ከ560 ሺህ በላይ ተፈታኞች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ ተመዝግበዋል። - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍልብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 24/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም ይሰጣል።
የመልቀቂያ ፈተናውን ለመውሰድ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ560 ሺህ በላይ ተፈታኞች መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።
ከተመዘገቡት ውስጥ አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ፈተናውን በበይነ-መረብ እንደሚወስዱ የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የመሰረተ ልማት ውስንነት ባሉባቸው አካባቢዎች ፈተናው በወረቀት እንደሚሰጥ ገልፀዋል።
የፈተና ሒደቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ የኢንተርኔት እና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አስተማማኝነትን ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሠራ መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል።
Seledadotio

13 days ago