Logo
Getu Temesgen

አስቸኳይ መልእክት ከገዳም እናቶች

እኛ የወሎ መርሣ ሰዳቱ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም እናቶች እና አባቶች እንዲሁም የአብነት ተማሪዎች በውኃ ጥም እየተሰቃዬን እንገኛለን። ለዚህም ከገጠር መጥተን አዲስ አበባ ከተቀመጥን ሁለተኛ ሳምንታችንን ያዝን።

አመጣጣችንም ግንቦት 29 እና 30/2018 የቀጥታ ሥርጭት የገቢ ማሰባሰብ እና የእራት መርሐግብር አድርገን ለገዳሙ የውኃ ፕሮጀክት 10,000,000 /ዐሥር ሚሊዬን ብር/ ለማሰባሰብ ነበር። ነገር ግን የአርሲው ጭፍጨፋ በወገኖቻችን እና በቤተክርስቲያን ላይ ተፈጸመ። እኛም ልባችን ተሠበረ። እንዴት በዚህ ሰዓት እራት እና ቀጥታ ሥርጭት እያልን እንለምናለን ቢያንስ ለአንድ ሳምንት እናራዝመው ብለን ወደ ሰኔ 5 እና 6 አርብ እና ቅዳሜ አሸጋግረነዋል።

ይኽን ስናደርግ እኛ ከገዳም የመጣን መነኮሳት ከሰው ቤት ለ15 ቀናት እንደምንቀመጥ ስናስብ በሁለት ነገር እናዝናለን። አንደኛ ከተማ መቀመጥ ለኛ አይገባም። ሁለተኛ ማረፊያ ለሰጡን ወገኖች ሸክም እንሆናለን።

ይኹንና ከገጠመን ኅዘን የሚበልጥ ነገር ስለሌለ አዛውረነዋል። እናንተም ሰኔ 5 እና 6
ከምሽቱ 1፡00 ጀምሮ በቀጥታ ሥርጭት እየገባችሁ ልጆቻችን አለን በሉን።

አደራ ልጆቻችን
ለበለጠ መረጃ በዚህ ስልክ ደውሉልን
0911644781
0911981096
0911216958
0911671379
0911631126
በዚህ አካውንትም የምትችሉትን አግዙን
ገዳሟን የምታግዙባቸው አካውንቶች
ንግድ ባንክ1000003780779
አባይ ባንክ 9841011002322017
አሐዱ ባንከ 0088911720301

https://gofund.me/401f3b99...
8 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.