7 hours ago
በፃድቃኔ ማርያም ቤተክርስቲያን ፀበል በተከሰተ ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወቷ ያለፈው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ
#ethiopia | በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የህግ ትምህርት ተማሪ የሆነችው ተማሪ ሀብታሟ በቀለ ለእረፍት ወደ ቤተሰብ ከመሄዷ ቀድማ በፃድቃኔ ማርያም ቤተክርስቲያን ፀበል በመከታተል ላይ ሳለች በአካባቢው በተከሰተ ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ/ም ከዚህ አለም ድካም አርፋለች።
ተማሪ ሀብታሟ በትምህርቷ ካስመዘገበችው ከፍተኛ ውጤት ባሻገር፣ በመልካም ስነ ምግባሯ፣ በታታሪ ተማሪነቷ፣ በክፍል ውስጥ ተሳትፎዋና ተግባቢ ስብዕናዎቿ የምትታወቅ፤ በተለይ በምስለ ችሎት ውድድሮች በምታሳየው የላቀ ችሎታ እና ውጤት እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው ለአካባቢው ማህበረሰብ በሚሰጠው የነፃ ህግ አገልግሎት ድጋፎች ዙሪያ በነበራት ተሳትፎ የምትታወቅ ተማሪያችን ነበረች፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት በተማሪ ሀብታሟ በቀለ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለፀ ለተማሪዋ ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ፣ እንዲሁም ለመላው የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ መፅናናትን ይመኛል፡፡
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ

8 hours ago
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪ በድንገተኛ አደጋ ህይወቷ አለፈ
#fastmereja I በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የህግ ትምህርት ተማሪ የሆነችው ሀብታሟ በቀለ ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቿ ከመሄዷ አስቀድሞ በፃድቃኔ ማርያም ቤተክርስቲያን ፀበል በመከታተል ላይ እያለች በተከሰተ ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወቷ ማለፉ ተገለጠ። አደጋው የተከሰተው ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ሲሆን፣ ተማሪዋ በአካባቢው በነበረችበት ወቅት ባጋጠመው የመሬት መንሸራተት ህይወቷን ልታጣ ችላለች።
ተማሪ ሀብታሟ በቀለ በትምህርት ገበታዋ ካስመዘገበችው የላቀ ውጤት ባሻገር በመልካም ስነ-ምግባሯ፣ በታታሪነቷ እና በተግባቢነቷ በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት የነበራት ተማሪ ነበረች። በተለይም በምስለ ችሎት ውድድሮች በምታሳየው የላቀ የህግ ችሎታ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው ለአካባቢው ማህበረሰብ በሚሰጠው የነፃ ህግ እርዳታ አገልግሎት ላይ በንቃት በመሳተፍ የጎላ አስተዋጽኦ ስታበረክት እንደነበር ተገልጻለች።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት በተማሪ ሀብታሟ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጾ፣ ለቤተሰቦቿ፣ ለወዳጅ ዘመዶቿ እና ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መፅናናትን ተመኝቷል።

23 hours ago
የታላቁ ዓሊም ሸይኽ አህመድ ኡስማን ሥርዓተ ቀብር በአዳማ ተፈጸመ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የእስልምና ትምህርት እና የተውሒድ ጥሪ አስተምህሮ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱት ታላቁ ዓሊም ሸይኽ አህመድ ኡስማን የቀብር ሥነ ሥርዓት በአዳማ ከተማ የሙስሊሞች መካነ መቃብር ተፈጸመ።
ለረጅም ዓመታት የእስልምናን ዕውቀት በማስተማርና በርካታ ዓሊሞችን በማፍራት ለአገሪቱ የእስልምና ትምህርት ዕድገት ትልቅ ሚና የተጫወቱት የሸይኽ አህመድ ኡስማን ህልፈት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ሐዘንን ፈጥሯል።
እንደ ሃሩን ሚዲያ ዘገባ በአዳማ ከተማ በተፈጸመው በዚህ ሥርዓተ ቀብር ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋን ጨምሮ በርካታ ዓሊሞች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ምዕመናን በመገኘት የመጨረሻ ሽኝት አድርገውላቸዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

1 day ago
ሶማሊያ በአማራ ክልል በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለኢትዮጵያ ማጽናኛ እና ሐዘኗን ገለጸች
#fastmereja I የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በአማራ ክልል በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ።
የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ አገሪቱ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆም አስታውቃለች። ሚኒስቴሩ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦች እና ወዳጆች መጽናናትን የተመኘ ሲሆን፣ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ደግሞ በፍጥነት እንዲያገግሙ መልካም ምኞቱን አስተላልፏል።
በተጨማሪም በአደጋው አካባቢ የተጎዱትን ለመታደግ እና የጎደሉትን ለመፈለግ እየተደረገ ያለውን የእርዳታና የመፈለግ ስራ ያደነቀው የሶማሊያ መንግሥት፣ በጸሎት እና በሐሳብ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እንደሚገኝ አረጋግጧል።

9 days ago
(ዘ-ሐበሻ ሕይወት) ይህን ዘገባ ትናንት በቪዲዮ አቅርበነው ነበር፤ ብዙዎቻችሁ፣ 'ኢንተርኔት ፍጥነት በሌለባቸው አካባቢዎች ቪድዮ ለማየት ስለሚቸገሩ' በጽሑፍ ይቅረብልን ባላችሁን መሠረት እንደሚከተለው ቀርቧል | ወዳጅነት... ከለላና መሸሸጊያ ይሆናል ተብሎ ይታሰባል፤ ለዲዛይነር ቅድሳን ይርጋለም ግን ወዳጅነት የሞት ወጥመድ ሆኖ አረፈው። የ2026ቱ የ"ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ" የውበት ንግሥት የሩት ይርጋለም ታላቅ እህት የሆነችው ቅድሳን፣ በሞዴሊንግ ዓለም ውስጥ ስኬትን ከምትመኘውና ከእህቷ ጋርም የትምህርት ቤት ትውውቅ ከነበራት ቅድስት ሙሉቀን ጋር የጠበቀ ጓደኝነት ነበራት። ሆኖም ከዚህ ጓደኝነት ጀርባ፣ ጥልቅ የሆነ ምቀኝነት እና አደገኛ ሴራ ተሸሽጎ ነበር።
ሁሉም ነገር የተጀመረው አርብ ዕለት በተደረገ አንድ የስልክ ጥሪ ነው። ለአንድ ዓመት ያህል ተጠፋፍታ የነበረችው ቅድስት፣ የናፍቆት በሚመስል የጓደኝነት መንፈስ ለቅድሳን ደወለች። "አዲስ ኮንዶሚኒየም ተከራይቻለሁ፤ መጥተሽ ቤቴን እዪልኝ። ደግሞም የማገናኝሽ አዲስ የስራ እድል አለ" በማለት የጓደኛዋን ልብ አባበለች። በጓደኛዋ ላይ አንዳችም ክፋት ያልጠረጠረችው ቅድሳን፣ ሜክሲኮ አካባቢ ተገናኝተው አብረው ወደ ኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም አመሩ። ቅድሳን የጓደኛዋን አዲስ ሕይወት ለማየት በደስታ ስትጓዝ፣ እየሄደች ያለችው ግን ወደራሷ የሞት ቀጠሮ ነበር።
አዲሱ ቤት ደጃፍ ላይ ደርሰው ወደ ውስጥ ሲገቡ፣ የነበረው ወዳጃዊ ድባብ ቅጽበታዊ በሆነ ሽብር ተተካ። ቤት ውስጥ አድፍጦ ይጠብቅ የነበረው የቅድስት ፍቅረኛ ደሳለኝ፣ ቅድሳን ድምጿን አውጥታ እንኳ ርዳታ እንዳትጠራ አፍኖ አሰራት። ያመነቻት ጓደኛዋ እጅ ከፍንጅ ለሞት አሳልፋ ሰጠቻት።
አጋቾቹ ወዲያውኑ የሟች ቤተሰቦች ጋር በመደወል የሁለት ሚሊዮን ብር ቤዛ ጠየቁ። የቤተሰብ ልብ በጭንቀት እየመታ የድርድር ሀሳቦች ሲለዋወጡ፣ አጋቾቹ አንድ ዘግናኝ እውነት ተገነዘቡ። የጠየቁትን ገንዘብ ቢያገኙ እንኳ፣ ሟች በቅርበት ስለምታውቃቸው ነገ ሚስጥራቸውን አሳልፋ እንደምትሰጣቸው አሰቡ። ፍርሃት እና ምቀኝነት ያደነደነው ልባቸው፣ እዚያው አርብ ዕለት ጭካኔ የተሞላበት ውሳኔ ላይ ደረሰ። የቅድሳንን ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ አጠፉ። አስከሬኗንም ማንም እንዳያገኘው በሚል እዚያው አካባቢ በተከራዩት ሌላ ተጨማሪ ቤት ውስጥ ደበቁት።
ይሁን እንጂ...የፈጸሙት ግፍ በጨለማ ሊቀበር አልቻለም። ፖሊስ ባደረገው አፋጣኝ እና የተቀናጀ ክትትል፣ ዋነኛ ተጠርጣሪዋ ቅድስት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ጎተራ አካባቢ በቁጥጥር ስር ዋለች። የወንጀሉ ተባባሪ የነበረው ደሳለኝ ደግሞ፣ ሁኔታው ሲከፋበት ለማምለጥ ሞክሮ አዳማ ከተማ ውስጥ ተደብቆ እያለ በፖሊስ መረብ ውስጥ ወደቀ። በአጠቃላይ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ስምንት ሰዎች ታሰሩ። ዋነኛ ተጠርጣሪዎቹም ወንጀሉን መፈጸማቸውን አምነው፣ እንዴት እንዳከናወኑት በቦታው ተገኝተው ለፖሊስ አሳይተዋል።
ይህ ክስተት የ2026ቷን የውበት ንግሥት ሩትን ብቻ ሳይሆን፣ መላውን ማኅበረሰብ በሐዘን እና በስጋት ውስጥ ጥሏል። ሩት በልብ ስብራት "ከጠላቴ እኔ እጠነቀቃለሁ፤ ከወዳጄ አንተ ጠብቀኝ" ብላ ያሰፈረችው መልእክት፣ የዚህን ትረካ አሳዛኝ ማጠቃለያ ይወክላል፦ ጠላት ፊቱን አውቆ ሲመጣ፣ ክህደት ግን በወዳጅ ፈገግታ ታጅቦ ይመጣል።

