Logo
Getu Temesgen
"እኔ አሰልጣኝ እንጂ የጽዳት ሰራተኛ አይደለሁም" ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ
#ethiopia | የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ፣ ስለ 2026ቱ ዓለም ዋንጫ ዝግጅት እና ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ስለመመለስ ያላቸውን ፍላጎት በተመለከተ በሰጡ አስተያየት መነጋገሪያ ሆነዋል። አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ በተለይ "እኔ አሰልጣኝ እንጂ የጽዳት ሰራተኛ አይደለሁም" በማለት የሰጡት ምላሽ በብዙዎች ዘንድ ትኩረት ስቧል።

የ54 ዓመቱ ፖቸቲኖ እንደገለጹት፣ የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ለ2026ቱ ዓለም ዋንጫ ራሱን በከፍተኛ ሁኔታ እያዘጋጀ ይገኛል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ መላው የአሜሪካ ሕዝብ ከቡድኑ ትልቅ ውጤት እንደሚጠብቅ እንደሚገነዘቡም ተናግረዋል። አሰልጣኙ አክለውም ለብሔራዊ ቡድኑ የሚመጥኑ ተጫዋቾችን ለመምረጥ አሁንም በቂ ጊዜ እንዳለ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ፖቸቲኖ በአሜሪካ ያለውን ቆይታ ቢወዱትም፣ የለንደን እና የእንግሊዝ እግር ኳስ ክርክርና ፉክክር እጅግ እንደናፈቃቸው አልሸሸጉም። "ከዓለም ዋንጫው በኋላ ወደ ለንደን ብመለስ ደስ ይለኛል፤ እኔ አሰልጣኝ እንጂ የጽዳት ሰራተኛ አይደለሁም፣ ስለዚህ ነጻነቴን እፈልጋለሁ" በማለት የወደፊት እቅዳቸውን አመልክተዋል።

ፖቸቲኖ ከዓለም ዋንጫው በኋላ ወደ እንግሊዝ የመመለስ ፍላጎት እንዳላቸው መነገሩን ተከትሎ፣ የቀድሞ ክለባቸው ቶተንሃም በድጋሚ ሊቀጥራቸው እንደሚችል ጭምጭምታዎች እየተሰሙ ነው። በተለይም ቶተንሃም በሊጉ የመቆየት እድሉ ካልተመናመነ፣ አመራሮቹ አርጀንቲናዊውን አሰልጣኝ በድጋሚ ወደ ክለቡ ለመመለስ ፍላጎት እንዳላቸው እየተገለጸ ይገኛል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ብስራትኤፍ ኤም #pochettino #usmnt #worldcup2026 #premier League #tottenham #london #footballnews #mauriciopochettino

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.