2 months ago
ሁለቱን የዓለም ጦርነቶችን ያዩት የምድራችን ዕድሜ ጠገቧ ኤተል ምን አሉ?
#ethiopia | በ117 ዓመታቸው የዓለማችን እድሜ ጠገብ የተባሉት እንግሊዛዊቷ ኤተል ካተርሃም የልደት በዓላቸውን አከበሩ።
በጊነስ የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ በህይወት ካሉ የዓለማችን እድሜ ጠገብ ሰው በመሆን እውቅና የተሰጣቸው እንግሊዛዊቷ ኤተል ካተርሃም 117ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል።
ኤተል የልደት በዓላቸውን ምክንያት በማድረግ ለኤቢሲ ኒውስ በላኩት የምስጋና መልዕክት "ለተመኛችሁልኝ በጎ የልደት ምኞት ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ ብለዋል።
በ117 ዓመቴ በምድር ላይ ሁሉንም አይቻለሁ ሲሉም ተናግረዋል።
አክለው "ከህጻናት እጅ መዳሰስ እስከ ንጉስ እጅ መያዝ ድረስ በህይወቴ በርካታ ታሪካዊና አስደናቂ ነገሮችን አድርጌያለሁ" ሲሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1909 የተወለዱት ኤተል ካተርሃም በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያላቸውን ሁለቱን የዓለም ጦርነቶች በርካታ የቴክኖሎጂና የፖለቲካ ውጣ ውረዶችን እንዲሁም በርካታ ታሪካዊ ሁነቶችን በህይወት አሳልፈዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #england #catrinham #abcnews #birthday #worldguinnessrecord

3 months ago
በመሳሳም ሪከርድ የሰበሩት ጥንዶች
የአለማችን ምርጥ ጥንድ አስብሏቸዋል
#ethiopia | ብራዚላዊያን የሆኑት እነዚህ ጥንዶች በ30 ሰከንድ ውስጥ 195 ጊዜ በመሳሳም አዲስ ሪከርድ አስመዝግበዋል።
ሬናቶ ባይማ ጋያ እና ናያራ ሮቤርታ ሪቤሮ ደ ማሪንስ የተባሉት እነዚህ ጥንዶች ይህንን ሪከርድ የግላቸው ያደረጉት በአለም አቀፍ የመሳሳም ቀን (International Kissing Day) ነው።
ጥንዶቹ ለጊነስ ወርልድ ሪከርድ እንደገለጹት ይህንን ውድድር ያደረጉት በአለም ላይ ምርጥ ጥንዶች ነን ብለው ስለሚያምኑ እና አብረው አንድ የማይረሳ ነገር ለመስራት በማሰብ እንደሆነ ተናግረዋል።
ሁለቱም ሙያቸው የሕክምና ባለሙያ ሲሆኑ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በግንባር ቀደምትነት ህዝባቸውን ያገለገሉ መሆናቸው ገልጸዋል።
ሬናቶ ባይማ ቀደም ሲልም በተለያዩ የሪከርድ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ የሚታወቅ ሲሆን የዚህኛው የሪከርድ ስኬት ግን ለናያራ የመጀመሪያዋ መሆኑን ተናግረዋል።
ጥንዶቹ በቀጣይ በአንድ ደቂቃ ውስጥ ብዙ ጊዜ በመሳሳም ያለውን ሌላ ሪከርድ ለመስበር እቅድ እንዳላቸውም ተናግረዋል ያለው ዩፒአይ ነው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #brazilbestcoupleintheworld #worldkissingday #worldguinnessrecord #upioddenews

Comments