7 days ago
ቬንዙዌላ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የወንጀል መጠን የሚፈጸምባት ሀገር ተባለች።
#ethiopia | የረቀቁና የተደራጁ ወንጀሎች በብዛት ከሚፈጸምባቸው ሀገራት ቬንዙዌላ አንዷ ስትሆን በትጥቅ የተደገፈ ዝርፊያ ግድያ እና እገታ በብዛት ይበዛበታል ተብሏል።
መረጃው እንደጠቆመው ከፍተኛ የወንጀል መጠን የሚመዘገብባቸው አገራት በዋናነት በኢኮኖሚ አለመረጋጋት በፖለቲካዊ ውጥረት እና በቡድን ሁከቶች የሚታወቁ ናቸው።
ፓፓዋ ጊኒ ከፍተኛ የወንጀል መጠን ከሚፈፀምባቸው ሀገራት መካከል በሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን ከከተሜነት መስፋፋት እና ሥራ አጥነት ባስከተለው ማኅበራዊ ውጥረት ምክንያት ከፍተኛ የወንጀል መጠን የሚመዘገብባት ሀገር ሆናለች።
ደቡብ አፍሪካ ከአለም ሶስተኛ ከአፍሪካ በቀዳሚነት ከፍተኛ የወንጀል መጠን የሚፈጸምባት ሀገር ተብላለች።
በጥናቱ መሠረት በሀገሪቱ የጦር መሣሪያ በቀላሉ መገኘቱ የኢኮኖሚ አለመመጣጠን እና የጎዳና ላይ ጥቃቶች መስፋፋታቸው ለወንጀሉ መጨመር በምክንያትነት ተጠቅሰዋል።
ከደቡብ አፍሪካ በመቀጠል ናይጄርያ በህገ-ወጥ እገታዎችና በሳይበር ወንጀሎች ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
እንዲሁም ሶማሊያ እና ሊቢያ በፖለቲካዊ አለመረጋጋትና በታጠቁ ቡድኖች እንቅስቃሴ ምክንያት ከአህጉሩ ከፍተኛ የወንጀል ስጋት ካለባቸው ሀገራት መካከል ሶስተኛና አረተኛ ደረጃን ይዘዋል።።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #reviewindex #venezuela #southafrica

10 days ago
"የዜሮ እዳ ባለቤቶች"
#ethiopia | በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) በኩል የሚሰጡ የብድር አቅርቦት እና የፋይናንስ ድጋፍ ለብዙ አፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ነው።
2026 ከተቋሙ አነስተኛ የብድር እዳ ያለባቸው የአፍሪካ ሀገራት ዝርዝር ይፋ ሆኗል።
እንደ አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ወቅታዊ መረጃ አነስተኛ የብድር እዳ ካለባቸው ሀገራት መካከል በመጀመሪያው ተሰልፈው የሚገኙት በድርጅቱ አሰራርና አጠራር መሠረት የዜሮ እዳ ባለቤት የሆኑት ሀገራት ናቸው።
በዚህም ቦትስዋና፣ ሊቢያ፣ ኤርትራ፣ አልጄሪያ፣ ናይጄሪያ እና ሞሪሸስ ከIMF ጋር አሁናዊ የብድር እዳ የሌለባቸው ሀገራት በመሆን የዝርዝሩን አናት ይዘዋል።
በሌላ በኩል ከተቋሙ ጋር ንቁ የብድር ፕሮግራም እያካሄዱ ነገር ግን በዝቅተኛ የብድር መጠን ዝርዝር ውስጥ የተካተቱት 10 የአፍሪካ ሀገራትም አሉ።
ሌሶቶ፣ ኤስዋቲኒ፣ ጂቡቲ፣ ኮምሮስ፣
ሳኦ ቶሜ ፕሬንስፔ፣ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ጊኒ ቢሳዎ፣ኬፕ ቨርዴ፣ ሲሸልስ እና ቡሩንዲ ከድርጅቱ አነስተኛ የብድር መጠን ያለባቸው የአፍሪካ ሀገራት ናቸው ተብሏል።
አነስተኛ የብድር እዳ ካለባቸው ሀገራት መሀከል አብዛኞቹ ደሴትና አነስተኛ የህዝብ ቁጥር ያላቸው ሀገራት ናቸው።
የIMF እዳ አነስተኛ መሆኑ ሀገራቱ የራሳቸውን የኢኮኖሚ ፖሊሲ በነጻነት ለመቅረጽና ከውጭ ጫና ለመጠበቅ ትልቅ እድል እንደሚፈጥርላቸው ነው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የሚናገሩት።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #imf #debt #economi

13 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ማሂ ኤል-ዲን ሳሌም፣ አሜሪካ፣ ብሪታንያ እና የአውሮፓ ኅብረት በሀገራቸው ላይ የጣሉት ማዕቀብ ግቡን የማያሳካ "የፖለቲካ መሣሪያ" መሆኑን ገለጹ። ሚኒስትሩ በወቅታዊ የሱዳን ጉዳዮች ላይ በሰጡት ሰፊ መግለጫ፣ በሱዳን ጦርነት ውስጥ የውጭ ኃይሎች እጅ እንዳለበት በተጨባጭ መረጋገጡን እና ከጦርነቱ በኋላ የሀገሪቱ ዲፕሎማሲ የተለየ መልክ እንደሚኖረው አስታውቀዋል።
አምባሳደር ማሂ ኤል-ዲን እንዳብራሩት፣ በሱዳን ጉዳይ የውጭ ሀገራት ጣልቃ ገብነት መኖሩን የሚነሱት ጉዳዮች ክስ ሳይሆኑ በተጨባጭ መረጃ የተረጋገጡ እውነታዎች ናቸው። ለአብነትም በአሜሪካ የሚገኘው የዬል ዩኒቨርሲቲ የሳተላይት መረጃዎችን በመጠቀም እንደ ኢትዮጵያ ባለ ቀጣና ውስጥ የጦር ካምፖች መቋቋማቸውን ማረጋገጡን፣ እንዲሁም እንደ ዋሽንግተን ፖስት ያሉ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጉዳዩን መዘገባቸውን አስታውሰዋል። ሚኒስትሩ አክለውም ኃይሎቹ እና ቅጥረኛ ተዋጊዎች ከቻድ፣ ከምስራቃዊ ሊቢያ (በሀፍታር ቡድን በኩል)፣ አልፎ ተርፎም ከኮሎምቢያ ሳይቀር ድንበር አቋርጠው ወደ ካርቱም እየገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል። በደቡብ ሱዳን በኩልም መንግሥት ቀጥተኛ ሚና ባይኖረውም፣ ሕገ-ወጦች እና አማፂያን በሌላ መንገድ ወደ ሱዳን እየገቡ መሆኑን ጠቁመዋል።
ምንም እንኳን አንዳንድ ጎረቤት ሀገራት ሚሊሺያዎችን እና ቅጥረኛ ተዋጊዎችን ቢያስተባብሩም፣ ሱዳን ግን ታሪክ ያላት፣ የጎለመሰች እና በመልካም ጉርብትና የምትታወቅ ሀገር በመሆኗ እስከ አሁን ድረስ ከእነዚህ ሀገራት የሚመጡ ስደተኞችን በክብር እያስተናገደች እንደምትገኝ አብራርተዋል። በሌላ በኩል፣ በሱዳን ላይ ለተቃጣው ፈተና ከጎናቸው ለቆሙት እንደ ኤርትራ እና ግብፅ ላሉ እህትማማች ሀገራት የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ጦርነቱን ተከትሎ የሱዳን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ላይ ትልቅ ለውጥ እንደሚደረግ ያረጋገጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ ከጦርነቱ በኋላ የሱዳን ዲፕሎማሲ የተለየ መልክ እንደሚኖረው እና የሀገራትን አቋም በድጋሚ መገምገም ግድ እንደሚል ተናግረዋል። "ማነው ከእኛ ጋር የቆመው? ማነው ከዚህ ሚሊሺያ ጋር በመሆን በሱዳን ህዝብ ላይ የቆመው? የሚለውን ቅርብም ሆኑ ሩቅ ያሉ ሀገራትን አቋም መገምገም አለብን" ብለዋል።
የሱዳን ህዝብ በለጋስነቱና በመቻቻል የሚታወቅ፣ እንዲሁም በየትኛውም ሀገር ላይ ጥቃት ሰንዝሮ የማያውቅ ሰላማዊ ህዝብ መሆኑን በመጥቀስ፤ በአሁኑ ወቅት በማያሻማ መልኩ በህዝቡ ላይ የተከፈተበት ጦርነት ግን የሁሉንም ሱዳናዊ ህይወት፣ ዘመድ፣ ንብረት፣ ትምህርት እና የህክምና አገልግሎት ያመሰቃቀለ ዘግናኝ ጥቃት በመሆኑ፣ ከዚህ እውነታ አንፃር ሀገሪቱ የዲፕሎማሲ ግንኙነቷን እንደገና ማስተካከል እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

17 days ago
አሜሪካ ወደ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የ«አትሂዱ» ጥብቅ መመሪያ አስተላለፈች
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም ሀገራትን የፀጥታ ሁኔታ መነሻ በማድረግ በሚያወጣው መመሪያ፣ በርካታ የአፍሪካ ሀገራትን በከፍተኛው የደረጃ 4 የጉዞ ማስጠንቀቂያ ዝርዝር ውስጥ አስፍሯል።
ዋሽንግተን የራሷ ዜጎች ወደነዚህ ሀገራት ፍጹም ጉዞ እንዳያደርጉ ያሳሰበችው በእነዚህ ቀጠናዎች ባለው እጅግ አሳሳቢ የፀጥታ ችግር፣ የሽብርተኝነት ስጋት፣ የእርስ በርስ ግጭቶች፣ የታጠቁ አማፂያን ጥቃት እና ለአሜሪካ ዜጎች የሚሰጠው የቆንስላ ወይም የድንገተኛ ጊዜ ድጋፍ እጅግ ውስን በመሆኑ ነው።
በዚህ የዩናይትድ ስቴትስ የ«አትሂዱ» ጥብቅ መመሪያ ውስጥ ከተካተቱት የአፍሪካ ሀገራት መካከል ቡርኪና ፋሶ፣ ሊቢያ፣ ማሊ፣ ኒጀር፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳንና ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በዋናነት የሚጠቀሱ ሲሆን፣ እንደ ቻድ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያሉ ሀገራት ደግሞ በተለይ ከጎረቤት ሀገራት ጋር በሚያገናኟቸው ድንበሮችና የተወሰኑ ከፍተኛ ስጋት ያለባቸው ግዛቶቻቸው ላይ ተመሳሳይ የደረጃ 4 እገዳ ተጥሎባቸዋል።
በሌላ በኩል ዩጋንዳ በደረጃ 3 (Reconsider Travel ወይም ጉዞን መልሶ ማሰብ) ስር የምትገኝ ሲሆን፣ ዜጎች ወደ ሀገሪቱ ከመጓዛቸው በፊት በወንጀል እና በሽብርተኝነት ስጋቶች ዙሪያ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተመክሯል።
ይህ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየጊዜው የሚሻሻለው የደረጃ 4 የጉዞ ማስጠንቀቂያ ከአፍሪካ ውጭ እንደ ሩሲያ፣ ዩክሬን፣ አፍጋኒስታን፣ ሰሜን ኮሪያ፣ የመን፣ ሶሪያ፣ ቬንዙዌላ፣ ኢራን እና ጋዛን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የጦርነትና የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ያሉ የዓለማችን አካባቢዎችንም ያጠቃልላል።
Seledadotio

Sponsored by
Surafel
23 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የግብፁ ፕሬዝደንት አልሲሲ ለቅሶ ለመድረስ ኳታር ገቡ፡፡ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትላንት ወደዶሀ ተጉዘው በአሚር ሼክ ሀማድ ቢን ከሊፋ አልታኒ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን መግለፃቸው ይታወሳል፡፡ ዛሬ ደግሞ የግብፁ ፕሬዝደንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በስፍራው ተገኝተው ለቅሶ ደርሰዋል፡፡
በዛሬው እለት በርካታ የአለማችን መሪዎች ዶሀ በመግባት በአሚሩ ሞት ሀዘናቸውን የገለፁ ሲሆን ከእነዚህ መካከል የሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ፣ የማልዲቭስ ፕሬዝደንት መሀመድ ሚዩዙ፣ የካዛኪስታን ፕሬዝደንት ካሳይም ጆማርት ቶካይቭ፣ የሞሮኮ ጠቅላይ ሚኒስትር አዚዝ አካኖች፣ የኢራቅ ፕሬዝደንት ናዚር አሚዲ፣ የሊቢያ አንድነት መንግስት ፕሬዝደንት አብዱል ሀሚድ ድቢባህ፣ የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋፍ ሳላም፣ የሶሪያ ፕሬዝደንት አህመድ አልሻራና የፊፋ ፕሬዝደንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ይገኙበታል፡፡

