2 hours ago
♦️1:45 ደቂቃ በቶሮንቶ ሠማይ ስር
♦️FIFA እና Destination Toronto በጋራ የሠጡኝ ወርቃማ የጉብኝት ዕድል(ክፍል አንድ)
♦️ቶሮንቶን ከሜዳ ውጪ(Off the Pitch)
የ2026ቱ የፊፋ የዓለም ዋንጫ ወደ ሌላ አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሮኛል FIFA እና Destination Toronto ለአለም ዋንጫ ዘገባ ከመጡ ኢንተርናሽናል ጋዜጠኞች ዛሬ የጉብኝት ዕድል ሠጥተውናል፤እኔም ይሄን ዕድል ካገኙት ጋዜጠኞች ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ሆኜ ቶሮንቶን ከእግር እስከራሷ የማየት ዕድል አግኝቻለሁ ከ1:45 ደቂቃ በላይ በዘለቀው የጉብኝት መርሃ ግብር የማውቃት የሚመስለኝ ነገር እንደማላውቃት የተረዳሁበትን አስገራሚ ጉብኝት አድርጌ በግርምት እጄን አፌ ላይ ጭኜ ተመልሻለሁ።ታሪክን፣ጥንታዊነትንና ዘመናዊነትን በውስጧ ሸሽጋ የያዘችው የኢኮኖሚ፣የቢዝነስ ከተማና ከ170+ አገሮች የመጡ ሰዎች የሚኖሩባት ባህላዊውን ከዘመናዊነት ጋር አጣምራ የያዘች ተወዳጅ ከተማ ናት።
በአንድ ጎዳና ላይ እየተራመዱ ብዙ ቋንቋዎችን ከሠሙ በትክክልም እርስዎ ያሉት ቶሮንቶ ነው፤ምክንያቱ ደግሞ ከ170 በላይ ሀገሮች የሚኖሩባት ብቻ ሳይሆን የተለየ ቋንቋ የሚነገርባት ዓለምን በአንድ ቦታ ሠብስባ የያዘች ከተማ ናትና።
በምሽት የካናዳ ምልክት ተደርጎ ከሚወሠደው፣ቶሮንቶን ልዩ ውበትና ድምቀት የሚያላብሳት CN Tower በሚፈልቀው ብርሃን፣በLake Ontario የባህር ዳርቻ ከወዳጅ ወይም ከፍቅረኛ ጋር የፍቅር ማር የሚቆረጥባት ከአለማችን ለኑሮ ምቹና ሠላማዊ ተብለው ከሚጠሩ ሀገሮች አንዷ፣ በዓመት ከ25–30 ሚሊዮን፣በበጋ ወቅት ደግሞ ከ150,000 በላይ ቱሪስቶች በቀን የምትጎበኘው የቱሪስቶች መዳረሻ የሆነችው ቶሮንቶን በToronto Double-Decker አውቶብስ አናት ላይ ተቀምጬ ታዘብኩትን የዛሬ የ1:45 ደቂቃ ጉብኝቴን በወፍ በረር ላስቃኛችሁ።
የተሳፈርንበትን Double-Decke Bus የሚዘውረው የህይወቱን ግማሽ ክፍል ለካናዳ የገበረው አቶ ፍቅሩ ብርሃኔ መሆኑ በጉብኝቴ የቤተሠብነት ስሜት እንዲሠማኝ ያደረገ ሲሆን በጣፍጭ አንደበቱ ታሪካዊ ቦታዎች የፍትፍት ያህል ፈትፍቶ ሲያጎርሠን የነበረውን አስጎብኚያችንን MASHAALን ከልብ ላመሠግነው ወደድኩ፤በቅድሚያ የጉብኝታችን መነሻ ስለነበረው
♦️University of Toronto
ዩኒቨርስቲ ኦፍ ቶሮንቶ ዕድሜ ጠገብ ነው፤የኛውን የቀድሞ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ የአሁኑን አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በ123 ዓመት ዬበልጠዋል፤የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የ76 ዓመት አዛውንት ሲሆን ዕድሜ ጠገቡ University of Toronto ደግሞ የ199 ዓመት አረጋዊ ነው፤እንደ አስጎብኚያችን MASHAALከ102 በላይ ተማሪዎችን እቅፍ ድግፍ አድርጎ በውስጡ ይዟል፤ዩኒቨርስቲውን ከአለማችን የተለየ የሚያደርገው ደግሞ ከ175 የዓለማችን ሀገሮች የመጡ ተማሪዎች መዳረሻ ብቻ ሳይሆን በባችለር፣በማስተርስና በፒኤችዲ ፕሮግራሞች በመታቀፍ ከህልማቸው የሚገናኙበት ትልቁ የዕውቀት ፋብሪካም ነው፤
በሚመደብለት ከ3.62 ቢሊየን የካናዳ ዶላር በካናዳ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች ቀዳሚ የሆነው University of Toronto ካሉት ከ16ሺ የበለጡ ስታፎች ከ9ሺ በላዩ አስተዳደሩን የሚዘውሩ አመራሮች መሆናቸው ቶሮንቶን ያለ አዋዜ አጣጥሞ እንደበላት በቃሉ የሚሠጠው መረጃ ከሚያሳብቅበት አስጎብኚያችን MASHAAL መረዳትም ተችሏል።
ከዓለማችን ምርጥ 30 ዩኒቨርስቲዎች አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት University of Toronto የአለምን በዕውቀታቸው እንዳሻቸው ከሚዘውሩ በዕውቀቱ የታጠቁ ሙሁራንን ከማፍራቱ በተጨማሪ የካናዳን ኢኮኖሚ በፍይናንስ ከሚያግዙ ተቋማት መካከልም አንዱ ነው፤በዚህም መሠረት ከ15 ቢሊየን የካናዳ ዶላር በላይ ወደ ካናዳ ፈሰስ መመድረጉ ይሄ ገቢዎች ነው?ወይስ ኢትዮ ቴሌኮም የሚል ጥያቄ ማስመዘዙ አልቀረም"
♦️TTC የቶሮንቶ ከተማ የልብ ምት
Toronto Transit Cooperation በምህፃረ ቃል TTC የደም ስር ወይም የከተማዋ የልብ ምት ቢባል ቃሉ አልተጋነነም፤በተለይም ለToronto እና አካባቢው ያበረከተው ጥቅም ከመጓጓዣነትም በላይ የሕይወት አገልግሎት ነው። ከተማዋን የሚያንቀሳቅስ ደም መስመር ተደርጎም ይቆጠራል፤TTC የከተማው የደም ሥር ነው።በቀላል አማርኛ
እንደ ደም ሥሮች ደምን ወደ ሰውነት ክፍሎች እንደሚያደርሱ ሁሉ TTC ሰዎችን ወደ ሥራ፣ ወደ ትምህርት ቤት፣ ወደ ሆስፒታል፣ ወደ ገበያ እና ወደ መዝናኛ ቦታዎች በየቀኑ በማመላለስ ህይወት በቶሮንቶ የቀለለ እንዲሆን እንዳደረገ በጉብኝታችን ወቅት ተረድተናል።
በቅርቡ የወጣ ጥናት እንደሌለ ነገር ግን የ2025ትን ጥናት መነሻ አድርጎ እንደ ነገረን አስጎብኚያችን MASHAAL መረጃ ከሆነነ የቶሮንቶን ከተማ ከጫፍ ጫፍ ለማገናኘት ማልደው የሚሠማሩት የTTC በእኛ ሀገር አጠራር የካናዳ አንበሳ አውቶቢስ አገልግሎት ከ2000 በላይ ቀይና ነጭ አውቶቢሶችን 250 የሚጠጉ ነኤሌክትሪክ፣ከ200 በላይ ረዣዥም ባሶችን ቶሮንቶ ትጠቀማለች።
የTTC የትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው ባይካድም ትራፊክን ይቀንሳል፣መኪና መግዛት፣ ነዳጅ መሙላት እና ፓርኪንግ መክፈል ከሚጠይቀው ወጪ ይልቅ ብዙ ጊዜ ይቀላል፤ሰዎች በቀላሉ ወደ ሥራ እና ወደ ንግድ ማዕከላት እንዲደርሱም ከማገዙም በላይ ለሁሉም ተደራሽ በመሆን በኩል መኪና የሌላቸው፣ ተማሪዎች፣ አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች ከተማው እንዳያገላቸው ይልቅ እንዲጠቀሙበት ትልቅ ዕድል ይሠጣል።ይህ ነፃና የተመቻቸ የትራንስፖርት ፍሠት ያለ TTC የባቡር አገልግሎት የተሳለጠ ይሆን ነበር ብሎ ለስህተት ይዳርጋል።ምክንያቱም የTTC ባቡር የትራንስፖርት አገልግሎት በዓመት ወደ ከ180 ሚሊዮን በላይ በቀን ደግሞ በየቀኑ ከ 690,000 በላይ ወይም 1ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎችን ከአንደኛው የከተማው ጫፍ ወደ ሌላኛው ጫፍ በማመላለስ የቶሮንቶ የጀርባ አጥንት መሆኑን ጉብኝቴ አሳይቶኛል።
♦️በቶሮንቶ ከ110 ካሬ ኪ.ሜ. በላይ የሚሸፍን የተፈጥሮ ሸለቆዎች ያለባት ከተማ
አብዛኛው ሠው ስለ ቶሮንቶ ሲያስብ ከፊቱ ቀድሞ የሚመጣበት ወይም የካናዳና የቶሮንቶ መለያ አድርጎ የሚወስደው CN Tower ን ነው፤ከትናንቱ የሚዲያ ጉብኝቴ የተረዳሁት ትልቁ ቁምነገር ግን ቶሮንቶን ከሌሎች ትልልቅ ከተሞች የሚለየው የRavine System (የተፈጥሮ ሸለቆዎች አውታረ መረብ) ያለበት ከተማ መሆኑ ነው እላለሁ።ከላይ ለማነሳት እንደሞከርኩት ብዙ ሰዎች ስለቶሮንቶ ሲያስቡ የመጀመሪያው የሚያስታውሱት CN Tower ን ነው፣ ነገር ግን የቶሮንቶ እውነተኛ ልዩነት በከተማው መሃል ውስጥ የሚያልፉ የተፈጥሮ ሸለቆዎች መኖራቸውን ስንቶቻችን እናውቃለን?በሚገርማችሁ ሁኔታ በከተማው ውስጥ በአጠቃላይ 110 ካሬ ኪ.ሜ. የሚሸፍን የሸለቆ ስርዓት አለ፤
ይህ ደግሞ የከተማውን 17% በላይ እንደሚሸፍን የአስጎብኚያችን መረጃ ይጠቁማል፤በዓለም ላይ ቀከተማ ውስጥ ካሉ የሸለቆ ስርዓቶች ትልቁ በመሆንም ቶሮንቶን ከፊት ያስቀምጣታል።ስለዚህ በቶሮንቶ አንድ ሰው በዳውንታውን ውስጥ ያሉ ቁመተ መለሎ ሠማይ ጠቀስ ፎቆች መካከል ሲሆን ከ10 ደቂቃ በኋላ በዱር ውስጥ እንዳለ ሊሰማው ቢችል አይፈረድበትም፤ይሄንን የታዘቡ ደግሞ ቶሮንቶን “city within a park” (በፓርክ ውስጥ ያለች ከተማ) ብለው እስከመግለፅ የተገደዱት።
ቶሮንቶ ሰማይን የሚነኩ ሕንፃዎችና የተፈጥሮ ዱር በአንድ ቦታ የሚገናኙባት ከተማ መሆኗ በእርግጥም የተለየች ከተማ የሚል ስያሜ እንዲሠጣት ያስገድዳል።።
የክፍል አንድ የወፍ በረር ጉብኝቴ ይሄንን ይመስላል፤በክፍል ሁለት ትዝብቴ ቀ1:45 ደቂቃ በፈጀው ጉብኝቴ የካናዳዊያን ምልክት ተደርጎ ስለሚወሠደው CN Tower፣ስለ ሮያል ኦንታሪዮ ሙዚየም፣ቶሮንቶንስላጥለቀለቁት ላይብረሪዎች፣የፍቅር ማር ስለሚቆረጥባትና የመዝናኛ ዋነኛ የልብ ምት ስለሆነችው Lake Ontario እና በካናዳ ስለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣የጉብኝት ባሳችንን Double-Decke ከሚዘውረው ኢትዮጵያዊ ህይወትና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የቃረምኩትን አካፍላችኋለሁ፤FIFA እና Destination Toronto በጋራ ይሄን ዕድል ስለሠጡኝ ከልብ አመሠግናለሁ🙏🙏...(ይቀጥላል)....
✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)ከከናዳ ቶሮንቶ

