መድፉ ተተኮሰ
#ethiopia | የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ፍጻሜ አርሰናል በድል ሲያጠናቅቅ ቶተንሃም በሊጉ መትረፉን አረጋግጧል ማንችስተር ሲቲ ደግሞ ሽንፈት አስተናግዷል
የ2025/26 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን ዛሬ በአንድ ሰዓት በተደረጉ አስር ጨዋታዎች ፍጻሜውን አግኝቷል።
ከ22 ዓመታት ረጅም ጥበቃ በኋላ የሊጉን ዘውድ የደፋው አርሰናል ወደ ክሪስታል ፓላስ ሜዳ በመጓዝ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
ለመድፈኞቹ የማሸነፊያ ግቦቹን ያስቆጠሩት ጋብርኤል ጄሱስ እና ኖኒ ማዱኤኬ ሲሆኑ ክለቡ የዓመቱን ጉዞ በ85 ነጥብ በበላይነት አጠናቋል።
ወደ ታችኛው ክፍል የመውረድ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ የነበረው ቶተንሃም ሆትስፐርስ ኤቨርተንን 1 ለ 0 በማሸነፍ በሊጉ መቆየቱን አረጋግጧል።
ለለንደኑ ክለብ ወሳኟን የህልውና ግብ ያስቆጠረው ጆአኦ ፓልሂንሃ ነው። በሌላ በኩል ላለመውረድ ሲፋለም የነበረው ዌስትሃም ዩናይትድ ሊድስ ዩናይትድን 3 ለ 0 ቢያሸንፍም ከውድድር መውረዱን ሊያስቀር አልቻለም።
ክለቡ ከቶተንሃም በሁለት ነጥብ በማነሱ ምክንያት በርንሌይ እና ዎልቭስን ተከትሎ ወደ ቻምፒየንሺፕ ወርዷል።
ከማንችስተር ሲቲ ጋር ለመለያየት የወሰነው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በመጨረሻው የሊግ ጨዋታው በአስቶንቪላ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ሽንፈት ገጥሞታል።
ታዋቂ ተጫዋቾቹን ሞሐመድ ሳላህ እና አንዲ ሮበርትሰንን በክብር ያሰናበተው ሊቨርፑል ከብሬንትፎርድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በአቻ ውጤት አጠናቋል።
ለአሰልጣኝ ማይክል ካሪክ የአንድ ዓመት ተጨማሪ ውል ያበረከተው ማንችስተር ዩናይትድ ብራይተንን ከሜዳው ውጪ 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል።
በዚህ ጨዋታ ላይ አንድ ግብ አስቆጥሮ ለሌላው ደግሞ አመቻችቶ ያቀበለው ብሩኖ ፈርናንዴዝ አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል። ፖርቹጋላዊው አማካይ በአንድ የውድድር ዓመት ውስጥ 21 ግብ የሆኑ ኳሶችን በማመቻቸት ቀዳሚው ተጫዋች መሆን ችሏል።
ወደ ሊጉ በቅርቡ ያደገው ሰንደርላንድ ቼልሲን 2 ለ 1 በማሸነፍ በቀጣዩ ዓመት በአውሮፓ መድረክ ላይ የመሳተፍ መብቱን አግኝቷል።
በተያያዙ ዜናዎች ፉልሃም ኒውካስትል ዩናይትድን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ ኖቲንግሃም ፎረስት ከቦርንማውዝ ጋር 1 ለ 1 ተለያይቷል።
ቀድመው መውረዳቸውን ያረጋገጡት በርንሌይ እና ዎልቭስ ያደረጉት ጨዋታም በተመሳሳይ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።
#የእንግሊዝፕሪምየርሊግ #አርሰናል #ቶተንሃም #ማንችስተርሲቲ #ማንችስተርዩናይትድ #ሊቨርፑል #እግርኳስ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

11 days ago