድሪድ ቶተንሃምን 5 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የአልቫሬዝ ሁለት ግቦች እንዲሁም የሎሬንቴ፣ ግሪዝማን እና ሌ ኖርማንድ ጎሎች ለስፔኑ ክለብ ወሳኝ ድል አስገኝተዋል።
የቶተንሃም ግብ ጠባቂ ኪንስኪ የሰራቸው ስህተቶች ለቡድኑ ሽንፈት ምክንያት ሆነዋል።
ኒውካስትል እና ባርሴሎና ባደረጉት ትንቅንቅ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
ባርንስ ለኒውካስትል መሪነቱን ቢያስገኝም፣ በጭማሪ ሰዓት (96ኛው ደቂቃ) ላሚን ያማል በፍጹም ቅጣት ምት ባርሴሎናን ከሽንፈት ታድጓል።
ባየር እና አትሌቲኮ ለሚቀጥለው ዙር ሰፊ ዕድል ሲኖራቸው፣ የባርሴሎና እና ኒውካስትል እጣ ፈንታ በሁለተኛው ጨዋታ ይለያል።

5 months ago