(ዘ-ሐበሻ ዜና) ቀይ ባህር እግር ኳስ ክለብ የኤርትራን ፕሪሚየር ሊግ ለማንሳት ተቃረበ፡፡ በዘንድሮው የኤርትራ ፕሪምየር ሊግ ቀይ ባህር እግር ኳስ ክለብ ሻምፒዮን የመሆን እድሉን አስፍቷል፡፡ ባለፉት ሁለት የውድድር አመታት በጦር ሀይሉ ስር በሚተዳደረው ደንደን ክለብ ሻምፒዮን በመሆን ቀይ ባህር በአገሪቱ ውስጥ የነበረውን የኳስ የበላይነት ለመንጠቅ መቻሉ ይታወሳል፡፡
ይሁንና ዘንድሮ ቀይ ባህር ይህንን የበላይነት በመመለስ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ተቃርቧል፡፡ ቀይ ባህር ይህንን ዋንጫ የሚያነሳ ከሆነ ለ15ተኛ ጊዜ የኤርትራ ሻምፒዮን በመሆን አዲስ ሪከርድ ያስመዘግባል፡፡ ደንደን ክለብ ዘንድሮ ጥሩ ተፎካካሪ በመሆን ሲጫወት የቆየ ቢሆንም ከአስመራ ቢራ ጋር ባደረገው ግጥሚያ አንድ ለዜሮ መሸነፉ የሻምፒዮንነት እድሉን አጥቦታል፡፡ ፕሪምየር ሊጉን ቀይባህር ክለብ በ33 ነጥብ የሚመራ ሲሆን ደንደን በ30 ነጥብ ይከተላል፡፡
ሁለቱ ክለቦች የፊታችን እሁድ በአስመራ ስታዲየም የውድድር ዘመኑን የመጨረሸ ግጥሚያ ያደርጋሉ፡፡ በጨዋታው ደንደን ቢያሸንፍ እንኳ ቀይ ባህር በግብ ክፍያ የበላይነቱን በመያዙ ዋንጫውን እንደሚወስደው ብዙዎች ገምተዋል፡፡ አፍሪካን ፉትቦል እንደዘገበው በእሁዱ ግጥሚያ ደንደን በ12 የግብ ልዩነት ያሸንፋል ብሎ መጠበቅ የማይታሰብ ነው፡፡

28 days ago