25 days ago
በመሳሳም ሪከርድ የሰበሩት ጥንዶች
የአለማችን ምርጥ ጥንድ አስብሏቸዋል
#ethiopia | ብራዚላዊያን የሆኑት እነዚህ ጥንዶች በ30 ሰከንድ ውስጥ 195 ጊዜ በመሳሳም አዲስ ሪከርድ አስመዝግበዋል።
ሬናቶ ባይማ ጋያ እና ናያራ ሮቤርታ ሪቤሮ ደ ማሪንስ የተባሉት እነዚህ ጥንዶች ይህንን ሪከርድ የግላቸው ያደረጉት በአለም አቀፍ የመሳሳም ቀን (International Kissing Day) ነው።
ጥንዶቹ ለጊነስ ወርልድ ሪከርድ እንደገለጹት ይህንን ውድድር ያደረጉት በአለም ላይ ምርጥ ጥንዶች ነን ብለው ስለሚያምኑ እና አብረው አንድ የማይረሳ ነገር ለመስራት በማሰብ እንደሆነ ተናግረዋል።
ሁለቱም ሙያቸው የሕክምና ባለሙያ ሲሆኑ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በግንባር ቀደምትነት ህዝባቸውን ያገለገሉ መሆናቸው ገልጸዋል።
ሬናቶ ባይማ ቀደም ሲልም በተለያዩ የሪከርድ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ የሚታወቅ ሲሆን የዚህኛው የሪከርድ ስኬት ግን ለናያራ የመጀመሪያዋ መሆኑን ተናግረዋል።
ጥንዶቹ በቀጣይ በአንድ ደቂቃ ውስጥ ብዙ ጊዜ በመሳሳም ያለውን ሌላ ሪከርድ ለመስበር እቅድ እንዳላቸውም ተናግረዋል ያለው ዩፒአይ ነው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #brazilbestcoupleintheworld #worldkissingday #worldguinnessrecord #upioddenews

Comments