12 days ago
የቅዱስ ፓትርያርኩ መግለጫ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።
ሓምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት እንደሚከተለው ነው፦
መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
"ገባሬ ሣህል እግዚአብሔር፥ ወይፈትህ ለኩሉ ግፉዓን፦
እግዚአብሔር ይቅርታ አድራጊ ነው፤ ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል።"
(መዝሙር ፻፪፥፮)
ከሁሉ በማስቀደም በሀገር ውስጥ እና በመላው ዓለም የምትኖሩ ኦርቶዶክሳውያን የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንን ሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓመተ ምሕረት በከፍተኛ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ለሚከበረው፤ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ በእምነታቸው የጸኑትን ቅዱስ ቂርቆስንና ቅድስት ኢየሉጣን በመከራቸው መካከል እየተራዳ የእሳቱን ነበልባል እንደክረምት ውኃ ላቀዘቀዘበት፤ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን የታመኑትንም እስከ ሰማዕትነት ፍጻሜ ድረስ የሚያጸና መሆኑን ለምንዘክርበት ታላቅ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ የወንጌልን ብርሃን በማብራት፣ የሰላምን መንገድ በማስተማር፣ ፍትሕን በማጽናት፣ የተጨነቁትንም በማጽናናት፣ ሕዝብንና ሀገርን እየደገፈች የኖረች ናት።
በዚህ ቅዱስ ተልእኮ ውስጥም መናንያን መነኮሳት እና መነኮሳይያት ዓለምንና ከዓለም የሚገኘውን ጊዜያዊ ክብር፣ ጥቅም፣ ምቾትና የመሳሰሉትን በፈቃዳቸው ትተው፤ በየገዳማቱ በበአታቸው በጾም፣ በጸሎት ተወስነው፤ ሕይወታቸውን በትሕትና ለእግዚአብሔር በመስጠት፤ ስለ ራሳቸው ብቻ ሳይሆን ስለ ሀገር፣ ስለ ሕዝብ፣ ስለ ሰላምና ስለ ዓለም ደኅንነት በመዓልትና በሌሊት የሚጸልዩ የምድራችን በረከቶች ናቸው።
መስቀልን በተሸከሙ፣ ጸሎትን መከታ ባደረጉ፣ ለፍጥረት ሁሉ ምሕረትን በሚለምኑ፣ ራሳቸውን ለመከላከልም ምንም ዓይነት ቁሳዊ ዝግጅት በሌላቸው በእነዚህ መናንያን ላይ እጅን ማንሣት በእግዚአብሔር ዘንድ የተከለከለ፣ በታሪክ ፊትም የሚያሳፍር ድርጊት ነው።
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን!
በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በቦረና ወረዳ በግዮን አባይ ገዳመ አስቄጥስ ቅድስት አርሴማ፣ አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶችና የእናቶች አንድነት ገዳም ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓመተ ምሕረት በተፈጸመው ጥቃት የመናንያን መነኮሳይያት ሕይወት በግፍ መጥፋቱን፤ በርካቶች መቁሰላቸውን፤ በገዳሙና በንዋየ ቅድሳቱ ውድመት መድረሱን ከሀገረ ስብከቱ መግለጫ በከፍተኛ ሐዘን የሰማን ሲሆን፤ በተመሳሳይም በዚሁ ዕለት በሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት የአምልኮ ሥፍራ በኃይል መፍረሱና በምእመናን ላይ ጥቃት መድረሱ የሚያሳዝንና በፍጹም ተቀባይነት የሌለው የተወገዘ ተግባር ነው።
በመሆኑም የጸሎት፣ የትምህርት፣ የሰላምና የመንፈሳዊ እሴት ማዕከል የሆኑትን ገዳማት መጠበቅ የአንድ ሃይማኖት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ የሰው ልጅ ክብርን፣ የሕግ የበላይነትንና የሀገር ሰላምን የማስጠበቅ ሓላፊነት ያላቸው በየደረጃው የሚገኙ ባለሥልጣናትና የሕግ አስከባሪ አካላት ጭምር እንደመሆኑ አሰቃቂ ጥቃት የፈጸሙት ተጠያቂዎች ለፍትሕ እንዲቀርቡ፤ ሌሎች ገዳማትና አድባራት ደኅንነታቸው እንዲጠበቅልን፤ ለተጎዱትም ተገቢው ድጋፍ እንዲደረግልን ዛሬም አበክረን እንጠይቃለን ።
በመጨረሻም ሕዝበ ክርስቲያንና መላው ኢትዮጵያውያን የጥቃት ሰለባ ከሆኑት ወገኖች ጋር በመንፈሳዊም ሆነ በሰብአዊ ድጋፍ አብራችሁ እንድትቆሙ ከአደራ ጭምር እያሳሰብን፤ በጽድቅ የሚፈርደው እግዚአብሔር አምላካችን ለተበደሉት ፍትሕን፣ ለቆሰሉት ፈውስን፣ በግፍ ሕይወታቸውን ለተነጠቁት ዕረፍተ ነፍስን፣ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ፍጹም ሰላምን ይስጥልን እያልን አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን።
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን።
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
© የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት

Sponsored by
Surafel
12 days ago
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በገዳማትና በምእመናን ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን በማስመልከት ጥብቅ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ በደቡብ ወሎ እና በሀድያና ስልጤ አህጉረ ስብከት በገዳማትና በምእመናን ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን በመኮነን አባታዊ መልእክት አስተላለፉ። ቅዱስነታቸው በደቡብ ወሎ ቦረና ወረዳ በግዮን አባይ ገዳመ አስቄጥስ በተፈጸመው ጥቃት የመነኮሳይያት ሕይወት ማለፉን፣ መቁሰልና የንዋያተ ቅድሳት ውድመት መድረሱን፤ እንዲሁም በሀድያና ስልጤ የአምልኮ ሥፍራ በኃይል መፍረሱን በከፍተኛ ሐዘን መረዳታቸውን ገልጸዋል።
በመግለጫቸውም ምንም ዓይነት ቁሳዊ ዝግጅት በሌላቸው መናንያን ላይ እጅ ማንሣት በታሪክና በእግዚአብሔር ፊት የሚያሳፍር ድርጊት መሆኑን ያሰመሩበት ቅዱስነታቸው፣ መንግሥትና የሕግ አስከባሪ አካላት ድርጊቱን የፈጸሙ አካላትን ለፍትሕ እንዲያቀርቡና የገዳማትን ደኅንነት እንዲያስጠብቁ በጥብቅ ጠይቀዋል። በተጨማሪም መላው ሕዝበ ክርስቲያንና ኢትዮጵያውያን ለተጎዱት ወገኖች አስፈላጊውን ሰብአዊና መንፈሳዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ አደራ ብለዋል።
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አባታዊ መልእክት ሙሉ ይዘት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!**
ገባሬ ሣህል እግዚአብሔር፥ ወይፈትህ ለኩሉ ግፉዓን፦ እግዚአብሔር ይቅርታ አድራጊ ነው፤ ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል።" (መዝሙር ፻፪፥፮)

በመሆኑም የጸሎት፣ የትምህርት፣ የሰላምና የመንፈሳዊ እሴት ማዕከል የሆኑትን ገዳማት መጠበቅ የአንድ ሃይማኖት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ የሰው ልጅ ክብርን፣ የሕግ የበላይነትንና የሀገር ሰላምን የማስጠበቅ ሓላፊነት ያላቸው በየደረጃው የሚገኙ ባለሥልጣናትና የሕግ አስከባሪ አካላት ጭምር እንደመሆኑ አሰቃቂ ጥቃት የፈጸሙት ተጠያቂዎች ለፍትሕ እንዲቀርቡ፤ ሌሎች ገዳማትና አድባራት ደኅንነታቸው እንዲጠበቅልን፤ ለተጎዱትም ተገቢው ድጋፍ እንዲደረግልን ዛሬም አበክረን እንጠይቃለን።

16 days ago
(ዘ-ሐበሻ ሕይወት) በሆሊውድ ዝነኛ የብሎክባስተር ፊልሞች "Godzilla vs. Kong" እና "Godzilla x Kong: The New Empire" ላይ “ጂያ” የተሰኘውን ቁልፍ ገጸ-ባህሪ በመወከል የምትታወቀው የ18 ዓመቷ መስማት የተሳናት ወጣት ተዋናይት ኬይሊ ሆትል ማክሰኞ ጠዋት በደረሰባት ድንገተኛ የመኪና አደጋ ሕይወቷ ማለፉን ፎክስ ኒውስ ዲጂታል አረጋግጧል።
የተዋናይቷ አባት ጆሹዋ ሆትል በሜሪላንድ ግዛት ውስጥ ስለደረሰው አደጋ በሰጠውና በፌስቡክ በኩል ባስተላለፈው የ23 ደቂቃ የአሜሪካ የምልክት ቋንቋ (ASL) ቀጥታ ስርጭት መግለጫ፣ ልጁ ወደ ሆስፒታል በመጓዝ ላይ እያለች ልቧ መቆሙን በለቅሶ አስታውቋል። ከተከታታይ መስማት የተሳናቸው ትውልዶች በተገኘችውና የቨርጂኒያ ተወላጅ በሆነችው ኬይሊ ሆትል ሞት ሳቢያ መላው የሆሊውድ የኪነ-ጥበብ ማኅበረሰብ በከባድ ሐዘን ውስጥ ወድቋል።
ይህንን ልብ ሰባሪ ክስተት እና የተዋናይቷን አጭር የሕይወት ጉዞ በጥልቀት ስንመለከተው ኬይሊ በሆሊውድ ውስጥ በገንዘብና በጥቅም ብቻ በሚመራው የፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥ መስማት ለተሳናቸው አካላት እውነተኛና ተጨባጭ የውክልና መድረክ የፈጠረች ስልታዊ ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆኗን ያሳያል። በ2021 ዓ.ም. “ጎድዚላ ቨርሰስ ኮንግ” በተሰኘው ታላቅ ፊልም ላይ ከግዙፉ “ኮንግ” ጋር ልዩ የልብ ትስስር ያላትን የጂያን ገጸ-ባህሪ ወክላ ስትወጣ፣ በሆሊውድ ታሪክ ውስጥ መስማት የተሳናቸው ተዋናዮች በትልልቅ የሳይንስ ልብወለድ ፊልሞች ላይ የመሪነት ሚና መጫወት እንደሚችሉ በተግባር ያሳየች ድንቅ ተሰጥኦ ነበረች።
በ2024 ዓ.ም. በወጣው ሁለተኛው ፊልም ላይም የምልክት ቋንቋን በፊልሙ ውስጥ በስፋት በማስተዋወቅ የራሷን ደማቅ አሻራ አኑራለች።
በተጨማሪም፣ ኬይሊ ሆትል ወደ ትልቁ የፊልም ዓለም ከመግባቷ በፊትም ቢሆን በተለያዩ የንግድ ማስታወቂያዎችና የጥበቃ ፕሮጀክቶች ላይ በመሳተፍ መስማት ለተሳናቸው ማኅበረሰቦች እኩል ዕድል እንዲሰጥ ስትሟገት የቆየች የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ጭምር ነበረች። ምንም እንኳን ገና በለጋ ዕድሜዋ መክሰሟ እና በሲኒማው ዓለም የጀመረችው ደማቅ ጉዞ በአሰቃቂ የመኪና አደጋ በአጭር የተቀጨ ቢሆንም፣ በሆሊውድ ውስጥ ያሉ መስማት የተሳናቸው ወጣት ተዋናዮች የወደፊት ዕድል እንዲቀየርና ማግለል እንዲቆም ያደረገችው ተጋድሎ ግን ዘላቂ ውርስ ሆኖ የሚቀጥል መሆኑን የፊልም ኢንዱስትሪ ተንታኞች በጥብቅ ያመለክታሉ።