25 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ትንሿን የባህረ ሰላጤዋን ሀገር በዓለማችን ላይ እጅግ ባለጸጋ እና ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ ወደ ሆነች ግዙፍ ሀገርነት የቀየሩት የቀድሞው የኳታር አሚር ሼክ ሐማድ ቢን ኻሊፋ አል ታኒ በ74 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ማራኪ ስብዕና እና ወዳጃዊ አቀራረብ የነበራቸው እኚህ "አባት አሚር"... የዘመናዊቷ ኳታር እውነተኛ አርክቴክት ተብለው በሰፊው ይወደሳሉ።
እ.ኤ.አ በጥር 1952 በዶሃ የተወለዱት ሼክ ሐማድ፣ ከብሪታንያው ሮያል ሚሊተሪ አካዳሚ ከተመረቁ በኋላ የኳታር የጦር ኃይሎች አዛዥ በመሆን አገልግለዋል። በ1977 አልጋ ወራሽ እና የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙ ሲሆን፣ በሰኔ 27፣ 1995 ደግሞ የሀገሪቱን የስልጣን መንበር በይፋ ተረከቡ። ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ሀገራቸው ያላትን እጅግ ሰፊ የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት በመጠቀም ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ማሻሻያዎችን ያካተተ ትልቅ የልማት ራዕይ ነድፈው በተግባር አሳይተዋል።
በሳቸው የስልጣን ዘመን የኳታር አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ከ24 እጥፍ በላይ በሚያስገርም ፍጥነት አድጓል። በተለይም ከኖርዝ ፊልድ የተገኘው ምርት፣ ኳታርን እ.ኤ.አ በ2006 የዓለማችን ትልቋ የፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ (LNG) ላኪ ሀገር እንድትሆን አድርጓታል። በመንግስት መረጃ መሰረት... ይህች ትንሽ ሀገር በአጭር ጊዜ ውስጥ የማምረት አቅሟን በዓመት ወደ 77 ሚሊዮን ቶን ማድረስ ችላ ነበር።
የሼክ ሐማድ የአመራር ዘመን በለውጥ የተሞላ ነበር። የኳታር ፋውንዴሽን መመስረት፣ በ1996 የዓለምን የሚዲያ ትኩረት የሳበው የአልጀዚራ የዜና ቻናል መከፈት፣ በ2004 የመጀመሪያው ቋሚ የኳታር ህገ-መንግስት መጽደቅ እና ሴቶች የመምረጥና የመመረጥ መብት ያገኙበት የማዘጋጃ ቤት ምርጫ መጀመር የሳቸው ትሩፋቶች ናቸው። ከዚህም በላይ ኳታር በ2022ቱን የፊፋ ዓለም ዋንጫ የማስተናገድ መብት እንድታገኝ ያደረጉት ጥረት፣ አንዲት አረብ ሀገር ይህንን ታላቅ ውድድር ስታስተናግድ በታሪክ የመጀመሪያው እንዲሆን አስችሏል።
ሼክ ሐማድ ኳታርን የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ማዕከል እና የሰላም አደራዳሪ እንድትሆን ሰፊ ራዕይ ነበራቸው። በሱዳን ዳርፉር ክልል፣ በሊባኖስ የውስጥ ትርምስ፣ እንዲሁም በፍልስጤሙ ሃማስ እና ፋታህ መካከል ለተፈጠረው ስምጥ ኳታር ቁልፍ አደራዳሪ ሆና አገልግላለች። ስልጣን ከመልቀቃቸው በፊትም በአሜሪካ ጥያቄ መሰረት ታሊባን በኳታር ጽህፈት ቤት እንዲከፍት አድርገዋል፤ ይህም በመጨረሻ ኔቶ እና አሜሪካ በ2021 ከአፍጋኒስታን ለወጡበት ታሪካዊ ድርድር በር ከፋች ሆኖ አልፏል።
በአረብ ጸደይ ወቅት ኳታር ከህዝባዊ አመጾች ጎን ከቆሙ ጥቂት ሀገራት አንዷ ነበረች። በግብፅ፣ አልጀዚራ የስርጭት እገዳን ጥሶ የዲሞክራሲ ደጋፊዎችን ድምፅ ለዓለም አሰምቷል። በሶሪያ፣ ሼክ ሐማድ መጀመሪያ ላይ ፕሬዝዳንት ባሻር አል አሳድ ስልጣን እንዲለቁ ለማሳመን ቢሞክሩም፣ የመንግስት ኃይሎች ሰልፈኞችን መግደላቸውን ተከትሎ ዶሃ ከደማስቆ ጋር ያላትን ግንኙነት አቋርጣለች። በሊቢያ ደግሞ የረጅም ጊዜ መሪ የነበሩትን ሙአመር ጋዳፊን ከስልጣን ያወረደውን የኔቶ ወታደራዊ ዘመቻ በመደገፍ ኳታር ትልቅ ሚና ተጫውታለች።
እ.ኤ.አ ሰኔ 25፣ 2013 ሼክ ሐማድ ባልተለመደ ሁኔታ እና በፍጹም ፈቃደኝነት ስልጣናቸውን ለ33 ዓመቱ ልጃቸው ለሼክ ታሚም ቢን ሐማድ አል ታኒ አስረከቡ። እንዲህ ዓይነቱ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በመካከለኛው ምስራቅ እጅግ ያልተለመደ እና ብርቅ ክስተት ነበር። ስልጣን ሲለቁም "ወጣቱ አመራር ባንዲራውን ከፍ አድርጎ ወደሚያውለበልብበት አዲስ ዘመን ስትገቡ፣ የወደፊቱ ጊዜ በፊታችሁ አለ" በማለት ለሀገሪቱ ልጆች ተስፋ ሰጥተዋል።
ከሁሉም በላይ ግን ለልባቸው እጅግ ቅርብ የነበረው የፍልስጤም የነጻነት ትግል ነው። ከዓመታት በኋላ የጋዛ ሰርጥን በመጎብኘት የመጀመሪያው የሀገር መሪ የሆኑት እሳቸው ነበሩ። ለፍልስጤም ህዝብ ላደረጉት ድጋፍ ክብር ሲባል፣ በጋዛ እና በደቡብ ሊባኖስ የሚገኙ ከተሞች በስማቸው ተሰይመዋል። ሼክ ሐማድ ቢን ኻሊፋ አል ታኒ ያሳደሩት ተጽዕኖ ከኳታር ድንበር እጅግ የራቀ ነበር፤ ህልፈታቸውም ልክ እንደ ህይወት ዘመናቸው ሁሉ በመላው ቀጠናው እና ከዚያም ባለፈ በዓለም ዙሪያ በጥልቅ የሚታወስ ይሆናል።

27 days ago
ግብፅ እና ኢትዮጵያ ሳይስማሙ ቀሩ
በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ለአራት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው 22ኛው የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር የሚኒስትሮች ምክር ቤት እና 37ኛው የአስተባባሪ ኮሚቴ አስቸኳይ ልዩ ጉባዔ ዛሬ ተጠናቋል።
ጉባዔው ያስፈለገው ግብፅና ሊቢያ ጨምሮ 13 አባል ሀገራት ያሉት ትስስሩ የመበታተን አደጋ የተጋረጠበት በመሆኑ ነው፡፡
አባል ሀገራቱን ከመበታተን ለመታደግ የህግ ማዕቀፎችን በማሻሻልና ማጠናከር ማስፈለጉን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ገልጸዋል።
በጉባዔው አዲስ የሚመሰረተው የኤሌክትሪክ ኃይል የገበያ ማዕከል ዋና መቀመጫን ለመወሰን ውይይት ተደርጓል፡፡
በዚህ አጀንዳ ኢትዮጵያ ከድርጅቱ አባል ሀገራት ብቸኛ የኃይል አቅራቢ እንደመሆኗ ለአራት ቀናት በዘለቀው የትስስሩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ከፍተኛ ሙግት ማካሄዱ ተገልጿል፡፡
በተለይም ከግብፅ ጋር የገበያ ማዕከሉ ኢትዮጵያ መሆን አለበት በሚለው ሃሳብ ከፍተኛ ሙግት መደረጉን ኢንጂነር ሃብታሙ ገልፀዋል።
በዚሁ ጉዳይ የግብፅ ተወካዮች ማዕከሉ ወደ ካይሮ ካልሆነ በሚል የያዙት አቋም ከኢትዮጵያ ጋር ከመግባባት ሳይደርሱበት ጉባዔው ተጠናቋል።

1 month ago
የሊቢያው ኦላ ኢነርጂ የቶታልኤነርጂስን የኢትዮጵያ ንብረቶች በሙሉ ጠቀለለ
የሊቢያው ኦላ ኢነርጂ ግሩፕ በኢትዮጵያ የሚገኙትን የፈረንሳዩ ቶታልኤነርጂስ ንብረቶች በሙሉ ለመጠቅለል የሚያስችለውን የግዢ ስምምነት በፓሪስ ተፈራረመ።
ይህ ስምምነት ኦላ ኢነርጂ በኢትዮጵያ የነዳጅ ማከፋፈል ገበያ ውስጥ ትልቁ የውጭ ኩባንያ ያደርገዋል።
ይህ ግዙፍ የአክሲዮን ግዢ በኢትዮጵያ የሚገኙ ወደ 120 የሚጠጉ የነዳጅ ማደያዎችን፣ የ13 ሺህ ሜትር ኩብ አቅም ያለውን የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናል እና ተያያዥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ያጠቃልላል።
በስምምነቱ ላይ የሊቢያ ዘይትና ጋዝ ሚኒስትር ከሊፋ አብዱልሳዲቅ እና የቶታልኤነርጂስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፓትሪክ ፑያን ጨምሮ የሁለቱም ወገኖች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ግዢው ሊቢያ በአፍሪካ አህጉር ያላትን የኢኮኖሚ ተፅዕኖ እና የውጭ ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት የምታደርገውን ጥረት የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል።

በ #ሱዳን በተፈጸሙ አስከፊ ወንጀሎች ውስጥ እጃቸው አለበት የተባሉ ከፍተኛ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣የ #ኢትዮጵያ እና የቀጠናው ባለሥልጣናት ላይ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ምርመራ እንዲደረግ ተጠየቀ‼️
ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች እና የሕግ ድርጅቶች ጥምረት፤ በሱዳን ዳርፉር ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ለተፈጸሙ አስከፊ ወንጀሎች ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ረገድ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ፣ የኢትዮጵያን ጨምሮ የቻድ፣የሶማሊያ፣ የሊቢያ እና የኬኒያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ምርመራ እንዲያደርግ ጠየቀ።
ሚድል ኢስት አይ ባወጣው ዘገባ መሠረት፤ ይህ ጥሪ ሰኞ ዕለት የቀረበው፤ ራውል ዋለንበርግ የሰብአዊ መብቶች ማዕከል (RWCHR) ከተለያዩ የሕግ፣ የምርመራ እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት ጋር በመሆን የቀረበ ነው። አቤቱታው የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዓቃቢያነ ሕግ የውጭ አገር ባለሥልጣናትና አሸማጋዮች በሱዳን ተፋላሚ ወገኖች የተፈጸሙ ወንጀሎችን ሆን ብለው በማገዝ ወይም በማበረታታት ረገድ የተሳተፉ መሆኑን እንዲመረምሩ ይጠይቃል።

ኢትዮጵያ፣ አውሮፓ ኅብረት ወደ አገራቸው ሊባረሩ የማይችሉ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ለመላክ ከመረጣቸው አገራት መካከል አንዷ መኾኗን ሂውማን ራይትስ ዎች ገለጠ።
ተቋሙ፣ ኅብረቱ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሦስተኛ አገራት ለመላክ አዲስ ስልቶችን እየቀየሠ ይገኛል በማለት ወቅሷል።
ጀርመን፣ ኦስትሪያ፣ ዴንማርክ፣ ግሪክ እና ኔዘርላንድስ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ለመላክ ከመረጧቸው አገራት መካከል፣ ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ቱኒዚያ፣ ግብጽ፣ ሊቢያ እና ሞሪቴኒያ እንደሚገኙበት ተቋሙ ጠቅሷል።
ተቋሙ፣ ተቀባይ አገራት የጥገኝነት ጠያቂዎቹን ሰብዓዊ መብት ያከብሩ፣ ወደ ትውልድ አገራቸው ይመልሷቸው ወይም ያስሯቸው እንደኾነ ግልጽ አይደለም ሲል ስጋቱን ገልጧል።
የኅብረቱ አገራት ይህንኑ እቅድ እንዲተውት ያሳሰበው ተቋሙ፣ ይህ ካልሆነ ግን እቅዱ ተግባራዊ ከመኾኑ በፊት ኅብረቱ ቢያንስ በተቀባይ አገራት የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ጥብቅ ግምገማ እንዲያደርግ እቅዱን የሚቃወሙት የፈረንሳይና ስፔን መሪዎች ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቋል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ አዲስ ሚኒስትር መሾማቸው ተሰማ፡፡ ከአስመራ ዛሬ እንደተሰራጩ መረጃዎች ከሆነ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ አዲስ የዞን መስተዳድሮች ሚኒስትር ሾመዋል፡፡ የተሾሙትም አምባሳደር አብዱላህ ሙሳ ናቸው፡፡
በኤርትራ ውስጥ የዞን መስተዳድር ሚኒስትር የሚለው ሹመት ኦፊሺያል ባልሆነ መንገድ ምክትል ፕሬዝደንት እንደማለት የሚቆጠር ነው፡፡ አምባሳደር አብዱላህ ከዚህ ቀደም በሊቢያ የኤርትራ አምባሳደር የነበሩ ሲሆን ከዚህ ሹመታቸው በፊት የአንሰባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ሲሰሩ የነበሩ ናቸው፡፡
በኤርትራ ውስጥ የአዳዲስ ሚኒስትሮች ሹመት በይፋ የማይገለፅ ሲሆን አምባሳደሩ ይህንን ሹመት እንዳገኙ የታወቀውም የመንግስት ሚዲያዎች ዛሬ ባሰራጩት ዜና ነው፡፡ ሚዲያዎቹ በዜናቸው ላይ የዞን መስተዳድር ሚኒስትር የሆኑት አምባሳደር አብዱላህ ከዞን አመራሮችና ከትምህርት ሚኒስትር ሀላፊዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ዘግበዋል፡፡

የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ሶማሊያ ዜጎች ወደ ምሥራቅ ሊቢያ ግዛት እንዳይገቡ ታገዱ።
ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ጨምሮ ወደ አውሮፓ መሻገር የሚፈልጉ የአራቱ አገራት ፍልሠተኞች በሊቢያ በኩል በሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት እንደሚያልፉ ይታወቃል።
የምሥራቅ ሊቢያ ባለሥልጣናት ይህን እገዳ የጣሉት፣ የውጭ ዜጎች ወደ አገሪቱ የሚገቡበትን ሁኔታ ለመቀየር በማስፈለጉ እንደሆነ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
እገዳው፣ ዲፕሎማቶችን፣ የቆንስላ ሠራተኞችንና ቤተሰቦቻቸውን እንዲኹም የቅጥር ፍቃድ ያላቸው በትምህርትና ሕክምና ዘርፍ የተሠማሩ የአገራቱን ሠራተኞች እንደማይመለከት ተገልጧል።
ባሁኑ ወቅት 900 ሺሕ ያህል የውጭ ዜግነት ያላቸው ፍልሠተኞች ሊቢያ ውስጥ እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።

