8 hours ago
ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት የሰረቀው የሆስፒታሉ ጥበቃ በ7 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ
ተከሳሽ እንድሪያስ ቶማስ ግያ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪና ሪፈራል ሆስፒታል የጥበቃ ሠራተኛ ሆኖ እየሰራ ሀምሌ 22 ቀን 2018 ከምሽቱ 4:00 እስከ 6፡00 ባለዉ ጊዜ የወንጀል ድርጊቱ ተፈፅሟል።
የሆስፒታሉ ንብረት የሆነውን ሶስት ማይክሮስኮፕ የእያንዳንዳቸዉ ዋጋ ሶስት መቶ ሀምሳ ሺ ብር በድምሩ አንድ ሚሊዮን ሀምሳ ሺ ብር የሚያወጣዉን ከክፍሉ ሠራተኞች ጋር በመተባበር ንብረቱ ያለበትን ክፍል በቁልፍ ከፍቶ ከወሰደ እና ንብረቱን በተቋሙ ዉስጥ ባለዉ ሳርና ሀረግ ዉስጥ ደብቆ ካቆየ በኋላ ሀምሌ 25 ከሌሊቱ 9 ሰዓት ንብረቱን ካቆየበት ሥፍራ አንስቶ እየወሰደ እያለ ከንብረቱ ጋር የተያዘ ስለሆነ ተከሳሽ በፈፀመው ከባድ ስርቆት ወንጀል ተከሷል ።
የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፍትህ መምሪያ ዐ/ሕግ ያቀረበውን ክስ ሲያከራክር የቆየው የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ ሙሉ በሙሉ ያመነ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት የጥፋተኝነት ውሳኔ ሰጥቷል። ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ ያመነ መሆኑን፣ የቤተሰብ አስተዳደር እንዲሁም ቀደም ስል የወንጀል ሪከርድ የሌለበት መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት በ7 አመት ጽኑ እስራት እንድቀጣ ውሳኔ አሳልፎል።
የተሰረቀው ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዋጋ የሚያወጣው ማይክሮስኮፕ ለኦቶና ሪፌራል ሆስፒታል ተመላሽ መደረጉን የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ኮሚኒኬሽን አስታውቋል።
Seledadotio

3 days ago
u1273u120bu1241 u12d8u1218u127b... u12a2u1275u12eeu1335u12eb u12e8u122bu1237u1295 u122au12a8u122du12f5 u120du1275u1230u1265u1228u12cd u1290u12cd...u12e8u12a0u1228u1295u1313u12f4u12cd u12a0u1265u12eeu1275 u1275u12cdu120du12f5 u1300u1265u12f1
#u12e8u1200u1308u122du1309u12f3u12ed ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ታላቁ ዘመቻ... ኢትዮጵያ የራሷን ሪከርድ ልትሰብረው ነው...የአረንጓዴው አብዮት ትውልድ ጀብዱ
#የሀገርጉዳይ
6 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የኒውካስሉ ተወዳጅ የቀድሞ አሰልጣኝ ኬቨን ኪጋን ካረፉ ገና አስር ቀናት ብቻ ቢቆጠሩም፣ ክለቡ ሌላ ያልተጠበቀ መርዶ አስተናግዷል፦ የኪጋንን ህልም እውን በማድረግ ክለቡን ለክብር ያበቁት አሰልጣኝ ኤዲ ሃው ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ይፋ አድርገዋል።
ከእጅግ አስከፊው የ2025-26 የውድድር ዘመን በኋላ በኃላፊነታቸው ለመቀጠል እና ክለቡን መልሰው ለመገንባት ቃል ገብተው የነበሩት ኤዲ ሃው፣ አዲሱ የፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ሊጀመር ሶስት ሳምንታት ብቻ ሲቀሩት ውሳኔያቸውን ቀልብሰዋል።
ማክሰኞ ምሽት በቅድመ-ውድድር ዝግጅት ኒውካስል ከብሪስቶል ሲቲ ጋር ባደረገው የወዳጅነት ጨዋታ 4-1 በሆነ አሳፋሪ ውጤት መሸነፉ ብዙ ነገሮችን የቀየረ ይመስላል። ከሜዳቸው ውጪ ስታዲየሙን ሞልተው የነበሩት የኒውካስል ደጋፊዎች ያሰሙት የተቃውሞ እና የቁጣ ድምፅ፣ ይህ "ትርጉም አልባ" የሚመስል የወዳጅነት ጨዋታ ትልቅ መዘዝ ይዞ እንደሚመጣ አመላካች ነበር።
በማግስቱ ረቡዕ ጠዋት እንደተሰማው ኤዲ ሃው ኃላፊነታቸውን ለመልቀቅ ወስነዋል። የቅርብ ምንጮች እንደሚያሳዩት ይህ ውሳኔ የቅጽበት የብስጭት ውሳኔ ሳይሆን፣ ከከባዱ የውድድር ዘመን መገባደጃ አንስቶ አሰልጣኙ በውስጣቸው ሲያብሰለስሉት የቆዩት እና ሊሸከሙት ያልቻሉት ከባድ ሸክም ውጤት ነው።
ለኤዲ ሃው፣ ይህ ስንብት እጅግ አስደናቂ ለነበረው የኒውካስል ቆይታቸው የማይመጥን አሳዛኝ ማብቂያ ነው። ከ30 ዓመታት በፊት ኬቨን ኪጋን እጅግ ተቃርበውት የነበረውን፣ ደጋፊውም ለ70 ዓመታት ሲናፍቀው የነበረውን ትልቅ ዋንጫ ወደ ሴንት ጀምስ ፓርክ ያመጡት እርሳቸው ነበሩ።
እ.ኤ.አ በ2021 ክለቡ በፕሪሚየር ሊጉ 19ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ወደ መውረድ አፋፍ በደረሰበት ወቅት ኃላፊነቱን የተረከቡት ሃው፣ ኒውካስልን በሊጉ ማቆየት ብቻ ሳይሆን በሚቀጥለው ዓመት ወደ ቻምፒዮንስ ሊግ መድረክ መልሰውታል። በ2024-25 ደግሞ በካራባኦ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ የሊጉን ሻምፒዮን ሊቨርፑልን በዌምብሌይ አሸንፈው ታሪካዊ ዋንጫ በማንሳት ስማቸውን በኒውካስል ታሪክ በወርቅ ቀለም አጽፈው ነበር።
ይህ የዋንጫ ድል የሳዑዲው የኢንቨስትመንት ፈንድ (PIF) በባለቤትነት ለሚያስተዳድረው እና የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለሚያልመው ኒውካስል እንደ ትልቅ መነሻ መታየት ነበረበት። ሆኖም፣ የ2025ቱ ክረምት የሁሉንም ነገር አቅጣጫ ቀየረው።
በተለይም አሌክሳንደር ኢሳክን በክለቡ ለማቆየት የተደረገው ተስፋ አስቆራጭ እና መራር ትግል፣ በመጨረሻም ስዊድናዊው አጥቂ በብሪታንያ የዝውውር ሪከርድ በዝውውር መስኮቱ መዘጋጃ ዕለት ወደ ሊቨርፑል ማምራቱ ክለቡን ክፉኛ ጎድቶታል። ኒውካስል የኢሳክን ክፍተት ሊተካ የሚችል ተጫዋች ማምጣት አልቻለም። እንደ ሁጎ ኤኪቲኬ፣ ቤንጃሚን ሴስኮ እና ጆአዎ ፔድሮ ያሉ ታላላቅ ኢላማዎቹን ለተቀናቃኝ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አሳልፎ ሰጠ።
በምትኩ ክለቡ እና ኤዲ ሃው በጋራ ያመጧቸው ኒክ ዎልቴማዴ፣ ዮአን ዊሳ እና አንቶኒ ኤላንጋ አጠቃላይ 180 ሚሊዮን ፓውንድ ($243m) ቢወጣባቸውም፣ ያሳዩት አቋም እና የገጠማቸው የጉዳት ችግር የተከፈለባቸውን ዋጋ ፈጽሞ ሊያጸድቅ አልቻለም። የኤላንጋ እና ዎልቴማዴ ብቃት ሲዋዥቅ፣ አጥቂው ዊሳ በሙሉ የውድድር ዘመኑ በሊጉ ያስቆጠረው አንድ ጎል ብቻ ነበር። በ43 ሚሊዮን ፓውንድ የመጣው ጃኮብ ራምሴይም በቁርጭምጭሚት ጉዳት ሲሰቃይ ጊዜውን አሳልፏል።
የዝውውር ውድቀቱ በሜዳ ላይ ውጤት ቢሸፈን ኖሮ የኤዲ ሃው ጫና ያን ያህል አይከፋም ነበር። ሆኖም የ2025-26 የውድድር ዘመን ለኒውካስል እውነተኛ ቅዠት ሆኖ አለፈ።
በዓመቱ መጀመሪያ ጥሩ አጀማመር ያሳየው ክለቡ፣ ከአዲሱ ዓመት በኋላ ግን የመውረድ ስጋት ወዳለባቸው ቡድኖች ወረደ። ከጥር መጨረሻ አንስቶ እስከ የውድድር ዘመኑ ማብቂያ ድረስ ካደረጋቸው 16 ጨዋታዎች በ10ሩ በመሸነፉ፣ ከ6ኛ ደረጃ ወደ 12ኛ ደረጃ በማሽቆልቆል ደጋፊውን በሀዘን እና በቁጣ ሞላው።
ይባስ ብሎ በኤፍኤ ካፕ እና በካራባኦ ካፕ በማንችስተር ሲቲ በቀላሉ ሲሰናበት፣ በቻምፒዮንስ ሊጉ ደግሞ ባርሴሎና በድምር ውጤት 8-3 በሆነ አሳፋሪ የጎል ናዳ አዋርዶ ከውድድሩ አስወጣው።
የኤዲ ሃው የወደፊት እጣ ፈንታ ጥያቄ ውስጥ የገባው ገና በጊዜ ነበር። በሚያዝያ ወር ኒውካስል በተከታታይ ለሶስተኛ ጊዜ በቦርንማውዝ ከተሸነፈ በኋላ፣ የክለቡ ታሪካዊ ሌጀንድ አላን ሺረር እንዲህ ብሎ ነበር፦ "ለኤዲ ምን ያህል ከባድ ጊዜ እንደሆነ ባውቅም፣ የወደፊት እጣ ፈንታው ምን እንደሚሆን አላውቅም። ዳግም የመዋጋት እና ክለቡን የማንሳት አቅሙ ያለው አይመስለኝም። በሚቀጥለው የውድድር ዘመን ኤዲ ሃው ኒውካስልን ያሰለጥናል ብዬ አላስብም።"
ሺረር እንዳለውም ሆነ ኤዲ ሃው ኒውካስልን ወደ ቀደመ ክብሩ የመመለስ ትልቅ ታሪክ ሰርተው፣ ነገር ግን በኋለኛው አመታቸው በዝውውር ውድቀት እና በሜዳ ላይ አስከፊ ውጤቶች ታጅበው የሴንት ጀምስ ፓርኩን በር ዘግተው ወጥተዋል።

