በትውልድ አከባቢው ምሳሌ የነበረው ሃኪም ራሱን አጠፋ
በሲዳማ ክልል ከኩታዮ ቀበሌ ፈልቆ፣ በኦሳ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ብርሃኑን ማብራት የጀመረው ድንቅ ኮከብ፤ የማትሪክ ውጤቱን ሰቅሎ ለአካባቢው አይንና ኩራት የሆነው ወጣት ምሳሌ ቡዙነህ በድንገት ተለየን።
በአርሲ ዩኒቨርስቲ የሕክምና ትምህርት ክፍልን በመቀላቀል በማዕረግ (With Distinction) የተመረቀ የነገ ትልቅ ተስፋ የነበረው ባለሙያ ነበር።
ለቤተሰቦቹ ብቸኛ ወንድ ልጅ በመሆኑ ከምንም በላይ የሚሳሱለት፣ በአካባቢው ታላላቅ ልጆች ዘንድ "ተከታያችን" ተብሎ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት፣ ታናናሾቹም እንደ ስሙ 'ምሳሌ' አድርገው የሚያዩት እጅግ ትሁት እና ከተባለው በላይ Excellent ልጅ ነበረ።
በቅርቡ በሞጆ አካባቢ በሚገኝ የሕክምና ተቋም ውስጥ በሙያው ማኅበረሰቡን ማገልገል ጀምሮ እንደነበር ሰምተን ሳይጠገብ፣ ትናንትና አመሻሽ ግን ሕይወት አዳኝ በነበሩት በእነዚያ ጎበዝ እጆቹ በራሱ ላይ ጨክኖ ሕይወቱን ማጥፋቱን ስንሰማ ልባችን በሐዘን ተሰበረ። ኦሳ መብራቷን አጥታለች፤ ሎካም የነገ ተስፋዋን ተነጥቃለች።
የውድ ልጃችን ሃኪም ምሳሌ ቡዙነህ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በነገው ዕለት በተወለደበት በኩታዮ ቀበሌ ልዩ ስሙ 'ባዲቻ' በሚባለው ቦታ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ ይፈጸማል።
ለተከበሩ ቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለጠቅላላው የኦሳ፣ የኩታዮ እና የሎካ ማኅበረሰብ ጥልቅ መጽናናትን እንመኛለን።
ነፍስህን በአጸደ ገነት ያኑራት ምሳሌ! 🕊️🕯️
Via: ምሳሌ ፈንታ

9 days ago