የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ነው
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ 1መቶ99 የፈተና ጣቢያዎች፣ የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዛሬው ዕለት በይፋ መሰጠት መጀመሩን የከተማዋ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
ከዛሬ ሰኔ 8 ጀምሮ እስከ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚቆየውን ይህንን ከተማ አቀፍ ፈተና ለመውሰድ 85 ሺህ 17 ተማሪዎች ተመዝግበው ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸው ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ በሰጡት መግለጫ፤ ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ በየደረጃው የኮማንድ ፖስት አደረጃጀቶች መዋቀራቸውን ገልጸዋል።
ለፈተናው ሂደት ጥራትና ተዓማኒነት ሲባልም፣ ልምድ ያላቸው የፈተና አስፈጻሚዎች ተመልምለው በየጣቢያዎቹ እንዲመደቡ መደረጉን ጠቁመዋል።
ከጸጥታ አኳያም ፈተናው ያለምንም ችግር እንዲከናወን አስፈላጊው የጸጥታ አካላት ጥበቃና የክትትል ሥራ መመቻቸቱ ተመላክቷል።
በአሁኑ ሰዓት በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች ሂደቱን የሚከታተሉ የቢሮው አመራሮችና ባለሙያዎች በሥራ ላይ እንደሚገኙ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
Ethio Fm

4 days ago