የአየር ንብረት ለውጥ አውሮፓን እያመሰ ነው
* በከፍተኛ ሙቀት እና በሰደድ እሳት ሺዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል
#ethiopia | የአየር ንብረት ለውጥ በአውሮፓ ከፍተኛ ሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሥነ-ምህዳራዊ ቀውስ እያስከተለ መሆኑን የቅርብ ጊዜ ዓለም አቀፍ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በሰኔ መጨረሻ እና በሐምሌ ወር የተከሰቱ ከባድ የሙቀት ማዕበሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለሕልፈት ዳርገዋል፤ በበርካታ አገራት ደግሞ ሰደድ እሳቶች መኖሪያ ቤቶችን፣ ደኖችንና የግብርና መሬቶችን አውድመዋል።
የአውሮፓ በሽታ መከላከያ ማዕከል (ECDC) እና የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በሚደግፉት የEuroMOMO የሞት ክትትል መረጃ መሠረት፣ በሰኔ 22 እስከ 28 ቀን 2026 ብቻ ከ10 ሺህ በላይ ተጨማሪ ሞቶች ተመዝግበዋል።
ከእነዚህ ውስጥ ከ9 ሺህ በላይ የሚሆኑት ዕድሜያቸው 65 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች ናቸው። ባለሙያዎች ይህን ያልተለመደ የሞት ጭማሪ በዋነኝነት ከከፍተኛ ሙቀት ጋር ያያይዙታል።
በጀርመን ብቻ በ2026 እስከ ሐምሌ መጨረሻ ድረስ 9,800 የሚጠጉ ከሙቀት ጋር የተያያዙ ሞቶች መመዝገባቸው ተገልጿል።
በእንግሊዝ ደግሞ 2,800 በላይ ሰዎች በሙቀት ምክንያት መሞታቸው ተነግሯል፤ ይህም የ2022 ሪከርድን ሊበልጥ እንደሚችል ባለሥልጣናት አስጠንቅቀዋል።
በፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ግሪክ፣ ጣሊያን እና ፖርቱጋል የተቀሰቀሱ ሰደድ እሳቶች በመቶ ሺዎች ሄክታር የሚቆጠር ደን እንዲቃጠል አድርገዋል።
በፈረንሳይ ብቻ ከ220 ሺህ በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል፤ በግሪክ ደግሞ ሶስት የአደጋ አደራሽ ሠራተኞች በእሳት ማጥፋት ስራ ላይ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ሳይንቲስቶች እንደሚገልጹት፣ በሰኔ መጨረሻ የተመዘገበው የሙቀት ማዕበል የሰው ልጅ የፈጠረው የአየር ንብረት ለውጥ ባይኖር ሊከሰት ፈጽሞ የማይችል ነበር።
አውሮፓ በዓለም ላይ ከሌሎች አህጉራት በበለጠ ፍጥነት እየሞቀች ያለች አህጉር መሆኗም ችግሩን እያባባሰው ነው።
በዚህ ሁኔታ የአውሮፓ መንግሥታት የሙቀት አደጋ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶችን ማጠናከር፣ ለአረጋውያንና ለተጋላጭ ማኅበረሰቦች የጤና ጥበቃን ማሳደግ፣ እንዲሁም የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ የበለጠ ቁርጠኛ እርምጃ እንዲወስዱ ተጠይቀዋል።
በሌላ በኩል፣ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በ"አረንጓዴ ዐሻራ" መርሃ ግብር ባለፉት ሰባት ዓመታት ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል የደን ሽፋኗን ለማሳደግና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ ጥረት እያደረገች ትገኛለች።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

የ18 አመቱ ፕሮፌሰር
በ18 አመቱ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያገኘው ናታን ቶማስ የ300 አመት ታሪክ ቀየረ
#ethiopia | ለ300 ዓመታት በላይ ተይዞ የቆየውን የጊነስ ቡክ ሪከርድስ ታሪክ የ18 አመቱ ናታን ቶማስ በእጅ አስገብቷል።
ናታን ቶማስ ይህንን ድንቅ ስኬት መጎናጸፍ የቻለው እ.ኤ.አ በ1717 በ19 ዓመታቸው ፕሮፌሰር በመሆን ለ306 ዓመታት ያህል ሪከርዱን ይዘው የቆዩትን ስኮትላንዳዊውን የማቲማቲክስ ሊቅ ኮሊን ማክላውሪን በመበለጥ አዲሱ ባለታሪክ ለመሆን ችሏል።

ገና በ10 ዓመቱ በማያሚ የኮሌጅ ትምህርቱን የጀመረ ሲሆን በ14 ዓመቱ ደግሞ ወደ ፍሎሪዳ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርስቲ በመዛወር ከፍተኛ ትምህርቱን ተከታትሏል።
የናታን ኢዚህ ደረጃ የመድረሱ ዋናው ምክንያት ወላጆቹ እንደሆኑ ይናገራል።
የናታን እናትና አባት ህዳዊ ሲሆኑ ሁለቱም በኢንጂነሪግ ትምህርት የተመረቁ ናቸው።
እሱም በዚህ የትምህርት ዘርፍ የመመረቁም ምክንያት የወላጆቹ ተጽዕኖ እንደሆነ ነው የተናገረው።
አብዛኞቹ የናታን እኩዮች የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለመጀመር በሚዘጋጁበት እድሜ ላይ ናታን በ18 ዓመቱ በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪውን በከፍተኛ ማዕረግ አጠናቋል።
ናታን ቶማስ ሲናገር እንዳህ ይላል እድሜ እዚጋ ቦታ የለውም የሚል።
ትኩረቴ ስራዬን በአግባቡ መስራትና ተማሪዎችን በምችለው መንገድ ሁሉ መርዳት ነው አሁን ፍላጎቴ ሲል ተናግሯል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #professor #guinnessworldrecords #nathanthomas

Sponsored by
Surafel
8 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ኬንያ በርካታ ችግኞችን በመትከል የአለምን ሪከርድ መስበሯን ገለጸች፡፡ የአለም ስነምህዳር ጥበቃ ቀንን ምክንያት በማድረግ በትላንትናው እለት በኬንያ ሞምባሳ ችግኝ የመትከል ዘመቻ ተከናውኗል፡፡ የኬንያ ስካውት ማህበር ከዛብሎን ኦኮቲና ከኤምፒሳ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ባከናወኑት በዚህ ዘመቻ የአለምን ሪከርድ ሰብረዋል፡፡ ሪከርዱ ከመሰበሩ በፊት የጊነስ የአለም ድንቃድንቅ መዝገብ አባላት በስፍራው ተገኝተው ሁኔታውን ተከታትለዋል፡፡
የጊነስ ባለሙያዎች ሪከርዱን ለመስበር በስፍራው ቢያንስ ሶስት ሺህ ሰዎች ችግኙን መትከል እንዳለባቸው የሚገልፅ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠው ነበር፡፡ ይሁንና በቦታው ላይ ከ5 ሺህ በላይ ወጣቶች ተገኝተው ችግኙን ተክለዋል፡፡ የጊነስ ባለሙያዎች ችግኞቹ ከተተከሉ በኋላ ባደረጉት ማጣራት በትክክል ችግኙን የተከሉት 4,124 ሰዎች መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ በመሆኑም በአለም ላይ በ30 ሰከንድ ውስጥ በርካታ ሰዎች የተሳተፉበት የችግኝ ተከላ በሚል አዲስ ሪከርድ መሰበሩን መዝገበው መሄዳቸውን ኬንያ ኤፍኤም ዘግቧል፡፡

10 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የአሜሪካ የኢሚግሬሽን እና የጉምሩክ አስከባሪ (ICE) ባለስልጣናት የወንጀል ሪከርድ ያለውንና በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በህገ-ወጥ መንገድ ይኖር የነበረውን ትውልደ ኬንያዊ የቀድሞ የNFL ተጫዋች ከሀገር ማባረራቸውን አስታወቁ።
የ37 ዓመቱ ዳንኤል ኦጋማ አዶንጎ በኢንዲያና ግዛት የህግ አስከባሪዎች ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት ውስጥ ለበርካታ ጊዜያት በቁጥጥር ስር ውሎ እንደነበር ተቋሙ ገልጿል። እ.ኤ.አ. በ2020 ላይ ንብረት በማውደም እና ጉዳት በማድረስ ወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ ለአንድ ዓመት የሚጠጋ የእስር ቅጣት ተፈግሎበት እንደነበርም ተጠቅሷል።
ዳንኤል አዶንጎ ከ2013 እስከ 2015 ባሉት ጊዜያት ለሁለት የውድድር ዘመናት 'ለኢንዲያናፖሊስ ኮልትስ' የአሜሪካ እግር ኳስ ክለብ ተጫውቷል። የኢሚግሬሽን ተቋሙ እንዳረጋገጠው፣ ግለሰቡ በአሜሪካ ይኖርበት የነበረው የመኖሪያ ፈቃድ (ቪዛ) በ2026 ጊዜው ያበቃ ነበር።
የ'ICE' የቺካጎ ረዳት የመስክ ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር ዳግላስ ቶምፕሰን በሰጡት መግለጫ፣ ግለሰቡ አደገኛ እና በማህበረሰቡ ላይ ግልጽ የሆነ ስጋት ደቅኖ የነበረ መሆኑን ጠቅሰው፣ አሁን እሱ ከሀገር በመባረሩ ማህበረሰቡ ይበልጥ ደህንነቱ የተጠበቀ ሆኗል ብለዋል። አክለውም፣ የኢሚግሬሽን ህግን የሚጥሱ ሰዎች የቀድሞ ፕሮፌሽናል አትሌቶች ቢሆኑም እንኳ በእኩልነት ተጠያቂ እንደሚሆኑ አሳስበዋል።
ከተያያዘ ዜና ጋር የአሜሪካ የኢሚግሬሽን እና የጉምሩክ አስከባሪ (ICE) በ2026 የበጀት ዓመት ውስጥ እስካሁን ከ350,000 በላይ ግለሰቦችን ከአሜሪካ ማባረሩን አስታውቋል።

የ13 እና የ18 ዓመት ሴት ልጆችን የግብረ ሥጋ ግንኙነት እና አስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸመ ግለሰብ በ 5 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።
ከ18 ዓመት በታች የሆኑትን ልጃገረዶች የግብረ ስጋ ግንኙነትና እና የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመ ግለሰብ በ5 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቱን የዲላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አስታውቋል፡፡
ተከሳሽ ወርቁ ሻመና ዕድሜያቸው 13 እና 18 አመት በሆኑ ሁለት ህፃናት ላይ መስከረም 20/2018 ከምሸቱ 5 ሰአት ገደማ በዚሁ ዲላ ከተማ ሀሮሬሣ ቀበሌ በደቻ ቀጠና ክልል ውስጥ የግል ተበዳይ ህፃን ትዕግሥት ዮሴፍ ከአሳዳጊዎች ቤት ጠፍታ ወደ አንዲዳ አከባቢ ከቤት ሰራተኛ ከሆነችው 2ኛ ተበዳይ ጋር እየሄደች እያለ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አከባቢ ተከሳሹ አግኝቶ " ጊዜው መሽቷል !! ጅብ ይበላችኋል!! " ብሎ ወደ ቀበሌ ወስጄ ቀጠና አሳድራችሃለሁ በማለት ወስዶ በአንድ ቤት ውስጥ ካስገባ ቦሃላ በመጀመሪያ ተበዳይ በሆነችሁ በህፃን ትዕግስት ዮሴፍ (13) ዓመቷ ላይ የወንጀል ጥቃት አስገድዶ ግብረ ስጋ ግንኙናት ሲሞክር ህፃኗ ያለ የሌለ አቅም በመጠቀም ራሷን ተከላከላለች።
ይህቺንማ አልችላትም !! በማለት ወደ ሁለተኛዋ ህፃን ኢየሩሳሌም ዕድሜ 18 የሆነችውን ይሄዳል እሷን ሌሊቱን ሙሉ በተደጋጋሚ ጥቃት በመድረስ ክፉኛ ጓድቷታል በዚህም አስገድዶ የግብረስጋ ግንኙነት በማድረግ ወንጀል መፈፀሙን አቃቤ ህግ ባቀረበው ማስረጃ አስረግጦ ለፍርድ ቤት ማስረዳቱን የችልቱ ዳኛ አቶ አብርሃም ኡዶ ገልፀዋል።
የዲላ ከተማ አቃቤ ህግ የሆኑት ወ/ሮ ዝናሽ ማሞ በተከሳሽ ላይ የክስ ማክበጃ ሀሳብ በአንቀፅ ጠቅሰው ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱ የአቃቤ ህግ እና የተከሳሽ የክስ ማቅለያን በደንብ መርምሮ ተከሳሽ የመንግስት ሰራተኛና የህዝብ አገልጋይ እንዲሁም የ9 ቤተሰብ አስተዳዳሪ በመሆኑ ከዚህ ቀደም የወንጀል ሪከርድ የለሌበት መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት አስተማሪ ሊሆን ይችላል የሚል የቅጣት ውሳኔ አሳልፏል።
በዚሁ መነሻ ፍ/ቤቱ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 149/1 ድንጋጌ መሰረት በተከሳሽ ወርቁ ሻመና ላይ የ5 አመት ፅኑ እስራት ማሳለፉን የዲላ ከተማ መንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል።