6 hours ago
የክረምት በጎ ባህሎቻችንን ወደ ላቀ መገለጫነት እናሻግራለን - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የክረምት በጎ ባህሎቻችንን ወደ ላቀ መገለጫነት እናሻግራለን አለ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት።
አገልግሎቱ ጉዳዩን አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ ሙሉ መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል።
ኢትዮጵያውያን ባለፉት የለውጥ ዓመታት ክረምት በመጣ ቊጥር የምንከውናቸው ሁለት አንኳር ባህሎችን እየገነባን መጥተናል፤ ኢትዮጵያን አረንጓዴ ማልበስ እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት፡፡
ኢትዮጵያ የደን ሀብቷ እየተመናመነ፣ የዐፈር መሸርሸር እና ድርቅ ተጋላጭነቷ እየጨመረ መምጣቱን በመገንዘብ መንግሥት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን በሚሊዮን ችግኞች ተከላ በማብሰር ከጥቂት ዓመታት በፊት ጀምሯል፡፡
ኢትዮጵያውያንም ይህንን በጎ ጅምር እና የመዳረሻ ትልም በላቀ ደረጃ በመገንዘብና የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብሩን በተነሣሽነት በመተግበር ዓለምን ያስደመሙ ስኬቶችን አስመዝግበናል፡፡ በሂደቱ የምግብ፣ የደን እና የውበት ችግኞችን በመትከል ዐሻራችን እያኖርን ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበስ ባህላችንን በእጅጉ አጎልብተናል፡፡
በየዓመቱ በርካታ ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል የዓለም ሕዝብን ከአምስት እጥፍ የሚበልጥ ከ48 ቢሊዮን ላይ ችግኞች ተክለናል፤ በዚህም የኢትዮጵያን የደን ሽፋን ትርጒም ባለዉ መጠን አሳድገናል፤ ለምግብ ሉዓላዊነታችን መሠረት መጣል ጀምረናል፤ የፍራፍሬ የወጪ ንግዳችን አሳድገናል።
ከሁለት ዓመታት በፊት ይፋ በተደረገ የጥናት ውጤት መሠረት የደን ሽፋናችን እጅግ ከተመናመነበት በከፍተኛ ፍጥነት አገግሞ ወደ 23.6% አድጓል፡፡
በልዩ ኹኔታ የኢትዮጵያውያንን የተቀናጀ እና የተሰናሰነ ተነሣሽነት በሚጠይቁ የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሮችም የዓለምን ትኩረት በሳበ መልኩ ሚሊዮኖች በአንድ ጀምበር እየወጣን በመትከል የራሳችንን ክብረ ወሰን በራሳችን ደጋግመን እያሻሻልን መጥተናል፡፡
በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የተከልናቸው የምግብ፣ የደን እና የውበት ችግኞች የኢትዮጵያን ኹለንተና የሚቀይሩ፣ የምግብ ሉዓላዊነታችንን የሚያረጋግጡ፤ የአበባ እና ፍራፍሬ ወጪ ንግዳችንን ዕድገት እየለወጡ ያሉ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም ዐቅም ያጎለበቱ ናቸው፡፡
በመኾኑም ይህ ክረምት በመጣ ቊጥር በንቅናቄ የሚከናወን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ባህል የበለጠ እንዲጠናከርና እንዲጎለብት በትጋት መሥራታችንን እንቀጥላለን፤ ኢትዮጵያን አረንጓዴ በማልበስ ንጹሕ አየር ለዓለም እናበረክታለን፡፡ ዘንድሮም የራሳችንን ክብረ ወሰን በራሳችን የላቀ የሚሊዮኖች ተሳትፎ በማሻሻል ጭምር ከ8 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን እንተክላለን፡፡
የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትም ሌላኛዉ ዐዲስ እያደገ የመጣ ልምምዳችን ነው፡፡ ወጣቶች ዕውቀታቸዉን እና ከትምህርት የተረፈ ጊዜያቸውን፣ ባለሀብቶች ደግሞ ሀብታቸውን በማዋጣት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያሉ ዐቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት በመገንባት፣ ማዕድ በማጋራት እጅግ የተዋጣለት ልምምድ አዳብረዋል፡፡
የመንግሥት ተቋማትም በቁጠባ ከሚጠቀሙት ሀብታቸው በማዋጣት ይህንን የበጎ አድራጎት ልምድ የማስፋት እና ወደ ላቀ ባህል ደረጃ የማሳደግ ኃላፊነትን እየተወጡ ይገኛሉ፡፡
በለውጡ ዓመታት በአዲስ አበባ እና በክልሎች የበርካታ ዐቅመ ደካሞች ቤት ታድሷል፤ በዐዲስ መልክ ተገንብቷል፤ ሕይወታቸዉ እንዲሻሻል ተደርጓል፡፡ በከተሞች የተጀመረዉ የኮሪደር ልማት ወደ ገጠር ተስፋፍቷል። ኢትዮጵያውያን ችግሮቻችንን ተጋግዞ የመፍታት ባህል እያዳበርን መጥተናል፡፡
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደየአካባቢያቸው በመሄድ እና በወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ታናናሾቻቸውን እያስተማሩ፣ እንደ ደም ልገሳ ያሉ ሕይወት አዳኝ ተግባራትን እያስተባበሩ፣ ዐቅመ ደካሞችን በማገዝ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው፡፡
በመኾኑም በየክረምቱ በበጎ ልምድነት እያሳደግናቸው የመጡ የአረንጓዴ ዐሻራ እና የበጎ ፈቃድ ሥራዎች የበለጠ ሀገራዊ መገለጫችንና ባህላችን እንዲኾኑ ዘንድሮም ካለፉት ዓመታት የላቀ ተሳትፎ የሚጠይቅ ዕቅድ ተዘጋጅቷል፤ ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል።
በተደመረ ዐቅማችን የኢትዮጵያን ዕቅድ በሚገባ ለማሳካት ቅድመ ዝግጅት ጨርሰን ወደ ትግበራ ገብተናል። ድላችንን በጋራ የምናበስርም ይኾናል።
የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

1 day ago
የፋርማሲ ተማሪዎች ቅሬታ‼️
የፋርማሲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ተፈታኞች ፈተናው አስቀድሞ ተሰርቋል በማለት ቅሬታ አቀረቡ፤ የሚመለከተው አካል ማብራሪያ እንዲሰጥም ጠይቀዋል።
ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም የተሰጠው የፋርማሲ ትምህርት ክፍል ብሔራዊ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) አስቀድሞ ተሰርቆ ለተወሰኑ ተማሪዎች ተሰራጭቷል ሲሉ ተፈታኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ ተማሪዎች እንዳሉት፤ ለፈተናው በርካታ ልፋትና ዝግጅት ቢያደርጉም፣ ኃላፊነት በማይሰማቸው አካላት አማካኝነት ፈተናው ቀድሞ ወጥቶ መሰራጨቱን የሚያሳዩ መረጃዎች እንደደረሷቸው ገልጸዋል።
ይህ መሆኑም በከፍተኛ ጥረትና በራሳቸው ልፋት የተፈተኑ ተማሪዎችን ስነ-ልቦና በእጅጉ የጎዳና ፍትሃዊነትን ያጓደለ ተግባር መሆኑን ጠቁመዋል።
ተፈታኞቹ አያይዘውም፣ ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት ትምህርት ሚኒስቴርና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንዲሁም በኢትዮጵያ ፋርማሲስቶች ማህበር (EPA) በኩል በአስቸኳይ ታይቶ፣ አስፈላጊው ማጣሪያ እንዲደረግና ተገቢው ምላሽ እንዲሰጣቸው በትህትና ጠይቀዋል።
Seledadotio

ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የክልሎች ዝግጅት…
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተናን ለማካሄድ ሰፊ የዝግጅት ሥራ ተከናውኗል አሉ የኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች፡፡
የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ካሳሁን ገላና (ዶ/ር)÷ በክልሉ 180 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናን እንደሚወስዱ ተናግረዋል፡፡
የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻልም በ1 ሺህ 406 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱን ነው የገለጹት፡፡
በዚህም ከመስከረም ወር ጀምሮ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ባሉ የትምህርት አይነቶች ላይ የማጠናከሪያ ትምህርት ሲሰጥ መቆየቱን ጠቁመዋል።
ተማሪዎች የመለማመጃ ጥያቄዎችን በግልና በቡድን እንዲሰሩ መደረጉን ጠቅሰው÷ በተለይም ለሴት ተማሪዎች ልዩ ድጋፍ መሰጠቱን አስረድተዋል።
በክልሉ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ ለመስጠት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መሰራቱን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በተመሳሳይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ 7 ሺህ 679 ተማሪዎችን ውጤታማ ለማድረግ ሰፊ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ተመስገን ዲሳሳ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ፈተናውን በስኬትና በታማኝነት ለመምራት የፈተና ማዕከላት ብዛት ቀድሞ ከነበረበት 2 ተነስቶ ወደ 18 ከፍ እንዲል መደረጉን አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም ከዘንድሮው የሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች መካከል 4 ሺህ 999 ወይም 65 በመቶ የሚሆኑት ፈተናውን በኦንላይን እንደሚወስዱ አመልክተዋል፡፡
ለዚሁ ተግባር የሚውሉ ታብሌቶች ተገዝተው ለፈተና ማዕከላቱ መሰራጨታቸውን ለፋና ዲጂታል አስረድተዋል።
የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተናን የሚወስዱ ተማሪዎች በቀሪ ቀናት አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉም ኃላፊዎቹ አሳስበዋል፡፡
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን÷ ለፈተናው በተፈጥሮ ሳይንስ 306 ሺህ 964 እና በማሕበራዊ ሳይንስ 257 ሺህ 255 በድምሩ 564 ሺህ 219 ተማሪዎች ተመዝግበዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናውን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና በ570 የክልል ማዕከላት ለመስጠት ዝግጅት መደረጉንም የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የትውልድ ግንባታ፦ የነገዋ ኢትዮጵያ አስተማማኝ ዋስትና
**********************
(የዕለቱ መልዕክት)
ቴክኖሎጂ በረቀቀበትና ዓለም አቀፋዊ ፉክክር በጠነከረበት በዚህ ዘመን፣ ያለ ትምህርት ጥራት ሁለንተናዊና ዘላቂ ብልጽግናን ማረጋገጥ በፍጹም አይቻልም።
ትምህርት የዕውቀት መቅሰሚያ ብቻ ሳይሆን የማኅበረሰብን የወል ትርክት መፍጠሪያ፣ ብሔራዊ መግባባትን መገንቢያና የሀገርን ሕልውና ዘላቂ የማድረጊያ ዋና ድልድይ ነው።
በዘርፉ ላይ የታዩ ታሪካዊና መዋቅራዊ ስብራቶችን ለመጠገን ላለፉት አምስት ዓመታት የተወሰዱት እርምጃዎችና የተመዘገቡት ስኬቶች፣ ኢትዮጵያ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን ለመቅረጽ የጀመረችውን ስልታዊ ሽግግር በግልጽ ያሳያሉ።
ለ28 ዓመታት የቆየውን አሮጌ ፖሊሲ በመቀየር፣ አዲስ የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ ካርታን መሠረት ያደረገ ፖሊሲ ወደ ትግበራ መግባቱ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፍቷል።
ይህ ማሻሻያ ለመጀመሪያ ጊዜ የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅና የብቃት ማዕቀፍ ሥርዓት እንዲዘረጋ በማድረግ ረገድ ትልቅ መሠረት መሆኑ ይታመናል።
ለትምህርት ዘርፉ የተሰጠው ይህ ከፍተኛ ቁልፍ ትኩረት፣ አሰልቺና ንድፈ ሐሳባዊ ብቻ የነበረውን አሠራር በመስበር በተግባር የታገዘና ተጨባጭ ውጤት ማምጣት የቻለ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው።
በትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ዙሪያም የተከናወኑ መዋቅራዊ ለውጦች በርካታ ዐበይት ምሰሶዎችን ያካትታሉ።
በ"ትምህርት ለትውልድ" ንቅናቄ አማካኝነት የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻልና የመሠረተ ልማት ግንባታን የማፋጠን ሥራ የተከናወነ ሲሆን፣ በተለይም ዓለም አቀፍ አድናቆት ያተረፈው የትምህርት ቤት ምገባ መርሐ ግብር ከ8 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን መመገብ አስችሏል።
ይህ ስልታዊ እርምጃ ተማሪዎች በትምህርታቸው እንዲገፉና የማቋረጥ ምጣኔው እንዲቀንስ በማድረግ፣ ለብዙ ወላጆች ትልቅ ማኅበራዊ እፎይታን ከመስጠቱም በላይ ለትምህርት ጥራት መሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።
ከዚህ ጎን ለጎን ትምህርትን ከተጨባጭ የሀገር እውነታ ጋር ለማገናኘት ሀገር በቀል ዕውቀት በሥርዓተ ትምህርቱ ውስጥ እንዲካተት መደረጉ፣ እንዲሁም "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" አጀንዳን መሠረት በማድረግ በርካታ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በኮምፒውተር ላብራቶሪና በኢንተርኔት መገናኘታቸው ለትምህርት ጥራት ሌላኛው መፍትሔ ተደርጎ ይወሰዳል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጥራትና ብቃት ለመለካት የዩኒቨርሲቲ መውጫ ምዘና (Exit Exam) ተግባራዊ መደረጉ በንድፈ ሐሳብና በተግባር መካከል ያለውን ክፍተት የደፈነ ቁልፍ እርምጃ ነው።
ይህ የፈተና ሥርዓትና የተዘረጋው የቁጥጥር ማዕቀፍ፣ ለአሥርት ዓመታት የአካዳሚክ ታማኝነትንና የትውልዱን የሥነ ልቦና መዋቅር ሲያናጋ የኖረውን የኩረጃ መጥፎነትና አውዳሚነት ለመግታት የተወሰደ ታሪካዊ እርምጃ ነው።
ኩረጃ የራስን አቅም አሳንሶ የመመልከትና የሌሎችን ጥረት በመስረቅ ሀገርንና ትውልድን የማታለል ትልቅ የሞራልና የማኅበረሰብ ውድቀት ነው። ኩረጃ ባለበት ቦታ እውነተኛ ዕውቀትና የፈጠራ ብቃት ሊበቅል አይችልም፤ ሀገርም በትክክለኛ ባለሙያዎች እጅ አትወድቅም።
ስለሆነም ይህንን አጥፊ ልማድ በቆራጥነት መዋጋትና የልፋትን ዋጋ የሚያስከብር ፍጹም የብቃት ሥርዓት መገንባት ከተመዘገቡት ውጤቶች ሁሉ የላቀ ስኬት ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል።
ዩኒቨርሲቲዎች በተልእኮ እንዲለዩና ወደ ራስ ገዝነት እንዲሸጋገሩ ሥርዓት መዘርጋቱም ይህንን ከኩረጃ የነጻ ተወዳዳሪ የሰው ኃይል የማፍራት ሂደት ይበልጥ ያረጋግጠዋል።
እስካሁን የተመዘገቡት ስኬቶች የሚደነቁና በትኩረት የተገኙ ቢሆኑም፣ ወደፊት የሚጠብቀን ጉዞ ግን የላቀ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የማያቋርጥ ክትትልን፣ ቀጣይነት ያለው ሥራንና መጠነ ሰፊ ኢንቨስትመንትን የሚጠይቅ ነው።
የትምህርት ጥራትን ማሻሻል የአንድ ጊዜ ዘመቻ ወይም የአጭር ጊዜ ፕሮጀክት ሳይሆን፣ የማያቋርጥ የሀብት በጀት መድቦ በትጋት መሥራትን የሚጠይቅ የረጅም ጊዜ ብሔራዊ ኢንቨስትመንት ነው።
የመማሪያ ቁሳቁሶችን ማሟላት፣ የነፍስ ወከፍ መጻሕፍት ተደራሽነትን ማረጋገጥ፣ የአስተማሪዎችን ሙያዊ ብቃት ማሳደግ እንዲሁም ዘመናዊ መሠረተ ልማቶችን በየደረጃው መገንባት ቀጣይነት ያለው ከፍተኛ የፋይናንስና የሰው ኃይል ኢንቨስትመንት ይሻል።
የነገው የሀገራችን ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ በ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ማዕቀፍ ውስጥ ሰው ሠራሽ አስተውሎትን (AI) በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ በስፋት ማካተት በመሆኑ፣ በሰው ኃይል ሥልጠና፣ በሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና በመሠረተ ልማት ማሟላት ላይ በግንባር ቀደምትነት መረባረብ ያስፈልጋል።
እንደ ሀገር ትምህርትን የነገ ተስፋችን ማለሚያ ቁልፍ መሣሪያና ለብሔራዊ የትውልድ ግንባታ ተልእኮ አድርገን በመውሰድ፣ መላው ማኅበረሰብ፣ የግል ባለሀብቶችና የትምህርት ባለሙያዎች በባለቤትነት ስሜትና በተግባራዊ ድጋፍ ሊረባረቡ ይገባል።
የሀገራችን ሁለንተናዊ ልማት፣ ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬና ብሔራዊ ሉዓላዊነት አስተማማኝ በሆነ ጽኑ መሠረት ላይ ሊቆም የሚችለው በኩረጃና በሐሰት ሳይሆን በእውነተኛ ዕውቀቱ፣ በታማኝ ስብእናውና በላቀ የፈጠራ ብቃቱ የጸና ትውልድ ሲገነባ ብቻ ነው።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
#ethiopia #ebc #education #educationquality

3 days ago
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ለዶክተር ሰለሞን አሊ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አፀደቀ
#ethiopia | የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ማኔጅመንት ቦርድ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ለዶክተር ሰለሞን አሊ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታውቋል።
ኮሌጁ የባለሙያውን ሰነዶችና የስራ አፈፃፀም በዝርዝር ከገመገመ በኋላ ይህንን ከፍተኛ የትምህርት ማዕረግ አፅድቆላቸዋል።
ፕሮፌሰር ሰለሞን አሊ በህክምና ምርምርና በማይክሮባዮሎጂ ዘርፍ በስፋት የሚታወቁ አንጋፋ ስፔሻሊስት ናቸው።
የምርምር ስራዎቻቸውም በዋናነት በተላላፊ በሽታዎች፣ በፀረ ጀርም መድኃኒቶች መላመድ እንዲሁም አዲስና ዳግም በሚቀሰቀሱ የቫይረስ አይነቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው።
ፕሮፌሰሩ ባለፉት 20 ዓመታት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅና በጅማ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በመምህርነት፣ በምርምርና በሕክምና አገልግሎት አገራቸውን በቅንነት ያገለገሉ ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ያላቸው ምሁር ናቸው።
በማስተማር ስራቸውም በርካታ የሕክምና፣ የጤና ሳይንስ፣ የማይክሮባዮሎጂና የክሊኒካል ሬዚደንት የቅድመና ድህረ ምረቃ ተማሪዎችን አፍርተዋል።
እስካሁንም በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባላቸው የምርምር መጽሔቶች ላይ 56 የምርምር ውጤቶችን ያሳተሙ ሲሆን ስድስት ታላላቅ ዓለም አቀፍ የትብብር የምርምር ፈንዶችንም ማሸነፍ ችለዋል።
በተጨማሪም ፕሮፌሰር ሰለሞን አሊ የሀገሪቱን የምርምርና የማይክሮባዮሎጂ አገልግሎት መሠረተ ልማት ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።
በዚህም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የመጀመሪያውን የጤና ምርምር መጽሔት፣ ዘመናዊ የተላላፊ በሽታዎች የዘረመል ምርምር ላቦራቶሪ፣ ለቀጣይ ጥናቶች የሚሆኑ ናሙናዎችን ለረጅም ጊዜ ማቆያ ማዕከልና የማይክሮባዮሎጂ መረጃዎችን በዲጂታል መንገድ የማደራጃ ሥርዓት መስርተዋል።
ፕሮፌሰር ሰለሞን አሊ በጤናው ዘርፍ ላበረከቱት የላቀ ሙያዊ አስተዋፅኦ በቅርቡ ከጤና ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም የብሔራዊ እውቅና ሽልማት መበርከቱ ይታወሳል።
The Managing Board of Saint Paul’s Hospital Millennium Medical College (SPHMMC), at its regular meeting held today, June 16, 2026, approved the promotion of Dr. Solomon Ali to the rank of Full Professor.
After carefully reviewing her academic, clinical, research, and service achievements, the Board endorsed his promotion in recognition of his outstanding contributions to medical education, research, and institutional leadership
Professor Solomon Ali is a distinguished microbiologist and medical research specialist whose work focuses on infectious diseases, antimicrobial resistance, and emerging/reemerging viral pathogens.
He has served his country for over 20 years at St. Paul’s Hospital Millennium Medical College (SPHMMC) and Jimma University (JU), contributing extensively to academic, clinical, and research activities.
Professor Solomon has trained, mentored, and supervised undergraduate, Master’s, and PhD students, guiding numerous research theses. Throughout his academic and research career, he has published more than 56 articles in reputable international journals and has secured six major competitive international research grants. Prof. Solomon has also played a pivotal role in strengthening research and health service infrastructures.
He has established Millennium Journal of Health, the first scholarly journal in SPHMMC, Infectious Diseases Research and Molecular Laboratory (IDReaM Lab) with integrated bio-banking system, and digitalizing hospital microbiology service laboratory data management system through a DHIS2 based platform.
Recently, Prof. Solomon Ali received national recognition from the Federal Ministry of Health of Ethiopia as the recipient of the 2026 Award for outstanding professional contribution in the health sector.
#stpaulshospital #medicalresearch #microbiology #educationethiopia #healthethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

4 days ago
የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ነው
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ 1መቶ99 የፈተና ጣቢያዎች፣ የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዛሬው ዕለት በይፋ መሰጠት መጀመሩን የከተማዋ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
ከዛሬ ሰኔ 8 ጀምሮ እስከ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚቆየውን ይህንን ከተማ አቀፍ ፈተና ለመውሰድ 85 ሺህ 17 ተማሪዎች ተመዝግበው ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸው ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ በሰጡት መግለጫ፤ ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ በየደረጃው የኮማንድ ፖስት አደረጃጀቶች መዋቀራቸውን ገልጸዋል።
ለፈተናው ሂደት ጥራትና ተዓማኒነት ሲባልም፣ ልምድ ያላቸው የፈተና አስፈጻሚዎች ተመልምለው በየጣቢያዎቹ እንዲመደቡ መደረጉን ጠቁመዋል።
ከጸጥታ አኳያም ፈተናው ያለምንም ችግር እንዲከናወን አስፈላጊው የጸጥታ አካላት ጥበቃና የክትትል ሥራ መመቻቸቱ ተመላክቷል።
በአሁኑ ሰዓት በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች ሂደቱን የሚከታተሉ የቢሮው አመራሮችና ባለሙያዎች በሥራ ላይ እንደሚገኙ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
Ethio Fm