18 days ago
ከጦርነት አዙሪት መውጣት የማይችለው ሕገ ወጡ ህወሓት
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሕዝብ ከግጭትና የጥፋት ሁኔታ ውስጥ ወጥቶ ሰላምን፣ ልማትንና አንድነትን አጥብቆ እየሻተ ባለበት ወቅት የትግራይ ክልል ሕዝብና ወጣቶችም የሰላምን አስፈላጊነት በተግባር እያረጋገጡ ይገኛል።
ሕገ ወጡ የህወሓት ቡድን የሰላም መንገዶችን በመዝጋትና የስልጣን ጥሙን ለማርካት ሲል ወጣቱን ዳግም ወደ ጦርነት ለመማገድ ቢሞክርም ሕዝቡ ይህን አፍራሽ አካሄድ በጽኑ እየተቃወመ ነው።
የትግራይ ወጣቶች ካለፉት ዓመታት የጦርነት ሰቆቃ በመማር ለጥቂቶች ጥቅምና የስልጣን ጥም ተብሎ ሕይወታቸውን ላለመገበር ፅኑ አቋም ወስደዋል።
በግዴታ ወደ ጦርነት የሚደረግ አፈሳን አጥብቀው በማውገዝ ከቀሪው የኢትዮጵያ ወንድሞቻቸው ጋር ያላቸውን ታሪካዊና ሀገራዊ ትስስር በማጠናከር የሰላምና የልማት ተምሳሌት ለመሆን ጥረት ጀምረዋል።
የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ዕድገት ለመግታት እና ሀገሪቱን በትርምስ አዙሪት ውስጥ ለመጣል የሚደክሙ የውስጥ ባንዳዎችና የውጭ ጠላቶች ሴራ በተግባር እየመከነ መጥቷል።
በሕገ ወጡ ቡድን የስልጣን ጥም የተነሳ የትግራይ ክልል ሕዝብ የሚያስፈልገው የልማት ጥያቄ ምላሽ እንዳያገኝ ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር እየሰራ ቢሆንም ይህ የኖረበት የጥፋት መንገድ በትግራይ ክልል ህዝብ ዘንድ እየገጠመው ያለው ብርቱ ተቃውሞ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ተስፋ ነው።
በአሁኑ ወቅት የህወሓት ቡድን የጦርነት ወሬ በማናፈስ፣ ህዝብን በማስፈራራት እና አፋኝ ሕጎችን በመደንገግ የትግራይን ህዝብ ለከፍተኛ መከራና ግፍ ዳርጓል።
ቡድኑ የወንጀል ድርጊቱን የሚደግፍ ህግ በመደንገግ ትግራይን በሁከትና በቀውስ ውስጥ ለማቆየት እየተንቀሳቀሰ ሲሆን፤ ለጦርነት ዓላማው በዚህ በደነገገው ህግ ወጣቶችን እያፈሰ ነው።
ይህንን ጨምሮ የቡድኑን የወንጀል ድርጊቶች የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ 'አፈሳ ይቁም፤ ሰላም ይስፈን' በሚል መሪ ሀሳብ ትናንት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተካሂዷል።
ሰላማዊ ሰልፉን ያዘጋጀው የትግራይ ሰላምና ለውጥ ምክር ቤት፤ ህገ ወጡ የህወሓት ቡድን ከመሰሎቹ አሸባሪ ኃይሎች ጋር ተጣምሮ ኢትዮጵያን ጨምሮ ቀጣናውን ለማተራመስ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
ሕገ ወጥ ቡድኑ ቀጣናውን የማያባራ ቀውስ ውስጥ ለመክተት እየሰራ ነው።
ቡድኑ ከመሰሎቹ የኢትዮጵያ ጠላት ከሆኑ በቀይ ባሕር ዳርቻ ከሚገኙ አሸባሪ ኃይሎች ጋር ተሳስሮ በመስራት ላይ ሲሆን፤ የትግራይ ወጣቶችን አስታጥቆ በኤርትራ በረሃዎች አሳልፎ ለሱዳን ጦርነት ለሽያጭ አቅርቦ እያዋጋ ነው።
በቡድኑ እየተፈጸመ ባለው አፈና እናቶች በጦርነት ያጧቸውን ልጆቻቸው ሐዘን እንኳን ሳይወጡ፤ የቀሩትን ልጆቻቸውን ለማዳን ድምጻቸውን በማሰማት ላይ ናቸው።
ይሁን እንጂ ይህ ህገ ወጥ ቡድን ለእነዚህ እናቶች ሰብዓዊ መብት ከመቆርቆር ይልቅ ድብደባ በመፈጸም እና ጥይት በመተኮስ ከፍተኛ ጥቃት እያደረሰባቸው ይገኛል።
በተለይም ወጣቶችን በግዳጅ እያፈሱ ወደ ኤርትራ እና ሱዳን ድንበር እያጋዘ የሚገኘው ይህ ህገወጥ አካሄድ፣ በሕዝቡ ላይ እየደረሰ ያለውን ሰቆቃ እጅግ አሳሳቢ አድርጎታል።
የቡድኑ ሕልውና በሙስና እና በዘረፋ የተሳሰረ በመሆኑ ከስልጣን ውጭ መሆንን እንደ አደጋ በመቁጠር የሰላም ሒደቱን ለማደናቀፍ እየሠራ ይገኛል።
ወጣቶችን እያፈሰ ወደ ኤርትራ እና ሱዳን እያጋዘ የሚገኘው ህገወጥ ቡድን የሚፈጽመውን ድርጊት በቃ ማለት ይገባል።
ትናንት በአዲስ አበባ የተካሄደው በትግራይ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን አፈና እና ጭቆና የሚያወግዝ እንዲሁም የጦርነት ዝግጅትን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ስኬታማ እንደነበርም የትግራይ የሰላምና ለውጥ ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

19 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ለአሥራ ስድስት ዓመታት ያህል.. “ጆሃንስበርግ” የምትለው ቃል ለስፔን እግር ኳስ ፍጹም ወርቃማ እና የተቀደሰች ትርጉም ነበራት። እሷ ከማድሪድ 8,000 ኪሎ ሜትር ርቃ የምትገኝ ከተማ ብቻ አልነበረችም፤ ይልቁንም አይከር ካሲያስ የወርቅ ጽዋውን ወደ ሰማይ የሰቀለባት፣ አንድሬስ ኢኒየስታ በ116ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ግብ ታሪክን ዘላለም ያደረገባት እና ስፔን “አንድ ቀን የዓለም ሻምፒዮን መሆን እችል ይሆን?” የሚለውን ጥያቄ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የቀበረችባት የታሪክ ማህደር እንጂ!
አሁን ግን የእግር ኳሱ የክብር ካርታ ወደ አዲሱ ዓለም፣ ወደ ኒውዮርክ እየመራን ነው። በሁድሰን ወንዝ ማዶ በኒው ጀርሲ፣ ሌላኛዋ አዲስ እና አስፈሪዋ የስፔን ብሔራዊ ቡድን እያንዳንዱ ታዳጊ በሕልሙ ሊጫወተው የሚመኘውን ያንን ታላቅ የፍፃሜ ጨዋታ ልታደርግ ተዘጋጅታለች። በዚያ በጆሃንስበርግ የኢኒየስታ ታሪካዊ ግብ ሲቆጠር አንዳንዶቹ የቡድኑ ተጫዋቾች ገና ዳዴ በማለት ላይ ነበሩ፤ ሌሎቹ ደግሞ በየሰፈሩና በየፓርኩ ያንን ግብ እየደገሙ ያደጉ ታዳጊዎች ናቸው። ዛሬ ግን ያቺ የመጀመሪያዋ የክብር ኮከብ በእነሱ ላይ ከባድ ሸክም መሆኗ ቀርቶ ወደ ቀጣዩ ታሪክ የሚመራቸው ፋኖስ ሆናለች።
ይህ ጉዞ ግን በምቾት የተሞላ ቀጥተኛ መንገድ አልነበረም። ለአሥራ ስድስት ዓመታት የፈጀ፣ ስድስት አሰልጣኞችን የቀያየረ እና የቡድኑን ማንነት ሙሉ በሙሉ የለወጠ ከባድ ጉዞ እንጂ። የመጀመሪያው ምዕራፍ የወርቃማው ትውልድ ቀጣይ ክፍል ነበር። ቪሴንቴ ዴል ቦስኬ የዓለም ሻምፒዮኑን ቡድን ይዘት ሳይበርዝ አስቀጥሎ፣ ከሁለት ዓመት በኋላ በኪየቭ ጣሊያንን 4 ለ 0 በሆነ አስደናቂ እግር ኳስ በማሸነፍ የዩሮ 2012 ዋንጫን በድጋሚ አነሳ። ያ ስብስብ በታሪክ ተወዳዳሪ የሌለው ታላቅ ታሪክ ጻፈ - የአውሮፓ ዋንጫን፣ የዓለም ዋንጫን እና የአውሮፓ ዋንጫን በተከታታይ በማሸነፍ ዓለምን በበላይነት የገዛበት ዘመን ነበር።
ነገር ግን ምንም ዓይነት ታላቅ ግዛት ለዘላለም አይኖርም! የ2014ቱ የብራዚል የዓለም ዋንጫ የዚያ ወደር የለሽ ትውልድ የውድቀት ማብሰሪያ ሆነ። በኔዘርላንድስ የደረሰባቸው አስደንጋጭ ሽንፈት እና በቺሊ መረታት ያንን ታሪካዊ ምዕራፍ በድንገት ዘጋው። ስፔን ከዓለም ሻምፒዮንነት ተነስታ በምድብ ደረጃ ተሸኝታ ወጣች። እግር ኳስ ለስፔናውያን ታላቅ ትምህርት ሰጣቸው - ክብር ለዘላለም የሚሰጥ ስጦታ አይደለም! ከሁለት ዓመት በኋላ በፈረንሳዩ ዩሮ፣ ጣሊያን ስፔንን በሩብ ፍፃሜ ስታስወጣ፣ የዴል ቦስኬ ዘመን እና ዋና የነበረው ያ ትውልድ ሙሉ በሙሉ ማክተሙ ታወጀ።
ከዚያ በኋላ ስፔን ወደ መልሶ ግንባታ ገባች። ጁለን ሎፔቴጊ የቡድኑን ታሪካዊ ቅርስ ሳይበታትን አዲስ ትውልድ የመፍጠር ከባድ ኃላፊነት ተረከበ። ቡድኑን በብቃት ለሩሲያው የዓለም ዋንጫ ቢያሳልፍም፣ ጨዋታው ከመጀመሩ ሁለት ቀን በፊት ከሪያል ማድሪድ ጋር ውል ማሰሩን ተከትሎ ከኃላፊነቱ መባረሩ በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ትልቁ ድራማ ሆነ። ፈርናንዶ ሄሮ ቡድኑን በድንገተኛ አደጋ ቢረከብም፣ ስፔን በሩሲያ በፔናሊቲ ተመትታ ስትወጣ ስሜቱ እጅግ መራራ ነበር።
በመቀጠል የመጣው ሉዊስ ኤንሪኬ ግን ፍጹም አዲስ አብዮት ይዞ መጣ። ያረጁ ተዋናዮችን በማስወገድ፣ ወጣቶችን ወደ ፊት በማምጣት ፈጣንና ኃይለኛ ቡድን ፈጠረ። በልጃቸው ሕመም ምክንያት ለጥቂት ጊዜ ቢርቁም፣ በረዳታቸው ሮበርት ሞሬኖ አማካኝነት ቡድኑ ሳይሸነፍ ጉዞውን ቀጠለ። ኤንሪኬ ሲመለሱም ፕሮጀክቱን አፋጠኑት። በ2021 ዩሮ ስፔን እስከ ግማሽ ፍፃሜ ተጉዛ በጣሊያን ብትሸነፍም፣ ቡድኑ ወደ ቀድሞ አስፈሪነቱ መመለሱን አበሰረ። ነገር ግን በኳታር የዓለም ዋንጫ ኮስታሪካን 7 ለ 0 በማሸነፍ በደመቀ ሁኔታ የጀመረው ጉዞ፣ በሞሮኮ የቅጣት ምት (ፔናሊቲ) ተረቶ በከባድ ሐዘን ተጠናቀቀ። ስፔን በተከታታይ ሦስት ትላልቅ ውድድሮች ሩብ ፍጻሜ እንኳን መድረስ አለመቻሏ ፌዴሬሽኑ አዲስ መንገድ እንዲፈልግ አስገደደው።
ሉዊስ ዴ ላ ፉየንቴ ለዓመታት በታችኛው የዕድሜ ክልል ውስጥ የስፔንን ወጣቶች ሲቀርጽ የቆየ ጥልቅ መሃንዲስ ነው። የዩሮ ከ19 እና ከ21 ሻምፒዮን፣ የኦሊምፒክ ሜዳሊያ ባለቤት በመሆኑ የወደፊቱን ትውልድ በደብ ያውቀው ነበር። የእሱ ስልት ግለሰብን ሳይሆን እንደ አንድ ጠንካራ ቤተሰብ መጫወትን ማዕከል ያደረገ ነበር። ውጤቱም ወዲያውኑ መጣ!
መጀመሪያ የኔሽንስ ሊግን አሸነፈ... በመቀጠልም የ2024ቱን የአውሮፓ ዋንጫ በታላቅ የበላይነት በማንሳት ስፔንን ዳግም ወደ አውሮፓ የክብር ማማ መለሳት። ያ ቡድን በሮድሪ፣ ፔድሪ፣ ፋቢያን፣ ላሚን ያማል እና ኒኮ ዊሊያምስ የሚመራ፣ ወጣቶችና አንጋፋዎች የተቀላቀሉበት፣ ፍጹም የማይፈራ ስብስብ ሆነ። አሰልጣኙ እንደተናገሩት ያ ዩሮ ገና ጅምር እንጂ ማሳረጊያ አልነበረም።
ባለፉት ሁለት ዓመታት ዴ ላ ፉየንቴ ኳስን መቆጣጠር ብቻ ሳይሆን፣ መሮጥ፣ መጫን፣ እና አስፈላጊ ሲሆን መከላከል የሚችል ሁለገብ ቡድን ገንብቷል። ይህ ቡድን በአጨዋወቱ ከ2010ዱ ቡድን ቢለይም፣ በአሸናፊነት ስነ-ልቦናው ግን ፍጹም አንድ አይነት ነው።
ከጆሃንስበርግ እስከ ኒውዮርክ በትክክል 5,852 ቀናት አልፈዋል። ተዋናዮቹ ተቀይረዋል፣ ስታዲየሞቹ ሌላ ሆነዋል፣ ተቀናቃኞቹም ተለውጠዋል። አይከር ካሲያስ የአምበልነቱን ማዕረግ ለአዲሱ ትውልድ አስረክቧል። ዣቪ፣ ኢኒየስታ እና ቪያ ቦታቸውን ለሮድሪ፣ ላሚን ያማል እና ኦያርዛባል ለቀዋል። ነገር ግን የዴል ቦስኬን ታሪካዊ መንገድ ዛሬ ዴ ላ ፉየንቴ በዚያው ወርቃማ ስሜት እያስቀጠለው ይገኛል—ያንን የመጀመሪያዋን የክብር ኮከብ በቴሌቪዥን እያዩ ያደጉት ታዳጊዎች፣ ዛሬ ሁለተኛዋን ኮከብ ለመጨበጥ በኒውዮርክ ሜዳ ላይ ታሪክ ለመጻፍ ተዘጋጅተዋል!

