ማይክል ካሪክ - የኦልድ ትራፎርድ የልብ ትርታ፣ በታላላቅ ኮከቦች ጥላ ስር ተደብቆ የኖረ ድንቅ ጥበበኛ
***********************
ስለ እርሱ ሲታሰብ አምስት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችና የሻምፒዮንስ ሊጉ ድል ትዝ ሊሉን ይችላሉ። ነገር ግን እውነተኛው ማይክል ካሪክ የተገነባው በብዙዎች ዘንድ በማይታወቁ፣ ልብ በሚነኩና አስገራሚ በሆኑ ድብቅ ታሪኮች ውስጥ ነው።
ዛሬ የምናውቀው ካሪክ በኳስ ቁጥጥሩና አርቆ አሳቢነቱ የሚታወቅ የአማካይ ስፍራ ኮከብ ነው። ነገር ግን ወደ ዌስትሃም አካዳሚ በ15 ዓመቱ ሲቀላቀል ሕልሙ ሌላ ነበር፤ ያኔ የፊት መስመር አጥቂ ነበር።
ካሪክ ያደገው እንደ አላን ሺረር እና ፒተር ቤርድስሌይ ያሉ ታላላቅ ሰዎችን ባፈራው ታዋቂው የዎልሰንድ ቦይስ አካዳሚ ውስጥ ነው። የኒውካስል ዩናይትድ ደጋፊ የነበረ ቢሆንም፣ በ15 ዓመቱ ኒውካስልን ትቶ ወደ ዌስትሃም ዩናይትድ አቀና።
በ15 ዓመቱ ወደ ዌስትሃም አካዳሚ ሲቀላቀል የመስመር አጥቂ ነበር። በአንድ ጨዋታ ላይ ግን የመሃል አማካይ በመጥፋቱ በአጋጣሚ ቦታው ተቀይሮ የክፍለ ዘመኑ ብልህ አማካይ ሊሆን አጋጣሚው ተፈጠረ።
ካሪክ በቦታው መጀመሪያ ባይደሰትም ያለ እንቢታ ተጫወተ። ይህ አጋጣሚ ግን የእግር ኳስን ታሪኩን ቀየረች፤ አጥቂው ካሪክ ቀርቶ፣ የአውሮፓን መድረክ የሚገዛው ብልሁ አማካይ ተወለደ።
የካሪክ የጉርምስና ዕድሜ ደግሞ ሌላ አስገራሚ ፈተናን ይዞ መጣ። 17 ዓመቱ ላይ በአንድ ጊዜ 8 ኢንች ያህል ቁመት ጨመረ። በወቅቱ የነበረው ቀጭን ሰውነቱ ከቁመቱ ጋር ባለመመጣጠኑ ሜዳ ላይ መሮጥ እስኪያቅተው ተቸግሮ እንደነበር የቀድሞ አሰልጣኙ ሃሪ ሬድናፕ ያስታውሳሉ።
ብዙዎች የወደፊት መንገዱን ተስፋ ሲያጡበት፣ እርሱ ግን በትጋትና በጽናት ሰውነቱን ገነባ፤ በመጨረሻም ከሪዮ ፈርዲናንድ እና ፍራንክ ላምፓርድ ጋር የዌስትሃም ወርቃማ ትውልድ አካል ሆነ።
ካሪክ ገና በወጣትነቱ ጨዋታን የማንበብ ብቃቱ ድንቅ ነበር። ከዌስትሃም፣ ስዊንደን፣ በርሚንግሃም እና ቶተንሃም በኋላ በ2006 ታላቁን ማንችስተር ዩናይትድን ሲቀላቀል፣ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በሮይ ኪን መልቀቅ የዛለውን የመሃል ሜዳ የሚያክምላቸውን የፈጠራ ሰው አገኙ።
በእንግሊዝ እግር ኳስ ታሪክ ስቲቨን ጄራርድ እና ፍራንክ ላምፓርድ በችሎታ እንደማይደረስባቸው የመሀል ሜዳ ጣኦታት ይታዩ ነበር። ነገር ግን ታላቁ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ልብ ውስጥ የነበረው እውነተኛው ንጉሥ ካሪክ ብቻ ነበር።
ፈርጉሰን በግል ማስታወሻቸው ላይ “...ላምፓርድና ጄራርድ ታላላቅ ስብዕና የነበራቸው ተጫዋቾች ናቸው፤ እውነተኛ ምርጥ ተጫዋቾች ግን አልነበሩም ፤ ካሪክ ግን የእግር ኳስ አዕምሮ ነበረው። የእንግሊዝ ሚዲያዎች ስለ እነርሱ አብዝተው በማወደስ ሲጮሁ፣ ካሪክ ግን በትህትናውና በአይናፋርነቱ ምክንያት በነርሱ ጥላ ስር ተደብቆ ተበደለ።” ሲሉ ነበር እንጋፋው አሰልጣኝ በብዕራችው ከትበው ስለካሪክ የመሰከሩት።