Sponsored by
Surafel
5 days ago
በሸገር ከተማ ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና…
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሸገር ከተማ አስተዳደር ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጊያለሁ አለ።
የከተማዋ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፊራኪያ ካሳሁን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት÷ ዘንድሮው 8 ሺህ 932 ተማሪዎች በከተማ አስተዳደሩ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ይወስዳሉ።
በከተማ አስተዳደሩ ለፈተናው ድጋፍ ከማድረግ ጀምሮ ግብዓቶችን በማሟላት ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ አስፈላጊ ዝግጅት መደረጉን አመላክተዋል።
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ጠንካራ የድጋፍ እና የክትትል ሥርዓት መዘርጋቱን ጠቅሰው÷ በዚህም በከተማዋ የትምህርት ተቋማትን ማስፋፋት፣ የተማሪዎችን ተሳትፎ ማጠናከርና ትምህርት ቤቶች የመገንባት ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።
እንዲሁም የመምህራንን አቅም ማጠናከር እና የመማሪያ መሳሪያዎችን በማሟላት ለመማር ማስተማር ስራ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል።
በትምህርት ጥራት ላይ ያሉ ክፍተቶችን በመለየትና በመቅረፍ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በተጠናከረ መንገድ መሰራቱንም አመልክተዋል።
በታሪክ አዱኛ

7 days ago
የ8 ዓመታት ምጥ በምስጋና ሊደመደም ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያ ምስጋና ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ላለፉት ስምንት ዓመታት በፍርድ ቤት ስትከራከርበት የቆየችውን መሬት በሕጋዊ መንገድ ሙሉ በሙሉ መረከቧንና በአዲስ አበባ 7ኛዋን፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ 780ኛዋን አዲስ አጥቢያ (የአምልኮ ስፍራ) በይፋ እንደምትጀምር አስታወቀች። ቤተ ክርስቲያኗ ይህንን ያስታወቀችው በለቡ አጥቢያ በሚገኘው አዲሱ ስፍራ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጠችው መግለጫ ነው።
የኢትዮጵያ ምስጋና ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያ ፕሬዚዳንት መጋቢ ዶ/ር ጌታሁን ነሲቡ
እንደገለጹት ፣ ይህ አዲሱ መሬት ከነሐሴ 2010 ዓ.ም. ጀምሮ የተሰጣት ቢሆንም፣ ባጋጠሙ የተለያዩ ተግዳሮቶችና ክርክሮች ምክንያት ላለፉት 8 ዓመታት ጉዳዩ በሕግ ጥላ ሥር ቆይቷል። አሁን ላይ ግን ሁሉንም ፈተናዎች በጽናትና በሕጋዊ መንገድ አልፋ መሬቱን በይፋ ለመረከብ መቻሏን ገልጸዋል።
በለቡ ከሆፕ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ በሚገኘው በዚህ አዲስ ስፍራ ላይ ቤተ ክርስቲያኗ የሚከተሉትን ሦስት ዘመናዊ የልማት ዕቅዶች ይዛ መነሳቷን አስታውቃለች። በመሆኑም
-ለምዕመናን ምቹ የሆነ ዘመናዊ የማምለኪያ አዳራሽ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ሁለንተናዊ ሥራዎች የሚያሳልጡ የቢሮዎች ግንባታ ይከናወናል።
-በአሁኑ ወቅት አገልግሎት እየሰጠ ለሚገኘው የስነ-መለኮት ኮሌጅ ተማሪዎችና አገልጋዮች የሚውሉ ዘመናዊ የማደሪያ ክፍሎች (Dormitories) ይገነባሉ።
-ግንባታው የአካባቢን ውበትና ስነ-ምህዳር ባገናዘበ መልኩ የሚከናወን ሲሆን፣ የወንዝ ዳርቻውን ልማት፣ የአረንጓዴ ስፍራዎችንና መንገዶችን ያካተተ ይሆናል። ይህም ለአካባቢው ማኅበረሰብ ጭምር ምቾትና ውበት የሚሰጥ ሥራ እንደሆነ ተገልጿል።
ቤተ ክርስቲያኗ ከዚህ ቀደምም በቦሌ አራብሳ ተመሳሳይ ዘመናዊ የዋና ፅህፈት ቤት እና የአጥቢያ አገልግሎት ሕንጻ በመገንባት ማኅበራዊ ፋይዳ ያላቸውን ሥራዎች ስታከናውን መቆየቷ ይታወሳል።
እነዚህን ታላላቅ የልማት ሥራዎች ከመጀመሯ በፊት፣ ያለፉትን 8 ዓመታት ፈታኝ የፍርድ ቤት ጉዞዎችን በድል እንድትወጣ የረዳትን እግዚአብሔርን ለማመስገን ልዩ የምስጋና መርሃ-ግብር ማዘጋጀቷን ቤተ ክርስቲያኗ አስታውቃለች።
በዚህም መሠረት የፊታችን ሰኔ 7 በአዲስ አበባ ያሉ የቤተ እምነቱ አጥቢያዎች በሙሉ በጋራ በመሆን ሙሉ ቀን የሚቆይ ታላቅ ታሪካዊ የጸሎት እና የአምልኮ ፕሮግራም ያካሂዳሉ።
የቤተ እምነቱ መሪዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና መላው ምዕመናን በተገኙበት ልዩ የምስጋና ፕሮግራም ይኖራል።
በየሳምንቱ እሁድ ከሰዓት በኋላ በዚህ በአዲሱ የለቡ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መደበኛ የአምልኮ አገልግሎት በይፋ መቀጠል ይጀምራል።
የኢትዮጵያ ምስጋና ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 45 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ውስጥ በወንጌል አገልግሎት እንዲሁም በልማትና ማኅበራዊ ሥራዎች ላይ በስፋት ስትሳተፍ የቆየች ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ሁሉም ክልሎች ውስጥ ከ780 በላይ አጥቢያዎች እንዳሏት በመግለጫው ወቅት ተነግሯል። ቤተ ክርስቲያኗ ለዚህ ስኬት መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉ የፍትሕ አካላት እና ለሚዲያ ተቋማት ምስጋናዋን አቅርባለች።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በምርምር እና በስትራቴጂያዊ ትንተና የተደገፈ “የተከዜ ፖለቲካ፤ ኃይል፣ ማንነትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት” የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ሊቀርብ መሆኑ ተገለጸ።
የመጽሐፉ ደራሲ ዶክተር ቹቹ አለባቸው ሲሆኑ፣ ደራሲው በአማራና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳዮች ትንታኔዎችን በማቅረብ የሚታወቁ ነባር ፖለቲከኛ ናቸው፡፡
ዶክተር ቹቹ በአዲሱ ሥራቸው በተከዜ ተፋሰስ እና በወልቃይት-ጠገዴ፣ ጠለምት ቀጠና ዙሪያ የሚታዩ ፖለቲካዊ፣ ታሪካዊ፣ ማኅበራዊ እና የደኅንነት ጉዳዮችን በምሁራዊ መንገድ የሚተነትን መሆኑ ተጠቁሟል።
ደራሲው እንደሚገልጹት፣ የተከዜ ተፋሰስ የውኃ ምንጭ ወይም የተፈጥሮ መልክዓ ምድር ብቻ ሳይሆን፣ ከኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ ከቀጠናዊ የኃይል ሚዛን፣ ከሕዝቦች ማንነት እና ከብሔራዊ ደኅንነት ጋር በቀጥታ የተሳሰረ ስትራቴጂያዊ ቀጠና ነው። መጽሐፉም ይህንን አቀራረብ በመነሻ በማድረግ የአካባቢውን ፖለቲካዊ እውነታ በጂኦ-ፖለቲካ፣ በኃይል፣ በማንነት እና በብሔራዊ ደኅንነት ማዕቀፎች አንጻር ይመረምራል።
መጽሐፉ በተለይ በ2013 ዓ.ም. በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ጦርነት እንደ መነሻ በመውሰድ፣ የተከዜ ተፋሰስ በሀገሪቱ የደኅንነት አወቃቀር ውስጥ ያለውን ስልታዊ ሚና በዝርዝር ያስረዳል። ደራሲው እንደሚገልጹት፣ የተፋሰሱን ይዞታ መቆጣጠር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት፣ በውኃ ሀብት አስተዳደር እና በቀጠናዊ ግንኙነቶች ላይ ወሳኝ ተፅዕኖ ያሳድራል።
በአጠቃላይ 20 ምዕራፎችን ያካተተው መጽሐፉ በአራት ዋና ክፍሎች ተዋቅሯል።
የመጀመሪያው ክፍል በጂኦ-ፖለቲካ ላይ ያተኩራል፤ የተከዜ ተፋሰስ ከኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት፣ ከዓባይ ተፋሰስ ፖለቲካ እና ከቀጠናዊ የኃይል አሰላለፍ ጋር ያለውን ግንኙነት ይተነትናል።
ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ኃይልን እንደ ፖለቲካዊ መሣሪያ በመመልከት፣ አካባቢውን መቆጣጠር ለባለቤቱ የሚሰጠውን ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ተምሳሌታዊ ጥቅሞች ያብራራል። እንደ መጽሐፉ ገለጻ፣ ተከዜ ተራ የመሬት ክፍል ሳይሆን የተለያዩ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች የሚገናኙበት የኃይል መድረክ ነው።
ሦስተኛው ክፍል በማንነት ፖለቲካ ላይ ያተኩራል። በዚህ ክፍል የብሔር ፌዴራሊዝም፣ የሥነ-ሕዝብ ለውጦች፣ የነባር እና የመጤ ትርክቶች እንዲሁም የማንነት ጥያቄዎች በታሪካዊ እና በንድፈ-ሐሳባዊ መሠረቶች ይመረመራሉ።
ደራሲው በወልቃይት፣ በጠገዴ እና በጠለምት አካባቢዎች የተፈጠሩ የማንነት ግጭቶችን እና የሕዝብ አወቃቀር ለውጦችን በሕጋዊ እና በታሪካዊ ማስረጃዎች ተደግፈው መቅረባቸውን ያስረዳሉ።
አራተኛው እና የመጨረሻው ክፍል የብሔራዊ ደኅንነት ጉዳዮችን ያዳስሳል። ይህ ክፍል የውኃ ደኅንነት፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት፣ የውጭ ስጋቶች፣ የፌዴራላዊ አንድነት ተግዳሮቶች እና የሰላም ግንባታ አማራጮችን በስፋት ይተነትናል።
በመጨረሻም ለፖሊሲ አውጪዎች እና ለውሳኔ ሰጪዎች የሚጠቅሙ የፖሊሲ ምክረ ሐሳቦችን ያቀርባል።ከይዘቱ ባሻገር መጽሐፉ የተለያዩ የአገር ውስጥ፣ የቀጠና እና የዓለም አቀፍ ተዋናዮችን ሚና በጥልቀት የሚያብራራ መሆኑ ተገልጿል። የፌዴራል መንግሥት፣ የክልል ፖለቲካ ኃይሎች፣ ጎረቤት አገራት እና በቀጠናው ፍላጎት ያላቸው ዓለም አቀፍ ኃይሎች በተከዜ ፖለቲካ ላይ የሚኖራቸው ተፅዕኖ በተለየ ትኩረት ቀርቧል።
ደራሲው መጽሐፉ ለፖሊሲ አውጪዎች፣ ለታሪክ ተመራማሪዎች፣ ለደኅንነት ባለሙያዎች፣ ለዲፕሎማቶች እና ለከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ጠቃሚ የማጣቀሻ ግብዓት እንደሚሆን ገልጸዋል።
የመጽሐፉ ዋና ዓላማም በተከዜ ተፋሰስ ዙሪያ ያሉ ውስብስብ ጉዳዮችን በምሁራዊ እይታ በማቅረብ፣ ለዘላቂ ሰላም፣ ለአገራዊ አንድነት እና ለጋራ ልማት የሚረዱ የፖሊሲ አማራጮችን ማበርከት መሆኑ ተጠቅሷል።
መጽሐፉ በከፍተኛ የቋንቋ ደረጃ እና በምሁራዊ ጥልቀት የተጻፈ ነው የተባለለት ሲሆን፤ ወቅታዊ ፖለቲካዊ ትንተናዎች ከታሪካዊ እውነታዎች ጋር ይበልጥ የተሰናሰሉ፣ መሆኑ ሥራው ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ትልቅ አበርክቶ እንደሚኖረው ተጠቁሟል፡፡
የመጽሐፉ ደራሲ ዶክተር ቹቹ አለባቸው እንዳረጋገጡት፣ “የተከዜ ፖለቲካ፤ ኃይል፣ ማንነትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት” የተሰኘው መጽሐፋቸው የፊታችን ዕረቡ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በገበያ ላይ ይውላል፡፡