ከስንብት ሐዘን ማግስት የሚደረግ የክብር ፍልሚያ
*******************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ዋዜማ ላይ ቆመናል። ዓለም ዋንጫ በግማሽ ፍፃሜ በለስ ያልቀናቸውን፣ ድል ከነርሱ ጋር ያልነበረውን እንዲሁ አያሰናብትም። ለሦስተኝነት ማዕረግ ዳግም ያፋልማል።
23ኛው ዓለም ዋንጫ ፍሎሪዳ ላይ የግማሽ ፍፃሜ ተሸናፊዎቹን ዛሬ እኩለ ሌሊት 6 ሰዓት ፍሎሪዳ ሚያሚ ላይ ያፎካክራል። በእርግጥ በብዙዎች፣ በተለይም በተሸናፊ ብሔራዊ ቡድኖች ዘንድ የደረጃው ጨዋታ ለመጫወት የተመረጠ አይደለም።
የዛሬው መርኃ ግብር ግን ብሔራዊ ቡድኖቹ ከሚያደርጉት ፉክክር ባልተናነሰ፣ በኮከብ ግብ አስቆጣሪነት በመላቅ የወርቅ ኳስ ሽልማቱን ለማግኘት ባለው ፉክክር ለውጥ እንደሚያስከትል ይጠበቃል። ከሊዮኔል ሜሲ ጋር የኮከብ ግብ አስቆጣሪነት ፉክክሩን በ8 ግቦች እየመራ የሚገኘው ኪሊያን ምባፔ እንዲሁም እያንዳንዳቸው ስድስት ግቦች ያስቆጠሩት ጁድ ቤሊንግሃም እና ሀሪኬን ከባለ አምስት ግቡ የዓለም ኮከብ ኡስማን ዴምቤሌ ጋር በሚያደርጉት የኮከብ ግብ አስቆጣሪነት ፉክክር ላይ አንዳች ለውጥ ሊያስከትል የሚችል ጨዋታ እንደሚሆን ታምኗል።
በዚህ መሀል ግን ከሽንፈት ማግስት የሚደረግ፤ ከዓለም ዋንጫ ስንብት ሀዘንም ሳያገግሙ የሚመጣ መርኃ ግብር መሆኑ የተጫዋቾችን ተነሳሽነት መቀነሱ፣ የተመልካቾችን ጉጉትም ማሳነሱ አይቀርም። ቶማስ ቱሄል ይህን የሚያስረግጥ ሃሳብ ነው የሰነዘሩት። "የእኛም ሆነ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ይህን ጨዋታ የማድረግ ፍላጎት የላቸውም" በማለት በውድድሩ ሙሉ የለፉትና የተዘጋጁት ለዓለም ሻምፒዮንነት በመሆኑና፤ ያም ባለመሳካቱ ለዚህ ጨዋታ የሚኖራቸውን ጉጉትና ፍላጎት እንደቀነሰው ተናግረዋል።
ቱሄል ይህንን ቢሉም የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዲዲየር ዴሻው ግን ከዚህ በአንፃራዊነት የተለየ ሃሳብ ነው የሰነዘሩት። 3ኛ ደረጃም ቢሆን የተሻለ መሆኑን በማንሳት፤ እርሱን ለማሳካት የቻሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። አክለውም የተፈጠረው ሀዘን የዓለም ሻምፒዮን ከመሆን ፅኑ መሻት የመጣ መሆኑን ጠቅሰው፤ የሆነውን ከመቀበል ውጪ አማራጭ የለንም ብለዋል።
በግማሽ ፍፃሜው እንግሊዝ እየመራች የነበረችውን ጨዋታ የኋላ ኋላ በአርጀንቲና 2 ለ 1 ተሸንፋ የፍፃሜ መንገዷ ሲቋረጥ፤ በአንፃሩ ፈረንሳይ ባልተጠበቀ ሁኔታ በስፔን ፍፁም ብልጫ ተወስዶባት 2 ለ 0 ተረታ ነው ከፍፃሜው የቀረችው።
የ23ኛው ዓለም ዋንጫ 103ኛው ጨዋታ በሁለት ሃሳቦች መሀል፤ የጨዋታውን አስፈላጊነት ተጠይቅ ውስጥ በሚከቱና የኮከብ ግብ አግቢነት ፉክክሩ ላይ የሚኖረውን ሚና በሚያጎሉ መሀል ሆኖ፤ እኩለ ሌሊት 6፡00 ሰዓት በሚያሚ ጋርደን ሀርድ ሮክ ስታዲየም ይካሄዳል።
በእድሪስ አህመድ
#worldcup #fifaworldcup #fifaworldcup2026 #3rdplaceplayoff #england #france #football #sports

23 days ago
የቀብር አስፈጻሚ ንግድ ስራ
በኢትዮጵያ ህግ ማእቀፍ
መግቢያ #ethiopia | ሰዎች በባህል በልምድ በሚያደርጓቸው ልውውጦች፣ መግባባቶች
የተነሳ የህግ ድጋፊ አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት መንግስት ወደ ህጋዊ ንግድ በመለወጥ በነጻነት የህግ ማእቀፍ ኖሮት የተሳለጠ እና ዘመናዊ የንግድ ልውውጥ እንዲኖረው ያደርጋል። ህግ ለዜጎች ዋስትና እንደመሆኑ መጠን በዚህ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሰወች ሳይፈሩ ሳይሸማቀቁ ከመንግሥት እና ከሚመለከቱአቸው የንግድ አጋሮቻቸው ደንበኞች ጋር ነጻ የህግ ግንኙነት በመፍጠር የንግድ ስራ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋሉ። ለሀገሩ እና ለዜጎች የሚጨነቅ መንግስት በህግ ማእቀፍ ውስጥ ያልተካተቱ ንግድ መሠል ድርጊቶችን ለህግና ለመልካም ጠባይ የማይቃረን ለዜጎች እና ለሀገር የሚጠቅም መሆኑን ሲረዳ በህግ እንዲጸድቅ ያደርጋል። የቀብር አስፈጻሚ ንግድ አዲሱ የንግድ አዋጅ ቁጥር 1243/13 ላይ የንግድ ዘርፍ ከመካተቱ በፊት በቀድሞው የንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 166/52 መሠረት የተካተተ አልነበረም። ይሁን እንጂ
ሰወች በዚህ ቀብር ማስፈጸም ስራ በህግ ያልታቀፈ ቢሆኑም ሲሰሩ እንደነበር ይታወቃል። በኋላም መንግስት አስፈላጊነቱን በመረዳት በአዲሱ ንግድ አዋጅ ቁጥር 1243/13 አንዱ የንግድ ዘርፍ ሆኖ እውቅና ተሰጥቶታል። በዚህ ጹሁፍ የምንመለከተው የዚህን የቀብር ስራ ንግድ ባህርያት ፣ አመሠራረት ፣ አፈጻጸም እና ተግዳሮት ከህግ አግባብ እንመለከታለን።
1. የቀብር ስራ ንግድ የህግ እውቅና
በአዲሱ አዋጅ ቁጥር 1243/13 አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 37 የንግድ ስራዎች ምን ምን እንደሆኑ የተዘረዘሩ ሲሆን አንደኛው የቀብር ስራ ንግድ ነው።
እነዚህ የተዘረዘሩት የንግድ ስራዎች በዚህ አዋጅ የተጠቀሱት እነዚህን የንግድ ስራዎችን ማስፈጸሚያ ደንብና መመሪያ ቢወጣ አፈጻጸም ላይ ወጥነት ከመኖሩም ባሻግር ዜጎች ፍትሀዊ ተጠቃሚ እንዲኖራቸው ፣ ፍትሀዊ ቁጥጥር እንዲጎለብት፣ የንግድ እንቅሰቃሴዎች ግልጽነት ከመኖራቸውም ባሻግር የዘመነ የአኮኖሚ እድገት እንዲኖር ፣ ዜጎች አዋጭነት ያለው አስተማማኝ የፋይናንስ እድገት እንዲኖራቸው የሚረዳ ነው። የቀብር ስራ ንግድም ህግን እና መልካም ጠባይ ፣ የተሻለ የንግድ ለውጥ እንዲኖረው፣ፍትሀዊ ተጠቃሚነት እንዲዘልቅ ከአዋጁ በተጨማሪ ግልጽ የሆነ ጠቃሚ አሰራር እንዲሰፍን ደንብ እና መመሪያዎች መኖሩ የበለጠ የህግ ስረአት መጎልበት እና ተጠቃሚነትን የሚያዳብር ነው። ስለሆነም ይህ ሊታሰብበት የሚገባ አበልጻጊ የዚህ ንግድ ስራ ሆኖ ሊታሰብበት ይገባል።
2. የቀብር ስራ ማስፈጸም ንግድ ስራ ባህሪያት
የቀብር ንግድ ሥራ (Funeral Business) በሰዎች ሐዘን እና አስቸጋሪ ወቅት ላይ የሚመሠረት በመሆኑ፣ ከሌሎች መደበኛ የንግድ ዘርፎች ፍጹም የተለዩ ልዩ ጠባያት አሉት።
ዋና ዋናዎቹ የቀብር ንግድ ሥራ ባህርያት የሚከተሉት ናቸው፦
2.1. ቋሚና የማይቀንስ ፍላጎት (Inelastic Demand)
የገበያ መረጋጋት፦ ሞት ተፈጥሯዊና የማይቀር በመሆኑ፣ ይህ የንግድ ሥራ በኢኮኖሚ መቀያየር ወይም በፋሽን አዝማሚያዎች አይነካም።
አስገዳጅ ወጪ፦ ደንበኞች በገንዘብ እጥረት ምክንያት የቀብር ሥነ-ሥርዓትን ሙሉ በሙሉ ለመተው አይችሉም፤ በመሆኑም ፍላጎቱ ሁልጊዜም ቋሚ ነው።
2.2. ከፍተኛ ስሜታዊነትና ኃላፊነት (High Emotional Sensitivity)
ከባድ የሐዘን ወቅት፦ ደንበኞች አገልግሎቱን የሚፈልጉት በሕይወታቸው እጅግ አስቸጋሪ እና በስሜት በተጎዱበት ወቅት ላይ ነው።
የባለሙያ ሥነ-ምግባር፦ የንግድ ሥራው ከትርፍ ይልቅ ለሐዘንተኞች ርኅራኄ፣ ክብር እና ትዕግሥት ማሳየትን እንደ ትልቅ መመሪያ ይወስዳል።
2.3. ፈጣንና የ24 ሰዓት አገልግሎት (Urgency & 24 hourh Availability)
ያልታቀደ ክስተት፦ ሞት መቼ እንደሚከሰት ስለማይታወቅ ሥራው አስቀድሞ ለመዘጋጀት ጊዜ አይሰጥም።
የሰዓት ገደብ የሌለው፦ የሬሳ ማደራጃ፣ የትራንስፖርት እና የክብር ዘበኛ አገልግሎቶች በማንኛውም ሰዓት (በሌሊትም ጭምር) ጥሪ ሲደርሳቸው ወዲያውኑ ምላሽ መስጠት አለባቸው።
2.4. በባህልና በሃይማኖት መገዛት (Cultural & Religious Influences)
የተለያዩ ሥርዓቶች፦ እያንዳንዱ ማኅበረሰብ፣ እምነት (ክርስትና፣ እስልምና፣ ወዘተ) እና ብሔረሰብ የራሱ የሆነ የቀብር አፈጻጸም ሥርዓት አለው።
ተለዋዋጭ ፍላጎት፦ ንግዱ ስኬታማ የሚሆነው የእነዚህን የተለያዩ እምነቶችና ባህሎች ዝርዝር ደንቦች በትክክል አውቆና አክብሮ ማስተናገድ ከመልካም ጠባይ አንጻር የሚጠበቅ ነው።
2.5 አስፈላጊ መዋዕለ-ነዋይና አቅርቦት
የመነሻ ካፒታል፦ ጥራት ያላቸው የሬሳ ሣጥኖች፣ አስክሬን ማቀዝቀዣዎች፣ ልዩ መኪናዎች (Hearses) እና የማከማቻ ቦታዎችን ለማሟላት ከፍተኛ መዋዕለ-ነዋይ ይጠይቃል።
የሕግ ቁጥጥር፦ ከጤና ጥበቃ፣ ከአካባቢ ጥበቃ እና ከማዘጋጃ ቤት የሚወጡ ጥብቅ የሕግና የንጽሕና ፈቃድ መስፈርቶችን ማሟላት አስፈላጊ ነው።
2.6. የማስታወቂያው ባህርይ ጠባይ፦
ይህ ንግድ እንደ ሌሎቹ በቪዲዮ ወይም በታላቅ የጎዳና ላይ ማስታወቂያ አይስፋፋም።
3. የቀብር ንግድ ስራ አመሠራረት በኢትዮጵያ ንግድ ማእቀፍ
ከዚህ በፊት ስለ ንግድ አመሠራረት ፣ አይነት እና ባህርያት እንደገለጽነው ንግዶች በህግ እውቅና እንዲኖራቸው ባህርያቱን፣የንግዱን አላማ ፣ የኢኮኖሚውን እንቅስቃሴ ራእይ ፣ የመስራቹን ፍላጎት ፣ አቅም ፣ ልምድ፣እውቀት ጭምር ማወቅ መረዳት ያስፈልጋል።
ንግድ በዋናነት ሁለት አይነት ሲሆኑ የግል እና ኃላፊነቱ የተወሰነ ባህርይ ያለው ራሱን የቻለ የህግ ሰውነት ያለው ብለን መክፈል እንችላለን። በግል ንግድ መመስረት የፈለገ የፈለገ ኃላፊነቱ የራሱ እና የድርጅቱ ንግድ ኃላፊነት ያልተነጣጠለ ሲሆን ሁለተኛው ግን ከኃላፊነት መወሰን ባህርይ ጋር የሚያያዝ ነው። ኃላፊነቱ የተወሰነ የንግድ ማህበር በህብረት ሆነው የሚያቋቁሙት ሲሆን በየትኛው አይነት የንግድ ማህበር ለመመስረት በአዋጁ አንቀጽ 174 ላይ ከተመሰረቱት ዝርዝር ውስጥ ከህግ አማካሪ ጋር በመሆን ተገቢውን የንግድ ማህበር መምረጥ አስፈላጊ ነው።
እንደ እኔ ግን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መምረጡ አስፈላጊ ሲሆን ይኸውም በአንድ ሰው አባልነት ወይም ሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ ባለ አክስዮኖች መመስረት የሚቻል ነው።
ለዚህም የቅድሚያ አባላት መዋጫ ከማህበሩ 1/4ኛ ካፒታል፣በዝግ ንግድ ባንክ(ማንኛውም) ባንክ ፣ ማስያዝ፣የመመስረቻ ጹሁፍ ማዘጋጀት፣ በንግድ መዝገብ መመዝገብ ለምሳሌ ያህል የሚጠቀሱ ሲሆን ለመመስረት በንግዱ የተቀመጡትን ከአንቀጽ 185 እስከ 189 የተደነገጉትን፣ በንግድና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 686/2002 የተደነገጉትን እና ሌሎች በንግድና አግባብነት ያለቸውን ድንጋጌዎች መከተልና መጠበቅ ያስፈልጋል።
4. የቀበር ስራ ንግድ በተመጣጠነ ዋጋ አገልግሎቱ እንዲቀርብ ምን መደረግ አለበት?
ማህበረሰቡ በልምድና ባህል በሚያቋቁሙት የእድር ማህበራት ተገቢውን የህግ ግንዛቤ በመስጠት የቀበር ንግድ ስራ በመሰማራት ለማህበረሰቡ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ተገቢውን ጥረት እና ትጋት የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አስፈላጊውን ድጋፍ ቢያደርጉ የተሻለ የቀብር ስራ ንግድ አገልግሎት ይኖራል የሚል እምነት አለኝ።
5. ማጠቃለያ እና የህግ ምክር
የቀብር ስራ ንግድ የህግ ማእቀፍ እንዳለው መጠን ይህንን
ከህግ፣ሞራልና ጠባይ አንጻር ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ተፈጻሚ እንዲሆን አዋጭ በሆነው የንግድ አይነት እንዴት መመስረት እንዳለበት እና ሌሎቾ በእድር መልክ የተደራጁ እና ሌሎች በዚህ ንግድ መሠማራት የሚፈልጉ ሰወችን በሚፈለገው የህግ መስፈርት መንገድ ጠብቀው እንዲመሠርቱ በማድረግ የቀብር ንግድ ስራ አገልግሎት በተመጣጠነ ዋጋ ለማህበረሰቡ ተደራሽ ከማድረጉም በላይ በዚህ ዘርፍ መሠማራት የሚፈልጉ ሰወችን ለስራ እድል ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው።
የቀድሞው አዋጅ (የንግድ ሕግ) ማጣቀሻ አዋጅ ቁጥር 166/1952 ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪ አዲሱ የንግድ ሕግ ከመጽደቁ በፊት የንግድ ምዝገባና ፈቃድን ለመምራት በዋናነት አዋጅ ቁጥር 686/2002 (በኋላም በማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 980/2008 እና 1152/2011) ሲተገበሩ ቆይተዋል።
ጠበቃና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው
+251-929-101037
https://t.me/Fantahunlawye...
tiktok.com/fantahun62395
https://www.facebook.com/s...
ማጣቀሻ/References/
1. የቀድሞ ንግድ አዋጅ ቁጥር 166/1952
2. አዲሱ የንግድ አዋጅ ቁጥር 1243/13
3. የንግድና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 686/2002 እና የዚህ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 980/2008 እና 1152/2011

