Logo
FBC
በሸገር ከተማ ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሸገር ከተማ አስተዳደር ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጊያለሁ አለ።

የከተማዋ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፊራኪያ ካሳሁን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት÷ ዘንድሮው 8 ሺህ 932 ተማሪዎች በከተማ አስተዳደሩ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ይወስዳሉ።

በከተማ አስተዳደሩ ለፈተናው ድጋፍ ከማድረግ ጀምሮ ግብዓቶችን በማሟላት ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ አስፈላጊ ዝግጅት መደረጉን አመላክተዋል።

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ጠንካራ የድጋፍ እና የክትትል ሥርዓት መዘርጋቱን ጠቅሰው÷ በዚህም በከተማዋ የትምህርት ተቋማትን ማስፋፋት፣ የተማሪዎችን ተሳትፎ ማጠናከርና ትምህርት ቤቶች የመገንባት ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

እንዲሁም የመምህራንን አቅም ማጠናከር እና የመማሪያ መሳሪያዎችን በማሟላት ለመማር ማስተማር ስራ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል።

በትምህርት ጥራት ላይ ያሉ ክፍተቶችን በመለየትና በመቅረፍ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በተጠናከረ መንገድ መሰራቱንም አመልክተዋል።

በታሪክ አዱኛ

4 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.