28 days ago
"የብራዚል እግር ኳስ ስብራት ገጥሞታል!"
የፔሌ ልጅ
#ethiopia | የብራዚል እግር ኳስ አስተዳደር በብልሹ አሰራር በመውደቁ እግርኳሱ ስብራት ገጥሞታል ስትል የፔሌ ልጅ ተናግራለች።
የአስተዳደሩ ግልጽነት እና ተጠያቂነት የጎደለው አሰራር በብሔራዊ ቡድኑ አፈጻጸም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል ብላለች።
የእግርኳሱ ኮኮብ የፔሌ ታላቅ ሴት ልጅ አክቲቪስት እና የፊልም ባለሙያ የሆነችው ኬሊ ናሲሜንቶ ፔሌ ለሮይተርስ በሰጠችው ቃለ መጠይቅ ብሔራዊ ቡድኑ የገጠመውን ችግር ተናግራለች።
የብራዚል እግር ኳስ ተበላሽቷል
ሙስናና ሌላም ችግር በአስተዳደሩ ይነጸባረቃል ይህ በጣም ግልጽ ነው ብላለች።
ሁሉም ሰው አስተዳደሩ ለምን እንደማይሰራ ያውቃል ነገር ግን አንድም አካል ሊያስተካክለው አልቻለም ስትል ናሲሜንቶ ገልጻለች።
የብራዚል እግር ኳስ አሁንም ተሰጥኦ ያላቸው ምርጥ ተጫዋቾችን ማፍራቱን ቢቀጥልም በዓለም አቀፍ መድረክ የሚያሳዩት ደካማ አፈጻጸም ግን ሥር የሰደዱ መዋቅራዊ ችግሮች ውጤት መሆኑን ገልጻለች።
ብራዚል እሁድ ዕለት በኖርዌይ 2 ለ 1 ከተሸነፈች በኋላ ከውድድሩ ውጪ መሆኗ ይታወሳል።
ይህ ውጤት ብራዚል ከ1990 ወዲህ ለሩብ ፍጻሜ ማለፍ ሳትችል ስትቀር የመጀመሪያዋ ነው።
ሀገሪቱ ሪከርድ የሆነውን አምስተኛ የዓለም ዋንጫዋን ያሸነፈችው እ.ኤ.አ በ2002 ነበር።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #brazilfootball #reuters #greatpeledaughter #kelynascimento #activistfilmmaker

Comments