"ጊዜ አይሄድም" እየመጣ ነው!
ሰላም የምወዳችሁና የማከብራችሁ የጥበብ ቤተሰቦቼና ውድ አድናቂዎቼ!
#ethiopia | ሐምሌ 10 በናሆም ሪከርድስ የማይረሳ ቀጠሮ አለን። በአዲሱ "ጊዜ አይሄድም" ቅጽ 3 አልበሜ ውስጥ ዘፈኖችን ብቻ ሳይሆን የሕይወቴን ተሞክሮ፣ ስሜትና ታሪክ በሙዚቃ ቋንቋ አቅርቤላችኋለሁ።
ይህ ሥራ ወደ እናንተ እንዲደርስ ከመጀመሪያው ጀምሮ ከጎኔ በመቆም ላልተቆጠበ ድጋፍ የናሆም ሪከርድስ ባለቤት አቶ ኤሊያስ ፍቅሩን ከልብ አመሰግናለሁ።
እንዲሁም ድምፃዊና ፕሮዲውሰር ደመላሽ ንጉሴ በዚህ አልበም ላይ በፕሮዲውሰርነት ላደረግኸው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
በግጥም ችሎታችሁ ለአልበሙ ልዩ ውበት ያከላችሁ፤ እልፍአግድ እምሻው፣ ናትናኤል ግርማቸው፣ ከድር አሊ፣ ምልዕቲ ኪሮስ፣ አቡዲ እና ወንድወሰን ይሁብ ሁላችሁንም ብዕራችሁ አይነጥፍ፤ ከልብ አመሰግናለሁ።
በሙዚቃ ቅንብር ደግሞ ለዘፈኖቼ ነፍስ የዘራችሁ፤ ታምሩ አማረ፣ ሚካኤል ሀይሉ (ሚኪ ጃኖ)፣ አንተነህ ተፈራ (አቡዝ)፣ አዲስ ፍቃዱ፣ ፋኑ ጊዳቦ እና ኤርሚያስ በዳዳ ሁላችሁንም በጣም አመሰግናለሁ።
እንዲሁም ሁሉንም ሙዚቃዎቼ በማስተር ሥራ የአለባበሰው ሰለሞን ሀ/ማርያም ላደረግኸው ድንቅ ሙያዊ አስተዋፅኦ ልዩ ምስጋናዬ ይድረስህ።
በአጠቃላይ በዚህ አልበም ጉዞ ላይ በሙያችሁ፣ በሀሳባችሁ እና በማበረታቻችሁ ከጎኔ ለቆማችሁ ወዳጆቼና ባለሙያዎች በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ።
ሐምሌ 10 በናሆም ሪከርድስ እንገናኝ! ከእናንተ ጋር ይህን ልዩ የሙዚቃ ጉዞ ለመጋራት በታላቅ ጉጉት እጠብቃለሁ።
ከፍቅር ጋር፣
አህመድ ተሾመ ( ዲንቢ )

30 days ago