የአህመድ ተሾመ(ዲንቢ) ‘ጊዜ አይሄድም’ የሙዚቃ አልበም ሐምሌ 10 ሊለቀቅ ነው
#ethiopia | ታዋቂው ድምፃዊና ዜማ ደራሲ አህመድ ተሾመ (ዲንቢ) ‘ጊዜ አይሄድም’ የተሰኘውን አዲስ የሙዚቃ አልበሙን መጪው ሐምሌ 10 ቀን በናሆም ሪከርድስ የዩቲዩብ ቻናል እና በተለያዩ የዲጂታል አማራጮች በኩል ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ታውቋል።
በአጠቃላይ 13 ትራኮችን የያዘው ይህ አልበም የወቅቱን ትውልድ ስሜትና የዘመኑን ምልከታ በጥሩ ሁኔታ የሚያንጸባርቅ ከመሆኑም በላይ አገራዊ ፍቅርን፣ ማኅበራዊ ሕይወትን፣ ተስፋንና እምነትን በጥልቀት የሚዳስስ ሰፊ ይዘት አለው።
በአልበሙ ዝግጅት ላይ የተሳተፉት ባለሙያዎች እንደገለጹት ይህ ሥራ ከተለመደው የሙዚቃ አቀራረብ ወጣ ባለ መልኩ በጥልቅ ሐሳቦችና በከፍተኛ ጥንቃቄ የተሰናዳ የጥበብ ውጤት ነው።
በተለይም በአልበሙ ላይ በሁለት ሥራዎች የተሳተፈው ከድር፣ ‘እሳሳታለሁ’ የተሰኘ የፍቅር ዘፈን እና ‘ከፍ በይ’ የተባለ አገራዊ ይዘት ያለው የሙዚቃ ሥራ ማበርከቱን ጠቅሶ፣ አልበሙ እያንዳንዱን የሰው ልጅ የሕይወት ውጣ ውረድ የሚዳስስ በመሆኑ የሙዚቃ አፍቃሪያንን ልብ እንደሚገዛ ሙሉ እምነት እንዳለው ገልጿል።
📸 ከበደ መክብብ
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

3 months ago