የሊቢያ መንግሥት ባለሥልጣናት የአራት አጎራባች የአፍሪቃ ሃገራት ዜጎች ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ አገዱ
የምሥራቅ ሊቢያ መንግሥት ባለሥልጣናት የአራት አጎራባች የአፍሪቃ ሃገራት ዜጎች ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ አገዱ። የባለሥልጣናቱ እርምጃ በምዕራባዊ የሊቢያ የባሕር ወደብ በኩል ወደ አውሮጳ ለመሻገር የሚያልሙ ተሰዳጆችን ቁጥር ለመቀነስ ያለመ መሆኑ ተገልጿል። በሊቢያ ባለሥልጣናት እገዳ የተጣለባቸው የሱዳን፤ የኤርትራ፣ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ዜጎች መሆናቸው ተገልጿል። የሊቢያ የባሕር ወደብ የተሻለ ሕይወትን አልመው ወደ አውሮጳ ለመሰደድ የሚሞክሩ በርካታ የአፍሪቃ ተሰዳጆች የሚያዘወትሩት መሸጋገሪያ መስመር ነው።
ተሰዳጆቹ በሕገወጥ ሰው አሸጋጋሪዎች አማካኝነት ለጉዞ አስተማማኝ ባልሆኑ ትናንሽ ጀልባዎች ከመጠን በላይ ተጠቅጥቀው የሚሳፈሩ ሲሆን ባሕር ላይ በሚያጋጥመው አደጋ በሺህዎች የሚቆጠሩት ካሰቡበት ሳይደርሱ ሕይወታቸው እንደሚቀጠፍ በየጊዜው ይዘገባል። ትናንት ይፋ የተደረገው እገዳ የሱዳን፤ የኤርትራ፤ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ተሰዳጆች በየብስም ሆነ በባሕር እና በአየር ወደ ሊቢያ ግዛት እንዳይገቡ ከልክሏል። መግለጫው አክሎም ክልከላው ዲፕሎማቶች፤ የጤና እና የትምህርት ዘርፍ ሠራተኞችን እንደማይመለከት አስታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ ከሌላ ሃገር ወደ ሊቢያ የሚላኩ ስደተኞችን ጉዳይ በተመለከተ በምሥራቅ እና ምዕራብ የሊቢያ መንግሥታት መካከል ላለፉት ወራት ውጥረት አስነስቷል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንደሚለው ስደተኞች ላይ በተደረገው ክትትል በሺህዎች የሚቆጠሩ በዚሁ ምክንያት ታስረዋል። የተመድ መረጃ እንደሚያመለክተው፤ ሊቢያ ውስጥ ከ900 ሺህ በላይ ስደተኞች ይገኛሉ። ከእነዚህ መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት የሱዳን ዜጎች ናቸው። አብዛኞቹ ስደተኞች ወደ አውሮጳ ለመሻገር የሚፈልጉ ቢሆንም ስደተኞችን የጫኑ ጀልባዎች በባሕር ላይ ቃኚዎች እየተያዙ ወደ ሊቢያ እንዲመለሱ እየተደረገ ነው። ስደተኞቹ በሊቢያ መንግሥታት እስር ቤቶች የሚያዙ ሲሆን እንግልት፤ የግዳጅ የጉልበት ሥራ፤ ድብደባ፣ አስገድዶ መድፈር እና ማሰቃየት እንደሚፈጸምባቸው ተገልጿል። የተመድ መርማሪ ኮሚሽንም ስደተኞቹ ላይ የሚደርሰውን እንግልት በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል ነው ብሎታል።
DW Amharic

ቶታል ነዳጅ ማደያ ኢትዮጵያን ለቆ ሊወጣ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ ከ75 አመታት በላይ በነዳጅ ችርቻሮ ንግድ ላይ ተሰማርቶ የቆየው ቶታል ኢነርጂስ ከኢትዮጵያ ለመውጣት ማቀዱ ተገለፀ፡፡
በመላው ኢትዮጵያ ወደ120 ያህል ማደያዎች ያሉት ይህ ተቋም ንብረቱን በሙሉ ለኦላ ኢነርጂ ወይንም ለቀድሞው ኦይልሊቢያ በሽያጭ ለማስተላለፍ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑ ተዘግቧል፡፡
አፍሪካ ቢዝነስ ባቀረበው ዘገባ ሁለቱ ድርጅቶች በሽያጩ ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልፆ በምን ያህል ዋጋ ግብይቱ እንደተከናወነ ያለው ነገር የለም፡፡
ቶታል ኢነርጂስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከብራዚል፣ ፓኪስታንና አንዳንድ የአውሮፓ አገራት የነዳጅ ማደያዎቹን ሸጦ የወጣ ሲሆን ይህ እርምጃውም የዚህ አካል እንደሚሆን ተገምቷል፡፡

ቶታል ነዳጅ ማደያ ከኢትዮጵያ ጠቅልሎ ሊወጣ መሆኑ ተሰማ
#ethiopia | የፈረንሳዩ ግዙፍ የነዳጅ ኩባንያ ቶታል ኢነርጂስ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን የነዳጅ ማደያዎች ለኦላ ኢነርጂ በመሸጥ ከሀገሪቱ የነዳጅ ችርቻሮ ገበያ ሊወጣ መሆኑ ተዘግቧል።
'ብር ሜትሪክስ' እንዳስነበበው ሁለቱ ተቋማት ወደ 120 የሚጠጉ የቶታል ነዳጅ ማደያዎችን ሽያጭ በተመለከተ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። ሆኖም የሽያጩ የገንዘብ መጠን እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን ኩባንያዎቹም ስምምነቱን እስካሁን በይፋ አላረጋገጡም።
ከፈረንጆቹ 1950 ጀምሮ በኢትዮጵያ ምርትና አገልግሎቱን ሲያቀርብ የቆየው ቶታል ኢነርጂስ ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው በዓለም አቀፍ ደረጃ የችርቻሮ ገበያውን ለማስተካከል ከያዘው ስትራቴጂ አኳያ መሆኑ ተጠቁሟል።
ይህ ሽያጭ በሕግ አግባብ ጸድቆ ከተጠናቀቀ ቀድሞ ‘ኦይልሊቢያ’ በመባል የሚታወቀውና በመላው አፍሪካ ሰፊ ተደራሽነት ያለው ኦላ ኢነርጂ በኢትዮጵያ የነዳጅ ሥርጭት ገበያ ላይ ያለውን ድርሻና አቅም በእጅጉ ያጠናክረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 months ago
ወደ እንግሊዝ ሲያቀኑ የነበሩ 300 ስደተኞች ታግተው ኩላሊታቸዉ እንደሚወጣ እንደተዛተባቸዉ ተሰማ
ባለፈው ክረምት ወደ እንግሊዝ ሲያቀኑ የነበሩ ከ300 በላይ ስደተኞች አፈና፣ድብደባ እና በግዳጅ የአካል ክፍሎችን እንደሚነጠቁ ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው ተሰምቷል።ወጣቶቹ ከኢራቅ ኩርዲስታን የመጡ ሲሆን ሁሉም በሊቢያ በሚኙ ሚሊሻዎች ከእያንዳንዳቸው ቤተሰቦቻቸው 5,000 ዶላር ለማስለቀቅ የተጠየቁ ሲሆን ገንዘቡን በፍጥነት ካልከፈሉ ኩላሊቶቻቸዉን እንደሚያጡ ተዝቶባቸዉ ነበር፡፡
ከእስር የተፈቱትን አንዳንድ ታጋቾች የግዳጅ ስራዎች መፈጸማቸውንም የሚያሳዩ የፎቶ ማስረጃዎችን አጋርተዋል፡፡የቀድሞዎቹ ምርኮኞች የደረሰባቸዉን የስቃይ ማስረጃ አሳይተዋል፡፡ ወደ 180 የሚጠጉ ሰዎች በአንድ ክፍል ውስጥ በጠባብ ሁኔታ ውስጥ እንደቆዩ ተናግረዋል፡፡ቢያንስ አንድ ታጋች የተገደለ ሲሆን ምን ያህሉ በምርኮ እንደሚቀሩ የታወቀ ነገር የለም።
ሚሊሻዎቹ በሊቢያ በኩል ወደ ሜዲትራኒያን ባህር ዳርቻ ድረስ ፍልሰተኞቹ እየመራቸው ነበር ተብሏል። ሆኖም የስደተኞቹን ጉዞ ካደራጀው ከኢራቅ የኩርድ ህዝብ-ህገ-ወጥ አዘዋዋሪ ኖህ አሮን ጋር በክፍያ ላይ አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር።አሮን አሁን በፈረንሳይ በተለያዩ የገንዘብ ማጭበርበር እና የኮንትሮባንድ ወንጀሎች የ10 አመት እስራት ተፈርዶበታል።
Via_dagu

የአሮጌው ዘመን አዙሪት ለትውልዱ አይመጥንም!!
******************
የሰው ልጅ የሥልጣኔ ጫፍ ላይ ለመድረስ የሚያደርገው አድካሚ ጉዞ፣ በሐሳብ ልዕልና፣ በምክንያታዊነት፣ በሰላማዊ መስተጋብር፣ እንዲሁም በምርምርና ቴክኖሎጂ ላይ የተገነባ ነው። ፖለቲካዊ ፍላጎትን በጉልበት ለማስፈጸም መሞከር፣ ከሰለጠነ ውይይት ይልቅ የጠመንጃን ቋንቋ መምረጥ፣ ንጹሐንን በመግደልና ተቋማትን በማኮላሸት ስጋትን ማንገስ የትላንቱ የጨለማ ዘመን እንጂ፣ የዛሬውና የነገው የፖለቲካ ስልት ሊሆን ከቶ አይችልም።
የሕዝብን የጠራ ፍላጎት በጠመንጃ አፈሙዝና በፍርሃት ቆፈን ሥር አድርጎ ለማሸነፍ የሚኬድበት አቋራጭ ጎዳና፣ ለዚህ ዘመን የነቃ እሳቤ የማያብር ያረጀና ያፈጀ ስልት ነው። የዛሬው ትውልድ ይህንን የጥፋት አዙሪት በጽኑ አመክንዮ እና በነቃ ተሳትፎው እያመከነው ይገኛል።
የታሪክ ጠባሳ እና የተማርነው እውነት
ያለፉት ዘመናት የታሪክ ማኅደሮቻችንን አቧራ ስናራግፍ፣ ኢትዮጵያ በጠመንጃ ፖለቲካ እና በኃይል እርምጃ ያተረፈችው መቆሚያ የሌለው የደም አበሳ እና የንብረት ውድመት እንጂ፣ ለኩራት የሚበቃ የሥልጣኔ ትሩፋት አልነበረም።
ፖለቲካዊ ልዩነቶችን በሰለጠነ የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት ከመፍታት ይልቅ፣ በየቋጥኙ ሥር መሽጎና ጦር መዝዞ የራስን እውነት በሌሎች ላይ ለመጫን የተደረጉ አፍራሽ ድርጊቶች ሀገሪቱን ለዘመናት ወደ ኋላ ጎትተዋታል። በዚህ ስሑት መንገድ ብዙ ተዳምተናል፣ እጅግ ውድ የሆነ የሰው ሕይወት ገብረናል፤ ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገንም ክፉኛ ጎድቶታል።
የዓለም ተሞክሮ፡ ከጥፋት ወደ ሐሳብ ልዕልና
ዓለም የደረሰችበትን የፖለቲካ ሥልጣኔ ስንቃኝ፣ ያደጉትና የበለጸጉት ሀገራት የደረሱበት የከፍታ ማማ ምስጢር የጠመንጃን አፈሙዝ ዘግተው ሐሳብን በማንገሳቸው መሆኑን እንረዳለን። እንደ ሶማሊያ፣ ሊቢያ እና የመን ያሉ ሀገራት፣ የፖለቲካ ፍላጎትን በኃይል ለማስገደድ በሞከሩ ጽንፈኛ ኃይሎች ሳቢያ ሀገረ መንግሥታቸው ፈርሶ (Failed State) ሕዝባቸው ለከፋ ስደትና መከራ ተዳርጓል።
ከእነዚህ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተሞክሮዎች የምንማረው አንድ ታላቅ እውነት ቢኖር፤ እውነተኛ የፖለቲካ አሸናፊነት የሚረጋገጠው የሕዝብን ልብ በበሳል ፖለቲካዊ ፕሮግራም እና በአሳማኝ ፖሊሲ በመማረክ እንጂ፣ አፈናን በመጠቀም አለመሆኑን ነው። የዘመኑ የኢትዮጵያ ትውልድ ይህንን የሰለጠነ ፖለቲካዊ ሒደት ጠንቅቆ ይገነዘባል፤ ሀገሩም ከተያያዘችው የሥልጣኔ እና የብልጽግና ጎዳና እንድትሰናከል አይፈቅድም።
ነባራዊው እውነታ እና የመንግሥት ጽኑ ጥረቶች
በአሁኑ የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ፣ መንግሥት የሕዝብን የሥልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ፣ ጠንካራና ገለልተኛ ተቋማትን ለመገንባት እና የዴሞክራሲ ሥርዓትን ለማጽናት በርካታ ወሳኝ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል። ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን በማቋቋም ዘመናትን የተሻገሩ ሀገራዊ የፖለቲካ ስብራቶችን ለመጠገን፣ እንዲሁም በቅርቡ የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በስኬት በማጠናቀቅ የሥልጣን ሽግግር ውሳኔ በድምጽ መስጫ ካርድ እንጂ በጥይት እንዳይሆን ሰፊ ጥረት አድርጓል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አሁንም የአሮጌው ዘመን እንደራሴ ነን ባዮች የራሳቸውን ፖለቲካዊ ፍላጎት በኃይል ለመጫን ይሞክራሉ። የሕዝብን ሰላማዊ ኑሮ ለማወክ ንጹሐንን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶችን በመፈጸም፣ እንዲሁም የዲጂታል ሚዲያዎችን በመጠቀም የሐሰት ትርክትን (Disinformation) በማሰራጨት ሕዝብን ከሕዝብና ከመንግሥት ለማጋጨት ይጥራሉ። ነገር ግን፣ "ውሸት ያሯሩጣል እንጂ አያደርስም" እንደሚባለው ጥልቅ አባባል፣ የእነዚህ ኃይሎች የሐሰት ፕሮፓጋንዳ እና የተንኮል ሴራ በጊዜ ሒደት ገመናው እየተገለጠ፣ በነቃው ሕዝብ ፊት እርቃኑን እየቀረ ይገኛል። መንግሥት እነዚህን የጥፋት ኃይሎች በሕግ አግባብ ከመመከት ባለፈ፣ ትዕግስትንና ሆደ ሰፊነትን መርሆው በማድረግ ለሰላም የዘረጋው እጅ፣ ለሀገር ግንባታ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ታላቅ ማሳያ ነው።
ትውልዱ ይህንን ሀገራዊ እውነት ጠንቅቆ ተረድቷል። አሁን ያለንበት የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ የትንሣኤ ዘመን፣ የቴክኖሎጂ ፈጠራና የመስፈንጠሪያ ዘመን እንጂ፣ ወደ ኋላ ተመልሰን በሽፍትነት የአሮጌውን ዘመን የጥፋት አዙሪት የምንለማመድበት ጊዜ አይደለም። ሀገረ መንግሥቱ ከሕዝቡ ጋር በመቀናጀት የሚያደርገውን የሕግ የበላይነት የማስከበር፣ ሰላምን የማረጋገጥ እና ልማትን የማፋጠን ጉዞ፣ አዲሱ ትውልድ በሙሉ አቅሙ ይደግፈዋል።
የፖለቲካ ፍላጎትን በጠመንጃ እና በሐሰት ትርክት ለማስፈጸም የሚደረገው ጥረት በመቃብር ያለ፣ ያለፈ ዘመን ትርክት ነው። ዛሬ ላይ የሐሳብ ልዕልና፣ የምክንያታዊነት እና የዴሞክራሲያዊ ውይይት ድምጽ ከፍ ብሎ እየተሰማ ነው። ትውልዱ የጥፋት ኃይሎችን አጀንዳ በማመከን፣ መንግሥት ለጀመረው ሀገረ መንግሥት ግንባታ፣ ለተቋማት ጥንካሬ እና ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ሒደት ጽኑ ዘብ በመቆም፣ የበለጸገች እና የተከበረች ኢትዮጵያን ወደፊት እያሻገረ ይገኛል። የአሮጌው ዘመን አዙሪት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተሰብሯል!
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
Ethiopian Broadcasting Corporation #ethiopia #ebc #ትውልድ

