Logo
SeledaPost
የፋርማሲ ተማሪዎች ቅሬታ‼️
የፋርማሲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ተፈታኞች ፈተናው አስቀድሞ ተሰርቋል በማለት ቅሬታ አቀረቡ፤ የሚመለከተው አካል ማብራሪያ እንዲሰጥም ጠይቀዋል።

ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም የተሰጠው የፋርማሲ ትምህርት ክፍል ብሔራዊ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) አስቀድሞ ተሰርቆ ለተወሰኑ ተማሪዎች ተሰራጭቷል ሲሉ ተፈታኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ ተማሪዎች እንዳሉት፤ ለፈተናው በርካታ ልፋትና ዝግጅት ቢያደርጉም፣ ኃላፊነት በማይሰማቸው አካላት አማካኝነት ፈተናው ቀድሞ ወጥቶ መሰራጨቱን የሚያሳዩ መረጃዎች እንደደረሷቸው ገልጸዋል።

ይህ መሆኑም በከፍተኛ ጥረትና በራሳቸው ልፋት የተፈተኑ ተማሪዎችን ስነ-ልቦና በእጅጉ የጎዳና ፍትሃዊነትን ያጓደለ ተግባር መሆኑን ጠቁመዋል።

ተፈታኞቹ አያይዘውም፣ ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት ትምህርት ሚኒስቴርና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንዲሁም በኢትዮጵያ ፋርማሲስቶች ማህበር (EPA) በኩል በአስቸኳይ ታይቶ፣ አስፈላጊው ማጣሪያ እንዲደረግና ተገቢው ምላሽ እንዲሰጣቸው በትህትና ጠይቀዋል።

Seledadotio
Seledadotio
1 day ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.