Logo
FBC
ኒውካስል ዌስትሃምን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ37ኛው ሳምንት እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኒውካስል ዩናይትድ ዌስትሃምን 3 ለ 1 አሸንፏል።

ከሰሜን ለንደኑ ቡድን ቶተንሃም ጋር እየተፎካከረ የሚገኘው ዌስትሃም በፕሪሚየር ሊጉ የመቆየት ዕድሉን ያጠበበ ሽንፈት በኒውካስል ዩናይትድ አስተናግዷል።

ዊሊያም ኦሱላ (ሁለት) እና ኒክ ዋልትማደ የኒውካስልን ግቦች ሲያስቆጥሩ፥ ታቲ ካስቴላኖስ የዌስትሃምን ብቸኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል።

በዚህ መሰረት ቶተንሃም ማክሰኞ ዕለት ከቼልሲ የሚያደርገውን ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለ ዌስትሃም ዩናይትድ መውረዱን የሚያረጋግጥ ይሆናል።

ቀደም ብለው በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ማንቼስተር ዩናይትድ ኖቲንግሃም ፎረስትን 3 ለ 2፣ ሰንደርላንድ እና ኤቨርተንን 3 ለ 1፣ ሊድስ ዩናይትድ ብራይተንን 1 ለ 0 አሸንፈዋል።

እንዲሁም ብሬንትፎርድ ከክሪስታል ፓላስ 2 ለ 2 እንዲሁም ወልቭስ ከፉልሃም 1 ለ 1 ተለያይተዋል።

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.