15 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካው የአገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤት (DHS) በቅርብ ታሪኩ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ መረጃዎችን ለሦስት ወራት ያህል አደናቅፎ ከቆየ በኋላ፣ ጁላይ 20 ቀን 2026 ዓ.ም. አዲስ የስደተኞች እገታና እስራት መረጃዎችን ይፋ አድርጓል። በሚኒስትር ማርክዌይን ሙሊን ( የሚመራው የኢሚግሬሽንና ጉምሩክ አስከባሪ አካል በአገሪቱ የውስጥ ክፍል የሚያካሂደውን የስደተኞች አደን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደጉን ሰነዶቹ ያረጋግጣሉ። የሰኔ ወር መረጃ እንደሚያሳየው በየቀኑ በICE ተይዘው ወደ ማቆያ የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር በአማካይ ከ1,300 በላይ የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ሚኒስትሩ ሥልጣን በያዙበት በኤፕሪል ወር ከነበረው አንጻር የ32 በመቶ ከፍተኛ ዕድገት ያሳየና ከ2021 ዓ.ም. ወዲህ በየትኛውም ወር ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛው የምዝገባ ቁጥር ነው።
ይህንን አዲስ ይፋ የተደረገ መረጃ በጥልቀት ስንመረምረው፣ በሁለተኛው የትራምፕ አስተዳደር ሥር የአሜሪካ የኢሚግሬሽን አስከባሪ ተቋም የተከተለውን ስልታዊና መዋቅራዊ የፖለቲካ ሽግግር ፍንትው አድርጎ ያሳያል። የማይግሬሽን ፖሊሲ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተንታኝ አሪኤል ሩዊዝ ሶቶ እንዳሉት፣ የICE ቀደሞ አሠራሮች ይበልጥ በግልጽ የሚታዩ፣ በአደባባይ አወዛጋቢ የነበሩ እና የትራምፕን አስተዳደር በሚቃወሙ ከተሞች ላይ ያነጣጠሩ ነበሩ። አሁን ግን የጸጥታው መሥሪያ ቤት የሚከተለው ስልት ብዙም ለአይን የማይታይና ድምፅ አልባ ቢሆንም፣ መሬት ላይ የሚያስመዘግበው ውጤት ግን ከዚያ በበለጠ መልኩ እጅግ አውዳሚና ሰፊ መሆኑን ያሳያል።
ይበልጥ አሳሳቢውና መዋቅራዊ ቀውሱን የሚያጋልጠው እውነታ፣ ምንም ዓይነት የወንጀል ሪከርድ ወይም ክስ የሌለባቸው ንጹሐን ስደተኞች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ነው። የአገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ተቋሙ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የወንጀል ታሪክ ያላቸውን ስደተኞች የማደንና የማባረር ቃላቸውን እየፈጸሙ ነው ቢሉም፣ መረጃው ግን ሌላ እውነታ ያሳያል። በጃንዋሪ 2025 ዓ.ም. የወንጀል ሪከርድ ሳይኖራቸው በቁጥጥር ሥር የዋሉ ስደተኞች ቁጥር ከጠቅላላው ታሳሪ 6 በመቶ ብቻ የነበረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ግን ይህ ቁጥር በከፍተኛ ዝላይ ወደ 37 በመቶ አሽቆልቁሏል። ይህ የሚያሳየው የICE የአደን መረብ ወንጀለኞችን ብቻ ሳይሆን ማናቸውንም ሰነድ አልባ ስደተኞች በጅምላ ማካተት መጀመሩን ነው።
በተጨማሪም፣ በቴክሳስ እና ሜይን ግዛቶች ውስጥ በቅርቡ የተከሰቱትን ገዳይ የተኩስ ልውውጦች ተከትሎ በICE ላይ የደረሰውን ሕዝባዊ ወቀሳና ተቋማዊ ተጠያቂነትን ለመሸሸግ ሲባል መሥሪያ ቤቱ መረጃዎችን ከ100 ቀናት በላይ ደብቆ ማቆየቱ በራሱ ሕግ አውጪው ምክር ቤት (ኮንግረንስ) በየሁለት ሳምንቱ መረጃዎች ይፋ እንዲሆኑ ያስቀመጠውን ትእዛዝ በግልጽ የጣሰ ነው። ምንም እንኳን እስራቱ በከፍተኛ ሁኔታ ቢጨምርም፣ ሰዎችን ከአገር የማስወጣቱ ሂደት ግን ካለፈው ዓመት አንጻር ለውጥ ሳያሳይ ባለበት የቆመ በመሆኑ የታሳሪዎች ቁጥር ማቆያዎችን እያጨናነቀ ይገኛል። ይህ መዋቅራዊ አለመረጋጋት፣ የስደተኞች መብት ተሟጋቾች እና የሕግ ባለሙያዎች በትራምፕ አስተዳደር የውስጥ የኢሚግሬሽን ፖሊሲ ላይ ያላቸውን ጥርጣሬና ተቃውሞ ይበልጥ የሚያበረታታው ከመሆኑም በላይ፣ አገሪቱን ወደ ከፋ ሰብዓዊ ቀውስና ሕጋዊ ፍጥጫ ሊመራት እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች በጥብቅ ያስጠነቅቃሉ።

18 days ago
ቼልሲ ሞርጋን ሮጀርስን በ117 ሚሊዮን ፓውንድ ለማስፈረም ከአስቶን ቪላ ጋር ተስማማ
***********************
የለንደኑ ክለብ ቼልሲ እንግሊዛዊዉን የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ሞርጋን ሮጀርስን በ117 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ዋጋ ለማስፈረም ከአስቶን ቪላ ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
ይህ ዝውውር ከተጠናቀቀ፣ ማንቸስተር ሲቲ ኤሊዮት አንደርሰንን ከኖቲንግሃም ፎረስት በ116 ሚሊዮን ፓውንድ ለማስፈረም የደረሰበትን ስምምነት በመብለጥ ከፍተኛ ገንዘብ የወጣበት እንግሊዛዊ ተጫዋች በመሆን ሪከርድ እንደሚሰብር ተነግሯል፡፡
በዘንድሮው የክረምት የዝውውር መስኮት የአርሰናል ዋነኛ የፊት መስመር ኢላማ የነበረው ይኸው አጥቂ፤ በአሁኑ ወቅት በዓለም ዋንጫው ላይ ከፈረንሳይ ጋር ለሚደረገው የደረጃ ጨዋታ ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር በመዘጋጀት ላይ ይገኛል።

19 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች ተከሶ በእስር ላይ የሚገኘው ታዋቂው የአር ኤንድ ቢ (R&B) አቀንቃኝ አር ኬሊ፣ ከእስር ቀድሞ ለመለቀቅ በሚያደርገው ጥረት የፕሬዝዳንት ምህረት እንዲደረግለት ጥያቄ ማቅረቡ ተገለጸ። በዚህ ሳምንት በአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ድረ-ገጽ ላይ የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ የ59 ዓመቱ አርቲስት የተፈረደበት የ30 ዓመት የእስር ቅጣት እንዲቀነስለት ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መደበኛ አቤቱታ አቅርቧል።
በአሁኑ ወቅት ማመልከቻው በፍትህ ሚኒስቴር የይቅርታ ቦርድ ዘንድ "ውሳኔ የሚጠብቅ" በሚል የተመዘገበ ሲሆን፣ አር ኬሊ የጠየቀው ሙሉ የፕሬዝዳንት ይቅርታን ሳይሆን የእስር ጊዜው እንዲቀነስለት ወይም እንዲቋረጥለት ነው። ይህ ማለት ጥያቄው ተቀባይነት ቢያገኝም፣ የተፈረደበት የወንጀል ሪከርድ ግን አይሰረዝም።
አር ኬሊ (ትክክለኛ ስሙ ሮበርት ሲልቬስተር ኬሊ) በአሁኑ ጊዜ በሰሜን ካሮላይና በሚገኝ የፌደራል ማረሚያ ቤት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ ለእስር የተዳረገውም ከፍተኛ ትኩረት በሳቡ ሁለት ተከታታይ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ነው። እ.ኤ.አ. በ2021 በኒውዮርክ ብሩክሊን ፍርድ ቤት በጾታ ብዝበዛ፣ በሰዎች ዝውውር እና አፈና ወንጀሎች የ30 ዓመት እስራት የተፈረደበት ሲሆን፣ በ2022 ደግሞ በትውልድ ከተማው ቺካጎ በህጻናት ፖርኖግራፊ እና በጾታዊ ጥቃት ጥፋተኛ ተብሎ ተጨማሪ የ20 ዓመት ቅጣት ተላልፎበታል። የፕሬዝዳንቱ የቅጣት ማቅለል ጣልቃ ገብነት ወይም የህግ ይግባኝ ካልተሳካ በስተቀር፣ አር ኬሊ እስራቱን አጠናቆ በ2045 (በ79 ዓመቱ) እንደሚፈታ ይጠበቃል።
ማመልከቻውን አስመልክቶ የቀረቡት ዝርዝር ሰነዶች ለህዝብ ይፋ ባይደረጉም፣ ይህ እርምጃ የአር ኬሊ ጠበቆች መደበኛ ካልሆኑ የህግ አግባቦች ውጭ እያደረጉት ያለው ሙከራ አካል ነው። የዘፋኙ ጠበቃ ቦ ብሪንድሊ ከዚህ ቀደም ባቀረቡት አቤቱታ፣ ደንበኛቸው በማረሚያ ቤት ውስጥ ህይወቱ አደጋ ላይ መሆኑን ገልጸው ነበር። የጥበቃ ሰራተኞች ምስክሮችን ለማስፈራራት ደብዳቤዎቹን እንደጠለፉበት፣ እንዲሁም አንድ በጠና የታመመ ነጭ ዘረኛ እስረኛ አር ኬሊን ከገደለ ነጻ እንደሚለቀቅ ቃል ተገብቶለት እንደነበር ጠበቃው ከሰዋል። በተጨማሪም በሳንባው ላይ ለተፈጠረ የደም መርጋት ተገቢውን የህክምና እርዳታ እንዳላገኘ የጠቀሱት ጠበቆቹ፣ እነዚህን የደህንነት ስጋቶች ፕሬዝዳንቱ ጣልቃ እንዲገቡበት እንደ ዋና ምክንያት አቅርበዋቸዋል።
ጉዳዩ በማህበራዊ ሚዲያ እና በዜና አውታሮች ሰፊ መነጋገሪያ ቢሆንም፣ የዋይት ሃውስ ባለስልጣናት ግን ማመልከቻው ማንኛውም ሰው ሊጠቀምበት በሚችለው የህዝብ መግቢያ በኩል የቀረበ መደበኛ ጥያቄ መሆኑን በማስረዳት ለጉዳዩ የተለየ የፖለቲካ ክብደት እንዳይሰጠው አድርገዋል። አንድ የዋይት ሃውስ ባለስልጣን በሰጡት አስተያየት፣ የይቅርታ ማመልከቻ መግባቱ አስተዳደሩ ለግለሰቡ ልዩ ድጋፍ እንዳለው አድርጎ መውሰድ እንደማይገባ አስረድተዋል። የይቅርታ ቦርዱ ጉዳዩን በተለመደው የህግ አግባብ ማጣራቱን የሚቀጥል ቢሆንም፣ ማመልከቻውን የመቀበል፣ የማሻሻል ወይም ውድቅ የማድረግ የመጨረሻው ሙሉ ስልጣን ግን በአሜሪካ ህገ-መንግስት መሰረት የፕሬዝዳንቱ ብቻ ይሆናል።

