Logo
Getu Temesgen
ቀዝቀዝ ሞቅ የሚለው የሩስያ ዩክሬን ጦርነት ዛሬ ሌላ እልቂት አስመዝግቧል
#ethiopia | ​በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት፣ ሩሲያ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በዩክሬን ላይ የሰነዘረችው እጅግ ከፍተኛ የተባለው የአየር ጥቃት የ18 ሰዎችን ህይወት ማለፉ ተረጋግጧል።

ከተጎጂዎቹ መካከል የስምንት ዓመት ህጻን እና አንዲት ሴት ከፍርስራሽ ውስጥ አስከሬናቸው የተገኘ ሲሆን፣ በጥቃቱ ሳቢያ በድኒፕሮ 12 እንዲሁም በዋና ከተማዋ ኪየቭ 6 ሰዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ገልጸዋል።

​የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እንደተናገሩት፣ የሩሲያ ኢላማዎች በመላው ዩክሬን የሚገኙ የሲቪል መሰረተ ልማቶችና የኃይል ማመንጫ ተቋማት የነበሩ ሲሆን፣ ከሟቾቹ በተጨማሪ ከ100 በላይ ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በሌላ በኩል ሩሲያ ጥቃቱን የፈጸመችው ቀደም ሲል 21 ተማሪዎች ለተገደሉበት ጥቃት ምላሽ ለመስጠት መሆኑን አስታውቃለች።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
​#የሩሲያ_ዩክሬን_ጦርነት #የአየር_ጥቃት #ዩክሬን #ሩሲያ #ሰብአዊ_ቀውስ

23 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.