26 days ago
የ2026 የዓለም ዋንጫ ድራማዊ እና አስደናቂ ትዕይንቶች በከፍተኛ ስሜት ቀጥለዋል። የዓለም ሻምፒዮኗ አርጀንቲና፣ እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ በአስደናቂ ፅናት ስትታገል የነበረችውን እና በሁለተኛው አጋማሽ በ10 ተጫዋቾች ለመጫወት የተገደደችውን ስዊዘርላንድን በከባድ ፉክክር 3ለ1 በመርታት ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፏን አረጋግጣለች። ይህንን ታሪካዊ ድል ተከትሎ... አርጀንቲና በሴሚ ፋይናሉ ኖርዌይን በአስጨናቂ ሁኔታ አሸንፋ የደረሰችውን የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን የምትገጥም ይሆናል።
የጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ግን ለገለልተኛ ተመልካች ያን ያህል ማራኪና ሳቢ አልነበረም። ስዊዘርላንዶች ወደ ፊት ተጭነው በመጫወት በጥሩ የሜዳው ክፍሎች ላይ ኳሶችን በተደጋጋሚ መንጠቅ ቢችሉም፣ ወደ አርጀንቲና የግብ ክልል ሲደርሱ ግን የሚያስፈልገው ጥራት እና የማጥቃት መጨረሻ በከፍተኛ ሁኔታ ጎድሏቸው ታይቷል። ይሁንና በመጀመሪያው አጋማሽ የአርጀንቲናውን እምብርት ሊዮኔል ሜሲን ጸጥ በማሰኘት እና ከጨዋታው ውጪ በማድረግ በኩል የስዊዘርላንድ ተከላካዮች ፍጹም ድንቅ ስራ ሰርተው ነበር።
ጨዋታው ለእረፍት ሲወጣ ግን በአርጀንቲና ካምፕ ውስጥ ትልቅ ድንጋጤ ተፈጥሮ ነበር። መሪው ሊዮኔል ሜሲ ከዓይኑ ጥቂት ከፍ ብሎ በደረሰበት አስቀያሚ እና ከባድ የመቆረጥ አደጋ ምክንያት በውሃ እረፍት ሰዓቱ ላይ በሀኪሞች ከፍተኛ የሕክምና እርዳታ ሲደረግለት ተስተውሏል። አርጀንቲና ጨዋታውን ለመቆጣጠር ተጨማሪ ግቦች እንደሚያስፈልጓት በግልጽ በታየበት በዚያ ፈታኝ ወቅት፣ የሜሲ መጎዳት የቡድኑን የወደፊት እጣ ፈንታ ጥያቄ ውስጥ ጥሎት ነበር።
በሁለተኛው አጋማሽ ግን የጨዋታው መልክ ሙሉ በሙሉ ተቀየረ። የጨዋታው ትልቅ ማዕበል የተነሳው የስዊዘርላንዱ አጥቂ ብሪል እምቦሎ በቀይ ካርድ ከሜዳ መባረሩን ተከትሎ ስዊዘርላንድ በ10 ተጫዋች እንድትቀጥል ስትገደድ ነው። እምቦሎ በቡድን አጋሮቹ እየተፅናና በእንባ ታጥቦ ሜዳውን የለቀቀ ሲሆን፣ ስዊዘርላንድ ተአምር ሰርታ ብታልፍ እንኳ እሱ በግማሽ ፍጻሜው መሰለፍ እንደማይችል በማወቁ የተሰማው ከባድ ሀዘን በግልጽ ይታይ ነበር። ይህንን የቁጥር ብልጫ በአግባቡ የተጠቀሙት አርጀንቲናውያን፣ የአጥቂ መስመራቸውን በማስፋት የስዊዘርላንድን የተከላካይ ግንብ ሰብረው በመግባት ጨዋታውን 3ለ1 በሆነ አስገራሚ ውጤት ሊያጠናቅቁ ችለዋል።
ዳኛው የጨዋታውን ማጠናቀቂያ ፊሽካ ሲነፉ በመላው ስታዲየም ውስጥ ያለው የደጋፊዎች ጩኸትና ሁካታ በአንድ ጊዜ በአስደናቂ ሁኔታ ፈንድቷል! አርጀንቲና ድሉን ሙሉ በሙሉ በማረጋገጥ ጉዳዩን ቋጭታዋለች። በአንጻሩ ስዊዘርላንዶች ያላቸውን አቅም፣ ጉልበትና ጥረት ሁሉ በሜዳው ላይ አፍስሰው እስከ መጨረሻው ሰከንድ ድረስ የተዋጉ ቢሆንም በመጨረሻ ግን መሸነፋቸው አይቀሬ ሆኗል። ጨዋታው እንደተጠናቀቀ በርካታ የስዊዘርላንድ ተጫዋቾች ፍፁም በሆነ ሐዘንና ቁጭት ተሰብረው በጉልበታቸው ሜዳው ላይ ተንበርክከው ታይተዋል።
ጨዋታው ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት በመላው ስታዲየም ውስጥ "ሜሲ፣ ሜሲ፣ ሜሲ" የሚለው የሺዎች ደጋፊዎች ነጎድጓዳዊ የክብር ጩኸት እና መዝሙር በአስደናቂ ሁኔታ አስተጋብቷል። አርጀንቲና አሁን ወደ ግማሽ ፍፃሜው ተሻግራለች። ይህ ድል አርጀንቲናን እና እንግሊዝን እ.ኤ.አ ከ2005 ዓ.ም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት የሚያገናኝ ታሪካዊ አጋጣሚን ፈጥሯል። የፊታችን ረቡዕ የሚጠበቀው ይህ የአርጀንቲና እና የእንግሊዝ ፍልሚያ፣ የሊዮኔል ሜሲ የመጨረሻው የዓለም ዋንጫ ክብር እና በጁድ ቤሊንግሃም የሚመራው የአዲሱ ትውልድ የእንግሊዝ ሃይል የሚጋጩበት እውነተኛ የእግር ኳስ ክላሲክ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም።