22 days ago
አህመድ ተሾመ (ዲንቢ) «ጊዜ አይሄድም» የተሰኘውን 3ኛ አልበሙን ሊለቅ ነው!
#fastmereja :-ታዋቂው ድምፃዊና የዜማ ደራሲ አህመድ ተሾመ (ዲንቢ) «ጊዜ አይሄድም» የተሰኘውን 3ኛ ሙሉ የሙዚቃ አልበሙን የፊታችን ሐምሌ 10 ቀን ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ በዛሬዉ እለት በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።
በናሆም ሪከርድስ (Nahom Records) አማካኝነት በተለያዩ የሙዚቃ ማሰራጫዎችና በዩቲዩብ የሚለቀቀው ይህ አልበም፣ በአጠቃላይ 13 ትራኮችን የያዘ ሲሆን የሀገር ፍቅርን፣ ማህበራዊ ህይወትንና ፍቅርን የሚዳስሱ ይዘቶች እንዳሉት ተገልጿል። አልበሙ «ጊዜ አይገድም» እና «ይረፍዳል» የሚሉ ተቃራኒ እውነታዎችን ያጣመረ ልዩ ፍልስፍናዊ ጭብጥም እንዳለዉ ነዉ የተገለፀዉ።
ይህም ተስፋ ላለው ሰው ጊዜ እንደማይሄድና ሁሌም ብርሃን እንዳለ የሚያሳይ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ጊዜ የማይጠብቅ መሆኑንና «ይረፍዳል» የሚለውን ተቃራኒ የህይወት እውነታ በአንድ ላይ አጣምሮ የያዘ ልዩ ፍልስፍናዊ ስራ ስለመሆኑም ነዉ የተገለፀዉ።
በአልበሙ ዝግጅት ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረገው ድምፃዊና የግጥም ደራሲ ካድር አሊ «እሳሳታለሁ» እና «ከፍ በል» የተሰኙ ሁለት ስራዎችን በግጥምና በድምፅ ያበረከተ ሲሆን፣ ስራው ዘመን ተሻጋሪና በጥራት የተሰራ መሆኑን ገልጿል።
አህመድ ተሾመ (ዲንቢ) ከዚህ ቀደም «እዮሪካ» እና «ኦሜርታ» የተሰኙ እጅግ ተወዳጅና ስኬታማ አልበሞችን ለአድማጮች ያበረከተ ሲሆን፤ «ዲንቢ ለዲንቢ»፣ «ተጠየቂ ናዝሬት»፣ «አውራአምባ»፣ «በትዝታው ፈረስ» እና «አይ መሬት ያለ ሰው» የተሰኙ በርካታ የራሱ ተወዳጅ ሙዚቃዎች አሉት።
ከዚህ ቀደም «እዮሪካ» እና «ኦሜርታ» የተሰኙ ተወዳጅ አልበሞችን ለአድማጮች ያበረከተው አህመድ ተሾመ (ዲንቢ)፤ ለማዲንጎ አፈወርቅ፣ ለፀሀዬ ዮሀንስ፣ ለብዙአየሁ ደምሴ እና ለዘቢባ ግርማ በርካታ ተወዳጅ ዜማዎችን በመስራት የሚታወቅ ስኬታማ ባለሙያ ነው።

የአህመድ ተሾመ(ዲንቢ) ‘ጊዜ አይሄድም’ የሙዚቃ አልበም ሐምሌ 10 ሊለቀቅ ነው
#ethiopia | ታዋቂው ድምፃዊና ዜማ ደራሲ አህመድ ተሾመ (ዲንቢ) ‘ጊዜ አይሄድም’ የተሰኘውን አዲስ የሙዚቃ አልበሙን መጪው ሐምሌ 10 ቀን በናሆም ሪከርድስ የዩቲዩብ ቻናል እና በተለያዩ የዲጂታል አማራጮች በኩል ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ታውቋል።
በአጠቃላይ 13 ትራኮችን የያዘው ይህ አልበም የወቅቱን ትውልድ ስሜትና የዘመኑን ምልከታ በጥሩ ሁኔታ የሚያንጸባርቅ ከመሆኑም በላይ አገራዊ ፍቅርን፣ ማኅበራዊ ሕይወትን፣ ተስፋንና እምነትን በጥልቀት የሚዳስስ ሰፊ ይዘት አለው።
በአልበሙ ዝግጅት ላይ የተሳተፉት ባለሙያዎች እንደገለጹት ይህ ሥራ ከተለመደው የሙዚቃ አቀራረብ ወጣ ባለ መልኩ በጥልቅ ሐሳቦችና በከፍተኛ ጥንቃቄ የተሰናዳ የጥበብ ውጤት ነው።
በተለይም በአልበሙ ላይ በሁለት ሥራዎች የተሳተፈው ከድር፣ ‘እሳሳታለሁ’ የተሰኘ የፍቅር ዘፈን እና ‘ከፍ በይ’ የተባለ አገራዊ ይዘት ያለው የሙዚቃ ሥራ ማበርከቱን ጠቅሶ፣ አልበሙ እያንዳንዱን የሰው ልጅ የሕይወት ውጣ ውረድ የሚዳስስ በመሆኑ የሙዚቃ አፍቃሪያንን ልብ እንደሚገዛ ሙሉ እምነት እንዳለው ገልጿል።
📸 ከበደ መክብብ
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

23 days ago
ድምፃዊ አህመድ ተሾመ አዲሱን "ጊዜ አይሄድም" አልበም ለታዋቂ የጥበብ ሰዎች አስቀድሞ አስደመጠ
#ethiopia | ድምፃዊና የዜማ ደራሲ አህመድ ተሾመ (ዲንቢ) በመጪው አርብ ሐምሌ 10 ቀን በናሆም ሪከርድስ አማካኝነት ለአድማጮች የሚያቀርበውን "ጊዜ አይሄድም" የተሰኘ 3ኛ የሙዚቃ አልበሙን ከመለቀቁ በፊት ለታዋቂ የሀገራችን የጥበብ ሰዎች ያስደመጠበት የአልበም ቅምሻ ዝግጅት በደብል ትሪ (ባይ ሂልተን) ሆቴል ተካሂዷል።
በዝግጅቱ ላይ ባለቅኔ፣ ገጣሚና ፀሐፊ ተውኔት አያልነህ ሙላት፣ አርቲስት አበበ ባልቻ፣ ፀሐፊ ተውኔት ሀይሉ ፀጋዬ፣ አርቲስት ታምሩ ብርሃኑ፣ የሙዚቃ ባለሙያዎች ጆርጋ መስፍን፣ ብሌን ዮሴፍ፣ ብሩክ አሰፋ እንዲሁም ድምፃዊ አብርሃም በላይነህ (ሻላዬ)፣ አርቲስት ዕድልወርቅ ጣሰው፣ ቲክቶከር ሀያት ናስር (ዩቲ ናስ) እና ሌሎች በርካታ የጥበብ ባለሙያዎች ተገኝተው አልበሙን ቀድመው አዳምጠዋል።
አህመድ ተሾመ፣ "አልበሜን ለመላው የሙዚቃ አፍቃሪ ከማስደመጤ በፊት መርቁኝ፤ ሀሳብና አስተያየታችሁን ንገሩኝ" በማለት ከተጋባዦቹ ጋር ሰፊ ውይይት አድርጓል።
አልበሙን ቀድመው ያዳመጡት የጥበብ ሰዎችም በሙዚቃዎቹ እጅግ እንደተደሰቱ በመግለጽ ለድምፃዊው መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
"ጊዜ አይሄድም" የተሰኘው 3ኛው የአህመድ ተሾመ (ዲንቢ) አልበም በመጪው አርብ በይፋ ለአድማጮች የሚቀርብ ሲሆን፣ በብዙ የሙዚቃና የጥበብ አፍቃሪዎች በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል።

25 days ago
በመሳሳም ሪከርድ የሰበሩት ጥንዶች
የአለማችን ምርጥ ጥንድ አስብሏቸዋል
#ethiopia | ብራዚላዊያን የሆኑት እነዚህ ጥንዶች በ30 ሰከንድ ውስጥ 195 ጊዜ በመሳሳም አዲስ ሪከርድ አስመዝግበዋል።
ሬናቶ ባይማ ጋያ እና ናያራ ሮቤርታ ሪቤሮ ደ ማሪንስ የተባሉት እነዚህ ጥንዶች ይህንን ሪከርድ የግላቸው ያደረጉት በአለም አቀፍ የመሳሳም ቀን (International Kissing Day) ነው።
ጥንዶቹ ለጊነስ ወርልድ ሪከርድ እንደገለጹት ይህንን ውድድር ያደረጉት በአለም ላይ ምርጥ ጥንዶች ነን ብለው ስለሚያምኑ እና አብረው አንድ የማይረሳ ነገር ለመስራት በማሰብ እንደሆነ ተናግረዋል።
ሁለቱም ሙያቸው የሕክምና ባለሙያ ሲሆኑ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በግንባር ቀደምትነት ህዝባቸውን ያገለገሉ መሆናቸው ገልጸዋል።
ሬናቶ ባይማ ቀደም ሲልም በተለያዩ የሪከርድ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ የሚታወቅ ሲሆን የዚህኛው የሪከርድ ስኬት ግን ለናያራ የመጀመሪያዋ መሆኑን ተናግረዋል።
ጥንዶቹ በቀጣይ በአንድ ደቂቃ ውስጥ ብዙ ጊዜ በመሳሳም ያለውን ሌላ ሪከርድ ለመስበር እቅድ እንዳላቸውም ተናግረዋል ያለው ዩፒአይ ነው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #brazilbestcoupleintheworld #worldkissingday #worldguinnessrecord #upioddenews

26 days ago
ከፖለቲካ ሽኩቻ የላቀው የጋራ ተቋማችንን እናክብር
****************
የአንድ ሀገር ጥንካሬ ከሚገለጽባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች መካከል አንዱ ዜጎች በጋራ የሚግባቡባቸው እና በኩራት የሚጠሯቸው ጠንካራ ብሔራዊ ተቋማት መኖራቸው ነው።
ከእነዚህ ተቋማት መካከል ደግሞ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀዳሚውን እና የክብር ማማውን ስፍራ ይይዛል።
የዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ስንመለከት፣ በሠለጠኑ ዴሞክራሲያዊ ሀገራት የሠራዊት አባላትን ማክበር ከፖለቲካዊ ሽኩቻዎች የላቀ ብሔራዊ መግባባት የተገነባበት ጉዳይ ሆኖ እናገኘዋለን።
በአሜሪካ የፖለቲካ ምኅዳር ውስጥ በፓርቲዎች መካከል የጎላ ርዕዮተ ዓለማዊ ልዩነት ቢኖርም፣ ሠራዊቱን ከፖለቲካ ፉክክር ውጪ የማድረግ ብሔራዊ ስምምነት አለ።
የፖለቲካ ፓርቲዎች የመንግሥትን ፖሊሲ በሚተቹበት ወቅት እንኳ በጦር ግንባር የተሰማሩትን ወታደሮች እንደ ጀግና በመቁጠር ውዳሴ እና ክብር ያቀርባሉ።
በዩናይትድ ኪንግደም "የጦር ኃይሎች ቃል ኪዳን" (Armed Forces Covenant) የተሰኘው ብሔራዊ ሰነድ የሠራዊት አባላት ልዩ ክብር እንዲያገኙ ያደርጋል።
ካናዳ ለአርበኞች ልዩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ስታቋቁም፣ ፈረንሳይ ደግሞ ሠራዊቷን የሀገሯ የክብር እና የአጋርነት ብሔራዊ ተምሳሌት በማድረግ በትልቅ ማዕረግ ትዘክራለች።
ወደ ሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ስንመጣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በባሕርይው እጅግ ሕዝባዊ የሆነ፣ ከሀገር አልፎ ለዓለም የሰላም ዘብ በመሆን ደሙን የገበረ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው።
የኢትዮጵያ ወታደር በኮሪያ ልሳነ ምድር በቃኘው ሻለቃ አማካኝነት "አንድም ወታደር አልተማረከም፤ የሞተ ጓዱንም ጥሎ አልመጣም" የሚል የዓለምን አስደናቂ ሪከርድ ያስመዘገበ ጀግና ነው።
በኮንጎ፣ በሩዋንዳ፣ በቡሩንዲ፣ በላይቤሪያ፣ በአብዬ፣ በዳርፉር እና በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ላይ በመሰማራት አፍሪካውያን ወንድሞቹን ከእልቂት የታደገ፣ የራሱን ሬሽን እያካፈለ የውጭ ሀገር ዜጎችን ያኖረ የሰብአዊነት ተምሳሌት ነው።
ይህ ሠራዊት በሀገር ውስጥም ቢሆን ጦር መሣሪያውን አስቀምጦ በክረምት የገበሬውን ማሳ ሲያርስ እና በመኸር ሲያጭድ፣ የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ከነፍስ አድን ሥራ እስከ አንበጣ መንጋ ማባረር ድረስ ከሕዝቡ ጎን የቆመ ታላቅ አለኝታ ነው።
ነገር ግን አለመታደል ሆኖ፣ የሀገራችን መከላከያ ሠራዊት በፖለቲካ ኃይሎች መካከል በሚደረጉ ፍልሚያዎች ውስጥ የከፉ ምኞቶች ሰለባ ሲሆን ይስተዋላል።
አንዳንዴም የፖለቲካ ልዩነትን እና የሀገርን የፀጥታ ምሰሶ መለየት ያቃታቸው አካላት ሠራዊቱን የማንቋሸሽ አዝማሚያ ያሳያሉ።
የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ማክበር እና ለሀገር ሕልውና የሚከፍለውን ዋጋ ማወቅ የአንድ ማኅበረሰብ የሥልጣኔ መገለጫ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተደጋጋሚ አስገንዝበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ በፓርላማ ባደረጉት ንግግር፣ ሀገርን ጠብቆ የሚያኖርን ኃይል እንደ "ገዳይ" መፈረጅ እና ተቋማዊ ክብሩን አለማወቅ የሲቪል-ወታደራዊ ግንኙነትን አለመረዳት እና ያለመሠልጠን ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
መንግሥት እና ፖሊሲ አውጪዎችን በጥብቅ መተቸት የዴሞክራሲ አካል ነው። ነገር ግን ለሀገር ሕልውና አጥንቱን የሚከሰክሰውን ሠራዊት ከተቋማዊ ትችት ነፃ አድርጎ በጀግንነት መዘከር ይገባል።
በመሠረቱ ሠራዊቱ ሕዝብን የመጠበቅ ግዴታ ሲኖርበት፣ መንግሥት እና ሕዝብ ደግሞ የሠራዊቱን መሥዋዕትነት የመካስ የሞራል ግዴታ አለባቸው።
ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ትኩረት አድርጋ ከሠራችባቸው የሪፎርም ሥራዎች መካከል የፀጥታ ተቋማት ግንባታ ዋነኛው የሆነውም ለዚሁ ነው።
ሠራዊታችን ከፖለቲካ ልዩነቶቻችን በላይ የሆነ የጋራ የብረት አጥራችን እና የሕልውናችን ምሰሶ በመሆኑ ዘወትር ክብር እና ሞገስ ይገባዋል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #endf #nationalpride #standwithourtroops