ማይክል ካሪክ ዛሬም ቢሆን ያው ነው - ዝምተኛ፣ አስተዋይና ልባም። የዩናይትድን ታላቅ ስም ለመታደግ በዋና አሰልጣኝነት ተሰይሟል። ትናንት በዝምታ ሜዳውን እንደገዛው ሁሉ፣ ዛሬም በዚያው ጥንቁቅ አዕምሮው የታላቁን ክለብ ታሪክ ለመጻፍ እየተዘጋጀ ነው።
ካሪክ እ.አ.አ በ2006 ከቶተንሃም ማንቸስተር ዩናይትድን ከተቀላቀለ በኋላ በ12 ወርቃማ ዓመታት 5 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን፣ የሻምፒዮንስ ሊግን እና የኤፍኤ ካፕን ጨምሮ በርካታ የክብር አክሊሎችን ደፍቷል።
ሆኖም ግን እንደ ፖል ስኮልስ ፣ ጄራርድ እና ላምፓርድ ባሉ ደማቅ ስሞች ጥላ ስር ተደብቆ አሳልፏል። ነገር ግን ሳይታይ የሚደምቅ የቡድኑ የጀርባ አጥንት ነበር።
በኦልድ ትራፎርድ የነበረው ስፍራ ከብዙ ተጫዋቾች የተለየ ነበር። ግቦችን ብዙ አያስቆጥርም፣ አስደናቂ ትርዒቶችንም አያሳይም፤ ነገር ግን ጨዋታው በእርሱ እግር ይጀምር፣ በእርሱም አዕምሮ ይመራ ነበር።
ከተጫዋችነት በኋላ በሞሪንሆ እና ሶልሻየር ስር በረዳትነት የሰራው ካሪክ በ2021 ለአጭር ጊዜ ዩናይትድን በጊዜያዊነት መርቶ ጥሩ ውጤት አሳይቷል።
በመቀጠል ሚድልስብሮን በዋና አሰልጣኝነት ይዞ አስደናቂ ጊዜ ካሳለፈ በኋላ፣ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሩበን አሞሪም ስር የተንኮታኮተውን ማንችስተር ዩናይትድን ለመታደግ በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ኦልትራፎርድ ሲደርስ ብዙዎች እምነት አልጣሉበትም ነበር።
ነገር ግን ዝምተኛው ካሪክ ፤ ትናንት በዝምታ ሜዳውን እንደገዛው ሁሉ፣ ታላቁን ክለብ ከመውረድ ውርደት ታድጎ ለሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ አበቃው።
ማይክል ካሪክ በተጫዋችነት ዘመኑ በማንቸስተር ዩናይትድ የቡድን አጋሮቹ "ሃቮክ" በሚል ቅጽል ስም ይጠሩት ነበር። ይህ ስም የመጣው በወቅቱ ተጫዋቾቹ በፒኤስፒ (PSP) ላይ "SOCOM US Navy SEALs: Fireteam Bravo" የተሰኘውን ታክቲካዊና ስውር የጦርነት ጨዋታ(ኮምፒዩተር ጌም) በጋራ ሲጫወቱ ከነበራቸው ትውስታ ነው።
ዌይን ሩኒ እንደተናገረው ይህ ጨዋታና የካሪክ መሪነት ቡድኑን አንድ ላይ ለማሰባሰብ ትልቅ ሚና ነበረው። ካሪክ በጨዋታው ላይ ብቻ ሳይሆን በሜዳው ላይም ያንን ስውር እና ጥንቁቅ ታክቲክ የሚተገብር መሪ ነበር።
ካሪክ ብዙ ጊዜ በሚያወሩ ኮከቦች መካከል በዝምታ የበራ ኮከብ ነበር። የጨዋታውን ስልተ-ምት በአንድ ንክኪ የሚቀይር፣ የቡድኑን ልብ በጸጥታ የሚያስመታ ረቂቅ የሙዚቃ መሪ።
እሱን የሚለየው ያሸነፋቸው ዋንጫዎች ብቻ አይደሉም፤ ያለ ጩኸት ታሪክ መፍጠር የቻለ ሰው መሆኑ ነው። አንዳንድ ኮከቦች በብርሃን ይደምቃሉ፤ ካሪክ ግን በዝምታው ታላቅ ሆነ።
ለዚህም ነው ዛሬም በኦልድ ትራፎርድ ታሪክ ውስጥ ከማይረሱ ስሞች አንዱ ሆኖ የሚጠራው፤ እየመጡ ያሉትን ብሩህ የአሰልጣኝነት ዘመናቱንም ያስናፈቀው።
በአዲስ የሺዋስ
Ethiopian Broadcasting Corporation EBC-መዝናኛ EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት #football

1 month ago