28 days ago
ለእናቱ የገባውን ቃል ለመጠበቅ አስክሬን ቤት አስቀምጦ ለተፈተነው ታዳጊ ካሊድ ቃሲም የመኖሪያ ቤት ሊገነባለት ነው::
ከሦስት ሳምንታት በፊት እናቱ ባረፉበት ዕለት የገባውን ቃል ለማክበር ሲል አስክሬን ቤት ውስጥ ትቶ የስምንተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተናውን በመፈተን መላውን የሀገሪቱን ሕዝብ በከፍተኛ ሐዘን ያስለቀሰውና ያስደመመው ታዳጊ ካሊድ ቃሲም፣ አዲስ የመኖሪያ ቤት ሊገነባለት መሆኑ ተሰማ።
በሸገር ከተማ አስተዳደር ኤካ ጣፎ ክፍለ ከተማ ከሁለት ታናናሽ ወንድሞቹ ጋር የሚኖረው ይህ የ14 ዓመት ታዳጊ፣ በወቅቱ እናቱ በጽኑ ታመው በነበሩበት ወቅት “እኔ አንድ ነገር ብሆን እንኳ ለዓመታት የለፋህበትን ፈተና እንዳታቋርጥ” በማለት ያስገቡትን ጥብቅ ቃል ለመጠበቅ የጠዋት ፈተናውን ተፈትኖ፣ ከሰዓት ደግሞ እናቱን አልቅሶና ቀብሮ በመመለስ የከሰዓት ፈተናውን ማጠናቀቁና “ቃልሽን አላጠፍኩም እማ!” ማለቱ ይታወሳል።
ዛሬ በተሰማው አዲስና ተስፋ ሰጪ መረጃ መሠረት፣ ለታዳጊውና ለታናናሽ ወንድሞቹ ቋሚ የቤት መፍትሔ ለመስጠት የሸገር ከተማ የኤካ ጣፎ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለቤት ግንባታ የሚሆን መሬት በይፋ አዘጋጅቶ አስረክቧል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የመኖሪያ ቤቱን ሙሉ በሙሉ ገንብቶ ለታዳጊዎቹ ለማስረከብ ቃል ገብቷል።
ወላጅ አባቱ ከእነርሱ ርቆ በጅጅጋ ከተማ ሌላ ትዳር መሥርቶ በመኖሩ ምክንያት እናታቸውን አጥተው ብቻቸውን ለቀሩት ለእነዚህ ወንድማማቾች የተደረገው ይህ የመሬትና የቤት ግንባታ ድጋፍ፣ የታዳጊውን ታማኝነትና ብርታት ያከበረ እንዲሁም ማኅበራዊ አጋርነትን በተግባር ያሳየ መሆኑ ተገልጿል።
Seledadotio

1 month ago
ደህና ሁኚ
#ethiopia | ታዋቂዋና አንጋፋዋ ድምፃዊት አርቲስት ራሔል ዮሐንስ በ80 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷን ተከትሎ፣ ሥርዓተ ቀብሯ ዛሬ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ በታላቅ ሐዘን ተፈጽሟል። በሕይወት ዘመኗ በሙዚቃው ዓለም ጉልህ አሻራ ያሳረፈችውና በመጨረሻ ዓመታትዋ ራሷን ለመንፈሳዊ አገልግሎት የሰጠችው ይህች ድንቅ አርቲስት፣ በትዳር ሕይወቷ የ6 ልጆች እናት፣ የ14 የልጅ ልጆች እንዲሁም የ5 የልጅ ልጅ ልጆች ባለጸጋ መሆን የቻለች ሲሆን፣ ያበረከተችው በጎነትና የጥበብ ሥራዎቿ ሁልጊዜም ሲታወሱ ይኖራሉ።
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ደብረ ምህረት ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያምና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴደራል ዛሬ ቀን ሥርዓተ ቀብሯ ተፈጽሟል።
***
የሕይወት ታሪክ እና የጥበብ ጉዞ
በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ በተለይም በዘመን አይሽሬ (Oldies) እና ባህላዊ ሥራዎቿ የብዙዎችን ልብ የማረከችው አንጋፋዋ ድምፃዊትና የዜማ ደራሲ **አርቲስት ራሔል ዮሐንስ** በተደረገላት የሕክምና እርዳታ ስትረዳ ቆይታ በ80 ዓመቷ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ ተሰምቷል።
የሕይወት ታሪክ እና የጥበብ ጉዞ
መጋቢት 20 ቀን 1938 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ በገዥኖችን አካባቢ ከአባቷ ከአቶ ዮሐንስ መኮንን እና ከእናቷ ከወ/ሮ ወይንእሸት ጎንፋ ተወለደች።
በአንድ እህትና በሁለት ወንድሞች መካከል በፍቅር አድጋ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በአስፋው ወሰን ትምህርት ቤት፣ ሁለተኛ ደረጃዋን ደግሞ በቀድሞው የኪነ-ጥበብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቃለች።
ወደ ሥራው ዓለም በመግባት በአዲስ አበባ በሚገኙት በጊዮን ሆቴል እና ሒልተን ሆቴል ውስጥ ለብዙ ዓመታት ያገለገለች ሲሆን፣ በፈርስት ኬተሪንግ ኤጀንሲም ለጥቂት ዓመታት ሠርታለች።
ከ1973 ዓ/ም ጀምሮ በሙዚቃው ዓለም ውስጥ በይፋ በመሳተፍ ከ13 በላይ አልበሞችንና በርካታ ነጠላ ዜማዎችን ለሕዝብ አበርክታለች።
በተለይም "አራዳ"፣ "ምኒልክ" እና "ይዳኘኝ ሰው" የተሰኙት ሥራዎቿ በብዙዎች ዘንድ የማይረሱ ድንቅ አሻራዎቿ ናቸው። በኪነ-ጥበብ ጉዞዋም ከበርካታ የኢትዮጵያ አንጋፋ ድምፃውያን ጋር በጋራ ለመሥራት ችላለች።
አርቲስት ራሔል ዮሐንስ ለሀገሯ ያላትን ፍቅር በሥራዎቿ የገለጸች ሲሆን፣ በተለይም ለኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ ለባሕር ኃይል እና ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያቀረበቻቸው ሥራዎቿ ተጠቃሽ ናቸው።
በማኅበራዊ ሕይወቷም ሰውን የምትወድ፣ የምታከብር እና ችግረኞችን በመርዳት የምትታወቅ የብዙዎች "ሩኅሩኅ እናት" ነበረች።
የሕይወት ምዕራፍ ለውጥ እና መንፈሳዊ ሕይወት
በሕይወቷ የመጨረሻዎቹ ዓመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ከዓለማዊ ሙዚቃ በመራቅ፣ ሕይወቷን ለሃይማኖቷና ለመንፈሳዊ አገልግሎት ሰጥታ ነበር።
በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነቷ ጸንታ፣ ቅዱስ ቁርባንን በመቀበል እስከ ዕለተ ሞቷ ድረስ በጠንካራ መንፈሳዊ ሕይወትና በምስጋና (በመዝሙር) ከፈጣሪዋ ጋር ኖራለች።
አርቲስት ራሔል የ2 ወንድና የ4 ሴት (በድምሩ የ6 ልጆች) እናት፣ የ14 የልጅ ልጆች አያት እንዲሁም የ5 የልጅ ልጅ ልጆች ቅድመ-አያት የመሆንን ትልቅ የቤተሰብ ጸጋ ተጎናጽፋ ነበር።
ሥርዓተ ቀብሯ ዛሬ፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በደብረ ምሕረት ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያምና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴደራል በ8:00 ሰዓት ላይ ተፈጽሟል።
ቤተሰቦቿ በሕመም ወቅት ለስታመሟት፣ በአካልም ሆነ በስልክ ላጠያቋት እንዲሁም በሥርዓተ ቀብሩ ላይ በድምቀት ለተገኘው ለመከላከያ ሠራዊት ማርች ባንድ በፈጣሪ ስም ከፍ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ለቤተሰቦቿ፣ ለአድናቂዎቿና ለመላው የጥበብ አፍቃሪያን መጽናናትን እንመኛለን።
#ethiopia #rahelyohannes #rip #artist #የረገፈች_ጥበብ

በኢራን መዲና ቴህራን ለሀዘን የወጡ ሰልፈኞች ሞት ለትራምፕ የሚሉ ባነሮችን ይዘው ታይተዋል
በቴህራን የሟቹን ጠቅላይ መሪ አሊ ካሜኔይ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙ ሰልፈኞች “ሞት ለትራምፕ ” የሚል ባነር ይዘው ሐዘንተኞቹ አሳይተዋል፤ ትራምፕ በሚለው ቃል ውስጥም ጥይት ተስሎ ታይቷል።
ሌሎች ሀዘንተኞችም የዩኤስ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ፣ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሰት እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ “ደም በእጃቸው አለ” የሚል መልዕክት የያዙ ምስሎችን ይዘው ነበር።
የኢራን ፕሬስ ቲቪ እንደዘገበው የቀብር ስነ ስርዓቱ ሂደት የጀመረው የካሜኔይ አስከሬን ለሁለት ቀናት ከተቀመጠበት የቴህራን ግራንድ ሞሳላ መስጊድ ነው።
አዘጋጆቹ ሂደቱ ከ10 እስከ 12 ሰዓታት እንደሚቆይ ይጠብቃል ብለዋል።
ይህም በዳማቫንድ ፣ በኢማም ሁሴን ፣ በእንቀላብ፣ በአዛዲ አደባባይ እና በሻሂድ ላሽጋሪ ሀይዌይ በኩል 10 ኪሎ ሜትር መንገድ ላይ ይጓዛል ብለዋል።
የታዝኒም የዜና ወኪል ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የካሜኔይ አስከሬን የያዘው ተሽከርካሪ “ወደ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ መንገድ ለመግባት ዝግጁ” መሆኑን ዘግቧል።

የአንጋፋዋ ድምፃዊት አርቲስት ራሔል ዮሐንስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ”
ሀገራችን ካፈራቻቸው እጅግ ድንቅና አንጋፋ ድምፃውያን መካከል አንዷ የሆነችው አርቲስት ራሔል ዮሐንስ በ80 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷን ተከትሎ፣ ሥርዓተ ቀብሯ ዛሬ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ደብረ ምህረት ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያምና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴደራል ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ተፈጽሟል።
ሁላችንም አንድ ቀን በምናገኘውና በማይቀረው የሞት መንገድ ቀድማን የተጓዘችው የዚህች ታላቅ ድምፃዊት ሕይወት ማለፍ መላውን የኪነጥበብ ማህበረሰብና የሀገራችንን ሕዝብ በታላቅ ሐዘን ውስጥ ጥሏል።
በሕይወት ዘመኗ በሙዚቃው ዓለም የራሷን ጉልህ አሻራ ማሳረፍ የቻለችው ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ፣ በሕይወቷ የመጨረሻ ዓመታት ላይ ሙሉ በሙሉ ከዓለማዊ ሙዚቃ በመራቅ ራሷን ለመንፈሳዊ አገልግሎትና ለምስጋና መዝሙሮች አውላ እንደነበር ይታወሳል።
በትዳርና በቤተሰብ ሕይወቷም የሁለት ወንድና የአራት ሴት ልጆች እናት ለመሆን የበቃች ሲሆን፣ የ14 የልጅ ልጆች እንዲሁም የ5 የልጅ ልጅ ልጆችን የመሳም ታላቅ የእድሜና የሕይወት ጸጋን አግኝታለች።
ይህች ድንቅ የጥበብ ሰው ዛሬ ምድራዊ ጉዞዋን አጠናቃ ወደ ዘላለማዊ እረፍቷ ብትሸኝም፣ ያበረከተቻቸው ስራዎችና ያሳየችው በጎነት ሁልጊዜም ሲታወሱ ይኖራሉ።
እኛም ለታላቋ ድምፃዊት ቤተሰቦች፣ ለአድናቂዎቿና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፈጣሪ ጽናቱንና መጽናናትን እንዲሰጥልን እንመኛለን።
Nahom Records

አንቸሎቲ፦ “ዛሬ ማሸነፍ ይገባን ነበር”
#ethiopia | የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ ቡድናቸው ከ2026 የዓለም ዋንጫ ውድድር መሰናበቱን ተከትሎ ከፍተኛ ሐዘን እንደተሰማቸው ገልጸዋል።
አንቸሎቲ ከጨዋታው በኋላ ለመገናኛ ብዙኃን ሲናገሩ፣ “ሁላችንም በጣም አዝነናል። ቡድኑ ድንቅ የዓለም ዋንጫ ባያሳልፍም ጥሩ ውድድር አድርጓል” ብለዋል።
አሰልጣኙ በዕለቱ በተደረገው ጨዋታ ብራዚል ድል ይገባት እንደነበር በመግለጽ፣ “ዛሬ ማሸነፍ ይገባን ነበር። እንደዚህ ያለ ሽንፈት ሲያጋጥም ይህንን እንደ አዲስ ጉዞና አዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ መመልከት አለብን” ሲሉ ተናግረዋል።
ብራዚል በ16 ቡድኖች ዙር በኖርዌይ 2 ለ1 ተሸንፋ ከውድድሩ ስትሰናበት፣ ኖርዌይ ደግሞ ወደ ሩብ ፍጻሜ ማለፏን አረጋግጣለች።