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ቀይ ባህር እግር ኳስ ክለብ የኤርትራን ፕሪሚየር ሊግ ለማንሳት ተቃረበ፡፡ በዘንድሮው የኤርትራ ፕሪምየር ሊግ ቀይ ባህር እግር ኳስ ክለብ ሻምፒዮን የመሆን እድሉን አስፍቷል፡፡ ባለፉት ሁለት የውድድር አመታት በጦር ሀይሉ ስር በሚተዳደረው ደንደን ክለብ ሻምፒዮን በመሆን ቀይ ባህር በአገሪቱ ውስጥ የነበረውን የኳስ የበላይነት ለመንጠቅ መቻሉ ይታወሳል፡፡
ይሁንና ዘንድሮ ቀይ ባህር ይህንን የበላይነት በመመለስ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ተቃርቧል፡፡ ቀይ ባህር ይህንን ዋንጫ የሚያነሳ ከሆነ ለ15ተኛ ጊዜ የኤርትራ ሻምፒዮን በመሆን አዲስ ሪከርድ ያስመዘግባል፡፡ ደንደን ክለብ ዘንድሮ ጥሩ ተፎካካሪ በመሆን ሲጫወት የቆየ ቢሆንም ከአስመራ ቢራ ጋር ባደረገው ግጥሚያ አንድ ለዜሮ መሸነፉ የሻምፒዮንነት እድሉን አጥቦታል፡፡ ፕሪምየር ሊጉን ቀይባህር ክለብ በ33 ነጥብ የሚመራ ሲሆን ደንደን በ30 ነጥብ ይከተላል፡፡
ሁለቱ ክለቦች የፊታችን እሁድ በአስመራ ስታዲየም የውድድር ዘመኑን የመጨረሸ ግጥሚያ ያደርጋሉ፡፡ በጨዋታው ደንደን ቢያሸንፍ እንኳ ቀይ ባህር በግብ ክፍያ የበላይነቱን በመያዙ ዋንጫውን እንደሚወስደው ብዙዎች ገምተዋል፡፡ አፍሪካን ፉትቦል እንደዘገበው በእሁዱ ግጥሚያ ደንደን በ12 የግብ ልዩነት ያሸንፋል ብሎ መጠበቅ የማይታሰብ ነው፡፡

"የብራዚል እግር ኳስ ስብራት ገጥሞታል!"
የፔሌ ልጅ
#ethiopia | የብራዚል እግር ኳስ አስተዳደር በብልሹ አሰራር በመውደቁ እግርኳሱ ስብራት ገጥሞታል ስትል የፔሌ ልጅ ተናግራለች።
የአስተዳደሩ ግልጽነት እና ተጠያቂነት የጎደለው አሰራር በብሔራዊ ቡድኑ አፈጻጸም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል ብላለች።
የእግርኳሱ ኮኮብ የፔሌ ታላቅ ሴት ልጅ አክቲቪስት እና የፊልም ባለሙያ የሆነችው ኬሊ ናሲሜንቶ ፔሌ ለሮይተርስ በሰጠችው ቃለ መጠይቅ ብሔራዊ ቡድኑ የገጠመውን ችግር ተናግራለች።
የብራዚል እግር ኳስ ተበላሽቷል
ሙስናና ሌላም ችግር በአስተዳደሩ ይነጸባረቃል ይህ በጣም ግልጽ ነው ብላለች።
ሁሉም ሰው አስተዳደሩ ለምን እንደማይሰራ ያውቃል ነገር ግን አንድም አካል ሊያስተካክለው አልቻለም ስትል ናሲሜንቶ ገልጻለች።
የብራዚል እግር ኳስ አሁንም ተሰጥኦ ያላቸው ምርጥ ተጫዋቾችን ማፍራቱን ቢቀጥልም በዓለም አቀፍ መድረክ የሚያሳዩት ደካማ አፈጻጸም ግን ሥር የሰደዱ መዋቅራዊ ችግሮች ውጤት መሆኑን ገልጻለች።
ብራዚል እሁድ ዕለት በኖርዌይ 2 ለ 1 ከተሸነፈች በኋላ ከውድድሩ ውጪ መሆኗ ይታወሳል።
ይህ ውጤት ብራዚል ከ1990 ወዲህ ለሩብ ፍጻሜ ማለፍ ሳትችል ስትቀር የመጀመሪያዋ ነው።
ሀገሪቱ ሪከርድ የሆነውን አምስተኛ የዓለም ዋንጫዋን ያሸነፈችው እ.ኤ.አ በ2002 ነበር።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #brazilfootball #reuters #greatpeledaughter #kelynascimento #activistfilmmaker

27 days ago
ፈረንሳይና አርጀንቲና በቅጣት ምቶች እኩል ሪከርድ አላቸው
#ethiopia | በመጨረሻዎቹ ሶስት የፊፋ ዓለም ዋንጫ ውድድሮች (2018፣ 2022 እና 2026) ፈረንሳይና አርጀንቲና እያንዳንዳቸው 8 የፍፁም ቅጣት ምቶች ተሰጥተዋል።
ይህ መረጃ ሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖች በተጠቀሱት ሦስት የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ተመሳሳይ ቁጥር ያለው የፍፁም ቅጣት ምት እንዳገኙ ያሳያል።
በ2026 የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ ከሞሮኮ ጋር በተደረገው ጨዋታም ፈረንሳይ የፍፁም ቅጣት ምት አግኝታ ቢሆንም፣ ኪሊያን ምባፔ ወደ ግብ መቀየር አልቻለም።
#fifaworldcup #france #argentina #mbappe #messi #getu

29 days ago
"ጊዜ አይሄድም" እየመጣ ነው!
ሰላም የምወዳችሁና የማከብራችሁ የጥበብ ቤተሰቦቼና ውድ አድናቂዎቼ!
#ethiopia | ሐምሌ 10 በናሆም ሪከርድስ የማይረሳ ቀጠሮ አለን። በአዲሱ "ጊዜ አይሄድም" ቅጽ 3 አልበሜ ውስጥ ዘፈኖችን ብቻ ሳይሆን የሕይወቴን ተሞክሮ፣ ስሜትና ታሪክ በሙዚቃ ቋንቋ አቅርቤላችኋለሁ።
ይህ ሥራ ወደ እናንተ እንዲደርስ ከመጀመሪያው ጀምሮ ከጎኔ በመቆም ላልተቆጠበ ድጋፍ የናሆም ሪከርድስ ባለቤት አቶ ኤሊያስ ፍቅሩን ከልብ አመሰግናለሁ።
እንዲሁም ድምፃዊና ፕሮዲውሰር ደመላሽ ንጉሴ በዚህ አልበም ላይ በፕሮዲውሰርነት ላደረግኸው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
በግጥም ችሎታችሁ ለአልበሙ ልዩ ውበት ያከላችሁ፤ እልፍአግድ እምሻው፣ ናትናኤል ግርማቸው፣ ከድር አሊ፣ ምልዕቲ ኪሮስ፣ አቡዲ እና ወንድወሰን ይሁብ ሁላችሁንም ብዕራችሁ አይነጥፍ፤ ከልብ አመሰግናለሁ።
በሙዚቃ ቅንብር ደግሞ ለዘፈኖቼ ነፍስ የዘራችሁ፤ ታምሩ አማረ፣ ሚካኤል ሀይሉ (ሚኪ ጃኖ)፣ አንተነህ ተፈራ (አቡዝ)፣ አዲስ ፍቃዱ፣ ፋኑ ጊዳቦ እና ኤርሚያስ በዳዳ ሁላችሁንም በጣም አመሰግናለሁ።
እንዲሁም ሁሉንም ሙዚቃዎቼ በማስተር ሥራ የአለባበሰው ሰለሞን ሀ/ማርያም ላደረግኸው ድንቅ ሙያዊ አስተዋፅኦ ልዩ ምስጋናዬ ይድረስህ።
በአጠቃላይ በዚህ አልበም ጉዞ ላይ በሙያችሁ፣ በሀሳባችሁ እና በማበረታቻችሁ ከጎኔ ለቆማችሁ ወዳጆቼና ባለሙያዎች በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ።
ሐምሌ 10 በናሆም ሪከርድስ እንገናኝ! ከእናንተ ጋር ይህን ልዩ የሙዚቃ ጉዞ ለመጋራት በታላቅ ጉጉት እጠብቃለሁ።
ከፍቅር ጋር፣
አህመድ ተሾመ ( ዲንቢ )

1 month ago
ምባፔ የዓለም ዋንጫ ታሪክን ሊቀይር አንድ ጎል ብቻ ቀረው
#ethiopia | የፈረንሳይ ካፒቴን ኪሊያን ምባፔ በ2026 የዓለም ዋንጫ ስዊድንን 3ለ0 በተሸነፈችበት ጨዋታ ሁለት ጎሎችን በማስቆጠር በዓለም ዋንጫ ታሪክ ያለውን የጎል ብዛት ወደ 18 አሳድጓል።
በዚህ ውጤት ምባፔ በዓለም ዋንጫ የምንጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች ዝርዝር ሁለተኛ ደረጃ ላይ በመውጣት 16 ጎሎች ያሉትን ሚሮስላቭ ክሎዝን በልጧል። አሁን ደግሞ 19 ጎሎች ካሉት ሊዮኔል ሜሲ አንድ ጎል ብቻ ይለየዋል።
በገና በወጣትነቱ ያለው ምባፔ፣ በቀጣዮቹ የውድድር ጨዋታዎች ይህን ሪከርድ የማሻሻል ትልቅ ዕድል አለው። ፈረንሳይም ወደ 16 ቡድኖች ካለፈች በኋላ ከፓራጓይ ጋር በምታደርገው ጨዋታ ሁሉም ዓይኖች በምባፔ ላይ ያተኩራሉ።
የፈረንሳይ ካፒቴን ኪሊያን ምባፔ በ2026 የዓለም ዋንጫ ስዊድንን 3-0 በተሸነፈችበት ጨዋታ ሁለት ጎሎችን በማስቆጠር በውድድሩ የጥሎ ማለፍ ዙር 10 ጎሎችን ያስቆጠረ በታሪክ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።
ይህ አስደናቂ ሪከርድ ምባፔ በትልልቅ ጨዋታዎች ያለውን ልዩ ብቃት በድጋሚ ያረጋገጠ ሲሆን፣ በዓለም ዋንጫ ታሪክ ውስጥ ስሙን በወርቅ ፊደል ለመጻፍ እየተቃረበ መሆኑንም ያሳያል።
የዓለም ዋንጫ ታሪክ አዲስ ባለሪከርድ ይኖረው ይሆን? የዚህ ጥያቄ መልስ በቀጣዮቹ ጨዋታዎች ይታወቃል።

