Logo
Getu Temesgen
በፃድቃኔ ማርያም ቤተክርስቲያን ፀበል በተከሰተ ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወቷ ያለፈው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ
#ethiopia | በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የህግ ትምህርት ተማሪ የሆነችው ተማሪ ሀብታሟ በቀለ ለእረፍት ወደ ቤተሰብ ከመሄዷ ቀድማ በፃድቃኔ ማርያም ቤተክርስቲያን ፀበል በመከታተል ላይ ሳለች በአካባቢው በተከሰተ ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ/ም ከዚህ አለም ድካም አርፋለች።

ተማሪ ሀብታሟ በትምህርቷ ካስመዘገበችው ከፍተኛ ውጤት ባሻገር፣ በመልካም ስነ ምግባሯ፣ በታታሪ ተማሪነቷ፣ በክፍል ውስጥ ተሳትፎዋና ተግባቢ ስብዕናዎቿ የምትታወቅ፤ በተለይ በምስለ ችሎት ውድድሮች በምታሳየው የላቀ ችሎታ እና ውጤት እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው ለአካባቢው ማህበረሰብ በሚሰጠው የነፃ ህግ አገልግሎት ድጋፎች ዙሪያ በነበራት ተሳትፎ የምትታወቅ ተማሪያችን ነበረች፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት በተማሪ ሀብታሟ በቀለ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለፀ ለተማሪዋ ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ፣ እንዲሁም ለመላው የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ መፅናናትን ይመኛል፡፡

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ

13 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.