ኢራን ለሟቹ አያቶላህ አሊ ካሜኒ የስድስት ቀናት የሽኝት ሥነ ስርዓት ዛሬ በይፋ ጀመረች
ኢራን ለሟቹ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ ከዛሬ ጀምሮ ለስድስት ቀናት የሚዘልቅ ህዝባዊ የሀዘን ሥነ ሥርዓት በይፋ መጀመሯን የሀገሪቱ የመንግስት ቴሌቪዥን ዘግቧል።ካሜኒ በጎርጎሪያኑ የካቲት 28 ቀን 2026 ዓ ም ቴህራን በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ላይ በተደረገ የጋራ የአየር ጥቃት ነበር የተገደሉት።
የበቀል ምልክት የሆነውን ቀይ ባነር የያዙ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሐዘንተኞች የቴህራንን ሰፊ የግራንድ ሞሳላ ሃይማኖታዊ ሕንፃ ግቢ ሞልተው የካሜኒ አስከሬን እስኪመጣ ድረስ ሲጠባበቁ እንደነበር የፈረንሳዩ የዜና ወኮል የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ጋዜጠኛ ተመልክቷል። ሐዘንተኞች የካሜኔይ እና በአየር ድብደባው የተገደሉት ቤተሰቦቻቸው አስከሬን በቦታው ሲደርስ ከምሬት ለቅሶ ባሻገር “ቃላችን አንድ ነው! ይህም በቀል! በቀል!” ነው የሚል መፈክር በተደጋጋሚ ማስተጋባታቸውን ዘገባው አመልክቷል።እንደ ዘገባው በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኑት የኢራን ከፍተኛ ተደራዳሪ በፋርስ ባሕረ ሰላጤ በሚገኘው የባህር ወሽመጥላይ የጋራ ቅኝት ሊጀመር እንደሚችል አስተያየት ለሰጡት ለፈረንሳይ እና ለብሪታኒያ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።
የካሜኔይ አስከሬን እስከ መጭው ሰኞ ቴህራን የሚቆይ ሲሆን፤ ሐሙስ ዕለት በሰሜን ምስራቅ ኢራን በምትገኘው ማሽሃድ ከተማ ግብዓተመረታቸው ከመፈፀሙ በፊት፤ ለሺዓ ሙስሊሞች ቅዱስ ወደሆነችው ከተማ ወደ ኩም እንዲሁም ወደ ጎረቤት ኢራቅ እንደሚወሰድ ዘገባው አመልክቷል።በሀዘን ሥነ ሥርዓቱ ወቅት የኢራን የአየር ክልል እና ከተማ ውስጥ ያሉ በርካታ መንገዶች ለደህንነት ሲባል ዝግ ሆነው ይቆያሉ ተብሏል።
ለካሜኔይ ሽኝት የፓኪስታን፣የሩሲያ፣የቻይና፣ የህንድ እና የአፍጋኒስታን ተወካዮች እና በእስራኤል ጥቃት የተገደለው የሂዝቦላህ መሪ የሃሰን ናስራላህ የቤተሰብ አባላት ተገኝተዋል።በካሚኒ እግር የተተኩት ሞጅታባ ካሜኔይ በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደሚገኙ አላረጋገጡም። ለወራትም በይፋ አልታዩም።
በ86 ዓመታቸው በእስራኤል እና በአሜሪካ የአየር ድብደባ የተገደሉት ካሜኒ ኢራንን ከጎርጎሪያኑ 1989 ዓ ም ጀምሮ እስከ ዕለተሞታቸው ድረስ መርተዋል።
BBC

ጃፓን ከ2026 የዓለም ዋንጫ ተሰናበተች፤
ተጫዋቾችና አሰልጣኙ ለደጋፊዎች ይቅርታ ጠየቁ
#ethiopia | የጃፓን ብሔራዊ ቡድን በ2026 የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ውድድር በብራዚል 2–1 ተሸንፎ ከውድድሩ ተሰናብቷል።
ከጨዋታው በኋላ የጃፓን ተጫዋቾችና ዋና አሰልጣኝ ወደ ደጋፊዎቻቸው በመሄድ በትህትና ጎንበስ ብለው ለተሰጣቸው ድጋፍ አመስግነዋል፣ እንዲሁም በውድድሩ ቀድመው በመሰናበታቸው ይቅርታቸውን ገልጸዋል።
ምንም እንኳን የዓለም ዋንጫ ጉዟቸው በሐዘን ቢጠናቀቅም፣ የጃፓን ቡድን ያሳየው ትጋት፣ ዲሲፕሊን እና ለሀገራቸው ያላቸው ቁርጠኝነት በብዙ የእግር ኳስ አፍቃሪዎች ዘንድ የሚታወስ ሆኖ ይቀራል።

በአውሮፕላን አደጋው እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ 11ሰዎች ሞተዋል
#ethiopia | በፈረንሳይ በደረሰ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ።
በምስራቅ ፈረንሳይ ቶምብላይን ከተማ አቅራቢያ በደረሰ የአነስተኛ አውሮፕላን መከስከስ አደጋ አብራሪውን ጨምሮ የ11 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡
ለአንድ ፓራሹት ማሰልጠኛ ት/ቤት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ሲቭል አውሮፕላን ከናንሲ ኢሴይ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ብዙም ሳይቆይ መከስከሱ ተመላክቷል፡፡
በተፈጠረው አደጋም አብራሪውን ጨምሮ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ የ11ዱም ሰዎች ሕይወት ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ከሟቾች መካከል አምስቱ የትምህር ቤቱ ተማሪዎች ሲሆኑ አምስቱ ደግሞ መምህራን እንደነበሩ ተጠቁሟል፡፡
የፈረንሳይ ትራንስፖርት ሚኒስቴር በተከሰተው አሰቃቂ አደጋ የተሰማውን ሐዘን ገልጾ የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
#ፈረንሳይቶምብላይንከተማ #ፈረንሳይየአውሮፕላንአደጋ #ጊጡተመስገንሚዲያኮሚኬሽን #getutemesgenmediacommunication

ጋዜጠኛ ሣህለገብርኤል ይትባረክ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
ሰኔ 19/2018 ዓ.ም
ከጋዜጠኝነት ሙያው በተጨማሪ በማረሚያ ፖሊስ አባልነት እስከ ረዳት ኢንስፔክተርነት ማዕረግ የደረሰው ረዳት ኢንስፔክተር ሣህለገብርኤል፣ ሕይወቱ እስካለፈበት ዕለት ድረስ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ክፍል የሚዲያ ማስተባበሪያ ኃላፊ በመሆን እያገለገለ ነበር።
በ18 ዓመቱ የማረሚያ ፖሊስን የተቀላቀለው ረዳት ኢንስፔክተር ሣህለገብርኤል ይትባረክ፣ ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት ነበር።
በጋዜጠኛ ሣህለገብርኤል ይትባረክ ሕልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለፅን፣ ለቤተሰቦቹ፣ ለሙያ አጋሮቹ እና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን እንመኛል።
የአብሥራ ተፈራ

የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (ኤኤምኤን) ዜና አንባቢው ሳህለገብርኤል ይትባረክ ከዚህ አለም በሞት ተለየ
#ethiopia | የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (ኤ ኤም ኤን) ዜና አንባቢ ምክትል ኢንስፔክተር ሳህለገብርኤል ይትባረክ ዛሬ ማለዳ በድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰማ።
ትናንት በሚዲያው ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕለታዊ ዜናውን አንብቦ የሄደው ጋዜጠኛው ዛሬ በድንገት ሕይወቱ ማለፉ መላውን የሥራ ባልደረቦቹን ወዳጅ ዘመዶቹንና ተመልካቹን በከፍተኛ ድንጋጤና ሐዘን ውስጥ ጥሏል።
በሁሉ ዘንድ በትሕትናውና በሥራ ወዳድነቱ የሚታወቀው የምክትል ኢንስፔክተር ሳህለገብርኤል ይትባረክ ድንገተኛ መርዶ፣ የሰውን ልጅ ሕይወት አጭርነትና ቅጽበታዊነት መሆኑን ያሳየና እጅግ ልብ የሚሰብር ሆኗል።
ይህንን መራራና አስደንጋጭ ዜና ተከትሎም፣ ለታዋቂው የዜና አንባቢ ቤተሰቦች፣ ለቅርብ ወዳጆቹና ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ ባልደረቦች በሙሉ ፈጣሪ መጽናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን።
ነፍስ ይማር 🕯

2 months ago
አስቸኳይ የፍለጋ ጥሪ
#ethiopia | ውድ እናታችን ወ/ሮ አለምነሽ ደሳ ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው የደረሱበት ቦታ ባለመታወቁ ቤተሰቦቻቸው በከፍተኛ ጭንቀትና ሐዘን ውስጥ ይገኛሉ።
ስም: ወ/ሮ አለምነሽ ደሳ
የጠፉበት ቦታ: ሰሜን ሸዋ፣ ስውሯ ማርያም ገዳም
የጠፉበት ቀን: 20/03/2018 ዓ.ም.
ሁኔታ: ከሌሊቱ 12:00 ሰዓት ለመጸበል ወጥተው ከዚያ በኋላ አልተመለሱም።
የለበሱት ልብስ: ሰማያዊ ቀሚስ እና ነጠላ
የሚናገሩት ቋንቋ: ጉራጊኛ ብቻ
የጠፉበት ጊዜ: ከ6 ወር ከ20 ቀን በላይ ሆኗቸዋል።
ወ/ሮ አለምነሽ ደሳን ያየ ወይም ያሉበትን ቦታ የሚያውቅ ሰው ካለ፣ እባክዎ ቤተሰቦቻቸውን ያሳውቁ። ቤተሰቦቻቸው ለሚያገኙበት መረጃ ተገቢውን ወረታ እና ምስጋና እንደሚሰጡ ገልጸዋል።
📞 የመገናኛ ስልኮች
• 09-06765262
• 09-20-95-90-46
• 09-29-09-49-69
• 09-21-31-34-64
• 09-89-00-66-15
• 09-89-00-66-14
• 09-13-53-83-56
እባክዎ ይህን መረጃ በማጋራት (Share) እናታችን ወደ ቤተሰቦቿ እንድትመለስ ድርሻዎን ይወጡ።
መልዕክቱን ማጋራት እናትን ከልጆቿ ሊያገናኝ ይችላል።
#አፋልጉኝ #አለምነሽደሳ #የጠፉሰዎች #እናት #ስውሯማርያም #ጉራጊኛ #ኢትዮጵያ #missingperson #helpfindher