ፈረንሳይ በምባፔ ድንቅ ብቃት ስዊድንን 3-0 አሸንፋ ወደ 16 ቡድኖች አለፈች
#ethiopia | ፈረንሳይ በ2026 የዓለም ዋንጫ የ32 ቡድኖች የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ስዊድንን 3-0 በማሸነፍ ወደ 16 ቡድኖች በድምቀት አልፋለች።
በጨዋታው የፈረንሳይ ካፒቴን ኪሊያን ምባፔ ሁለት ጎሎችን በማስቆጠር የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ሲያበራ፣ ብራድሌይ ባርኮላ ሦስተኛውን ጎል በማከል ድሉን አረጋግጧል።
ፈረንሳይ ከጨዋታው መጀመሪያ ጀምሮ የኳስ ቁጥጥርና ፈጣን የማጥቃት አጨዋወት በማሳየት ስዊድንን ጫና ውስጥ አስገብታለች።
ምባፔ ከዕረፍት በፊት የመጀመሪያውን ጎል ሲያስቆጥር፣ ባርኮላ በሁለተኛው አጋማሽ ልዩነቱን አስፍቶታል። ምባፔ በድጋሚ መረብን በማንቀጥቀጥ የ3-0 ድሉን አጠናቋል።
በዚህ ድል ፈረንሳይ በውድድሩ ያላትን ፍጹም ሪከርድ ጠብቃ ወደ 16 ቡድኖች ማለፏን አረጋግጣለች። በቀጣዩ ዙርም ከፓራጓይ ጋር ትገናኛለች።
የፈረንሳይ አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሻምፕ ቡድናቸው በማጥቃት፣ በፍጥነት እና በቡድናዊ ቅንጅት ከዋንጫው ዋና ተፎካካሪዎች መካከል መሆኑን በድጋሚ አሳይቷል።
ምባፔም በተከታታይ አስደናቂ ብቃቱ በውድድሩ ትልቅ ተፅዕኖ እያሳደረ ይገኛል።

"ናና" የተወዳጇ ድምፃዊት ራሄል ጌቱ አዲስ የሙዚቃ ስራ የፊታችን አርብ በናሆም ሪከርድስ ይለቀቃል!
በላቀ የድምፅ ብቃቷ እና በተወዳጅ ስራዎቿ ሁሌም የምታስደንቀን ድምጻዊት ራሄል ጌቱ፣ የፊታችን አርብ ሐምሌ 26, 2018 ዓ.ም "ናና" የተሰኘ አዲስ የሙዚቃ ቪዲዮ ለአድማጭ ታቀርባለች::
በ16 ፊልም ፕሮዳክሽን ተሰርቶ የቀረበዉ ይህ ስራ በናሆም ሪከርድስ (Nahom Records) የዩቲዩብ ቻናል ላይ የሚለቀቅ ይሆናል። ከ"ጥሎብኝ" እስከ "እቴሜቴ አልበሞ" በልዩ ስራዎቿ ልባችንን የገዛችው ራሄል፣ በዚህኛው ደግሞ "ናና" በተሰኘው አዲስ ስራዋ ድንቅ ስራ ይዛልን መጥታለች።
#rahelgetu #nana #newethiopianmusic #ethiopianmusic #habeshamusic #ናና

''በጣም ደስ ብሎናል ምኞታችን ሞላ፣
አሸንፎ መጣ አበበ በቂላ''
📌ባዶ እግሩን ሮጦ ዓለምን ያስደነቀው የምንግዜውም ድንቅ አትሌት ሻምበል አበበ በቂላ
#ethiopia | በዓለም አቀፍ የስፖርት ታሪክ ውስጥ ስሙ በወርቅ ፊደላት የተጻፈውና የኢትዮጵያ ኩራት የሆነው ሻንበል አበበ በቂላ ለአፍሪካ አህጉር በኦሊምፒክ መድረክ የመጀመሪያውን ወርቅ ያስገኘ ድንቅ የኢትዮጵያ ልጅ ነው።
ይህ ድንቅ አትሌት በተለይ በ1960 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) በሮም ኦሊምፒክ የተካሄደውን የማራቶን ውድድር ባዶ እግሩን በመሮጥና በአንደኝነት በማጠናቀቅ መላውን ዓለም ያስደነቀ ሲሆን ድሉም ጥቁር ሕዝቦች በዓለም መድረክ ላይ ያላቸውን ታላቅ የጽናትና የአሸናፊነት አቅም በተግባር ያሳየ ታሪካዊ ክስተት ነበር።
ከዚህ ታላቅ ስኬት በኋላም አትሌት አበበ በቂላ በ1964 ዓ.ም በቶኪዮ ኦሊምፒክ የራሱን የዓለም ሪከርድ በማሻሻል ለሁለተኛ ጊዜ ተከታታይ የወርቅ ሜዳሊያ ማሸነፍ የቻለ ሲሆን ይህም በኦሊምፒክ ታሪክ የማራቶን ድልን በተከታታይ በመውሰድ የመጀመሪያው ስፖርተኛ አድርጎታል።
በወቅቱ የኢትዮጵያ ክብር ዘበኛ አባል የነበረው አበበ በቂላ በስፖርቱ ዓለም ላሳየው ተወዳዳሪ የሌለው ጽናትና ለሀገሩ ባበረከተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሻምበልነት ማዕረግ የተሰጠው ሲሆን ዛሬም ድረስ ለቀጣዩ የአፍሪካና የዓለም አትሌቶች ትውልድ የመንፈስ ጥንካሬና የድል ፈር ቀዳጅ ተምሳሌት ሆኖ በክብር ይነሳል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለዚህ ጀግና መታሰቢያው ይሆን ዘንድ በእርሱ ስም የሚያሰናዳው ''42ኛው የሻ/ል አበበ በቂላ ማራቶን ውድድር በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ማለዳ እንዲጀመር ቀጠሮ ቢያዝለትም በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ወደ 5:00 ሰዕት ተሸጋሽጓል።
ዝግጅት ክፍላችን ውድድሩን ለመዘገብ በስፍራው የተገኘ ሲሆን ለሁሉም አትሌቶች
መልካም ምኞታችንን እንገልጻል።
ለ Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽንስ
ያፌት ገ/ህይወት
ከሲዳማ ፤ ሐዋሳ