(ከተዋሕዶ ወርልድ) የአርሲ ተራሮች ለዘመናት የሰላም፣ የግብርና እና የአብሮነት ምልክት ሆነው ኖረዋል። የጠዋቱ ጸሐይ ሲወጣ የከብቶች ጩኸት፣ የእረኞች ዜማ እና የቤተ ክርስቲያን የደወል ድምፅ ተቀናጅተው መንፈስን የሚያድስ ተስፋን ይሰጡ ነበር። ዛሬ ግን... ዛሬ ከእነዚህ ተራሮች ጀርባ የሚወጣው ጭስ የዕጣን አይደለም፤ የቃጠሎ ነው። ዛሬ የሚሰማው ድምፅ የዝማሬ ሳይሆን የእንባ እና የዋይታ ነው። ከግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሺርካ እና በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች ላይ ያንዣበበው የሞት ጥላ፣ ንጹሐንን በግፍ ቀጥፏል፤ ታሪካዊ መቅደሶችንም ወደ አመድነት ቀይሯል።
ይህ የተዋህዶ ወርልድ ትንታኔ የቁጥሮች ድምር አይደለም፤ የ13 የከበሩ የሰው ልጆች ሕይወት መነጠቅ፣ የ101 ዓመት ታሪክ መቃጠል፣ እና የ280 ዜጎች በባዶ እጅ መሰደድ ታሪክ እንጂ። ይህ፣ ሃይማኖት እና ማንነትን መሠረት አድርጎ የሚፈጸም አክራሪነት የሰውን ልጅ ምን ያህል ወደ አውሬነት እንደሚቀይረው የሚያሳይ የዘመናችን ህያው ማሳያ ነው።
የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንን እናስበው። ለ101 ዓመታት ሙሉ፣ አባቶች እና እናቶች በደጃፉ ተንበርክከው ፈጣሪያቸውን ተማጽነዋል። በዚያ መቅደስ ውስጥ ስንቱ ተጠምቋል? ስንቱ ተክሊል አስሯል? ስንቱስ በጸሎት ተጽናንቷል? ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ የቆመው ይህ የጸጋ ቤት፣ የበርካታ ትውልዶች የእምነት ማህደር ነበር። ነገር ግን፣ ጥላቻ ታሪክን አያውቅም፤ ክፋት ቅድስናን አይረዳም። በአንድ ጀንበር፣ ያ ሁሉ ታሪክ፣ ያ ሁሉ የእንጨት ጠረንና የዕጣን መዓዛ፣ በጭካኔ እሳት ተበላ።
በሌላ በኩል ደግሞ የካራ ኩፍተና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ዕጣ ፈንታ ሌላ ልብ ሰባሪ ትዕይንት ነበር። ታጣቂዎች መቅደሱን ሲዘርፉ፣ አማኞች የራሳቸውን ሕይወት እና ንብረት ለማዳን አልተጣደፉም። ይልቁንም፣ መኖሪያ ቤታቸው እያዩት በእሳት ሲጋይ፣ የዕድሜ ልክ ጥሪታቸው፣ ከብቶቻቸውና ማሳቸው ሲዘረፍ፣ እነርሱ ግን ከሁሉ የሚያስበልጡትን የቤተ ክርስቲያኑን ጽላት (ታቦት) በደረታቸው አቅፈው በጨለማ ወደማያውቁት ስደት መጓዝን መረጡ።
ይህ ትዕይንት ወደ ኋላ መለስ ብለን የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪክ እንድናስታውስ ያደርገናል። እስራኤላውያን ታቦተ ጽዮንን ተሸክመው በበረሃ እንደተጓዙት ሁሉ፣ የአርሲ ምእመናንም አምላካቸውን በደረታቸው አቅፈው መከራውን ተቀበሉ።
ሞት በቁጥር ሲገለጽ ስሜት አይሰጥም፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ቁጥር ከጀርባው ቤተሰብ፣ ተስፋ እና ህልም አለው። በአጠቃላይ 13 ንጹሐን ኦርቶዶክሳውያን በግፍ ተገድለዋል።
የ80 ዓመቱን አቶ አማረ በላይነህን እንመልከት። እኚህ አረጋዊ በህይወት ዘመናቸው ስንት መንግስታትን አይተዋል? ስንት የሀገር መከራን አሳልፈዋል? በስተእርጅናቸው ዘመን ክፋት አላርፍ ብሎ አስጨናቂ ሞትን አመጣባቸው። የ70 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ የሆኑት አቶ ደምረው አበራ፣ አቶ ሐይሉ ንጉሴ እና አቶ ሰሙ አባይነህም እንዲሁ የዚህ ጭካኔ ሰለባ ሆነዋል። እነዚህ አባቶች ለሀገር ምርቃት እንጂ መርገም ያልነበሩ፣ በእምነታቸው ጸንተው የኖሩ የሰላም ሰዎች ነበሩ።
እንደነ እሸቴ ዳመና (42 ዓመት) እና አበባየሁ ዳኜ (42 ዓመት) ያሉ የጎልማሳነት ዘመናቸው ላይ የነበሩ አባወራዎች ሲገደሉ፣ ከጀርባቸው ስንት ቤተሰብ በትነው እንደሄዱ ማሰብ ያሳምማል። ገና ለሀገር እና ለወገን ይደርሳሉ የተባሉ ወጣቶችም የዚህ ጽዋ ቀማሾች ሆነዋል። ተሬ ደሴ (የ25 ዓመት ወጣት)፣ ገነነ ጥላሁን እና ሙርቴሳ ጥላሁን በሺርካ ወረዳ ሕልማቸው ተጨናግፎ፣ ደማቸው በመሬት ላይ ፈሷል።
አቶ ንጉሱ ማንደፍሮ፣ አቶ በቀለ ኃ/ሚካኤል፣ ከፈለኝ ልክየለው... እነዚህ ስሞች ዝም ብለው በወረቀት ላይ የሰፈሩ አይደሉም። እነዚህ አባቶች ያሏቸው፣ እናቶች ያሳደጓቸው፣ ልጆች የሚጠብቋቸው ነፍሶች ነበሩ። በሃይማኖታቸው ምክንያት ብቻ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።
ይህ ዓይነቱ እምነትን መሠረት ያደረገ መከራ፣ በዓለማችን ታሪክ አዲስ አይደለም። የሰው ልጅ በፈጣሪው በማመኑ ብቻ የተከፈለው ዋጋ ብዙ ነው።
ወደ ሩቅ ጎረቤት ሀገር ግብጽ ስንሄድ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ለዘመናት በእምነታቸው ምክንያት ከፍተኛ ዋጋ ሲከፍሉ ኖረዋል። በተለይም እ.ኤ.አ. በ2015 በሊቢያ የባህር ዳርቻ አይ ኤስ በተባለው አሸባሪ ቡድን የታረዱት 21 የግብጽ ኮፕቲክ ክርስቲያኖችን ዓለም መቼም አይረሳም። ቢላዋ በአንገታቸው ላይ ሲያርፍ እንኳን የፈጣሪያቸውን ስም እየጠሩ በድፍረት ሰማዕትነትን ተቀብለዋል። የአርሲዎቹም ሰማዕታት ከዚሁ የጽናት መንገድ የወጡ አይደሉም። ኢትዮጵያውያንም በተመሳሳይ በሊቢያ እንዲሁ።
ወደ ምዕራብ አፍሪካ ስናቀና ደግሞ ናይጄሪያ እናገኛለን። በቦኮሃራም እና በአክራሪ የፉላኒ ታጣቂዎች አማካኝነት በሰሜን እና በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍል በሺዎች የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች አብያተ ክርስቲያናቶቻቸው ተቃጥለውባቸው፣ መንደራቸው ወድሞ በግፍ ተጨፍጭፈዋል።
የአርሜንያ የዘር ማጥፋት ታሪክም ሌላው ትልቅ ትምህርት ነው። በ1915 በኦቶማን ኢምፓየር ዘመን፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ አርመናውያን በክርስትና እምነታቸው እና በማንነታቸው ምክንያት ብቻ በግፍ ተጨፍጭፈዋል፣ በበረሃም ተሰደው አልቀዋል። ነገር ግን ዛሬ አርሜንያውያን ከየትኛውም ጊዜ በላይ አብበው፣ እምነታቸውንም አጽንተው ይገኛሉ። ጥይት እና እሳት ስጋን ሊገድል ይችላል፣ እምነትን እና መንፈስን ግን መቼም ሊያጠፋ አይችልም።
ታዋቂው የጥንት ቤተ ክርስቲያን ጸሐፊ ቴርቱሊያን እንዳለው፡-
"የሰማዕታት ደም የቤተ ክርስቲያን ዘር ነው።"
በአርሲ ተራሮች ላይ የፈሰሰው የነ አቶ አማረ፣ የነ ወጣት ተሬ ደሴ ደም በከንቱ አይቀርም። የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚያስተምረን፣ መከራ በበዛ ቁጥር፣ መቅደሶች በነደዱ ቁጥር፣ የእምነት ስር ይበልጥ ይጠልቃል እንጂ አይደርቅም።
በእንደዚህ ዓይነት ጥልቅ ሀዘን እና የሰብአዊነት ውድቀት ውስጥ ስናልፍ፣ የሰው ልጅ ታሪክ ካፈራቸው ታላላቅ መሪዎች እና ፈላስፎች የምንማረው ብዙ ነገር አለ። ጭካኔን በጭካኔ መመለስ የትም አያደርስም።
የሰብአዊ መብት ታጋዩ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር (የተናገረው ኃያል ቃል በዚህ ጊዜ ትዝ ይለናል፡-
"ጨለማ ጨለማን ሊያባርር አይችልም፤ ይህንን ማድረግ የሚችለው ብርሃን ብቻ ነው። ጥላቻ ጥላቻን ሊያጠፋ አይችልም፤ ይህንን ማድረግ የሚችለው ፍቅር ብቻ ነው።"
በአርሲ የተፈጸመው ድርጊት የጨለማ እና የጥላቻ ፍሬ ነው። ነገር ግን የተፈናቀሉት ምዕመናን ጽላቱን አቅፈው መውጣታቸው፣ ብርሃንን እና ፍቅርን ምርጫቸው እንዳደረጉ ያሳያል።
የሰላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊው እና የሆሎኮስት (የአይሁዳውያን ጭፍጨፋ) ተራፊው ኤሊ ዊሰል ስለ ግፍ ዝምታ ሲናገር፡-
"ዝምታ ሁልጊዜም የሚጠቅመው አጥቂውን እንጂ ተጠቂውን አይደለም። ገለልተኝነት የሚረዳው ጨቋኙን እንጂ ተጨቋኙን አይደለም።" ብሎ ነበር።
ስለሆነም የነዚህን ንጹሐን መገደል፣ የ101 ዓመት ታሪካዊ ቅርስ መቃጠል፣ እና የ280 ሰዎች መፈናቀል እንደ ቀላል ዜና አልፈነው ልንሄድ አይገባም። ህመማቸውን ልንጋራ፣ ድምጻቸው ልንሆን ይገባል።
ታላቁ የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ደግሞ ስለ መጽናት እንዲህ ይላሉ፡-
"ትልቁ የህይወት ክብር ያለው ፈጽሞ ባለመውደቅ ውስጥ ሳይሆን፣ በወደቅን ቁጥር ተመልሶ በመነሳት ውስጥ ነው።"
ኦርቶዶክሳውያኑ ዛሬ ቤታቸው ፈርሶ፣ ዘመዶቻቸው ተገድለውባቸው ሜዳ ላይ ወድቀው ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን እምነታቸው እስካለ ድረስ፣ ነገ ከአመዱ ላይ ተመልሰው ይነሳሉ።
በአሰኮ ወረዳ ብቻ ከ280 በላይ የሚሆኑ ዜጎች ተፈናቅለዋል። መፈናቀል ማለት መጓዝ ብቻ አይደለም። መፈናቀል ማለት ትዝታን፣ ልፋትን፣ የልጅነት የቦረቁበትን አፈር፣ እና የዘመዶችን መቃብር ትቶ መሄድ ማለት ነው። እነዚህ ሰዎች አሁን ያሉት ሜዳ ላይ ነው። የለበሱት ልብስ ብቻ ነው ያላቸው። የሌሊቱ ብርድ ሲቆራርጣቸው፣ የጠዋቱ ጸሐይ ሲያቃጥላቸው፣ የልጆቻቸው ርሃብ አንጀታቸውን ሲበላው... ያላቸው ብቸኛ መጽናኛ በደረታቸው ያቀፉት እምነታቸው ብቻ ነው።
"ስለ አንተ ሁልጊዜም ተገድለናል እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል" (መዝሙር 43:22)። የአርሲና ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሀዘን መግለጫቸውን የጀመሩት በዚህ የዳዊት መዝሙር ነበር። ይህ ቃል የዛሬን ብቻ ሳይሆን የዘመናትን የክርስቲያኖችን ህይወት የሚገልጽ ነው።
በእርግጥም እንደ በግ ለመታረድ የተሰለፉት እነዚህ ወገኖች ጥፋታቸው ምንድን ነው? ከማንም ጋር ያልተጣሉ፣ የፖለቲካ አጀንዳ የሌላቸው፣ ኑሯቸውን ለማሸነፍ መሬት የሚጭሩ ምስኪን ገበሬዎች ነበሩ። ነገር ግን በአክራሪነት የታወረው አእምሮ ይህንን ሊረዳ አይችልም።
እሳት ሁሉንም ነገር ያወድማል፤ መጽሐፍትን ያቃጥላል፣ ግድግዳን ያፈርሳል፣ ስጋን ያጠፋል። ነገር ግን እሳት እምነትን ሊያቃጥል አይችልም። የ101 ዓመቱ የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ዛሬ በአካላዊ ገጽታው ባይኖርም፣ ያ መቅደስ የሰራው መንፈሳዊ ህንጻ ግን አሁንም በምዕመናኑ ልብ ውስጥ ጸንቶ ይገኛል።
የ13ቱ ሰማዕታት ነፍስ በሰላም ታርፋለች፤ ደማቸው ግን ለትውልድ የሚተላለፍ የጽናት ትምህርት ሆኖ ይኖራል። የተሰደዱት ወገኖቻችን ዛሬ ሜዳ ላይ ቢሆኑም፣ የታሪክ ጌታ የሆነው አምላክ ነገን አዲስ አድርጎ ይሰራላቸዋል። የጥላቻ ኃይሎች በክፋታቸው መቅደሱን አፍርሰውታል፤ ሆኖም እውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን የድንጋይ እና የእንጨት ክምር ሳትሆን፣ ያቺ በስደት መሃልም ጽላቷን አቅፋ የምትጓዘዋ የሰው ልጅ ልብ ናት።
እስከዚያው ግን እንደ አቡነ ኤልሳዕ ጸሎት፤ ፈጣሪ የሞቱትን ነፍስ በመንግሥተ ሰማያት ያሳርፍ፣ የተፈናቀሉትን፣ የተራቡትን እና የተራቆቱትን ደግሞ በምህረት እጁ ይጎብኝ፣ ያጽናናም። ከጭስ እና ከአመድ በስተጀርባ፣ ብርሃን አለና።