የኢትዮጵያ ምስጋና ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን የ3 ሳምንታት ታላቅ የምስጋና እና የጸሎት መርሃ-ግብር አዘጋጀች!
#fastmereja I የኢትዮጵያ ምስጋና ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ከተማ ለቡ አካባቢ ከመንግስት የተሰጣትንና ላለፉት ስምንት ዓመታት በፍርድ ቤት ክርክር ውስጥ የነበረውን 10 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው መሬት በሕጋዊ መንገድ በይፋ መረከቧን አስታወቀች።
ቤተ ክርስቲያኒቱ በዚህ አዲስ ይዞታ ላይ በአገር አቀፍ ደረጃ 78ዐኛውን፣ በአዲስ አበባ ደግሞ 7ኛውን አዲስ አጥቢያ በይፋ እንደምትጀምር በዛሬዉ እለት በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጻለች።
የኢትዮጵያ ምስጋና ወንጌላዊት ቤተክርስትያን ፕሬዝዳንት መጋቢ ዶ/ር ጌታሁን ነሲቡ በለቡ አጥቢያ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳመለከቱት፤ አዲሱ ይዞታ (ለቡ 01 ሆፕ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ) በ2010 ዓ.ም ከመንግስት የተሰጠ ቢሆንም፣ ባለፉት ስምንት ዓመታት ባጋጠሙ የተለያዩ ይዞታ ነክ ተግዳሮቶችና ክርክሮች ምክንያት ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ መቆየቱን ገልፀዉ በአሁኑ ወቅት ግን ተቋሙ ሁሉንም ፈተናዎች በሕጋዊ መንገድ በማለፍ መሬቱን በይፋ ለመረከብ መቻሉን አስታውቀዋል።
በይፋ በተረከቡት አዲሱ ስፍራ ላይ በቀጣይ ታላላቅ የልማት ዕቅዶች እንደሚከናወኑ የተገለፀ ሲሆን ከታቀዱት ዋና ዋና ፕሮጀክቶች መካከል የዘመናዊ አምልኮ እና የቢሮ ሕንጻ ግንባታ፣ ለስነ-መለኮት ኮሌጅ አገልግሎት የሚውሉ ዘመናዊ የተማሪዎችና የአገልጋዮች ማደሪያ ክፍሎች (Dormitories) ግንባታ፣ እና ከአካባቢው ወንዝ ተያያዥነት ያለው የ10 ሺህ ካሬ የወንዝ ዳርቻ ልማትና የአረንጓዴ ስፍራ ጥበቃ እንደሚገኙበት ጠቁመዋል።
ቤተ ክርስቲያኒቱ እነዚህን ታላላቅ የልማትና የህንጻ ግንባታ ዕቅዶች ከመጀመሯ በፊት፣ ባለፉት 8 ዓመታት የነበሩትን ፈታኝ የፍርድ ቤት ጉዞዎች በድል እንድትወጣ የረዳትን አምላክ ማመስገን ቀዳሚ ተግባሯ መሆኑን ገልጻ የሦስት ሳምንት ተከታታይ መርሃ-ግብር ማዉጣቷን አስታዉቃለች።
የፊታችን እሁድ ሰኔ 07 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ያሉ የቤተ እምነቱ አጥቢያዎች በሙሉ በጋራ በመሆን ሙሉ ቀን የሚቆይ ታላቅ ታሪካዊ የጸሎት እና የአምልኮ ፕሮግራም ያካሂዳሉ።
እሁድ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ደግሞ የቤተ እምነት መሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ልዩ የምስጋና ፕሮግራም ይደረጋል።
ከእሁድ ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በየሳምንቱ እሁድ ከሰዓት በኋላ በዚህ በአዲሱ 7ኛ ለቡ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መደበኛ የአምልኮ አገልግሎት በይፋ እንደሚቀጥል ታውቋል።
የኢትዮጵያ ምስጋና ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 45 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ውስጥ በወንጌል አገልግሎት እንዲሁም በልማትና ማኅበራዊ አገልግሎቶች ላይ በስፋት ስትሳተፍ የቆየች ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ሁሉም ክልሎች ላይ ከ780 በላይ አጥቢያዎች እንዳሏት ከመግለጫው ለመረዳት ተችሏል።
ዶ/ር ጌታሁን ነሲቡ ለዚህ ታሪካዊ ስኬት መሳካት አምላካቸውን እያመሰገኑ፣ ክርስቲያኒቱ ጎን ለቆሙ አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

8 days ago
አስቸኳይ መልእክት ከገዳም እናቶች
እኛ የወሎ መርሣ ሰዳቱ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም እናቶች እና አባቶች እንዲሁም የአብነት ተማሪዎች በውኃ ጥም እየተሰቃዬን እንገኛለን። ለዚህም ከገጠር መጥተን አዲስ አበባ ከተቀመጥን ሁለተኛ ሳምንታችንን ያዝን።
አመጣጣችንም ግንቦት 29 እና 30/2018 የቀጥታ ሥርጭት የገቢ ማሰባሰብ እና የእራት መርሐግብር አድርገን ለገዳሙ የውኃ ፕሮጀክት 10,000,000 /ዐሥር ሚሊዬን ብር/ ለማሰባሰብ ነበር። ነገር ግን የአርሲው ጭፍጨፋ በወገኖቻችን እና በቤተክርስቲያን ላይ ተፈጸመ። እኛም ልባችን ተሠበረ። እንዴት በዚህ ሰዓት እራት እና ቀጥታ ሥርጭት እያልን እንለምናለን ቢያንስ ለአንድ ሳምንት እናራዝመው ብለን ወደ ሰኔ 5 እና 6 አርብ እና ቅዳሜ አሸጋግረነዋል።
ይኽን ስናደርግ እኛ ከገዳም የመጣን መነኮሳት ከሰው ቤት ለ15 ቀናት እንደምንቀመጥ ስናስብ በሁለት ነገር እናዝናለን። አንደኛ ከተማ መቀመጥ ለኛ አይገባም። ሁለተኛ ማረፊያ ለሰጡን ወገኖች ሸክም እንሆናለን።
ይኹንና ከገጠመን ኅዘን የሚበልጥ ነገር ስለሌለ አዛውረነዋል። እናንተም ሰኔ 5 እና 6
ከምሽቱ 1፡00 ጀምሮ በቀጥታ ሥርጭት እየገባችሁ ልጆቻችን አለን በሉን።
አደራ ልጆቻችን
ለበለጠ መረጃ በዚህ ስልክ ደውሉልን
0911644781
0911981096
0911216958
0911671379
0911631126
በዚህ አካውንትም የምትችሉትን አግዙን
ገዳሟን የምታግዙባቸው አካውንቶች
ንግድ ባንክ1000003780779
አባይ ባንክ 9841011002322017
አሐዱ ባንከ 0088911720301
https://gofund.me/401f3b99...
8 days ago
በዲጂታሉ ዓለም የጀመርነው ታሪካዊ ምዕራፍ ብሔራዊ ርዕያችንን የምናፋጥንበት መነሻ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዲጂታሉ ዓለም በልኩ ለመዘጋጀት የጀመርነው ታሪካዊ ምዕራፍ የጉዟችን ማብቂያ ሳይሆን ብሔራዊ ርዕያችንን ይበልጥ የምናፋጥንበት መነሻ ነው አሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ በሦስት ዓመታት ውስጥ ለማሳካት የታቀደውን የ5 ሚሊየን ኮደሮች ግብ ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ማሳካት ተችሏል ብለዋል።
የ5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደሮች ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም መጀመሩን አስታውሰው፥ በኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ፣ በመረጃ ትንተና፣ በአንድሮይድ ሶፍትዌር ልማትና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ ትምህርት ሲሰጥ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡
በዚህም 5 ሚሊየን 5ሺህ 146 ሰልጣኞች መመዝገባቸውን ገልጸው፥ ከእነዚህም ውስጥ ከ3 ሚሊየን በላይ ሰልጣኞች ስልጠናውን አጠናቅቀዋል ነው ያሉት።
ይህ ስኬት የሕዝባችንን ቁርጠኝነት እና ወሰን የሌለው አቅም ማረጋገጫ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
እስከ ነሐሴ 2018 ዓ.ም. ድረስ የሰልጣኞችን ቁጥር 7 ሚሊየን ለማድረስ የተሰነቀውን ግብ ለማሳካት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የዚህ ብሔራዊ ተልዕኮ አካል እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ለወጣት ተማሪዎቻችን መጭው የክረምት ወቅት ትልቅ ዕድላችሁ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በዚህ የክረምት ወቅት ስልጠናውን በመውሰድ ተማሪዎች ብቻ ሳትሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላችሁ የዲጂታል መሪዎች እንድትሆኑ አሳስባለሁ ነው ያሉት።
ሥልጠናዎቹ ሙሉ በሙሉ በነጻ የሚሰጡ ሲሆን የምስክር ወረቀቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ:
ethiocoders.et/

9 days ago
በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል በሚያስችሉ ስራዎች ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የሚያስችሉ የሪፎርም ስራዎች ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የክልሉ ትምህርት ቢሮ።
በክልሉ "የዘመነ ፈተና አስተዳደር ስርዓት፤ ለላቀ የትምህርት ጥራት" በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀ የ2018 ዓ.ም ሀገራዊና ክልላዊ ፈተና አስተዳደር ምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ በዚህ ወቅት÷ ባለፉት ዓመታት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የሚያስችሉ የሪፎርም ስራዎች ላይ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።
የትምህርት ስርዓቱን ለማሻሻል በርካታ የሪፎርም ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቅሰው÷ ጥራት ያለው ትምህርት ለማቅረብ ጥራት ያለው የምዘና ስርዓት ውስጥ ማለፍ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ለዚህም የፈተና ምዘና እና የፈተና አስተዳደር ሥርዓት ማዘመን አስፈላጊ መሆኑን አጽንዖት ሰጥተዋል።
በዘንድሮው ክልላዊ ፈተና የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል 89 ሺህ 538 ተማሪዎችን ለማስፈተን ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል።
የሀገር አቀፍ እና ክልል አቀፍ ደረጃ የሚሰጡ ፈተናዎችን ከኩረጃ የጸዳ እንዲሆኑ እና ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወን መቻሉም ተገልጿል።
በመድረኩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾን (ዶ/ር) ጨምሮ የሚመለከታቸው ባለድርሻዎች መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ለፋና ዲጂታል ገልጿል።