ያልተዘመረለት ጀግና!
* በኢትዮጵያ 30 ትምህርት ቤት አስገንብቷል
***
የአቶ አዲስ ገሠሠ አጭር የሕይወት ታሪክ
#ethiopia | አቶ አዲስ ገሰሰ ከአባታቸው ከግራዝማች ገሰሰ መንገሻ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ አስናቀች መልሴ ጥር 8 ቀን 1945 ዓ.ም. በቀድሞው ኢሊባቦር ጠቅላይ ግዛት ጎሬ ከተማ ተወለዱ፡፡
እስከ 9ነኛ ክፍል በጎሬ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ት/ቤት ከተማሩ በኋላ፤ የ10ኛ ክፍል ትምህርታቸውን አዲስ አበባ በዳግማዊ ምንሊክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተምረው፤ ወደ ጅማ በመሄድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሚያዝያ 27 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል፡፡
አቶ አዲሱ ገሰሰ በህይወታቸው ትልቅ ቦታ የሚሰጡትና “ ስብዕናዬን በዲሲፕሊን ገንብቶታል” የሚሉትን የኢትዮጵያ አየር ኃይልን በ1961 ዓ.ም. በመቀላቀል ከወታደራዊ ስልጠና ጋር በበረራ ቴክኒሻንነት ተመርቀዋል፡፡
በሙያቸው አንድ ዓመት ካገለገሉ በኋላ፤ በ1964 ዓ.ም. ነፃ የትምህርት እድል በማግኘታቸው ወደ አሜሪካ ሀገር ሺካጎ ከተማ በማቅናት በራንቱል ኤርፎርስ ቤዝ፤ እና በቴክሳስ ላክላንድ ኤርፎርስ ቤዝ ትምህርታቸውን አጠናቀው ተመርቀዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ በወጣትነት ዘመናቸው ያን ጊዜ ሉፕ ኮሌጅ በሚባለው ሃሮልድ ዋሺንግተን ዩኒቨርሲቲ የሜካኒካል ኢንጅነሪንግ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡ በመቀጠልም በኖርዝ ኢስተርን ኢሊኖይ ዩኒቨርሲቲ በማኔጅመንት ትምህርታቸውን አጠናቀዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ ወንድሞቻቸውን ሙሉጌታ ገሰሰን፤ ዘለቀ ገሰሰንና ጓደኞቻቸውን እነ መላኩ ረታን ወደ ሺካጎ ካመጡ በኋላ ዳሎል ባንድን መስርተዋል፡፡ አቶ አዲስ ገሰሰ በሚማሩበት ኖርዝ ኢስተርን ኢሊኖይ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር ታሪክ ወር /Black History Month/ በሚል መጠሪያ በየዓመቱ የካቲት ወር ላይ በተለያየ መዘክር በሚከበር በዓል ላይ፤ ዳሎል ባንድ ሙዚቃ እንዲያቀርብ በማስቻል የሙዚቃ ማኔጅመንት የህይወት ጉዟቸውን ሀ ብለው ጀመሩ፡፡
በመቀጠልም ዳሎል ባንድን ይዘው በዋሺንግተን፤ በሎስ አንጀለስ እና በመላው አሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢትዮጵያውያን-በኢትዮጵያ ባንድ የሙዚቃ ኮንሰርት በማቅረብ ፈር ቀዳጅ እና ውጤታማ ስራ ሰርተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ ሙዚቃን ማኔጅ በማድረግ ጉዟቸው የእውቁን የሬጌ ሙዚቃ ንጉስ የቦብ ማርሌን ቤተሰብ ሃብትና ንብረቱን በማስተዳደር ብቻ ሳይሆን፤ የቦብን ልጆች በስነ ምግባር ኮትኮቶ ለማሳደግ ከአሜሪካ ኒውዮርክ -ጃማይካ ኪንግስተን እየተመላለሱ በትጋትና በታማኝነት ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡
በዚያን ጊዜም ዘመን አይሽሬውን የቦብ ማርሌይ “ሌጀንድ አልበም" እንዲሰራ ባቀረቡት ንድፈ-ሃሳብ መሰረት ከአይላንድ ሪከርዲንግ ጋር በመፈራረም ውጤማ ስራ ሰርተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ በቦብ ማርሌይ ቤተሰቦች የተዘጋጁትንና ከምድር ዳር እስከ ምድር ዳር ድረስ የተደረጉትን ዓለም አቀፍ የሬጌ ሙዚቃ ኮንሰርቶች ሃሳብ ከመጠንሰስ ጀምሮ ለሃያ ሁለት ዓመታት ያክል ስራውን በሃላፊነት መርተዋል፡፡ አስተዳድረዋል፡፡
በዚሁ የአስተዳደር ዘመናቸው በዘረጉት መንገድ እስካሁን ድረስ በየዓመቱ የሚደረገውን ዓለም አቀፍ የሬጌ ሙዚቃ ፌስቲቫል በማይናወጥ መሰረት ላይ አፅንተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ ዚጊ ማርሌይን ከጃማይካ… የነዘለቀን ገሰሰን ዳሎል ባንድ ደግሞ ከሺካጎ ወደኒዮርክ በማምጣት ካጣመሩ በኋላ ፤ ከሲግማ ስቱዲዮ እና ከቨርጂኒያ ሪከርድስ ጋር ውል በመፈራረም በአሜሪካ ምድር ቁጥር አንድ ተደማጭ የነበረውን ኮንሺየስ ፓርቲ አልበም እንዲለቀቅ አድርገዋል፡፡
በአልበሙ ከተካተቱት ስራዎች መካከል ቱሞሮ ፒውፕል የተሰኘው ሙዚቃ በዓለም ላይ እጅግ ከመወደዱ የተነሳ ብዙዎች እንደ ብሔራዊ መዝሙር ያዜሙት ነበር፡፡
በአቶ አዲስ ገሰሰ ማናጀርነት በተመራው በዚሁ የሙዚቃ አልበም ዚጊ ማርሌይ የአሜሪካንን ትልቁን ግራሚ አዋርድ ሽልማት ሲያገኝ፤ የኢትዮጵያው ዳሎል ባንድ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ባንድ የግራሚ ሽልማት እንዲወስድ በማስቻል ታሪክ የማይረሳውን ስራ ሰርተዋል፡፡
ለሀገራቸው ኢትዮጵያ የተለየ ፍቅር የነበራቸው አቶ አዲስ ገሰሰ ከወንድማቸው ከአርቲስት ዘለቀ ገሰሰ ጋር በመሆን የቦብ ማርሊ 60ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ለመዘከር የሚዘጋጀውን “አፍሪካ ዩናይት” ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ዝግጅት ኢትዮጵያን መዳረሻ በማድረግና አንድ አመት የፈጀ የዘመቻ /ካምፔይን/ በመስራት ፤ በ1997 ዓ.ም. መስቀል አደባባይ የተካሄደውን የሙዚቃ ፌስቲቫል ስኬታማ እንዲሆን አስችለዋል፡፡ በዚሁ ፌስቲቫል ላይ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ጨምሮ ሪታ ማርሌይና አምስቱ የቦብ ልጆች ተገኝተዋል፡፡
ይኸው ፌስቲቫል በፈጠረው መልካም አጋጣሚም ሀገራችንን በዓለም ዙሪያ ለማስተዋወቅ፤ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግና ኢንቨስመንት ለመሳብ በማለም ከ50 በላይ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን ጋብዘው የራሳቸውን የዜግነት ድርሻ ተወጥተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ በሙዚቃ ማኔጅመንት የሕይወት ጉዟቸው ያካበቱትን እውቀትና ልምድ ተጠቅመው ተሰጥዎ ያላቸውን ልጆች በመቃኘት ሀገራቸውን በሙዚቃው ኢንደስትሪ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ ትልቅ ህልም ነበራቸው፡፡ ለዚህም ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮን/ከመጀመሪያው አልበሙ ጀምሮ ማኔጅመንቱን በመያዝ ፤ እንዲሁም እጅጋየው ሽባባው /ጂጂን/ ከአጋራቸው ፓልም ሪከርዲንግ ጋር በመሆን ተወዳጅ የሆነ አልበሟን እንድተሰራ ያደረጉት አስተዋፅኦ የሚጠቀስ ነው፡፡
ይሄም ብቻ ሳይሆን ጃኖ ባንድን በመመስረት ለልጆቹ ውጤታማነት አቶ አዲስ ገሰሰ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ አቶ አዲስ “ጃናናይት” የተባለ ተሰጥዎ ያላቸውን ሴቶች የያዘ ባንድ መስርተው ስኬታማ ለማድረግ ያደረጉት ጥረትም የሚወሳ ነው፡፡
በሙዚቃ ኢንዱስትሪው- እጅግ ገዝፈው፤ በተለያየ የአድናቆት ቃል የሚጠሩት አቶ አዲስ ገሰሰ ከሀገራችን ውጪ እንደ ዚጊ ማርሌ፤ ስቴፈን ማርሌ፤ ሎረን ሂል፣ ፊል ኮሊንስ፣ ኧርዝ ዊንድ ኤንድ ፋየር እና ሌሎችንም በርካታ የሙዚቃ ከዋክብትን በማግኘትና በማስተዳደር በዓለም አቀፍ ደረጃ የብዙ ታላላቅ የሙዚቃ ሰዎች ስራን መስመር አሲዘዋል።
አቶ አዲስ ገሰሰ መደበኛ መኖሪያቸውን ወደ ኢትዮጵያ ካዞሩ በኋላ በሆቴሊንግ ዘርፍ በመሰማራት ላየንስ ዴን ሆቴልን፤ በማእድን ዘርፍም ዩኒቨርሳል ማይኒንግን፤ በግብርና መስክ አድሶጌት ኩባንያን በማቋቋም ለሀገራቸው እድገት ቀን ከሌት ያለእረፍት ሰርተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ በሙዚቃ ማኔጅመንትና በኢንቨስትመንት ስራቸው ብቻ ሳይሆን በበጎ አድራጎታቸውም አርአያነት ያለው ተግባር ፈፅመዋል፡፡ በግል ከደገፏቸው ግለሰቦች በተጨማሪ በሀገራችን በተለያዩ ወቅቶች በተፈጠሩ ሰብአዊ ችግሮች ቀድመው በመድረስ ያደረጉት አስተዋፅኦ የሚጠቀስ ነው፡፡
በዋናነትም ከወንድማቸው ዘለቀ ገሰሰ ጋር በመሆን በተለያዩ ገጠራማ አካባቢዎች 30 ትምህርት ቤቶችን አሰርተዋል፡፡
አቶ አዲስ ስለእነኚሁ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ስላሰሯቸው 30 ትምህርት ቤቶች ሲናገሩ “ተስፋ ሳልቆርጥ በፅናት የታገልኩበት በጎ ተግባር በመሆኑ ያስደስተኛል” ይሉ ነበር፡፡
ቤተ-ክርስቲያን በጠራቻቸው ጊዜ ሁሉ እየተገኙም በመላው ኢትዮጵያ አዳዲስ ቤተክርስቲያኖችን በማሰራት ፤ የተጎዱ ገዳማትንና ቤተክርስቲያኖችን በማደስ ፤ የተዘጉ ቤተክርስቲያኖችን በማስከፈት፤ የቤተክርስቲያኖችን ንዋየ ቅዱሳን በማሟላትና የካህናት ደሞዝን በመክፈል እስከ ህይወት ፍፃሜያቸው ድረስ ድምፃቸውን አጥፍተው አገልግለዋል፡፡
አቶ አዲሱ ገሰሰ በማህበራዊ ህይወታቸው ቀልድ አዋቂ፤ ተጫዋች እና በቀላሉ ከሰዎች ጋር ተግባብተው የመኖር ፀጋ የነበራቸው ሲሆን ከሁሉም ግን ሰው አካባሪ እና ስነ-ምግባር ያለው ቀረቤታቸው ተወዳጅና በሰው ልብ አይረሴ አድርጓቸዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ ከወ/ሮ ሶስና ሽፈራው ጋር በነበራቸው የፀና ትዳር አንድ ወንድና አንዲት ሴት ልጅ አፍርተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ፤ በአሜሪካ ሀገር ኒውጄርሲ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል፡፡
የቀብር ሥነ ስርዓቱ ዛሬ፣ ሰኔ 20 ቀን 2018ዓ.ም በ6:00 ሰዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።
አቶ አዲስ ገሰሰን ከአጠገቡ ሳትለዩ ላስታመማችሁትና ለጠየቃችሁት ወዳጅ ዘመዶች ልዑል እግዚአብሔር ብድራችሁን ይከፈላችሁ፡፡
የአቶ አዲስ ገሰሰን ነፍስ ልዑል እግዚአብሔር በአፀደ ገነት ከደጋጎቹ አብርሃም ይስሐቅ እና ያቆብ ጎን ያሳርፍልን፡፡
ለቤተሰቡ፤ ለወዳጆቹ፤ ለዘመዶቹ፤ ለሙያ አጋሮቹ፤ ለአድናቂዎቹ ሁሉ መፅናናቱን ይስጣቸው፡፡

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ዛሬ በቦስተን ስታዲየም የዓለማችን ምርጦቹ ሁለት አጥቂዎች ፊት ለፊት ሲገናኙ የእግር ኳስ አፍቃሪው አይን ሁሉ ወደዛው ያመራል። ፈረንሳይ ከኪሊያን ኤምባፔ ጋር፣ ኖርዌይን ከኤርሊንግ ሃላንድ ጋር ታፋልማለች! ሁለቱም ሀገራት በኮከብ አጥቂዎቻቸው አስደናቂ ብቃት ታግዘው የምድባቸውን የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎች በድል አጠናቀዋል። ኤምባፔ እና ሃላንድ በሁለቱ ጨዋታዎች እያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ግቦችን በማስቆጠር በአጠቃላይ 4 ግቦችን አስመዝግበው ውድድሩን አሙቀውታል። በአሁኑ ሰዓት ሊዮኔል ሜሲ በ5 ግቦች የኮከብ ግብ አግቢነቱን እየመራ ይገኛል።
ሁለቱም ሀገራት ወደ ጥሎ ማለፉ ማለፋቸውን ቢያረጋግጡም፣ የምድብ 9 (Group I) አንደኛ ሆኖ ለማጠናቀቅና በጥሎ ማለፉ የተሻለ ተጋጣሚ ለማግኘት ሲሉ ሁለቱም ኮከቦች በቋሚነት ይሰለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህን ልብ አንጠልጣይ ፍልሚያ ከመመልከታችን በፊት፣ ቢቢሲ ስፖርት ተጫዋቾቹ ለሀገራቸው ያላቸውን ፋይዳ እንደሚከተለው ዳስሶታል።
በክለቦቻቸው ያላቸው ወሳኝነት እንዳለ ሆኖ፣ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ የሁለቱ ተጫዋቾች ተጽእኖ እጅግ የገዘፈ ነው። ከነሐሴ 2022 ጀምሮ ፈረንሳይ ኤምባፔን አሰልፋ 69.8% ጨዋታዎቿን ስታሸንፍ፣ እርሱ በሌለበት ግን የማሸነፍ መጠኗ ወደ 50% ይወርዳል። የምንጊዜም የፈረንሳይ ከፍተኛ ግብ አግቢው ኤምባፔ በሜዳ ላይ ሲኖር ፈረንሳይ በጨዋታ በአማካይ 2.3 ግቦችን ስታስቆጥር፣ በሌለበት ደግሞ 1.9 ግቦችን ታስቆጥራለች። በሌላ በኩል ኖርዌይ ያላት የተጫዋቾች ስብስብ ጥልቀት አነስተኛ በመሆኑ፣ ሃላንድ ለሀገሩ ያለው ወሳኝነት ከማንም በላይ ነው። ከነሐሴ 2022 ጀምሮ ኖርዌይ ሃላንድን አሰልፋ 64.5% ጨዋታዎቿን ስታሸንፍ፣ እርሱ በሌለበት ግን የማሸነፍ መጠኗ በከፍተኛ ሁኔታ ወደ 33.3% ይንኮታኮታል።
ይህ የዓለም ዋንጫ ሁለቱም ተጫዋቾች በትልልቅ መድረኮች ጫና እንደማይበገሩ በሚገባ አሳይቷል። ትኩረቱ ሁሉ በሜሲ ላይ ቢሆንም፣ ኤምባፔ የዓለም ዋንጫ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አግቢነት ሪከርድን ለመስበር የጊዜ ጉዳይ ብቻ የሆነለት ይመስላል። በ16 የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች 16 ግቦችን ያስቆጠረው ፈረንሳዊው ኮከብ፣ ከ39 ዓመቱ ሜሲ የሚያንሰው በሁለት ግቦች ብቻ ነው። ኤምባፔ ከሜሲ በ12 ዓመት ማነሱ ደግሞ ሪከርዱን በእጁ ለማስገባት ሰፊ እድል ይሰጠዋል።
በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ተሳትፎውን እያደረገ ያለው ሃላንድ በበኩሉ፣ ውድድሩን እንደለመደው እያመሰቃቀለው ይገኛል። በመጀመሪያዎቹ ሁለት የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ከአንድ በላይ ግቦችን ያስቆጠረ በታሪክ 6ኛው ተጫዋች ሲሆን፣ ባለፉት 50 ዓመታት ደግሞ ከእንግሊዙ ሃሪ ኬን (2018) ቀጥሎ ሁለተኛው ተጫዋች ሆኗል። የሃላንድ የቅርብ ጊዜ የብሔራዊ ቡድን አቋምም እጅግ አስደንጋጭ ነው። በተከታታይ 12 የብሔራዊ ቡድን የውድድር ጨዋታዎች ላይ ግብ ያስቆጠረ ሲሆን፣ ባለፉት 6 ጨዋታዎች ብቻ 16 ግቦችን መረብ ላይ አሳርፏል። አጠቃላይ የብሔራዊ ቡድን ግቦችን ስንመለከት በ100 የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች 60 ግቦችን ካስቆጠረው ኤምባፔ ጋር ሲነጻጸር፣ ሃላንድ በ52 ጨዋታዎች ብቻ 59 ግቦችን በማስቆጠር (ከኤምባፔ በ48 ጨዋታዎች አንሶ) አንድ ግብ ብቻ ዝቅ ብሎ ይገኛል።
የሁለቱን ኮከቦች አጠቃላይ እንቅስቃሴ ስናነጻጽር በዚህ የውድድር ዘመን በክለብ ደረጃ ኤምባፔ ኳስ በመንካት፣ እድል በመፍጠር እና ሙከራ በማድረግ ከሃላንድ ይበልጣል። ምንም እንኳን ሃላንድ በማንችስተር ሲቲ የተሻለ አሲስት ቢኖረውም፣ በዚህ የዓለም ዋንጫ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ኤምባፔ 14 ስኬታማ ኳስ የማታለል እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ፣ ሃላንድ ያደረገው አንድ ብቻ ነው። ነገር ግን ኳስን ወደ ግብ በመቀየር ሃላንድ ትልቅ የበላይነት አለው። ባለፉት አራት የክለብ የውድድር ዘመናት 23.43% ሙከራዎቹን ወደ ግብ ሲቀይር፣ ኤምባፔ ግን 18.24% አሳክቷል። የመከላከል አስተዋጽኦን በተመለከተ ኤምባፔ ወደ ኋላ ተመልሶ በመከላከል ረገድ ከሃላንድ እጅግ ያንሳል። ለሪያል ማድሪድ በዚህ ዓመት ሲጫወት ከ900 ደቂቃ በላይ ከተጫወቱ 1,483 የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ተጫዋቾች ውስጥ በመከላከል አስተዋጽኦ 1,481ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የሁለቱ ኮከቦች ለሀገራቸው ያላቸው ፋይዳ በቅርብ ጊዜ የግብ ተሳትፎአቸው በግልጽ ይታያል። ከነሐሴ 2022 ጀምሮ ኤምባፔ በ44% የፈረንሳይ ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ በማድረግ 33 ግቦችን እና 17 አሲስቶችን ሲያበረክት፣ ሃላንድ ደግሞ በ43.9% የኖርዌይ ግቦች ላይ ተሳትፎ በማድረግ 39 ግቦችን እና 4 አሲስቶችን አድርጓል።
ፈረንሳይ ዋንጫውን ለማንሳት ከፍተኛ ግምት ከተሰጣቸው ሀገራት ቀዳሚዋ ናት፤ ሃላንድ ራሱ ሳይቀር ፈረንሳይ ዐርቡን ጨዋታ አሸንፋ ዋንጫውን ልትወስድ እንደምትችል በቅርቡ ተናግሯል። ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት በዓለማችን እጅግ አደገኛው የግብ ክልል አጥቂ የሆነውን ሃላንድን የያዘችው ኖርዌይ፣ በፈረንሳይ ላይ ያልታሰበ አደጋ ልትፈጥር እንደምትችል መገመት አያዳግትም። ሃላንድን ይዞ የኖርዌይን ጉዞ ይሄን ያህል ነው ብሎ መገደብ ሞኝነት ነው!