3 months ago
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ሰብዓዊ ክብር እና ሕይወት በተመለከተ የተላለፈ ሐዋርያዊ ጥሪ
“ምሕረት የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፤ ምሕረትን ያገኛሉና”. (ማቴ 5:7)
ለፖለቲካ መሪዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ ሚዲያዎች እና በጎ ፈቃድ ላላቸው ሰዎች ሁሉ
የተከበራችሁ ወንድሞች እና እህቶች
እኛ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት በመላው አለም ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወቅታዊ ሁኔታች እንዳሳሰበን ለመግለጽ እንፈልጋለን። በአገራችን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣት ወንዶችና ሴቶች አገራቸውን ለቀው የሚወጡት ለአገራቸው ፍቅር በማጣት ሳይሆን፣ የተሻለ የሥራ ዕድል እና የኑሮ ሁኔታ በመፈለግ ነው። ተነሳሽነታቸው እጅግ ሊከበር የሚገባው እና መስዋዕትነት የሚጠይቅ ነው፤ ይህም ህይወታቸውን ለማሻሻል፣ ቤተሰቦቻቸውን ለመደገፍ እና በመጨረሻም ለአገራቸው እድገት አስተዋጽኦ ለማድረግ ነው። ነገር ግን እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ስደተኞቻችን የሚያስፈልጋቸውን ሰብዓዊ ክብር ከማግኘት ይልቅ በመዋቅራዊ ብዝበዛ፣ በፍርሃት፣ በገለልተኝነት እና በከባድ ተጋላጭነት ወጥመድ ውስጥ ይገባሉ። ሁኔታቸው ምንም ያህል ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም፣ ቅዱስ የሆነው ሰብአዊ ክብራቸው ግን በድንበር፣ በሕጋዊ ሁኔታ ወይም በኢኮኖሚ ስርዓት ችላ ሊባል ወይም ሊጠፋ አይችልም።
የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ እንዲህ ይላል፤ “በኢኮኖሚ የበለጸጉ መንግስታት፣ ሰዎች በትውልድ አገራቸው ጸጥታንና ለመተዳድሪያ የሚሆን ገቢ በማጣታቸው ወደ አገራቸው ሲገቡ ተቀብለው የተቻላቸውን እርዳታ መስጠት አለባቸው” (CCC 2241)። ይህ ትምህርት ስደተኞች እንደ ውጭ ወይም እንደሸክም መታየት እንደሌለባቸው ይልቁንም እንደ ወንድምና እህት ሰብዓዊ ክብራቸው ሊከበርና ሊጠበቅ እንደሚገባ ያስተምረናል።
ይሁን እንጂ፣ ብዙ ስደተኞች በስደት ጉዟቸው ወቅት ከባድ ፈተናዎች ያጋጥሟቸዋል፤ በእጅጉም ይሰቃያሉ። እኛም ከዚህ በታች የተገለጹትን ቁልፍ የስደት መዳረሻዎች እና ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የሚያጋጥሟቸውን ተያያዥ ችግሮች ተመልክተናል።
1) አንዳንድ የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች፡-
• ሳውዲ አረቢያ፡- በሳውዲ አረቢያ መንግሥት የሚኖሩ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች አሉ። የኢትዮጵያ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ በተለያዩ የሚዲያ ዘገባዎች በሰማነው መሰረት በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ላይ በተፈረደው የሞት ፍርድ ያለንን ስጋት፣ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን። የሳውዲ አረቢያ ባለስልጣናት ለዜጎቻችን ሁሉ ርህራሄ እና ምሕረት እንዲያደርጉ ክቡር የሆነውን የሰው ሕይወት እንዲጠብቁ እንጠይቃለን።
• የመን፡- በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደ የመን ለመግባት ወይም ወደ ሳውዲ አረቢያ ለመጓዝ በቀይ ባህር፣ በጅቡቲ ወይም በኤደን ባሕረ ሰላጤ በኩል ያልፋሉ። የመን ብዙውን ጊዜ ወደ ሌሎች የባህረ ሰላጤ አገሮች እንደ መጓጓዣ መንገድ ትጠቀማለች፤ ሆኖም ግን፣ ብዙ ስደተኞች በመንገድ ላይ ከፍተኛ ሥቃይ ይደርስባቸዋል፣ ዓመፅ፣ በደል እና ኢ-ሰብአዊ ተግባራት ይደርስባቸዋል። በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች በጉዞው አደገኛ ባህሪ እና በሚገጥሟቸው አስቸጋሪ ሁኔታዎች ምክንያት ሕይወታቸውን ያጣሉ።
• ሊባኖስ፡- በሊባኖስ የሚገኙ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በአገሪቱ ውስጥ ባለው ግጭትና አለመረጋጋት ምክንያት ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው። በዚህም ምክንያት በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ወደ ትውልድ አገራቸው በሰላም ለመመለስና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመገናኘት ይፈልጋሉ።
• የባህረ ሰላጤ አገሮች፡- በእነዚህ አገሮች ውስጥ የሚገኙ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በአሌሪካ በእስራኤል እና በኢራን መሃከል በተፈጠረው ጦርነት እና ግጭት ምክንያት በጭንቅ ውስጥ ይገኛሉ።
2) የደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ ለብዙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ሌላ መዳረሻ ናት። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ለሕይወታቸውና ለንብረታቸው ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ይገኛሉ። አንዳንዶቹ ወደአስቡበት ሳይደርሱ በጉዞ ላይ እያሉ እስራት ይገጥማቸዋል፣ ሌሎቹ ደግሞ ወደ መድረሻቸው የሚደርሱ ሰዎች በፍርሃትና ውስጥ በምኖር ላይ ናቸው። በሚደርሱን ዘገባዎች መሰረት በደቡብ አፍሪካውያን የውጭ ዜጎች ጥላቻ የተነሳ በዓመፅ፣ እና በግድያ በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ክቡር ሕይወታቸው እየጠፋ ነው።
3) የሱዳን - ሊቢያ - የአውሮፓ መንገድ፡ ይህ መንገድ ለረጅም ጊዜ በሕገወጥ አዘዋዋሪዎች በብዛት ከሚጠቀሙባቸው መንገዶች አንዱ ሲሆን፣ ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ስደተኞች ከፍተኛ ስቃይ እና ህልፈተ ህይወት አስከትሏል። ብዙዎች አስቸጋሪ እና አደገኛ የሆነውን የበረሃ መንገድ በኢሰብአዊ ሁኔታዎች ሲያቋርጡ ሕይወታቸውን አጥተዋል። በአሁኑ ጊዜ በሱዳን እየተካሄደ ያለው ግጭት ይህንን ጉዞ የበለጠ አደገኛ አድርጎታል። ሊቢያ የሚደርሱ ሰዎች ብዙውን ጊዜ እስር፣ ዝርፊያ፣ የጉልበት ብዝበዛ እና ከባድ በደል ይደርስባቸዋል። አንዳንዶቹ በክርስትና እምነታቸው ምክንያት ስደት ደርሶባቸዋል እና ህይወታቸውን አጥተዋል። በአደገኛ ጀልባዎች የሜዲትራኒያንን ባህር ለመሻገር የሚሞክሩ ስደተኞች ሲሰምጡ፤ ብዙዎቹ በሚያሳዝን ሁኔታ ህይወታቸውን ያጣሉ፣ ጥቂቶች ብቻ ወደ ላምፔዱዛ ዳርቻ መድረስ ችለዋል። ላምፔዱዛ የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ በአንድ ወቅት በባህር ላይ ለሞቱት ሰዎች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፤ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለስደተኞች ያላትን አንድነት፣ ርህራሄ እና ለስደተኞች ድምጽ የመሆን ተልዕኮ ለማስቀጠል ደሴቲቱን በቅርቡ እንደሚጎበኙም ይጠበቃል።
ይህ የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ስቃይ ከቁጥርም በላይ ውድ እና የተከበረ ህይወት ያላቸው እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው በእንባ፣ በመስዋዕትነት እና በተስፋ የሸኟቸው ልጆች ናቸው። ብዙ ጊዜ ግን እነዚህ ስደተኞች በብዝበዛ፣ በፍርሃት፣ በደል፣ በመገለል እና ለጥቃት በመጋለጥ አላስፈላጊ ስርዓቶች ውስጥ ይወድቃሉ። ብዙዎች ለማሰብ አዳጋች በሆኑ ሁኔታዎችን ውስጥ በህይወት ለመቆየት ይታገላሉ።
በክርስቲያያዊ የበጎ አድራጎት እና በዓለም አቀፍ የወንድማማችነት መንፈስ፣ ለሳውዲ አረቢያ መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከኢትዮጵያውያን ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ ማናቸውም የታቀዱ ግድያዎች እንዲቆሙ እና በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ምሕረትን እንዲያደርጉ ልመና እናቀርባለን። ምህረት ፍትህን አያዳክምም። ምህረት ፍትህን ከፍ በማድረግ ተስፋ ለቆረጡ ተስፋን ይሰጣል።
ይህ አሳዛኝ ሁኔታ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን የሚያባብሱትን ጥልቅ ምክንያቶች ከመሰረቱ ለማስወገድ ይተባበር ዘንድ ዕድል የሚሰጥ ሊሆን ይገባል። ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች፣ የከባቢ አየር ሁኔታ መቃወስ እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ምክንያቶች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን በዓለም ዙሪያ አደገኛ የፍልሰት መንገዶችን እንዲከተሉ እንደሚያስገድዳቸው አስተውለናል። እነዚህን ዋና ዋና ምክንያቶች ችላ የሚል ዓለም የፍልሰት ቀውስን መፍታት አይችልም። በእርግጥም፣ የሰብዓዊነታችን እና የሥልጣኔ መለኪያ በዙሪያችን ያሉ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች በምናሳሳየው እንክብካቤ ላይ የተመሠረተ ነው።
እንደ ኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት፣ ውይይት፣ ምሕረትና ጥበብ ተስፋ መቁረጥንና ሞትን እንዲያሸንፉ አጥብቀን መጸለያችንን እንቀጥላለን። እነዚህን ተጋላጭ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ስደተኞች፣ ቤተሰቦቻቸውን እና ሁሉንም ውሳኔ ሰጪዎች ለሁሉ ቻይ በሆነው የእግዚአብሔርን አምላክ ምህረት እና እገዛ ያገኙ ዘንድ እንጸልያለን።
የኢትዮጵያ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ
አዲስ አበባ
10/09/2018

4 months ago
አሰልጣኝ አሊዮ ሲሴ ከሊቢያ ብሔራዊ ቡድን ጋር መለያየታቸውን ገለጹ
#ethiopia | የቀድሞው የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ስኬታማ አሰልጣኝ አሊዮ ሲሴ፣ በሊቢያ ብሔራዊ ቡድን የነበራቸውን የአንድ ዓመት ቆይታ በይፋ ማጠናቀቃቸው ታውቋል።
ባለፉት 12 ወራት የሊቢያን "የሜዲትራኒያን ፈረሰኞች" ሲመሩ የቆዩት ሲሴ፣ ቡድኑን በአስር ጨዋታዎች ላይ መርተዋል።
አሊዮ ሲሴ ከሊቢያ ጋር መለያየታቸውን ተከትሎ፣ ስማቸው ከሌላኛው የአፍሪካ ግዙፍ ተገዳዳሪ ጋና (ጥቁር ከዋክብት) ጋር በስፋት እየተያያዘ ይገኛል።
ሲሴ ሴኔጋልን ለረጅም ዓመታት በመምራትና የአፍሪካ ዋንጫን በማንሳት የነበራቸው ልምድ፣ ለጋና ብሔራዊ ቡድን ትልቅ ግብዓት ሊሆን ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።
አሊዮ ሲሴ በተለይ በሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ለ9 ዓመታት በቆዩበት ወቅት ለሀገራቸው የመጀመሪያውን የአፍሪካ ዋንጫ በማምጣት ትልቅ ታሪክ የሰሩ ድንቅ አሰልጣኝ መሆናቸው ይታወሳል።
አሁን ደግሞ አዲስ ፈተና ፍለጋ ወደ ጋና የሚያደርጉት ጉዞ እውን ይሆን እንደሆን ወደፊት የሚታይ ይሆናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #alioucisse #libyafootball #ghanablackstars #africanfootball #soccernews #senegal #footballcoach

በአለም አቀፍ ደረጃ ሲፈለግ የነበረው አደገኛ የሰው አዘዋዋሪ በቁጥጥር ስር ዋለ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና በዓለም አቀፉ የጸጥታ መረጃ ትብብር (ROCK) በተደረገ የተቀናጀ ኦፕሬሽን፣ ለዓመታት ሲፈለግ የነበረው አደገኛ የሰው አዘዋዋሪ ይትባረክ ዳዊት (ክብሮም) በትግራይ ክልል ሽረ ከተማ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ይህ ግለሰብ በስዊድን፣ ሱዳን፣ ጅቡቲ እና ኬንያ ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ክብሮም፣ ሙኒር፣ አድሀኖም እና አህመድ የተባሉ የሀሰት ስሞችን በመጠቀም ወንጀሉን ሲያስፋፋ የቆየ ሲሆን፣ ከእርሱ ጋር ዘጠኝ ግብረ-አበሮቹም አብረው ተይዘዋል።
ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ የተወጣጡ ከ3,000 በላይ ወጣቶችን ለከፍተኛ ስቃይ ዳርጓል።
በህገ-ወጥ ዝውውሩ ምክንያት የ100 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፣ በ50 ሴቶች ላይ ደግሞ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈጽሟል።
ወንጀለኞቹ ተጎጂዎችን ሊቢያ ውስጥ በሚገኙ 5 መጋዘኖች በማገትና ቤተሰቦችን በማስፈራራት ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ሲያንቀሳቅሱ እንደነበር ተደርሶበታል።
የፌደራል ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን ለማጠናከር በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት (ሊቢያ፣ ቤልጂየም፣ ካናዳ እና እንግሊዝን ጨምሮ) ከሚገኙ 100 በላይ ምስክሮች ቃል ተቀብሏል። በአሁኑ ወቅት የተጠርጣሪዎቹ የባንክ ሂሳብና ንብረት የታገደ ሲሆን፣ መዝገቡ ለዓቃቤ ሕግ መላኩ ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ethiopia #federalpolice #humantrafficking #justice #shire #internationalcrime #news #update

