Logo
EBC
ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች አዲስ ምዕራፍ ከፍተዋል
****************************

በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች እየተተገበሩ ያሉ ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች፣ የዜጎችን ክብርና ምቾት በማስቀደም በኢትዮጵያ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፍተዋል።

እነዚህ ፕሮጀክቶች ጥራት ያላቸው የጤና ተቋማትን፣ የመዝናኛ ስፍራዎችንና የምገባ ማዕከላትን ያካተቱ ሲሆን፤ የጤና ተቋማቱ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርገዋል።

የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም ደግሞ በትምህርት ገበታ የመቆየት ምጣኔን በማሳደግ ረገድ ዓይነተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

በ2017 የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ 1.6 ሚሊዮን፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ከ8 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ሆነዋል። ይህም ለ36 ሺህ እናቶች የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ፣ ለምገባው የሚሆኑ ምርቶች ከአካባቢው አርሶ አደሮች የሚሸመቱ በመሆናቸው ኢኮኖሚያዊ ትስስሩን አጠናክሮታል።

በሌላ በኩል፣ በአቅመ ደካሞች የኑሮ ማሻሻያ ዘርፍ በመንግስትና በበጎ ፈቃደኞች ትብብር ከ45 ሺህ በላይ የመኖሪያ ቤቶች ተገንብተው ተላልፈዋል።

የዲጂታል ዘርፉን ለማሳደግ ታቅዶ እየተተገበረ ባለው የ«5 ሚሊዮን ኮደሮች» ሥልጠናም እስካሁን ከ3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተሳታፊ ሆነዋል።

ባለፉት ዓመታት በቱሪዝም፣ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ በቀዳማዊ ልጅነት (Early Childhood) እንዲሁም በአረንጓዴ ኢኮኖሚ የተከናወኑ ተግባራት ዜጎችን ማዕከል ያደረገ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት በማስመዝገብ ኢትዮጵያን ወደ አዲስ ምዕራፍ አሸጋግረዋል።

በንፍታሌም እንግዳወርቅ

9 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.