በዛሬው ዕለት፣ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም.፣ የእግዚአብሔር ሰው ነቢይ ኢዩ ጩፋ የማስተርስ ኦፍ ክርስቲያን ቲዎሎጂ (Master of Christian Theology) ዲግሪ ምረቃ ሥነ-ሥርዓታቸው በበርካታ እንግዶች፣ ቅዱሳን፣ ወዳጆችና አገልጋዮች በተገኙበት እጅግ ደማቅና የተዋበ ሁኔታ ተካሂዷል።
ነቢይ ኢዩ ጩፋ ላለፉት ዓመታት ትምህርታቸውን በትጋት፣ በጽናትና በታማኝነት ሲከታተሉ ቆይተዋል። ሆኖም ግን፣ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወራት በፊት በእናታቸው ወደ ጌታ ማረፍ ምክንያት በጥልቅ ሐዘን ውስጥ ስለነበሩ፣ የምረቃ ሥነ-ሥርዓታቸውን በታቀደለት ጊዜ ማካሄድ አልቻሉም። ሐዘንና ደስታ በአንድ ጊዜ አብረው ሊከበሩ እንደማይችሉ በመግለጽ፣ ለትምህርት ተቋሙ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ፈቃድ ተሰጥቷቸው የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ለዛሬው ዕለት ተላልፎ ተካሂዷል።
በሌላ በኩል፣ ነቢዩ የዶክትሬት (PhD) ትምህርታቸውን ያለማቋረጥ በመቀጠላቸው፣ በቅርቡ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን እንደሚያገኙም ተረጋግጧል።
እንደ መምህራኖቻቸው ገለጻ፣ ነቢይ ኢዩ ጩፋ በትምህርታቸው ጠንካራ፣ ትጉህና ተስፋ ሰጪ ተማሪ የነበሩ ሲሆን፣ በጥናት ዘርፍም የተለየ ብቃት አሳይተዋል። በምረቃ መድረኩ ላይ ያቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍም ለተሰብሳቢው ማኅበረሰብ ይፋ ተደርጓል።
በተያያዘም፣ ነቢይ ኢዩ ጩፋ የስኬታቸው ምንጭ ለሆነው ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ካቀረቡ በኋላ፣ ለክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን፣ ለቦርድ አባላት፣ ለጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች፣ ለአብሮ ሠራተኞቻቸው (ፓርትነሮች)፣ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ለሚገኙ ወዳጆቻቸው፣ እንዲሁም ለኮሌጁ ፕሮፌሰሮችና ዶክተሮች ከልብ የመነጨ ታላቅ ምስጋና አቅርበዋል።
በአጠቃላይ፣ የእግዚአብሔር ሰው ነቢይ ኢዩ ጩፋ የማስተርስ ዲግሪ ምረቃ ሥነ-ሥርዓት በበርካታ ቅዱሳን፣ ወዳጆችና እንግዶች በተገኙበት እጅግ ደማቅና ታሪካዊ በሆነ ሁኔታ ተካሂዶ ተጠናቋል።

የእናቱን አስክሬን ቤት አስቀምጦ የእናቱን ቃል ለማክበር የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና ከቀብር በፊት እና በኃላ ለፈተና የተቀመጠው ካሊድ
ይሕ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ታዳጊ ካሊድ ይባላል ገና የአስራ አራት ዓመት ልጅ ነው።ከሑለት ታናናሽ ወንድሞቹ ጋር በሸገር ከተማ አስተዳደር ኤካ ጣፎ ክፍለ ከተማ ከእናቱ ጋር ይኖራል።
ካሊድ ከእናቱ ጋር ሲኖር ወላጅ አባቱ ከእነርሱ ርቆ ሌላ ትዳር መስርቶ ጅጅጋ ከተማ ይኖራል። ካሊድ ሠሞኑን እናቱ ታምወው በነበረበት ወቅት እኔ አንድ ነገር ብሆን ምንም ቢፈጠር አመት የለፋሕበትን ፈተና እንዳታቋርጥ ብለው ቃል ያስገቡታል።
እናትም በነጋታው የስምንተኛ ክፍል ፈተና ሊሲጥ ሠዓታት ሲቀረው ሕይወታቸው ያልፋል።ካሊድ በእናቱ ሞት ከፍተኛ ሐዘን ቢሰማውም ለእናቱ የገባው ቃል አክብሮ የእናቱን አስክሬን እቤት ጥሎ የጥዋት ፈተናውን ተፈተነ።
ካሊድ ከሠዓት እናቱን አልቅሶ ቀብሮ ተመልሶ የከሰዓት ፈተናውን ተፈተነ።የዚሕ የአስራ አራት አመት ታዳጊ የሕይወት ፈተና ብዙዎችን በሐዘን ማስለቀሱን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ ድምጽ የነበረው ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ተከትሎ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በይፋዊ የትስስር ገጹ ገልጿል።
ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በመልዕክቱ፣ "በተወዳጅ እና በልዩ የዜማ ስልቱ ስንወደው በነበረው ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ህልፈት የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽኩ፣ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለመላው የኪነጥበብ ማህበረሰብ መጽናናትን እመኛለሁ" ብሏል።
ቴዲ አፍሮ አክሎም ሰማኸኝ በለው የባህል ሙዚቃውን በአንቱታ ያገለገለ እና በኪነጥበቡ ዓለም ትልቅ አሻራ ጥሎ ያለፈ ሰው መሆኑን በማውሳት፣ "ነፍሱ በገነት ትረፍ፤ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፤ ፍቅር ያሸንፋል" በማለት መልእክቱን አጠናቋል።
የድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ህልፈት የኢትዮጵያን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ በታላቅ ሐዘን ውስጥ የጣለ ክስተት ሆኗል። አርቲስቱ በተለይም በባህል ሙዚቃው ዘርፍ የነበረው የላቀ አስተዋጽኦ ለዘመናት በኪነጥበብ አፍቃሪዎች ዘንድ ሲዘከር የሚኖር ነው። የድምጻዊውን ማለፍ አስመልክቶ ቴዲ አፍሮን ጨምሮ በርካታ የሙያ ባልደረቦቹ እና አድናቂዎቹ የህመም እና የሀዘን መግለጫዎችን በመላክ ላይ ይገኛሉ።

በትውልድ አከባቢው ምሳሌ የነበረው ሃኪም ራሱን አጠፋ
በሲዳማ ክልል ከኩታዮ ቀበሌ ፈልቆ፣ በኦሳ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ብርሃኑን ማብራት የጀመረው ድንቅ ኮከብ፤ የማትሪክ ውጤቱን ሰቅሎ ለአካባቢው አይንና ኩራት የሆነው ወጣት ምሳሌ ቡዙነህ በድንገት ተለየን።
በአርሲ ዩኒቨርስቲ የሕክምና ትምህርት ክፍልን በመቀላቀል በማዕረግ (With Distinction) የተመረቀ የነገ ትልቅ ተስፋ የነበረው ባለሙያ ነበር።
ለቤተሰቦቹ ብቸኛ ወንድ ልጅ በመሆኑ ከምንም በላይ የሚሳሱለት፣ በአካባቢው ታላላቅ ልጆች ዘንድ "ተከታያችን" ተብሎ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት፣ ታናናሾቹም እንደ ስሙ 'ምሳሌ' አድርገው የሚያዩት እጅግ ትሁት እና ከተባለው በላይ Excellent ልጅ ነበረ።
በቅርቡ በሞጆ አካባቢ በሚገኝ የሕክምና ተቋም ውስጥ በሙያው ማኅበረሰቡን ማገልገል ጀምሮ እንደነበር ሰምተን ሳይጠገብ፣ ትናንትና አመሻሽ ግን ሕይወት አዳኝ በነበሩት በእነዚያ ጎበዝ እጆቹ በራሱ ላይ ጨክኖ ሕይወቱን ማጥፋቱን ስንሰማ ልባችን በሐዘን ተሰበረ። ኦሳ መብራቷን አጥታለች፤ ሎካም የነገ ተስፋዋን ተነጥቃለች።
የውድ ልጃችን ሃኪም ምሳሌ ቡዙነህ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በነገው ዕለት በተወለደበት በኩታዮ ቀበሌ ልዩ ስሙ 'ባዲቻ' በሚባለው ቦታ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ ይፈጸማል።
ለተከበሩ ቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለጠቅላላው የኦሳ፣ የኩታዮ እና የሎካ ማኅበረሰብ ጥልቅ መጽናናትን እንመኛለን።
ነፍስህን በአጸደ ገነት ያኑራት ምሳሌ! 🕊️🕯️
Via: ምሳሌ ፈንታ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ታዋቂው የእስልምና ሃይማኖት መምህር ኡስታዝ ያሲን ኑሩ በምስራቅ አርሲ ዞን በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ጥቃት አጥብቀው በማውገዝ የተሰማቸውን ጥልቅ እና መሪር ሐዘን ገልጸዋል። ኡስታዙ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት "ምነው የተከበረው የሰው ልጅ ህይወት እንዲህ ረከሰ?" በማለት በመገረም፣ ድርጊቱን የዜጎችን ነፍስ ለርካሽ ዓለማዊ ግብ ማሳኪያነት ለመጠቀም የሚደረግ "ሀገር አጥፊ" ተግባር ሲሉ በጽኑ ኮንነውታል።
የብዝሃ ሃይማኖት እና ብሔር ብሔረሰቦች እናት የሆነችውን ሀገራችንን ሰላም ለማናጋት፣ እንዲሁም ለዘመናት የተገነባውን የሕዝቦች የጠበቀ ትስስር ለመበጠስ ያሰፈሰፉ ኃይሎች የሚያደርጉትን ጥፋት ያወገዙት ኡስታዝ ያሲን፤ የሚመለከተው የመንግሥት አካል አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርበዋል። የሚመለከታቸው አካላት ይህንን የሀገር ዕድገት የሚገታ እኩይ ተግባር በማስቆም፣ የዜጎችን በሰላም ወጥቶ የመግባት ሰብዓዊ መብት ማረጋገጥ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
ዜጎች በሰላም ወጥተው ስለመግባታቸው መተማመኛ የሌላቸውን ሀገር ወደፊት የመራመድ እና የማደግ ዕድሏ የመነመነ መሆኑን ያስገነዘቡት ኡስታዙ፣ "ስለ ሀገሬ ያገባኛል፣ ይመለከተኛል የሚል ሁሉ 'ሀይ' ሊል ይገባል" ሲሉ ሁሉም ዜጋ የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል።
"እንዲህ ዓይነቱን አስነዋሪ ድርጊት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በሕዝቦች መካከል አለመተማመንን የሚዘሩ ኃላፊነት የጎደላቸው ግለሰቦች የጉዳዩን አደገኛነት ተገንዝበው ቆም ብለው እንዲያስቡ እና ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ " ኡዝታዙ አበክረው መክረዋል።
ፈጣሪ የተበዳዮችን እምባ እንዲያብስ፣ ለበዳዮችም የእጃቸውን እንዲሰጣቸው እና በሀገሪቱ ፍትሕን እንዲያሰፍን ጸሎት በማድረግ መልእክታቸውን አጠቃልለዋል።

ምነው የተከበረው የሰው ልጅ ህይዋት እንዲህ እረከሰ ?!!!
ደመ*ና—ደም መና!!
በምስራቅ አርሲ በውድ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ጥቃት በመስማቴ የተሰማኝን ጥልቅና መሪር ሐዘን ለመግለፅ እወዳለሁ።
የብዝኃ ኃይማኖትና ብሔር ብሔረሰቦች እናት የሆነችውን ሀገራችንን ሰላም ለማናጋት፤ ለዘመናት የተገነባውን የሕዝቦች የእርስ በርስ የጠበቀ ትስስር ለመበጠስ፤ ብሎም የዜጎችን ነፍስ ለርካሽ ዓለማዊ ግባቸው ማሳኪያ ለመጠቀም ያሰፈሰፉ እኩያን በተደጋጋሚ እየፈፀሙት ያለውን ሀገር አጥፊ ድርጊት አጥብቄ እኮንናለሁ። አወግዛለሁም።
የሰውን ልጅ ክቡር ህይዎት የሚያጠፉና የሃገራችን ኢትዮጵያን ዕድገት የሚገታ እኩይ ተግባር ላይ ተሰማርተው በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እየፈፀሙት ያለውን መጠነ ሰፊ ጥፋት የሚመለከተው አካል አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ የዜጎችን በሰላም ወጥቶ የመግባት ሰብዓዊ መብት ማረጋገጥ ይገባዋል።
በሰላም ወጥተው ስለመግባታቸው መተማመኛ የሌላቸውን ዜጎች ያቀፈች ሀገር ወደፊት የመራመድ ዕድሏ የቀጨጨ፣ የማደግ ተስፋዋ የመነመነ ነውና ስለ ሀገሬ ያገባኛል፣ ይመለከተኛል የሚል ሁሉ ‹ሀይ› ሊል ይገባል።
ከምንም በላይ ደሞ መሰል አስነዋሪ ድርጊቶችን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም በሕዝቦች መካከል አለመተማመንን የሚዘሩ ኃላፊነት የጎደላቸው ግለሰቦች የጉዳዩን አደገኛነት ከግምት በማስገባት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ቆም ብለው እንዲያስቡ አበክሬ ለመግለፅ እወዳለሁ።
አላህ የተበዳዮችን እምባ እንዲያብስ፤ ለበዳዮችም የእጃቸውን እንዲሰጣቸውና ፍትሕን እንዲያሰፍንልን የበረታ ዱዓዬ ነው።
ሰላም ለሀገራችን!
(ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ል)
ኡስታዝ ያሲን ኑሩ

Comments