ዓለም አቀፍ የሰዎች አዘዋዋሪ ይትባረክ ዳዊት (ክብሮም) በቁጥጥር ስር ዋለ
#fastmereja I የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከ3 ሺህ በላይ ዜጎችን በሕገ-ወጥ መንገድ ያዘዋወረውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲፈለግ የነበረው አደገኛ ወንጀለኛ ይትባረክ ዳዊት (ክብሮም) ከ9 ግብረ-አበሮቹ ጋር መያዙን አስታወቀ። ተጠርጣሪው በትግራይ ክልል ሽሬ ከተማ ውስጥ በድብቅ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ስር የዋለው፣ ፖሊስ ከዓለም አቀፉ የ"ROCK" ተቋም ጋር ባደረገው የጋራ ክትትልና የመረጃ ልውውጥ ነው።
ተጠርጣሪው ይትባረክ ዳዊት በተለያዩ አገራት አድሀኖም፣ አህመድ፣ ሙኒር እና ክብሮም የሚሉ ስድስት የሀሰት ስሞችንና ፓስፖርቶችን በመጠቀም ለዓመታት ሲያመልጥ ቆይቷል። በምርመራው እንደተረጋገጠው፣ ግለሰቡና ቡድኑ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳንና ሶማሊያ ወጣቶችን በመመልመል ሊቢያ ውስጥ በሚገኙ አምስት መጋዘኖች አግተው ኢ-ሰብአዊ ስቃይ ሲያደርሱባቸው ነበር።
በዚህ የወንጀል ድርጊት ሳቢያ፦
ከ100 በላይ ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል።
ከ50 በላይ ሴቶች ተደፍረዋል።
ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ በሕገ-ወጥ መንገድ ተንቀሳቅሷል።
ፌደራል ፖሊስ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በ9 አገራት የሚገኙ 16 ተጎጂዎችን ጨምሮ የ100 ሰዎችን ምስክርነት ተቀብሏል። ተጠርጣሪዎቹ በወንጀል ያፈሩት ሀብትና የባንክ ሂሳብ እንዲታገድ የተደረገ ሲሆን፣ የፖሊስ ምርመራ ተጠናቆ መዝገቡ ለዓቃቤ ሕግ መላኩ ተረጋግጧል።
መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም

"ዴሞክራሲ ገዳይ ነው፤ አፍሪካውያን ሊረሱት ይገባል" — የቡርኪና ፋሶው መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ
#ethiopia | የቡርኪና ፋሶው ወታደራዊ መሪ ካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ፣ የምዕራባውያን የዴሞክራሲ ሥርዓት በአፍሪካ ምድር ላይ "ደም መፋሰስን" እንጂ እድገትን አላመጣም ሲሉ በፅኑ ተቃወሙ። መሪው ባደረጉት የቴሌቪዥን ቆይታ፣ የሀገሪቱ ሕዝብ ስለ ዴሞክራሲ ያለውን ሃሳብ "መዘንጋት" እንዳለበትና ሥርዓቱ ለአህጉሪቱ የማይበጅ "ባዕድ መጫወቻ" መሆኑን ገልጸዋል።
"ዴሞክራሲ ወይስ ጥፋት?"
ትራኦሬ በንግግራቸው ምዕራባውያን ዴሞክራሲን ለማስፈን ጣልቃ በገቡባቸው ሀገራት ሁሉ ውጤቱ ውድመት መሆኑን ጠቅሰዋል። ለዚህም እንደ አብነት ያነሱት ሊቢያን ነው።
"በሙአመር ጋዳፊ ዘመን ሕዝቡ ነፃ ትምህርት፣ ሕክምናና መኖሪያ ቤት ያገኝ ነበር፤ ምዕራባውያን ጣልቃ ገብተው ጋዳፊን ከገደሉ በኋላ ግን ሊቢያ በማብቂያ የሌለው ትርምስ ውስጥ ትገኛለች" ሲሉ የሥርዓቱን "ገዳይነት" አስረድተዋል።
መሪው በአፍሪካ ፖለቲከኞች ላይ ያላቸውን ዕይታም አልሸሸጉም። "እውነተኛ ፖለቲከኛ የሚባለው ውሸታም፣ አድርባይና በአፈ-ጮሌነት ሕዝብን የሚያታልል ነው" ያሉ ሲሆን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ለሀገር አንድነት እንቅፋትና "ከፋፋይ" በመሆናቸው በሀገራቸው እንዳይታገዱ ማድረጋቸውን ተከላክለዋል።
ከምዕራባውያን ኮፒ-ፔስት (Copy-paste) አሰራር ወጥቶ የራስን መንገድ መከተል እንደሚገባ የገለጹት ትራኦሬ፣ የሚከተሉትን ነጥቦች እንደ መፍትሄ አስቀምጠዋል፦
ከታች የሚነሳና በባሕላዊ መሪዎች የሚታገዝ አዲስ ሥርዓት መገንባት።
በቀን 6 ወይም 8 ሰዓት በመሥራት ብቻ ሀገርን ማሳደግ እንደማይቻልና አፍሪካውያን የሥራ ባህላቸውን መቀየር እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ከምዕራባውያን ዕርዳታ መላቀቅና በኢኮኖሚም ሆነ በወታደራዊ መስክ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ።
ካፒቴን ትራኦሬ በሐምሌ 2024 ምርጫ እንደሚያካሂዱ መጀመሪያ ላይ ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም፣ የሥልጣን ዘመናቸውን ለተጨማሪ 5 ዓመታት ማራዘማቸው ይታወሳል። ይህ የዴሞክራሲ "አይበጀንም" ንግግራቸውም በሥልጣን ላይ ለቆዩባቸው ዓመታት እንደ ርዕዮተ-ዓለማዊ መከራከሪያ እየቀረበ ይገኛል።
በአጠቃላይ የ38 ዓመቱ ወጣት መሪ መልእክት ግልጽ ነው፦ "የእኛ መንገድ አብዮታዊ ነው፤ የማንንም ፈለግ አንከተልም!"
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ibrahimtraore #burkinafaso #africapolitics #democracy #sovereignty #panafricanism #westafrica #politicalshift

የኢራናውያን ለትራምፕ እና ለኔታንያሁ '' መንግስታችሁን በሃይል ተቆጣጠሩ'' ጥሪ ጀርባ የሰጡበት ሚስጥር
የኔታ ሚዲያ
በመካከለኛው ምስራቅ ፖለቲካ ውስጥ የኢራን መንግስት እና የምዕራባውያን (በተለይም የአሜሪካ እና የእስራኤል) ግንኙነት ለበርካታ አስርት ዓመታት በጠላትነት የፈረጀ ነው።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በተደጋጋሚ የኢራን ህዝብ አሁን ያለውን አብዮታዊ መንግስት እንዲገለብጥና የራሱን እድል እንዲወስን ጥሪ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።
ሆኖም ግን በኢራን ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ቢነሱም እነዚህ የውጭ መሪዎች ያቀረቡት ጥሪ በኢራናውያን ዘንድ የሚፈለገውን ውጤት ሳያመጣ ቀርቷል።
ይህ የሆነው ኢራናውያን ከመንግስታቸው ጋር ያላቸው ቅሬታ ወደ ጎን አድርገው ለውጭ ጣልቃ ገብነት ያላቸው አመለካከት በታሪክ በሃይማኖት እና በብሔራዊ ማንነት የታጠረ በመሆኑ ነው።
ኢራናውያን የትራምፕን እና የኔታንያሁን ጥሪ ወደ ጎን ለማለት ያስገደዷቸው ዋና ዋና ምክንያቶች
1. የሉዓላዊነት እና የብሔርተኝነት ስሜት
ኢራናውያን ረጅም እና ኩራት የሚሰማቸው የታሪክ ባለቤት ናቸው። የፋርስ (Persian) ብሔርተኝነት ከመንግስት ፖለቲካ በላይ የቆመ ነው። ህዝቡ የውስጥ ችግሩን በራሱ ለመፍታት እንጂ በታሪካዊ ጠላቶቹ በኩል በሚመጣ "ነፃ አውጭ" ተብዬ ሀይል መመራት አይፈልግም።
ትራምፕ እና ኔታንያሁ በኢራን ላይ የሚሰነዝሩት ንግግር በህዝቡ ዘንድ እንደ ድጋፍ ሳይሆን የሀገርን ክብር የመንካት ሙከራ ተደርጎ ይወሰዳል።
2. የታሪክ ትምህርት እና የውጭ ጣልቃ ገብነት ፍርሃት
እ.ኤ.አ. በ1953 አሜሪካ እና እንግሊዝ የኢራንን ዴሞክራሲያዊ መንግስት በመፈንቅለ መንግስት ማውረዳቸው በህዝቡ ልብ ውስጥ ትልቅ ጥርጣሬ ጥሏል። ይህ ታሪክ ምዕራባውያን ለኢራን ህዝብ ጥቅም ሳይሆን ለራሳቸው ፍላጎት ይቆማሉ የሚል እምነት እንዲሰርጽ አድርጓል።
ኔታንያሁ እና ትራምፕ ለኢራን ህዝብ ነፃነት እንደሚመኙ ሲናገሩ ህዝቡ ንግግሩን ከታሪካዊው ጣልቃ ገብነት ጋር በማያያዝ በጥርጣሬ ይመለከተዋል።
3. የሃይማኖታዊ እና የመንግስት ምስረታ እሳቤ
የኢራን መንግስት የተገነባው በሺዓ እስልምና መርሆዎች እና "የሃይማኖት ሊቃውንት የበላይነት" (Velayat-e Faqih) በሚለው ፍልስፍና ላይ ነው።
ለመንግስት ታማኝ መሆን ለብዙሃኑ ኢራናውያን ሃይማኖታዊ ግዴታ ጭምር ነው።
የምዕራባውያን መሪዎች የሚያቀርቡት የለውጥ ጥሪ ከአካባቢያዊ ባህል እና ሃይማኖት የራቀ በመሆኑ እንደ ባዕድ ባህል ወረራ ይቆጠራል።
4. የደህንነት እና የመበታተን ስጋት
ኢራናውያን በጎረቤቶቻቸው (ኢራቅ፣ ሶሪያ፣ ሊቢያ እና አፍጋኒስታን) የታዩትን የውጭ ጣልቃ ገብነቶች ውጤት በሚገባ ይገነዘባሉ።
መንግስት በውጭ ሀይል ግፊት ቢወድቅ ሀገሪቱ ወደ ማያልቅ የእርስ በእርስ ጦርነት እና ትርምስ ውስጥ ትገባለች የሚል ከፍተኛ ስጋት አለ።
ብዙዎች አሁን ያለውን መንግስት ቢጠሉ እንኳ ሀገር ከመበታተን አሁን ያለው ሁኔታ ይሻላል የሚል ስሌት ይከተላሉ።
5. የተቃራኒ ፖሊሲዎች ተፅዕኖ (Inconsistency)
ትራምፕ በኢራን ህዝብ ላይ የጣሉት "ከፍተኛ ጫና" (Maximum Pressure) ማዕቀብ ህዝቡን ለከፋ ድህነት ዳርጓል። ህዝቡን በኢኮኖሚ እየቀጡ "ነፃ ላወጣችሁ እፈልጋለሁ" ማለት በኢራናውያን ዘንድ ተቀባይነት የሌለው ንግግር ነው።
በተመሳሳይ ኔታንያሁ የኢራን ህዝብ ጠላት መሆናቸውን በየመድረኩ እየገለጹ በቪዲዮ ወጥተው "ወዳጆቼ" ማለታቸው እንደ ፖለቲካዊ ማላገጫ ነው የሚታየው።
በአጠቃላይ ኢራናውያን ለውጭ ጥሪዎች ጀርባቸውን የሰጡት አሁን ባለው ስርዓት ደስተኛ ስለሆኑ ሳይሆን የለውጥ ፍላጎታቸው ከሀገራዊ ክብራቸው እና ከሉዓላዊነታቸው ጋር ስለማይደራደር ነው።
የውጭ ጣልቃ ገብነት የሚያስከትለው መዘዝ እና የታሪክ ጠባሳ ህዝቡ የትራምፕን እና የኔታንያሁን ጥሪ እንደ መርዳት ሳይሆን እንደ አዲስ የወረራ ስልት እንዲመለከተው አድርጎታል።
ለኢራናውያን በቤት ውስጥ ያለ ጠብ በቤት ውስጥ ባሉ ሰዎች ብቻ መፈታት አለበት የሚለው መርህ ከምንም በላይ ይገዝፋል።

