Logo
FastMereja
አህመድ ተሾመ (ዲንቢ) «ጊዜ አይሄድም» የተሰኘውን 3ኛ አልበሙን ሊለቅ ነው!
#fastmereja :-ታዋቂው ድምፃዊና የዜማ ደራሲ አህመድ ተሾመ (ዲንቢ) «ጊዜ አይሄድም» የተሰኘውን 3ኛ ሙሉ የሙዚቃ አልበሙን የፊታችን ሐምሌ 10 ቀን ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ በዛሬዉ እለት በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።

በናሆም ሪከርድስ (Nahom Records) አማካኝነት በተለያዩ የሙዚቃ ማሰራጫዎችና በዩቲዩብ የሚለቀቀው ይህ አልበም፣ በአጠቃላይ 13 ትራኮችን የያዘ ሲሆን የሀገር ፍቅርን፣ ማህበራዊ ህይወትንና ፍቅርን የሚዳስሱ ይዘቶች እንዳሉት ተገልጿል። አልበሙ «ጊዜ አይገድም» እና «ይረፍዳል» የሚሉ ተቃራኒ እውነታዎችን ያጣመረ ልዩ ፍልስፍናዊ ጭብጥም እንዳለዉ ነዉ የተገለፀዉ።

ይህም ተስፋ ላለው ሰው ጊዜ እንደማይሄድና ሁሌም ብርሃን እንዳለ የሚያሳይ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ጊዜ የማይጠብቅ መሆኑንና «ይረፍዳል» የሚለውን ተቃራኒ የህይወት እውነታ በአንድ ላይ አጣምሮ የያዘ ልዩ ፍልስፍናዊ ስራ ስለመሆኑም ነዉ የተገለፀዉ።

በአልበሙ ዝግጅት ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረገው ድምፃዊና የግጥም ደራሲ ካድር አሊ «እሳሳታለሁ» እና «ከፍ በል» የተሰኙ ሁለት ስራዎችን በግጥምና በድምፅ ያበረከተ ሲሆን፣ ስራው ዘመን ተሻጋሪና በጥራት የተሰራ መሆኑን ገልጿል።

አህመድ ተሾመ (ዲንቢ) ከዚህ ቀደም «እዮሪካ» እና «ኦሜርታ» የተሰኙ እጅግ ተወዳጅና ስኬታማ አልበሞችን ለአድማጮች ያበረከተ ሲሆን፤ «ዲንቢ ለዲንቢ»፣ «ተጠየቂ ናዝሬት»፣ «አውራአምባ»፣ «በትዝታው ፈረስ» እና «አይ መሬት ያለ ሰው» የተሰኙ በርካታ የራሱ ተወዳጅ ሙዚቃዎች አሉት።

ከዚህ ቀደም «እዮሪካ» እና «ኦሜርታ» የተሰኙ ተወዳጅ አልበሞችን ለአድማጮች ያበረከተው አህመድ ተሾመ (ዲንቢ)፤ ለማዲንጎ አፈወርቅ፣ ለፀሀዬ ዮሀንስ፣ ለብዙአየሁ ደምሴ እና ለዘቢባ ግርማ በርካታ ተወዳጅ ዜማዎችን በመስራት የሚታወቅ ስኬታማ ባለሙያ ነው።

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.