10 days ago
አስቸኳይ መልእክት ከመርሣ ተክለሃይማኖት ገዳም አባቶች
እኛ የወሎ መርሣ ሰዳቱ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም እናቶች እና አባቶች እንዲሁም የአብነት ተማሪዎች በውኃ ጥም እየተሰቃዬን እንገኛለን። ለዚህም ከገጠር መጥተን አዲስ አበባ ከተቀመጥን ሁለተኛ ሳምንታችንን ያዝን።
አመጣጣችንም ግንቦት 29 እና 30/2018 የቀጥታ ሥርጭት የገቢ ማሰባሰብ እና የእራት መርሐግብር አድርገን ለገዳሙ የውኃ ፕሮጀክት 10,000,000 /ዐሥር ሚሊዬን ብር/ ለማሰባሰብ ነበር። ነገር ግን የአርሲው ጭፍጨፋ በወገኖቻችን እና በቤተክርስቲያን ላይ ተፈጸመ። እኛም ልባችን ተሠበረ። እንዴት በዚህ ሰዓት እራት እና ቀጥታ ሥርጭት እያልን እንለምናለን ቢያንስ ለአንድ ሳምንት እናራዝመው ብለን ወደ ሰኔ 5 እና 7 አርብ እና ቅዳሜ አሸጋግረነዋል።
ይኽን ስናደርግ እኛ ከገዳም የመጣን መነኮሳት ከሰው ቤት ለ15 ቀናት እንደምንቀመጥ ስናስብ በሁለት ነገር እናዝናለን። አንደኛ ከተማ መቀመጥ ለኛ አይገባም። ሁለተኛ ማረፊያ ለሰጡን ወገኖች ሸክም እንሆናለን።
ይኹንና ከገጠመን ኅዘን የሚበልጥ ነገር ስለሌለ አዛውረነዋል። እናንተም ሰኔ 5 እና 6
ከምሽቱ 1፡00 ጀምሮ በቀጥታ ሥርጭት እየገባችሁ ልጆቻችን አለን በሉን።
አደራ ልጆቻችን
ለበለጠ መረጃ በዚህ ስልክ ደውሉልን
0911644781
0911981096
0911216958
0911671379
0911631126
በዚህ አካውንትም የምትችሉትን አግዙን
እኛ የወሎ መርሣ ሰዳቱ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም እናቶች እና አባቶች እንዲሁም የአብነት ተማሪዎች በውኃ ጥም እየተሰቃዬን እንገኛለን። ለዚህም ከገጠር መጥተን አዲስ አበባ ከተቀመጥን ሁለተኛ ሳምንታችንን ያዝን።
አመጣጣችንም ግንቦት 29 እና 30/2018 የቀጥታ ሥርጭት የገቢ ማሰባሰብ እና የእራት መርሐግብር አድርገን ለገዳሙ የውኃ ፕሮጀክት 10,000,000 /ዐሥር ሚሊዬን ብር/ ለማሰባሰብ ነበር። ነገር ግን የአርሲው ጭፍጨፋ በወገኖቻችን እና በቤተክርስቲያን ላይ ተፈጸመ። እኛም ልባችን ተሠበረ። እንዴት በዚህ ሰዓት እራት እና ቀጥታ ሥርጭት እያልን እንለምናለን ቢያንስ ለአንድ ሳምንት እናራዝመው ብለን ወደ ሰኔ 5 እና 7 አርብ እና ቅዳሜ አሸጋግረነዋል።
ይኽን ስናደርግ እኛ ከገዳም የመጣን መነኮሳት ከሰው ቤት ለ15 ቀናት እንደምንቀመጥ ስናስብ በሁለት ነገር እናዝናለን። አንደኛ ከተማ መቀመጥ ለኛ አይገባም። ሁለተኛ ማረፊያ ለሰጡን ወገኖች ሸክም እንሆናለን።
ይኹንና ከገጠመን ኅዘን የሚበልጥ ነገር ስለሌለ አዛውረነዋል። እናንተም ሰኔ 5 እና 6
ከምሽቱ 1፡00 ጀምሮ በቀጥታ ሥርጭት እየገባችሁ ልጆቻችን አለን በሉን።
አደራ ልጆቻችን
ለበለጠ መረጃ በዚህ ስልክ ደውሉልን
0911644781
0911981096
0911216958
0911671379
0911631126
በዚህ አካውንትም የምትችሉትን አግዙን
11 days ago
ኬብሮን አማኑኤል በ“ጣፋጭ ሕይወት” ልዩ ተመስጋኝ ሆናለች
#fastmereja I በጎ ተግባርን ማዕከል በማድረግ ለ6ኛ ዙር በተካሄደው የ“ጣፋጭ ሕይወት” የምስጋና መርሃ ግብር ላይ፣ “ልጄ ሆይ” በተሰኘው የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴዋ የምትታወቀው ኬብሮን አማኑኤል የዘንድሮው የ“ልዩ ተመስጋኝ” ተሸላሚ ሆና ተመርጣለች።
ባለፉት ዓመታት በልጆች፣ በወላጆችና በችግረኛ ማህበረሰብ ክፍሎች ላይ ትኩረት አድርጋ ስትሠራ የቆየችው ኬብሮን አማኑኤል፣ ማኅበረሰቡን ማገልገል ግዴታዋ እንደሆነ ብታምንም ድርጅቱ ለታናናሾች ተምሳሌት እንድትሆንና ለወደፊቱ ይበልጥ እንድትተጋ ይህንን ዕውቅና እንደሰጣት ተገልጿል። ተሸላሚዋ ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ብቻ 38 ሕፃናትን በትምህርት፣ በቁሳቁስና በነፃ ሕክምና ከመርዳቷም በላይ በሚኪሊላንድ መንግሥት ትምህርት ቤት የእናት አምባሳደር በመሆን አገልግላለች። በተጨማሪም በሆለታ፣ በፋኖስ እና በጅማ ለሚገኙ ከ3,000 በላይ ሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገች ሲሆን፣ በአረጋውያን፣ በተጣሉ ሕፃናት እና በካንሰር ታማሚዎች ዘንድ በመገኘት ማህበራዊ ድጋፍ ስትሰጥ መቆየቷ ተመልክቷል።
በዓመት ሦስት ጊዜ የደም ልገሳ ፕሮግራም በማዘጋጀትና ብቻቸውን ልጆቻቸውን የሚያሳድጉ እናቶችን እንዲሁም ከሱስ ለማገገም የሚጥሩ ሴቶችን በመደገፍ የምትታወቀው ኬብሮን፣ ሽልማቱን ከተቀበለች በኋላ ባስተላለፈችው መልዕክት “ውስጥ ካለኝ ሳይሆን ከሌለኝ ያካፈልኩት የኖርኩት ኑሮዬ ነው” በማለት ምስጋናዋን አቅርባለች። ወደፊትም በ“ልጄ ሆይ” ተግባሯ የተጣለባትን አደራ ለመወጣት ቃል የገባች ሲሆን፣ በገንዘብና በሃሳብ ከጎኗ ለቆሙት የ“200 ብር ቻሌንጅ” ተሳታፊዎችና የቅርብ ደጋፊዎቿ ምስጋናዋን አቅርባለች።
በርቺ ብለናል 🤝

13 days ago
ከ560 ሺህ በላይ ተፈታኞች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ ተመዝግበዋል። - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍልብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 24/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም ይሰጣል።
የመልቀቂያ ፈተናውን ለመውሰድ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ560 ሺህ በላይ ተፈታኞች መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።
ከተመዘገቡት ውስጥ አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ፈተናውን በበይነ-መረብ እንደሚወስዱ የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የመሰረተ ልማት ውስንነት ባሉባቸው አካባቢዎች ፈተናው በወረቀት እንደሚሰጥ ገልፀዋል።
የፈተና ሒደቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ የኢንተርኔት እና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አስተማማኝነትን ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሠራ መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል።

#በኢተማሪ የትም ሆነው ሕልምዎን ያሳኩ!!
✅ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞችን በልዩ ሁኔታ ለፈተና ያዘጋጃል
📚 ከ9-12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ጠቃሚ የትምህርት ማቴሪያሎች
❔📝 ራስን መገምገሚያ ኩዊዞች፣ አጫጭር ኖቶች እንዲሁም ያለፉት ዓመታት ጥያቄዎች ከጥልቅ ማብራሪያ ጋር!
💬 ለዕለታዊ A፣ ለሳምንታዊ B ብለው ወደ 9429 ይላኩ!
🌐 ለኢተማሪ ብቻ የሚያገለግል የኢንተርኔት ጥቅል ለዕለታዊ 75 ሜ.ባ፣ ለሳምንታዊ 500 ሜ.ባ በነጻ ያገኛሉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡ http://www.etemari.net
#etemari #ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና በአርሲ ዞን በተፈጸሙ ጥቃቶች የሰው ህይወት ጠፋ
በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ምርጫውን ለማደናቀፍና በህዝቡ ላይ ሽብር ለመፍጠር የታለሙ ጥቃቶች መፈጸማቸውን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች የስፖርት ውድድር (Champions League) በመመልከት ላይ እያሉ በተሰነዘረ ጥቃት አንድ ተማሪ ሲሞት 26 የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በተመሳሳይ ሁኔታ በአርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ "ሸኔ" ተብሎ በሚጠራው ቡድን በተሰነዘረ ጥቃት አምስት የሚሊሻ አባላት፣ ሶስት የፖሊስ አባላት እና አራት ሲቪሎች መገደላቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በጥቃቱ አንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፣ የመንግስት ጤና ጣቢያ እና የቀበሌ ጽህፈት ቤት መቃጠላቸው እንዲሁም 65 የግለሰብ ቤቶች መውደማቸው ተገልጿል።
በተጨማሪም በሸርካ እና በእንቆሌ ዋቤ ወረዳዎች ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውና ታግተው የነበሩ ግለሰቦች ህይወት ማለፉ በመግለጫው ተጠቅሷል።