የመጨረሻው ዘመን ፍጻሜ ድራማ
ከኤፍራጥስ መድረቅ እስከ ክርስቶስ ግርማ
ዓለማችን አሁን ካለችበት አንጻራዊ ሰላም ወጥታ ወደማይታሰብ ትርምስና መለኮታዊ ፍርድ የምታደርገው ጉዞ የሚጀምረው በአንድ ወንዝ ነው።
1. የምልክቶች መጀመሪያ፡
የሚንገላወደው ታላቁ ወንዝ
ታላቁ የኤፍራጥስ ወንዝ ለሺህ ዓመታት ሲያፈስ የነበረው ውኃው በድንገት እየዛለ ይሄዳል። ወንዙ ሲደርቅ፣ ቀደም ሲል በውኃው ሥር ተቀብረው የነበሩ ጥንታውያን ከተሞችና መቃብሮች ለአይን ይገለጣሉ። ይህ የውኃ መድረቅ ግን የተፈጥሮ ክስተት ብቻ አይደለም፤ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው "ከፀሐይ መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት" መንገድ እየተጠረገ ነው። ግዙፍ የምስራቅ ኃይሎች ያለምንም እንቅፋት ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚጎርፉበት ድልድይ ይሆናል።
2. የኃያላን መሰባሰብና የ"ጎግ" ግስጋሴ
በዓለም ዙሪያ የታላላቅ ሠራዊት ድምፅ ይሰማል። ከሰሜን ራቅ ካለ ስፍራ (ከአሁኗ ሩሲያ አካባቢ) "ጎግ" የተባለ ኃያል መሪ ይነሳል። ከእርሱም ጋር የጥንቷ ፋርስ (ኢራን)፣ ሊቢያ እና ኩሽ (ኢትዮጵያ) በወታደራዊ ስምምነት ይሰለፋሉ። ምንም እንኳን ኢትዮጵያና ሩሲያ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ቢሆኑም፣ በዚያ ዘመን ያሉ መሪዎቻቸው በፖለቲካዊ ጥቅምና በዓለም አቀፍ ጫና ምክንያት በዚህ አስፈሪ ጥምረት ውስጥ ይገኛሉ። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወታደሮችና ዘመናዊ መሣሪያዎች ወደ እስራኤል ተራራዎች ይተማሉ።
3. የሐሰተኛው ክርስቶስ መውጣትና የሰላም ጭንብል
ዓለም በጦርነትና በኢኮኖሚ ቀውስ ስትታመስ፣ አንድ አስገራሚ መሪ ከመካከላቸው ብቅ ይላል። እርሱ ንግግሩ ሰላም፣ መፍትሔውም ድንቅ ይመስላል። ራሱን እንደ "ዓለም አዳኝ" ያቀርባል።
* የአይሁድ መታለል፦ አይሁዳውያን መሲሕን እንደ ምድራዊ ንጉሥ ስለሚጠብቁ፣ ይህ ሰው በኢየሩሳሌም ሦስተኛውን ቤተ መቅደስ እንዲገነቡ ሲፈቅድላቸው "የጠበቅነው መሲሕ መጣ" ብለው በደስታ ይቀበሉታል።
* አንድ የዓለም መንግሥት፦ ይህ መሪ ዓለምን በአንድ ፖለቲካ፣ በአንድ ሃይማኖትና በአንድ ኢኮኖሚ ሥር ይጠቃልላል።
4. የዲጂታል ሰንሰለት፡ 666 እና የኢኮኖሚው ቁጥጥር
በዚህ አዲሱ የዓለም ሥርዓት ውስጥ ነፃነት ይጠፋል። ጥሬ ገንዘብ (Cash) ታሪክ ይሆናል፤ ሁሉም ግብይት በዲጂታል ገንዘብ (CBDC) ይተካል።
ማንም ሰው በሰውነቱ ላይ (በእጁ ወይም በግንባሩ) "የአውሬውን ምልክት" 666 ካልያዘ በቀር መግዛትም ሆነ መሸጥ አይችልም። ይህ ምልክት መታወቂያ ብቻ ሳይሆን የአገዛዙ ታማኝ መሆንህን የሚያረጋግጥ ዲጂታል ማረጋገጫ ነው። ብዙዎች ለጉሮሮአቸው ሲሉ ይሰግዳሉ፤ እውነተኛ አማኞች ግን በዚህ መከራ ውስጥ ያልፋሉ።
5. ክህደቱና የታላቁ መከራ ሰዓት
ከሦስት ዓመት ተኩል በኋላ የሰላሙ ጭንብል ይወልቃል። ሐሰተኛው ክርስቶስ በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ተቀምጦ "እኔ አምላክ ነኝ፣ አምልኩኝ" ሲል ዓለም ይደነግጣል። አይሁዳውያን እንደተታለሉ ይረዱና ይቃወሙታል። በዚህ ሰዓት ሄኖክና ኤልያስ ከሰማይ ወርደው ሐሰተኛውን ያጋልጣሉ። ምድር በታሪክ አይታው የማታውቀው "የታላቁ መከራ ዘመን" ውስጥ ትገባለች።
6. አርማጌዶን፡ የክርስቶስ ግርማና የመጨረሻው ፍርድ
የዓለም ኃይላት በሙሉ (ኢትዮጵያንና ሩሲያን ጨምሮ በመሪዎቻቸው የተሰለፉት) እስራኤልንና ቅዱሳንን ለማጥፋት በአርማጌዶን ሸለቆ ይሰበሰባሉ። የጦርነቱ ድምፅ ምድርን ሲያናውጥ፣ በድንገት ሰማይ እንደ መጋረጃ ይከፈታል።
* የንጉሡ መገለጥ፦ እውነተኛው መሲሕ ኢየሱስ ክርስቶስ በግርማና በኃይል፣ በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ይገለጣል። በአፉ ቃል ብቻ (በመለኮታዊ ኃይሉ) ሐሰተኛውን ክርስቶስንና ግዙፍ ሠራዊቱን ድል ያደርጋል።
* የአይሁድ መመለስ፦ አይሁዳውያን ቀደም ሲል የቀበሩትንና ያልተቀበሉትን ኢየሱስን ሲያዩት "የወጉትን ያዩታል" የሚለው ትንቢት ይፈጸማል፤ በለቅሶና በንስሐ ወደ እርሱ ይመለሳሉ።
7. የሺህ ዓመቱ መንግሥትና የዘላለም ተስፋ
ድሉ ተጠናቋል። ክፋት ተሸንፏል። እንደ ኦርቶዶክስና ካቶሊክ አስተምህሮ፣ ይህ የሺህ ዓመት ዘመን ክርስቶስ ካረገበት ጊዜ ጀምሮ በቅዱሳኑ ልብና በቤተክርስቲያን እየገዛ ያለበት የጸጋ ዘመን ነው።
በመጨረሻው ምጽዓት ግን ዓለም ትታደሳለች። አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ይተካሉ፤ ሞትና ለቅሶ በሌለበት የዘላለም መንግሥት ቅዱሳን ይነግሣሉ።
የኢትዮጵያ ተስፋ፦ በመጨረሻው ሰዓት፣ ምንም እንኳን በፖለቲካው ጦርነት ውስጥ ብትጠቀስም፣ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር የዘረጋችው ኢትዮጵያና አማኝ ሕዝቦቿ ከመለኮታዊው ድልና በረከት ጋር ይቆማሉ።

5 months ago
ነደጅ ፣ ዶላር እና የጦር መሣሪያ ሽያጭ - የእውነተኛው የጦርነት መንስኤዎች
ከሚካሊስ ፕሲሎስ ፅሁፍ የተወሰደ
በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል ያለው ግንኙነት ባለፉት አራት አስርት ዓመታት ውስጥ ከታዩት እጅግ ውስብስብ ጂኦፖለቲካዊ ጉዳዮች አንዱ ነው።
በኢራን ያለውን ሥርዓት መለወጥና የኒውክሌር መርሃ ግብሯን ማፍረስ የፕሬዝዳንት ትራምፕ ግልጽ ግብ ነው። ነገር ግን ከትዕይንቱ በስተጀርባ ወሳኝ የሆኑ የንግድ ጥቅሞች አሉ።
"ከነዳጅ እስከ ተፈጥሮ ጋዝ፣ እንዲሁም 'ወሳኝ ማዕድናት' ተብለው እስከሚጠሩት ድረስ፣ ጥቃት እየተፈጸመባት ባለችው ሀገር ውስጥ ትልቅ የተደበቀ አቅም አለ።
የወደፊት የኢራን መንግ ስት ከምዕራቡ ዓለም ጋር፣ በተለይም ከአሜሪካ ጋር ሊፈጠር የሚችለው ጥምረት ትልቁ ጉዳይ ነው" ሲሉ የገበያ ተንታኞች ይናገራሉ።
ኢራን በዓለም አቀፍ ደረጃ አራተኛዋ ግዙፍ የነዳጅ እና የጋዝ አምራች ስትሆን፣ በተፈጥሮ ጋዝ ምርት ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። እንደ ዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ (IEA) መረጃ ከሆነ፣ ኢራን በአሁኑ ጊዜ በቀን 3.3 ሚሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ወደ ውጭ ትልካለች። ይህ ደግሞ ከጠቅላላው የዓለም ምርት ከ3% እስከ 4.5% ይሸፍናል።
በተጨማሪም ኢራን የዓለምን 7% የተፈጥሮ ጋዝ ታመርታለች። የሆርሙዝ ሰርጥ ስልታዊ ጠቀሜታም እጅግ ከፍተኛ ነው፤ የዓለም የነዳጅ ፍጆታ 20% ያህሉ (በቀን 20 ሚሊዮን በርሜል) በዚህ ጠባብ መተላለፊያ በኩል ያልፋል።
ቀድሞውንም በኢራን አብዮታዊ ዘብ ሰርጡን መዘጋቱ የነዳጅ ዋጋን ወደ 100 ዶላር እንዲጠጋ አድርጎታል።
ሳውዲ አረቢያ ብቻዋን በቀን ስድስት ሚሊዮን በርሜል በዚህ መስመር ትልካለች። ቻይናም 47% የባህር ላይ ነዳጇን የምታገኘው ከዚሁ ቀጠና ነው።
ከ1970ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ የዓለም የነዳጅ ንግድ በአሜሪካ ዶላር ላይ የተመሰረተ ነው። ይህ ሥርዓት ለዶላር ዓለም አቀፍ ፍላጎት እንዲኖር በማድረግ ለአሜሪካ ኢኮኖሚ ትልቅ የበላይነት ሰጥቷል።
ኢራን ከ1979 አብዮት ጀምሮ ለነዳጅ ሽያጭ በዶላር ላይ የምታደርገውን ጥገኝነት ለመቀነስ ስትሞክር ቆይታለች። እ.ኤ.አ. በ2008 በኪሽ ደሴት ላይ የኢራን የነዳጅ ልውውጥ ማዕከል በማቋቋም በዩሮ እና በሌሎች ገንዘቦች ንግድ ለመጀመር ሞክራለች። ብዙ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ፣ እንደ ኢራቅ (በሳዳም ሁሴን ጊዜ) እና ሊቢያ (በጋዳፊ ጊዜ) ሁሉ ዶላርን ለመቀየር የሚደረጉ ሙከራዎች ለአሜሪካ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት እንደ ትልቅ ምክንያት ያገለግላሉ።
መካከለኛው ምስራቅ ለአሜሪካ የመከላከያ ኢንዱስትሪ እጅግ ትርፋማ ገበያ ነው። በጥር 2026 አሜሪካ ለሳውዲ አረቢያ እና ለእስራኤል የ15.7 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሣሪያ ሽያጭ አጽድቃለች። እንደ ሎክሂድ ማርቲን እና ቦይንግ ያሉ ኩባንያዎች በቀጠናው ንቁ የሆነ የመከላከያ ወይም የመሳሪያ ገበያ እንዲኖር ከፍተኛ የገንዘብ ፍላጎት አላቸው።
የሳውዲ አረቢያ፣ የእስራኤል እና የኢራን ፉክክር ውስብስብ ነው። ሳውዲ አረቢያ ከእስራኤል ጋር ግንኙነትን ወደ መደበኛነት ለመቀየር እና ከአሜሪካ ጋር የደህንነት ጥምረት ለመፍጠር ትፈልጋለች። ኢራን በበኩሏ የአብዮቷን አስተሳሰብ ለማስጠበቅ ትጥራለች።
አሁን ላይ አዳዲስ ጥምረቶች እየታዩ ነው፦
ሳውዲ አረቢያ እና ፓኪስታን፦ የመከላከያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና እስራኤል፦ ከህንድ ጋር አዲስ ትብብር መስርተዋል።
አሁን ላይ ጦርነት ማዕቀብን ተክቷል። ይሁን እንጂ 92 ሚሊዮን ህዝብ ባላት ሀገር ላይ የሚጣል ቦምብ ለውጥ ሊያመጣ እንደማይችል ተንታኞች ያስጠነቅቃሉ። ይልቁንም ጦርነቱ መላውን ቀጠና የማተራመስ እና የዓለምን ኢኮኖሚ የመጉዳት ከፍተኛ ስጋት አለው።

ግብፅ ለኢትዮጵያ አዲስ አማራጭ አቀረበች፦ "ለዓባይ ውሃ ተለዋዋጭ ከሆናችሁ፣ ለባህር በር ድጋፍ እናደርጋለን"
#fastmereja I ግብፅ በዓባይ ውሃ ክፍፍል ላይ ኢትዮጵያ "ተለዋዋጭ" አቋም የምታሳይ ከሆነ፣ ሀገሪቱ ቀይ ባህርን የምታገኝበትን መንገድ ከአፍሪካ ወዳጆቿ ጋር በመሆን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን ገለጸች። "ዘ ናሽናል" የካይሮ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ይህ ሃሳብ ባለፈው ሳምንት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ደርሷቸዋል።
ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ የተገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለህልውናዋ "ስጋት" እንደሆነ በመግለጽ፣ የውሃ አጠቃቀሙን የሚገዛ ሕጋዊ ስምምነት እንዲኖር ትፈልጋለች።
ኢትዮጵያ በውሃው ጉዳይ ላይ ስምምነት ላይ የምትደርስ ከሆነ፣ ግብፅ ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ ያላትን የባህር በር ፍላጎት ለማሳካት ከጎኗ እንደምትቆም ገልጻለች።
ይህ የግብፅ ሃሳብ ለዋይት ሃውስ ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መላኩ የተገለጸ ሲሆን፣ ፕሬዝዳንቱ በዓመታት የዘለቀውን ይህንን የውሃ ውዝግብ ለማስታረቅ ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል።
ግብፅ ይህንን አማራጭ ስታቀርብ ስውር ማስጠንቀቂያም አክላለች። ኢትዮጵያ ጥያቄውን ውድቅ ካደረገች፣ ግብፅ በሱዳን፣ በሶማሊያ፣ በጅቡቲ እና በኤርትራ ያላትን ከፍተኛ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ተጽዕኖ እንዲሁም በቀይ ባህር ደቡባዊ ክፍል ያለውን የባህር ኃይል ኃይሏን በመጠቀም ኢትዮጵያ የወደብ አገልግሎት እንዳታገኝ "እንቅፋት" እንደምትሆን አመልክታለች።
ምንም እንኳን አዲስ አበባ ለግብፅ ጥያቄ እስካሁን ይፋዊ ምላሽ ባትሰጥም፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ ከቱርክ ፕሬዝዳንት ረጅብ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ኢትዮጵያ የባህር በር እንደሚያስፈልጋት በድጋሚ አጽንኦት ሰጥተዋል። "ከ130 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ሀገር የባህር በር ተከልክላ 'የመልክዓ ምድር እስረኛ' ሆና መቀጠል አትችልም" ብለዋል።
ለዓመታት ተቃቅረው የነበሩት ካይሮ እና አንካራ አሁን ላይ ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ ሲሆን፣ በሱዳን፣ በሊቢያ እና በሶማሊያ ጉዳዮች ላይ ያላቸው አቋም እየተቀራረበ መጥቷል።
ግብፅ፣ ሶማሊያ እና ቱርክ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የባህር በር ለማግኘት ያደረገችውን የመግባቢያ ስምምነት እንዲሁም እስራኤል ሶማሊላንድን እውቅና መስጠቷን በጽኑ ተቃውመዋል።
ግብፅ በአሁኑ ወቅት በጅቡቲ እና በኤርትራ (በአሰብ ወደብ) ላይ ያላትን ተጽዕኖ በማሳደግ እና የባህር ኃይል ጦር ሰፈሮችን በማጠናከር፣ ወደፊት በግድቡ ጉዳይ ላይ ለሚደረግ ድርድር እንደ ትልቅ የመደራደሪያ ካርድ ልትጠቀምበት እንደምትችል ተገምቷል።
#ፖለቲካ ዘገባ

