(ዘ-ሐበሻ ዜና) ኬንያ በርካታ ችግኞችን በመትከል የአለምን ሪከርድ መስበሯን ገለጸች፡፡ የአለም ስነምህዳር ጥበቃ ቀንን ምክንያት በማድረግ በትላንትናው እለት በኬንያ ሞምባሳ ችግኝ የመትከል ዘመቻ ተከናውኗል፡፡ የኬንያ ስካውት ማህበር ከዛብሎን ኦኮቲና ከኤምፒሳ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ባከናወኑት በዚህ ዘመቻ የአለምን ሪከርድ ሰብረዋል፡፡ ሪከርዱ ከመሰበሩ በፊት የጊነስ የአለም ድንቃድንቅ መዝገብ አባላት በስፍራው ተገኝተው ሁኔታውን ተከታትለዋል፡፡
የጊነስ ባለሙያዎች ሪከርዱን ለመስበር በስፍራው ቢያንስ ሶስት ሺህ ሰዎች ችግኙን መትከል እንዳለባቸው የሚገልፅ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠው ነበር፡፡ ይሁንና በቦታው ላይ ከ5 ሺህ በላይ ወጣቶች ተገኝተው ችግኙን ተክለዋል፡፡ የጊነስ ባለሙያዎች ችግኞቹ ከተተከሉ በኋላ ባደረጉት ማጣራት በትክክል ችግኙን የተከሉት 4,124 ሰዎች መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ በመሆኑም በአለም ላይ በ30 ሰከንድ ውስጥ በርካታ ሰዎች የተሳተፉበት የችግኝ ተከላ በሚል አዲስ ሪከርድ መሰበሩን መዝገበው መሄዳቸውን ኬንያ ኤፍኤም ዘግቧል፡፡

9 days ago