14 days ago
የመርሐግብር ለውጥ
ከግንቦት 29 እና 30 ወደ ሰኔ 5 እና 6 ተዛውሯል
ከሕንፃ ቤተክርስቲያን ሕንፃ ሥላሴ ይቀድማል
እኛ የወሎ መርሣ ሰዳቱ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም እናቶች እና አባቶች እንዲሁም የአብነት ተማሪዎች በውኃ ጥም እየተሰቃዬን እንገኛለን። ለዚህም ከገጠር መጥተን አዲስ አበባ ከተቀመጥን ሳምንት አለፈን።
አመጣጣችንም ግንቦት 29 እና 30/2018 የቀጥታ ሥርጭት የገቢ ማሰባሰብ እና የእራት መርሐግብር አድርገን ለገዳሙ የውኃ ፕሮጀክት 10,000,000 /ዐሥር ሚሊዬን ብር ለማሰባሰብ ነበር። ነገር ግን የአርሲው ጭፍጨፋ በወገኖቻችን እና በቤተክርስቲያን ላይ ተፈጸመ። እኛም ልባችን ተሠበረ። እንዴት በዚህ ሰዓት እራት እና ቀጥታ ሥርጭት እያልን እንለምናለን ቢያንስ ለአንድ ሳምንት እናራዝመው ብለን ወደ ሰኔ 5 እና 7 አርብ እና ቅዳሜ አሸጋግረነዋል።
ይኽን ስናደርግ እኛ ከገዳም የመጣን መነኮሳት ከሰው ቤት ለ15 ቀናት እንደምንቀመጥ ስናስብ በሁለት ነገር እናዝናለን። አንደኛ ከተማ መቀመጥ ለኛ አይገባም። ሁለተኛ ማረፊያ ለሰጡን ወገኖች ሸክም እንሆናለን።
ይኹንና ከገጠመን ኅዘን የሚበልጥ ነገር ስለሌለ አዛውረነዋል። እናንተም ሰኔ 5 እና 6
ከምሽቱ 1፡00 ጀምሮ በቀጥታ ሥርጭት እየገባችሁ ልጆቻችን አለን በሉን።
አደራ ልጆቻችን
ለበለጠ መረጃ በዚህ ስልክ ደውሉልን
0911644781
0911981096
0911216958
0911671379
0911631126
ከግንቦት 29 እና 30 ወደ ሰኔ 5 እና 6 ተዛውሯል
ከሕንፃ ቤተክርስቲያን ሕንፃ ሥላሴ ይቀድማል
እኛ የወሎ መርሣ ሰዳቱ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም እናቶች እና አባቶች እንዲሁም የአብነት ተማሪዎች በውኃ ጥም እየተሰቃዬን እንገኛለን። ለዚህም ከገጠር መጥተን አዲስ አበባ ከተቀመጥን ሳምንት አለፈን።
አመጣጣችንም ግንቦት 29 እና 30/2018 የቀጥታ ሥርጭት የገቢ ማሰባሰብ እና የእራት መርሐግብር አድርገን ለገዳሙ የውኃ ፕሮጀክት 10,000,000 /ዐሥር ሚሊዬን ብር ለማሰባሰብ ነበር። ነገር ግን የአርሲው ጭፍጨፋ በወገኖቻችን እና በቤተክርስቲያን ላይ ተፈጸመ። እኛም ልባችን ተሠበረ። እንዴት በዚህ ሰዓት እራት እና ቀጥታ ሥርጭት እያልን እንለምናለን ቢያንስ ለአንድ ሳምንት እናራዝመው ብለን ወደ ሰኔ 5 እና 7 አርብ እና ቅዳሜ አሸጋግረነዋል።
ይኽን ስናደርግ እኛ ከገዳም የመጣን መነኮሳት ከሰው ቤት ለ15 ቀናት እንደምንቀመጥ ስናስብ በሁለት ነገር እናዝናለን። አንደኛ ከተማ መቀመጥ ለኛ አይገባም። ሁለተኛ ማረፊያ ለሰጡን ወገኖች ሸክም እንሆናለን።
ይኹንና ከገጠመን ኅዘን የሚበልጥ ነገር ስለሌለ አዛውረነዋል። እናንተም ሰኔ 5 እና 6
ከምሽቱ 1፡00 ጀምሮ በቀጥታ ሥርጭት እየገባችሁ ልጆቻችን አለን በሉን።
አደራ ልጆቻችን
ለበለጠ መረጃ በዚህ ስልክ ደውሉልን
0911644781
0911981096
0911216958
0911671379
0911631126
15 days ago
የኢትዮጵያ የፋሽን ባለሙያዎች በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ስራዎቻቸውን ሊያስተዋውቁ ነው
#ethiopia | ታዋቂዋ የካሜሩን አርቲስት ሽሪ አቹ የአፍሪካን አህጉራዊ ትስስር በስነ-ጥበብና በፋሽን ለማጠናከር ያለመውን ፓን አፍሪካን ኢኒሼቲቭ የተሰኘ ዓለም አቀፍ የጨርቅ ዲዛይን ፕሮጀክት ይፋ አድርጋለች።
ይህንን ተከትሎም የኔክስት ፋሽን ዲዛይን ኮሌጅ መምህራንና ተማሪዎች የተሳተፉበት ትልቅ የፋሽን ውድድር በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የአፍሪካን ባህል፣ ታሪክ እና መገለጫዎች በልዩ ሁኔታ በሚያንጸባርቅ ጨርቅ ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀው ይህ ውድድር፣ ከኢትዮጵያ የተሳተፉትን ባለሙያዎች ለመለየት ነገ በሚካሄድ የቀጥታ ስርጭት የፋሽን ትዕይንት እና በዳኞች ምዘና አማካኝነት ማጠቃለያውን ያገኛል።
የፕሮጀክቱ አዘጋጅ ሽሪ አቹ ቀደም ሲል በአውስትራሊያ ባቀረበቻቸው የስዕል ስራዎቿ አማካኝነት በርካታ ተመልካቾች አፍሪካን ለመጎብኘት መነሳሳታቸውንና ይህም ትልቅ እርካታ እንደሰጣት ገልጻለች።
ይህንኑ መነሻ በማድረግ ሰዎችን በባህል ማስተሳሰር የሚችለውን የፓን አፍሪካን ጨርቅ ሀሳብ ያመጣች ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፈው ዓመት በካሜሩን ኤምባሲ ውስጥ ይፋ ተደርጓል።
ጨርቁ የሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምዕራብ አፍሪካን የሚወክሉ የዘጠኝ አገራትን ታሪክና ምልክቶች የያዘ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም አገራቱ ጨርቁን በመጠቀም አስደናቂ ዲዛይኖችን እንዲፈጥሩ እና የአፍሪካን አንድነት እንዲያሳዩ ማስቻል ነው።
የዘንድሮው የመጀመሪያው ውድድር በካሜሩን እና በኢትዮጵያ ብቻ እንዲካሄድ የተወሰነ ሲሆን፣ ሽሪ አቹ በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ላይ የቀረበውን የኔክስት ፋሽን ዲዛይን ኮሌጅ እንቅስቃሴና የኮሌጁን ዲሬክተር ቃለ-መጠይቅ ከተመለከተች በኋላ ከተቋሙ ጋር አብራ ለመስራት መወሰኗን አስታውቃለች።
በዚሁ መሠረት ለዋናው የብቃት ውድድር ያለፉት የኢትዮጵያ ዲዛይነሮች ናታንሊ አስፋው፣ ያሲሚን ኢብራሂም እና ሜቴ ሀይለማሪያም መሆናቸው ታውቋል።
እነዚህ ሶስት ወጣት ዲዛይነሮች ያዘጋጇቸው አልባሳት ነገ በሚካሄደው የቀጥታ ስርጭት የፋሽን ሾው ላይ በሞዴሎች አማካኝነት ለዕይታ የሚቀርቡ ሲሆን፣ አሸናፊውን ለመለየት ከኢትዮጵያ የሚሰበሰበው የሕዝብ ድምፅ 25 ፐርሰንት ድርሻ ይኖረዋል።
ጠቅላላው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት እና የዳኞች ግምገማ ተደምሮ የፊታችን ሰኔ ወር ላይ ውጤቱ በይፋ የሚገለጽ ሲሆን፣ ከአገሪቱ አሸናፊ የሚሆነው ዲዛይነር በመጪው መስከረም 26 ቀን በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ታዋቂው የስሚዝሶኒያን ብሔራዊ የአፍሪካ ስነ-ጥበብ ሙዚየም ላይ በሚዘጋጀው ታላቅ የፋሽን ሾው ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ የመቅረብ እና ስራዎቹን ለዓለም የማሳየት ሰፊ ዕድል ያገኛል።
#fashion #art #panafrican #design #ethiopiandesigners #nextfashioncollege #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

16 days ago
ሁለተኛው የኢትዮጵያ እና ፊንላንድ የፖለቲካ ምክክር በአዲስ አበባ ተካሄደ
*********************
ሁለተኛው የኢትዮጵያ እና ፊንላንድ የፖለቲካ ምክክር በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ የተካሄደ ሲሆን በምክክሩ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በትምህርት እና በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ሰፊ ግምገማ ተደርጓል።
ምክክሩን በጋራ የመሩት አምባሳደር መለስ ዓለም እና የፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ዋና ጸሐፊ አምባሳደር ኦውቲ ሆሎፓይነን የሁለቱን ሀገራት የቆየ ግንኙነት እና አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።
በዚሁ ወቅት ማብራሪያ የሰጡት አምባሳደር መለስ ዓለም በኢትዮጵያ ስላለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ ስለ 7ኛው አጠቃላይ ምርጫ፣ ስለ ብሔራዊ ምክክር ሂደት እና ስለ ፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ለፊንላንድ ልዑካን ገልጸዋል።
አምባሳደሩ የፊንላንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በፈጠራ፣ በቴክኖሎጂ እና በግብርና ማቀነባበሪያ ዘርፎች እንዲሰማሩ ጥሪ በማቅረብ ንግድን ለማሳደግ የሁለቱ ሀገራት የንግድ ምክር ቤቶች በቅርበት እንዲሠሩ አሳስበዋል።
የፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ዋና ጸሐፊ አምባሳደር ኦውቲ ሆሎፓይነን በበኩላቸው፣ በአዲስ አበባ እየታየ ያለውን ፈጣን የልማት ለውጥ አድንቀዋል።
አምባሳደሩ ኢትዮጵያ ለሀገራቸው ቁልፍ አጋር መሆኗን ገልጸው፣ ፊንላንድ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ተናግረዋል።
በተለይም በዲጂታላይዜሽን፣ በከፍተኛ ትምህርት፣ በሜትሮሎጂ እና በአስተማሪዎች ሥልጠና ዙሪያ የሚደረገው ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀው፣ መሰል መደበኛ ውይይቶችን አጠናክሮ ለመቀጠል መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#ethiopia #ebc #finland #ethiopiafinlandconsultation #addisababa

ቀዝቀዝ ሞቅ የሚለው የሩስያ ዩክሬን ጦርነት ዛሬ ሌላ እልቂት አስመዝግቧል
#ethiopia | በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት፣ ሩሲያ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በዩክሬን ላይ የሰነዘረችው እጅግ ከፍተኛ የተባለው የአየር ጥቃት የ18 ሰዎችን ህይወት ማለፉ ተረጋግጧል።
ከተጎጂዎቹ መካከል የስምንት ዓመት ህጻን እና አንዲት ሴት ከፍርስራሽ ውስጥ አስከሬናቸው የተገኘ ሲሆን፣ በጥቃቱ ሳቢያ በድኒፕሮ 12 እንዲሁም በዋና ከተማዋ ኪየቭ 6 ሰዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ገልጸዋል።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እንደተናገሩት፣ የሩሲያ ኢላማዎች በመላው ዩክሬን የሚገኙ የሲቪል መሰረተ ልማቶችና የኃይል ማመንጫ ተቋማት የነበሩ ሲሆን፣ ከሟቾቹ በተጨማሪ ከ100 በላይ ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በሌላ በኩል ሩሲያ ጥቃቱን የፈጸመችው ቀደም ሲል 21 ተማሪዎች ለተገደሉበት ጥቃት ምላሽ ለመስጠት መሆኑን አስታውቃለች።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#የሩሲያ_ዩክሬን_ጦርነት #የአየር_ጥቃት #ዩክሬን #ሩሲያ #ሰብአዊ_ቀውስ

19 days ago
አሳዛኝ መረጃ‼️ ትናንት ግንቦት 22/2018 ዓ.ም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ከምሽቱ 2:00 አካባቢ በየተማሪዎች DSTV ውስጥ ኳስ እያዩ በነበሩ ተማሪዎች ላይ በተጣለ ቦንብ ሁለት ተማሪዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ከ20 በላይ ተማሪዎች መቁሰላቸውን እና ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ምንጮቻችን ገልፀዋል። በዚህ የተነሳ ከጠዋት 12:00 በፊት መውጣት እንዲሁም ማታ ከ12:00 በኋላ ወደ…
19 days ago
አሳዛኝ መረጃ‼️
ትናንት ግንቦት 22/2018 ዓ.ም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ከምሽቱ 2:00 አካባቢ በየተማሪዎች DSTV ውስጥ ኳስ እያዩ በነበሩ ተማሪዎች ላይ በተጣለ ቦንብ ሁለት ተማሪዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ከ20 በላይ ተማሪዎች መቁሰላቸውን እና ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ምንጮቻችን ገልፀዋል።
በዚህ የተነሳ ከጠዋት 12:00 በፊት መውጣት እንዲሁም ማታ ከ12:00 በኋላ ወደ ግቢው መግባት እንደማይችል ምንጮቻችን ገልጸዋል።
ለሞቱት ተማሪዎች ነፍስ ይማር እያልን የተጎዱ ተማሪዎች በቶል እንዲያገግሙ እንመኛለን።