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ሊዮኔል ሜሲ ትላንት እጅግ ትልቅ ታሪክ ሰርቷል፡፡ የአርጀንቲናው አምበል በአለም ዋንጫ ላይ 18 ጎሎችን በማስቆጠር አዲስ ሪከርድ አስመዝግቧል፡፡ በዳላስ ስታዲየም ተገኝተው ይህን ታሪክ በአይናቸው ከተመለከቱት ውስጥ ድምፃዊት ሻኪራ አንዷ ናት፡፡ ሜሲ ሁለቱንም ጎሎች ሲያስቆጥር በከፍተኛ ደስታ ውስጥ ሆና ስሜቷን ስትገልፅ ታይታለች፡፡
ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላም በኢንስታግራም ገፃ ላይ ‹‹እጅግ ኮርቼብሀለሁ ሊዮ፡፡ ለአገርህ፣ ለቤተሰብህና ለመላው የላቲን ማህበረሰብ የምታደርገው ሁሉ የሚያኮራ ነው፡፡ ቁርጠኝነትህና ብርታትህ ብዙዎችን ያነሳሳም፡፡ በዚሁ ቀጥልበት›› በማለት ፅፋለች፡፡ ሻኪራ በአለም ዋንጫው የተለያዩ ጨዋታዎችን እየተመለከተች ሲሆን ትላንትም በዳላስ ስታዲየም ክብር ትሪቢዩን ታድማለች፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ ከፊፋ ጋር ያላትን 20 አመታት የዘለቀ ቁርኝት ተከትሎ ነው፡፡
በ2010 የአለም ዋንጫ ‹‹ዋካ ዋካ›› የተሰኘውን ሙዚቃ ከሰራች ጀምሮ ከፊፋ ጋር ግንኙነት የመሰረተችው ሻኪራ በ2014ቱ አለም ዋንጫም ‹‹ላ ላ ላ›› በሚለው ሙዚቃ ውስጥ ተሳትፎ አድርጋ ነበር፡፡ በዘንድሮው ውድድር ደግሞ ከበርና ቦይ ጋር በመሆን ‹‹ዳይ ዳይ›› የተሰኘውን የፊፋ ይፋዊ ሙዚቃ መስራቷ ይታወቃል፡፡ በዘንድሮው የአለም ዋንጫ መዝጊያ እረፍት ሰአት ላይ በሚከናወነው የፊፋ ‹‹ሀፍ ታይም ሾው›› ላይ ስራዋን እንደምታቀርብም ይጠበቃል፡፡

(ዘ-ሐበሻ ዜና)፡በምድብ 11 ኮሎምቢያ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን (ዲ.አር. ኮንጎ) ባገናኘው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ምንም ግብ 0 ለ 0 በሆነ የአቻ ውጤት ተጠናቋል። ኮሎምቢያ በጨዋታው ላይ ሙሉ ብልጫ መውሰድ ብትችልም፣ የኮንጎው ግብ ጠባቂ ሊዮኔል ምፓሲ ባደረጋቸው ድንቅ ማዳኖች እና በኮሎምቢያ አጥቂዎች የውሳኔ አሰጣጥ ችግር ምክንያት ግብ ማስቆጠር አልቻለችም።
ጨዋታው እንደተጀመረ ኮሎምቢያዎች የኮንጎን የተከላካይ መስመር ለማፈራረስ ብዙም ጊዜ አልፈጀባቸውም። ገና በ4ኛው ደቂቃ ላይ ጆን አሪያስ ከቅርብ ርቀት የሞከረውን ኳስ ግብ ጠባቂው ምፓሲ ሲመልስበት፣ ያገረሸውን ኳስ ዳንኤል ሙኖዝ አግኝቶ ቢመታውም ኳሷ መረቡን ታካ ወጥታለች። በ7ኛው ደቂቃ ላይ ደግሞ ያው ክሪስታል ፓላስን የሚጫወተው ዳንኤል ሙኖዝ ኳስ ከመረብ ማሳረፍ ቢችልም፣ ከጨዋታ ውጪ በመሆኑ ግቡ በVAR ተሽሯል።
በመጀመሪያዎቹ 20 ደቂቃዎች ውስጥ ብቻ ኮሎምቢያ አምስት ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎችን ማድረግ የቻለች ሲሆን፣ ይህ በዚህ የዓለም ዋንጫ በየትኛውም ቡድን ያልታየ ሪከርድ ሆኖ ተመዝግቧል።
የዲ.አር. ኮንጎ ግብ ጠባቂ ሊዮኔል ምፓሲ ለቡድኑ የጀርባ አጥንት ሆኖ አሳልፏል። የባየር ሙኒኩ የክንፍ ተጫዋች ሉዊስ ዲያዝ እና የኮሎምቢያው ኮከብ ጄምስ ሮድሪጌዝ ያደረጓቸውን እጅግ አደገኛ ሙከራዎች በሚገርም ብቃት አድኗቸዋል። በተለይም ሉዊስ ዲያዝ በተደጋጋሚ በግራ መስመር ሰብሮ በመግባት ለኮንጎ ተከላካዮች ትልቅ የራስ ምታት ሆኖባቸዋል።
ምንም እንኳን የኮሎምቢያውያን ደጋፊዎች ስታዲየሙን በመሙላት ጨዋታውን የኮሎምቢያ የሜዳ ላይ ጨዋታ እስኪመስል ድረስ ቢያደምቁትም፣ የቡድኑ አጥቂዎች ግን ያገኟቸውን በርካታ እድሎች ወደ ግብ መቀየር አለመቻላቸው የብስጭት ስሜት ፈጥሮባቸዋል።
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሚጫወቱትን እንደ አሮን ዋን-ቢሳካ፣ ዮአን ዊሳ እና አርተር ማሱዋኩን የመሳሰሉ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾችን የያዘችው ዲ.አር. ኮንጎ፣ አብዛኛውን ጊዜዋን በመከላከል ብታሳልፍም በመልሶ ማጥቃት ስትሞክር ታይታለች። በተለይም ከውሃ መጠጫ እረፍት በኋላ መጠነኛ መነቃቃት በማሳየት ወደ ኮሎምቢያ የግብ ክልል ለመጠጋት ጥረት አድርገዋል። በ44ኛው ደቂቃ ላይ አርተር ማሱዋኩ ያሻማው አደገኛ ኳስ በትንሹ ዮአን ዊሳን አልፎ መውጣቱ ኮንጎዎችም አደገኛ መሆናቸውን ያሳየ አጋጣሚ ነበር።
የቀድሞው ተጫዋች ጋብርኤል ዛኩዋኒ በሰጠው ትንታኔ "0 ለ 0 መሆኑ ለዲ.አር. ኮንጎ ትልቅ እፎይታ ነው። በመጀመሪያው አጋማሽ ኮሎምቢያን ለማስቆም የሚያስችል እቅድ ማውጣት አለባቸው። አሮን ዋን-ቢሳካ ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው" ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።
የመጀመሪያው አጋማሽ ሲጠናቀቅ ኮሎምቢያውያን ያገኙትን የበላይነት ወደ ግብ መቀየር ካልቻሉ፣ ኮንጎዎች ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመው በሁለተኛው አጋማሽ ድንገተኛ ጥቃት ሊሰነዝሩ እንደሚችሉ የጨዋታው ሂደት ያሳያል።

2 months ago
''በሰፈሩት ቁና መሠፈር''
ደቡብ አፍሪካውያን ከአየርላንድ ተባረሩ
#ethiopia | አየርላንድ በሀገሯ ውስጥ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲኖሩ የነበሩ 42 የደቡብ አፍሪካ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ያባረረች ሲሆን ለዚህም የመንቀሳቀሻ መነሻ ወጪ 735,000 ዩሮ 853,000 ዶላር ማውጣቷን አስታውቃለች።
ይህ የስደት እርምጃ የተወሰደው ግለሰቦቹ በፈቃደኝነት ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የተሰጣቸውን ዕድል ሳይጠቀሙ በመቅረታቸው በተላለፈ የማባረር ትዕዛዝ ሲሆን ከተባረሩት መካከል ሁለቱ የወንጀል ሪከርድ ያለባቸው መሆኑ ታውቋል።
ይህ ከአየርላንድ የተሰማው ዜና በአሁኑ ወቅት በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ስለ ስደት ስለ መጤ ወንድምን ማሳደደ እና ሰነድ የሌላቸው የውጭ ዜጎች ማዋከብ ላይ የሚደረገውን የጦፈ ክርክር እና ውጥረት ዳግም ቀስቅሶታል።
የዚህ የስደት እርምጃ መጨመር እንደሚያሳየው፣ የስደት ጉዳይ ለደቡብ አፍሪካ “ባለ ሁለት ገፅታ” ፈተና እየሆነባት መጥቷል። በአንድ በኩል በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎቿ በሕገ-ወጥ ስደት ምክንያት እየተባረሩ የሚመለሱባት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በሀገሯ ውስጥ ከሚኖሩ የውጭ ዜጎች ጋር በተያያዘ ከሕዝብ የሚነሳባትን ጠንካራ ተቃውሞ እና የስደተኞች ጥላቻ ስጋትን ለማስተናገድ እየተገደደች ትገኛለች።

Comments