ምነው የተከበረው የሰው ልጅ ህይዋት እንዲህ እረከሰ ?!!!
ደመ*ና—ደም መና!!
በምስራቅ አርሲ በውድ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ጥቃት በመስማቴ የተሰማኝን ጥልቅና መሪር ሐዘን ለመግለፅ እወዳለሁ።
የብዝኃ ኃይማኖትና ብሔር ብሔረሰቦች እናት የሆነችውን ሀገራችንን ሰላም ለማናጋት፤ ለዘመናት የተገነባውን የሕዝቦች የእርስ በርስ የጠበቀ ትስስር ለመበጠስ፤ ብሎም የዜጎችን ነፍስ ለርካሽ ዓለማዊ ግባቸው ማሳኪያ ለመጠቀም ያሰፈሰፉ እኩያን በተደጋጋሚ እየፈፀሙት ያለውን ሀገር አጥፊ ድርጊት አጥብቄ እኮንናለሁ። አወግዛለሁም።
የሰውን ልጅ ክቡር ህይዎት የሚያጠፉና የሃገራችን ኢትዮጵያን ዕድገት የሚገታ እኩይ ተግባር ላይ ተሰማርተው በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እየፈፀሙት ያለውን መጠነ ሰፊ ጥፋት የሚመለከተው አካል አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ የዜጎችን በሰላም ወጥቶ የመግባት ሰብዓዊ መብት ማረጋገጥ ይገባዋል።
በሰላም ወጥተው ስለመግባታቸው መተማመኛ የሌላቸውን ዜጎች ያቀፈች ሀገር ወደፊት የመራመድ ዕድሏ የቀጨጨ፣ የማደግ ተስፋዋ የመነመነ ነውና ስለ ሀገሬ ያገባኛል፣ ይመለከተኛል የሚል ሁሉ ‹ሀይ› ሊል ይገባል።
ከምንም በላይ ደሞ መሰል አስነዋሪ ድርጊቶችን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም በሕዝቦች መካከል አለመተማመንን የሚዘሩ ኃላፊነት የጎደላቸው ግለሰቦች የጉዳዩን አደገኛነት ከግምት በማስገባት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ቆም ብለው እንዲያስቡ አበክሬ ለመግለፅ እወዳለሁ።
አላህ የተበዳዮችን እምባ እንዲያብስ፤ ለበዳዮችም የእጃቸውን እንዲሰጣቸውና ፍትሕን እንዲያሰፍንልን የበረታ ዱዓዬ ነው።
ሰላም ለሀገራችን!
(ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ል)
ኡስታዝ ያሲን ኑሩ

2 months ago