23 days ago
ጊዜው ደርሷል! በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው 29ኛው ዓመታዊ በሚኒሶታ የኢትዮጵያ ተማሪዎች የባህል ምሽት (Annual Cultural Show) የፊታችን አርብ፣ ሜይ 29 በኖርዝሮፕ (Northrop) አዳራሽ በድምቀት ይካሄዳል! የዘንድሮው ዝግጅታችን እጅግ ለየት ያለ ነው... በአንድ ተወዳጅ የኢትዮጵያ ፊልም ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀውን እና የ'ዳዊት'ን የህይወት ውጣ ውረድ የሚያሳየውን "BOUND BY LAND" የተሰኘ መድረካዊ ትዕይንት ከዚህ ቀደም አይታችሁት በማታውቁት ማራኪ አቀራረብ ተማሪዎቹ ከተለያዩ ባህላዊ ዝግጅቶች ጋር ይዘውላችሁ ይቀርባሉ... ፈጽሞ እንዳያመልጣችሁ!
ሜይ 29, 2026 (የፊታችን አርብ) ከቀኑ 4:30 PM በር ይከፈታል (ማሳሰቢያ፡ 6:00 PM ላይ በሮች በጥብቅ ስለሚዘጉ ዝግጅቱን ከመጀመሪያው ለመታደም በጊዜ እንድትገኙ ተማሪዎቹ አሳስበዋል።
ቦታው ፡ Northrop | 84 Church St SE, Minneapolis, MN 55455
⚠️ ማሳሰቢያዎች፡
* ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ዕድሜው 21 እና ከዚያ በላይ በሆነ አሳዳጊ መታጀብ አለባቸው (አንድ ወላጅ እስከ 2 ታዳጊዎችን ብቻ ይዞ መግባት ይችላል)።
* ሁሉም ታዳሚ ህጋዊ መታወቂያ መያዝ አለበት።
* ወደ አዳራሹ ማንኛውንም ዓይነት ቦርሳ ይዞ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው።
ባህላችንን በጋራ ልናከብር ጓጉተናል፤ አርብ በቦታው እንገናኝ! 👏🏽 #esa #ethiopianculturalshow #boundbyland #umn #ethiopianstudents

24 days ago
ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች አዲስ ምዕራፍ ከፍተዋል
****************************
በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች እየተተገበሩ ያሉ ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች፣ የዜጎችን ክብርና ምቾት በማስቀደም በኢትዮጵያ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፍተዋል።
እነዚህ ፕሮጀክቶች ጥራት ያላቸው የጤና ተቋማትን፣ የመዝናኛ ስፍራዎችንና የምገባ ማዕከላትን ያካተቱ ሲሆን፤ የጤና ተቋማቱ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርገዋል።
የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም ደግሞ በትምህርት ገበታ የመቆየት ምጣኔን በማሳደግ ረገድ ዓይነተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
በ2017 የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ 1.6 ሚሊዮን፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ከ8 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ሆነዋል። ይህም ለ36 ሺህ እናቶች የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ፣ ለምገባው የሚሆኑ ምርቶች ከአካባቢው አርሶ አደሮች የሚሸመቱ በመሆናቸው ኢኮኖሚያዊ ትስስሩን አጠናክሮታል።
በሌላ በኩል፣ በአቅመ ደካሞች የኑሮ ማሻሻያ ዘርፍ በመንግስትና በበጎ ፈቃደኞች ትብብር ከ45 ሺህ በላይ የመኖሪያ ቤቶች ተገንብተው ተላልፈዋል።
የዲጂታል ዘርፉን ለማሳደግ ታቅዶ እየተተገበረ ባለው የ«5 ሚሊዮን ኮደሮች» ሥልጠናም እስካሁን ከ3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተሳታፊ ሆነዋል።
ባለፉት ዓመታት በቱሪዝም፣ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ በቀዳማዊ ልጅነት (Early Childhood) እንዲሁም በአረንጓዴ ኢኮኖሚ የተከናወኑ ተግባራት ዜጎችን ማዕከል ያደረገ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት በማስመዝገብ ኢትዮጵያን ወደ አዲስ ምዕራፍ አሸጋግረዋል።
በንፍታሌም እንግዳወርቅ

በጤናና መሰል ማህበራዊ ዘርፎች የግሉ ዘርፍ ሚና ሊጠናከር ይገባል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጤና፣ ትምህርትና መሰል ማህበራዊ ዘርፎች ላይ የሚታየው ችግር በመንግሥት ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ የግሉ ዘርፍ ድጋፍ ሊጠናከር ይገባል አሉ፡፡
መንግሥታት ክፍተት እያዩ መሙላት ይጠበቅባቸዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የግሉ ዘርፍም መደገፍ እንደሚጠበቅበት ጠቁመዋል።
አዲስ አበባ ውስጥ በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን ሆስፒታል ለመስራትና ክፍተቱን ለመሙላት የማይናቅ ሚና እንደተጫወቱም አንስተዋል።
በቦታ እጥረት ምክንያት ሊሰሩ እየፈለጉ ያልቻሉ እንዳሉ ገልጸው፥ የከተማ አስተዳደሩ እነዚህን የግል ዘርፎች መደገፍ ይኖርበታል ብለዋል።
መንግሥት እና የግሉ ዘርፍ ሲተባበር ኢትዮጵያ በርካታ ሐኪሞች ታፈራለች፣ መሰረተ ልማት ትገነባለች እንዲሁም ዜጎችን አክማ ታድናለች ነው ያሉት።
በአገልግሎት ዘርፍ፣ በትምህርት በተለይ በተማሪዎች ምገባና በመምህራን የኑሮ ማሻሻል ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚያስመሰግን ሥራ መስራቱንም ተናግረዋል።
በሚቀጥሉት ዓመታት በጤናው ዘርፍ ማንኛውም ዜጋ ታክሞ የሚሄድበትን መንገድ በመፍጠር ተጨባጭ ውጤት ማምጣት እንደሚገባም አሳስበዋል።
በብርሃኑ አበራ

ጤና ልክ እንደ ሰላም በጣም አስፈላጊ ነገር ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጤና ልክ እንደ ሰላም በጣም አስፈላጊ ነገር ነው አሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተገነባው የላፍቶ ሆስፒታል በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በኢትዮጵያ የጤና ፖሊሲ ባለፉት 10 ዓመታት ስንጠቀምት የነበረው ፖሊሲ ቅድሚያ መከላከል ላይ ያተኮረ ነበር፡፡
በዚህም መከላከል እንደተጠበቀ ሆኖ ታመው ከመጡ ማከም የሚለው ሀሳብ ተካትቶበት ፖሊሲው መሻሻሉን አውስተዋል፡፡
ጤና ልክ እንደ ሰላም በጣም አስፈላጊ ነገር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ካላመመን አናውቀውም፤ ሲያመን ነው የምናውቀው ሲሉም አስረድተዋል፡፡
በሽታ ልክ እንደ ጦር ሰራዊት ውጊያ እንደሚፈልግ ጠቅሰው፥ ውጊያው ደግሞ ትጥቅ ይፈልጋል ትጥቁ ደግሞ ምግብ ነው ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች የመመገቢያ ማዕከል የተገነባው ሰዎች መብላት እንዲችሉና ማዕድ ማጋራት ልማድ አንዲሆን ነው ሲሉም አብራርተዋል፡፡
ተማሪዎች ቢያንስ በቀን ሁለቴ መብላት እንዲችሉ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው የሚቸገሩ ሰዎች ስላሉ ይህ ልምምድ መጠናከር አለበት ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ዜጎቿን መርዳትና መመገብ እስክትቸል ድረስ ዜጎች በትብብር ይህንን ችግር ማለፍ ይኖርባቸዋል ነው ያሉት፡፡
ይህንን እያደረግን ስንሄድ የተሟላ ጤንነት ያለው ትውልድና ማህበረሰብ ይፈጠራል ብለዋል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ሚያዚያ 13 እና 14፣ 2018 ዓ.ም. በአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ ባህር ዳር ያደረጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት አስመልክቶ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ከአንድ ወር በኋላ ዛሬ የቪድዮ መግለጫ አውጥቷል። ኤምባሲው በትዊተር (ኤክስ) ገጹ እንዳስታወቀው፣ ይህ የአምባሳደሩ ጉብኝት አሜሪካ ለአማራ ህዝብ ሰላም፣ ደህንነት እና ብልጽግና ያላትን ዘላቂ ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየ ነው።
አምባሳደር ማሲንጋ ጣና ሀይቅ ዳርቻ ላይ ሆነው በሰጡት እና ኤምባሲው ባጋራው የቪዲዮ መልዕክት ላይ፣ በስልጣን ዘመናቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የአማራ ክልልን ርዕሰ ከተማ ለመጎብኘት በመቻላቸው የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸዋል። በቆይታቸውም ከህዝቡ እና ከባለስልጣናቱ እጅግ ደማቅ እና ሞቅ ያለ አቀባበል እንደተደረፈላቸው ተናግረዋል።
አምባሳደሩ በንግግራቸው ክልሉ እና ህዝቡ እጅግ ፈታኝ የሆኑ ጊዜያትን ማሳለፋቸውን እና ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ መቆየታቸውን አስምረውበታል። "ይህ ቀጠና ብዙ መከራዎችን እንዳሳለፈ ግልጽ ነው፤ ብዙ ስቃይ ነበረ። ይህንን ችላ ማለትም ሆነ መካድ አንችልም" በማለት ያለውን ነባራዊ ሁኔታ አምነዋል። ይሁን እንጂ፣ ከፖለቲካ መሪዎች አልፎ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ተራ ዜጎች ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ህዝቡ የተሻለ ነገን ተስፋ ከማድረግ ባለፈ ይህ አሁን ያለው ቀውስ በተቻለ ፍጥነት እንዲያበቃ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጠብቅ መገንዘባቸውን አብራርተዋል።
አምባሳደር ማሲንጋ በጉብኝታቸው ወቅት የኤም.ኤስ.ኤ የፋብሪካ ማዕከልን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። ይህ ተቋም እንስሳት መኖ እና የምግብ ዘይት በማምረት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ከፍተኛ ጥራት ያለውን የፕሮቲን ምርት ወደ አሜሪካ እና ሌሎች ሀገራት ጭምር በመላክ ላይ ይገኛል። አምባሳደሩ ድርጅቱ በዚህ ፈታኝ ወቅት ውስጥ ሆኖም በአብዛኛው ከአሜሪካ በመጣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ እና ኢንቨስትመንት በመጠቀም የባህር ዳርን እና የአማራን ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በመለወጥ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው አድናቆታቸውን ችረዋል።
አክለውም አምባሳደሩ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (በተለይም በኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት) ሰፊ ጊዜ አሳልፈዋል። ተቋሙ የገጠመውን ፈተና ወደ መልካም እድል በመቀየር ከፍተኛ ጥራት ያለው ትምህርት እየሰጠ በመሆኑ፣ በአሁኑ ወቅት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ለሚያጠናቅቁ ተማሪዎች ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ መሆን መቻሉን ተናግረዋል። አሜሪካም ዩኒቨርሲቲው ራሱን የቻለ ተቋም ለመሆን የጀመረውን ጉዞ በመደገፍ አብራ ለመስራት በጉጉት እንደምትጠብቅ አስታውቀዋል።
አምባሳደር ማሲንጋ አደረኩት ባሉት የሁለት ቀናት ጉብኝት፣ የአማራ ህዝብ አሁን ካለበት ቀውስ አገግሞ በቀጣዮቹ ዓመታት ለመበልጸግ ዝግጁ እና ሙሉ አቅም ያለው መሆኑን በሚገባ እንዳመኑበት በማረጋገጥ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Comments