6 months ago
#ethiopia | ያሳዝናል 53 ስደተኞች ዛሬ በሊቢያ ሞተው ተገኙ | የህውሓት አስደንጋጭ ክስ ለምን?ከግዛቴ ውጡ | ውንጀላው መሠረተ ቢስ ነው
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...
6 months ago
በሊቢያ የባህር ዳርቻ በደረሰ የጀልባ መገልበጥ አደጋ የ53 ሰዎች ህይወት አለፈ
በሊቢያ የባህር ዳርቻ ላይ 55 ስደተኞችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች የጎማ ጀልባ በመገልበጧ የሁለት ህጻናትን ጨምሮ የ53 ሰዎች ህይወት ማለፉን የተባበሩት መንግስታት የዓለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቀ።
📍 ስለ አደጋው ዝርዝር መረጃ፡
የተረፉት፡ ከ55 ተጓዦች መካከል በህይወት የተረፉት ሁለት ናይጄሪያውያን ሴቶች ብቻ ናቸው። አንደኛዋ ባሏን ስታጣ፣ ሁለተኛዋ ደግሞ ሁለት ጨቅላ ህጻናት ልጆቿ በአደጋው እንደሞቱባት ተገልጿል።
የጉዞው መነሻ፡ ጀልባዋ ከሊቢያ አል-ዛዊያ ከተማ ተነስቶ ስድስት ሰአት እንደተጓዘች ውሃ በመሙላቱ መገልበጧ ታውቋል።
ተጎጂዎች፡ ተጓዦቹ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተሰባሰቡ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ናቸው።
📉 የ2026 አስከፊ አሃዞች፡
እ.ኤ.አ. 2026 ከጀመረ አንስቶ እስካሁን ድረስ በሜዲትራኒያን ባህር ላይ በደረሱ አደጋዎች ወደ 500 የሚጠጉ ስደተኞች መሞታቸው ወይም መጥፋታቸው ተመዝግቧል። በጥር ወር ብቻ በከባድ የክረምት አየር ሁኔታ ምክንያት 375 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።
⚠️ በሊቢያ ያለው ሁኔታ፡
ከ2011 ወዲህ ሊቢያ ወደ አውሮፓ ለመሻገር ለሚነሱ ስደተኞች ዋነኛ መሸጋገሪያ ሆናለች። ይሁን እንጂ ስደተኞች በሀገሪቱ ውስጥ በሚገኙ የማቆያ ማእከላት ውስጥ ለሚከተሉት ጥቃቶች ይጋለጣሉ፡
ኢ-ሰብአዊ ስቃይ እና ድብደባ
የሰዎች ዝውውር እና አስገዳጅ ስራ
ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር (Extortion)
🌍 ዓለም አቀፍ ጥሪ፡
IOM እና የተለያዩ ሀገራት (ዩኬ፣ ስፔን፣ ኖርዌይ እና ሴራሊዮን ጨምሮ) የሊቢያ መንግስት ሰብአዊ መብት የሚጣስባቸውን የማቆያ ማእከላት እንዲዘጋ እና በህገ-ወጥ አጋቾች ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ እያሳሰቡ ይገኛሉ።

የጌዲዮን ዳንኤል 'መኖር ፈራሁ'፦ በጊዜ መጋረጃ ጀርባ ያለ የህልውና ቀውስና የነፍስ ጩኸት
በኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ታሪክ ውስጥ፣ ከዜማው በላይ የቃላቱ ክብደት ነፍስን የሚረብሹ ጥቂት ስራዎች አሉ። የጌዲዮን ዳንኤል "መኖር ፈራሁ እንደገና" ግጥም አንዱ ነው። ይህ ግጥም ተራ የሀዘን እንጉርጉሮ ሳይሆን፣ የሰው ልጅ በዚህ ግራ በተጋባ ዓለም ውስጥ ያለውን የህልውና ጭንቀት (Existential Dread) በኪነ-ጥበብ መነጽር የፈተሸበት፣ የዘመናዊነትን ስብራት ያሳየበት ጥልቅ ስራ ነው።
1. የጊዜ "ጭካኔ" እና የፍልስፍናው መነሻ
ጀርመናዊው ፈላስፋ ማርቲን ሄይዴገር
"Being and Time" በሚለው መጽሐፉ፣ የሰው ልጅ መኖር ማለት "ወደ ሞት መገስገስ" እንደሆነ ይገልጻል። ጌዲዮን "ጊዜ ሲሸኝ ጊዜን ወልዶ፣ ዓመት ሲያልፍ መዓት ወልዶ" ሲል፣ ይህንኑ የሄይዴገርን ፍልስፍና በግጥም ይተረጉመዋል። እያንዳንዱ ያለፈ ቀን ለደስታ ሳይሆን ለሌላ "መዓት" በር መክፈቱ፣ የሰው ልጅ በጊዜ ፊት ያለውን አቅመ-ቢስነት ያሳያል።
አልቤር ካሙ ደግሞ የሕይወትን ትርጉም አልባነት (Absurdity) ሲገልጽ፣ ሰው ትርጉም በሌለው ዓለም ውስጥ ትርጉም ለመፈለግ ሲዳክር የሚገጥመውን ሰቆቃ ያሳያል። "ወይ አንዴ አይዘንብ ወይ አያባራ" የሚለው የጌዲዮን ስንኝ፣ ካሙ የገለጸው አይነት መሀል ላይ የመቅረት ስቃይ ነው። ዝናቡ (መከራው) አልጨረሰንም፤ ፀሐዩም (ተስፋው) አልወጣልንም። ይህ "ግርዶሽ" የዘመናችን ሰው ትልቁ የስነ-ልቦና ቀውስ ነው።
2."የአረጋኸኝ የማይነጋ ሌሊት"
ይህንን ስሜት በደንብ ለመረዳት አንድ እውነተኛ ታሪክ እንመልከት። በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ይኖር የነበረው ወጣት "አረጋኸኝ" (ስሙ የተቀየረ) የዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ነበር። በደረሰበት ተደራራቢ የቤተሰብ ሞት ምክንያት አእምሮው መሸከም አልቻለም። አንድ ቀን ዝናብ አበስብሶት በመንገድ ዳር ቆሞ ሳለ እንዲህ አለ፡
"ሰው አዲስ ዓመት ሲመጣ ይደሰታል፤ እኔ ግን ይጨንቀኛል። ምክንያቱም ዓመቱ በጨመረ ቁጥር ሞት ይቀርበኛል፣ የናፈቁኝ ሰዎች ደግሞ ይርቁኛል። መኖር መፍራት ብቻ ሳይሆን መኖር ሰልችቶኛል።"
አረጋኸኝ ልክ እንደ ጌዲዮን ግጥም፣ "መኖርን ፈርቶ ተሳቅቋል"። ለነዚህ ሰዎች ጊዜ ፈዋሽ ሳይሆን፣ ያለፈውን ቁስል የሚቀሰቅስ ድብቅ ጠላት ነው። "የጊዜ ቅጣት ፈሪ አደረገኝ" የሚለው ስንኝ የአረጋኸኝን ህይወት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
3. የሳይኮሎጂስቶች ትንታኔ፡ "Anticipatory Anxiety"
ከሳይኮሎጂ አንጻር፣ ግጥሙ የነገን ፍርሃት (Anticipatory Anxiety) በግልጽ ያሳያል። ቪክቶር ፍራንክል በመከራ ውስጥ ትርጉም ማጣትን እንደ ትልቅ መንፈሳዊ በሽታ ይገልጸዋል። ጌዲዮን "መኖር ፈራሁ እንደገና" ሲል፣ ቀደም ሲል የነበረው ህይወት በቁስል የተሞላ እንደነበርና ያንን ድጋሚ ለመጋፈጥ አቅም እንደሌለው ይነግረናል።
ይህ ስሜት በተለይ በጦርነት፣ በረሃብና በማህበራዊ ቀውሶች ውስጥ ላለፉ ሰዎች የሚሰማ "Trauma" ነው። ደራሲው "ዘንድሮስ ውሃ እሳትን ፈራ" ሲል፣ በተፈጥሮ ህግጋት ላይ እንኳ መተማመን ማጣቱን ይገልጻል። ውሃ እሳትን የሚያጠፋ ሳይሆን እሳትን የሚፈራበት ደረጃ ላይ መድረስ፣ የሞራልና የእምነት መላሸቅን (Moral collapse) ያሳያል።
4. "የስደተኛቹ እናት ሰቆቃ"
በሊቢያ በኩል ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሲሉ ልጆቿን በባህር ላይ ያጣችውን የሮማንን ታሪክ እናስታውስ። ሮማን ልጆቿ ካለቁ በኋላ ቀንና ሌሊት የሚቆጥራት ሰዓት ጠላት ሆነባት። "ጊዜ ሲሸኝ ጊዜን ወልዶ..." የሚለው ስንኝ ለእሷ ትርጉሙ ሌላ ነው።
እያንዳንዱ ቀን ትዝታን ይወልዳል፤ እያንዳንዱ ዓመት ደግሞ የልጆቿን እድሜ እያሰላች የምታለቅስበት "መዓት" ይወልዳል።
ሮማን በአንድ ወቅት እንዲህ ብላ ነበር፦ "ሰው ነገ ይሻላል ይላል፤ እኔ ግን ነገ ሌላ ምን መጥፎ ዜና እሰማ ይሆን ብዬ እፈራለሁ። መኖር ራሱ እንደገና የሚጀመር ቅጣት ሆኖብኛል።" ይህ የሮማን ስሜት በጌዲዮን ግጥም ውስጥ "እንደገና እንደገና መኖር ፈራሁ እንደገና" ከሚለው የልብ ስብራት ጋር ፍጹም የተቆራኘ ነው።
5. የደራሲያን እይታ፡ የቃላት ሰቆቃ
ታላቁ ሩሲያዊ ደራሲ ፊዮዶር ዶስቶየቭስኪ "The Brothers Karamazov" ላይ "ገሀነም ማለት መውደድ የማይቻልበት ስቃይ ነው" ይላል። ጌዲዮንም ዓለምን መውደድ አቅቶታል። "አዘጋጅልኝ ቤቴን በልኬ" የሚለው ልመና፣ ከዚህ ምድራዊ "ከንቱ ጊዜ" ወጥቶ ወደ ዘላለማዊ እረፍት ለመሄድ ያለውን ጥልቅ ፍላጎት ያሳያል።
እንደ ሌቪ ቶልስቶይ ገጸ-ባህሪያት፣ ጌዲዮንም የህይወትን ትርጉም በምድራዊ ስኬት ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ፊት በሚቀርብ ትህትና እና "ዳግም ውልደት" ውስጥ ይፈልገዋል።
"ጉም አዝሎ ሰማይ ቀኑ ከበደኝ" የሚለው አገላለጽ፣ በደራሲያን ዘንድ "Pathetic Fallacy" ይባላል—ይህም የተፈጥሮ ሁኔታ ከሰውየው ስሜት ጋር ሲመሳሰል ነው። ሰማዩ ጭጋጋማ የሆነው አየሩ ስለተቀየረ ሳይሆን፣ የደራሲው ነፍስ በጭንቀት ስለታፈነች ነው።
6. "የታመመው ሐኪም"
ከጥቂት ዓመታት በፊት በካንሰር ህመም ምክንያት ህይወቱ ያለፈ አንድ ወጣት ሐኪም ነበር። ይህ ሐኪም የብዙዎችን ህይወት ታድጓል፤ ነገር ግን የእርሱ ተራ ሲመጣ ጊዜው እንዳለቀ ተረዳ። በመጨረሻዎቹ ሳምንታት ግጥም ይጽፍ ነበር። በአንድ ማስታወሻው ላይ እንዲህ ብሏል፦
"ጊዜ ድብቅ ነው። ጤነኛ ሳለሁ ጊዜን የኔ መሰለኝ ነበር። አሁን ግን ጊዜ 'ከንቱ' እንደሆነ ገባኝ። ነገን መመኘት ትቼ፣ ነገ ምን ይዞብኝ ይመጣል ብዬ መፍራት ጀምሬያለሁ።"
ይህ ሐኪም ልክ እንደ ጌዲዮን "አዬ ጊዜ፣ አቤት ጊዜ፣ ድብቅ ጊዜ..." እያለ የጊዜን አታላይነት መስክሯል። ሞት መቃረቡን የሚያውቅ ሰው መኖርን የሚፈራው፣ ህይወትን ስለጠላ ሳይሆን ህይወት የምትሰጠውን ስቃይ መሸከም ስላቃተው ነው።
7. መንፈሳዊነት እንደ ብቸኛ መውጫ
ግጥሙ የሚደመደመው በተስፋ መቁረጥ ሳይሆን በእምነት ነው። "ዳግም ውልደቴን ላንተ ትቻለሁ... ጥራኝ አምላኬ" የሚለው ቃል፣ የሰው ልጅ ከምድራዊ መከራ ሊያመልጥ የሚችለው ወደ ሰማያዊው ኃይል ሲጠጋ ብቻ መሆኑን ያሳያል።
ይህ በሳይኮሎጂ "Spiritual Coping" ይባላል። አንድ ሰው በራሱ አቅም መኖር ሲከብደው፣ ሸክሙን ለፈጣሪ ይሰጣል።
"አዘጋጅልኝ ቤቴን በልኬ" የሚለው ስንኝ፣ ከምድራዊው ሰፊ ግን መከራ የበዛበት ቤት ይልቅ፣ ሰማያዊውንና ሰላማዊውን ቤት የመናፈቅ መግለጫ ነው። ይህ ስሜት በብዙ የሀገራችን ቅዱሳንና ጻድቃን ህይወት ውስጥ የታየ፣ ዓለምን "የስደት ሀገር" አድርጎ የመቁጠር ጥንታዊ ጥበብ ነው።
ማጠቃለያ
የጌዲዮን ዳንኤል "መኖር ፈራሁ" ግጥም የለቅሶ ድምፅ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም የሰው ልጅ በጊዜ ፊት ያለውን አቅመ-ቢስነት፣ የነገን ስጋትና የመንፈሳዊ መጠጊያ ፍለጋን የሚያሳይ ፍልስፍናዊ ድርሰት ነው። "ውሃ እሳትን ፈራ" በሚልበት ዓለም ውስጥ፣ የሰው ልጅ ትልቁ ጠላቱ "ጊዜ" ሳይሆን "ተስፋ ማጣት" ነው።
ይህ ትንተና እንደሚያሳየው፣ መኖርን መፍራት የጥካኔ ሳይሆን የጥልቅ ስሜት መገለጫ ነው።
እንደ አረጋኸኝ፣ እንደ ሮማንና እንደዛ ወጣት ሐኪም ሁሉ፣ እያንዳንዳችን በጊዜ መጋረጃ ውስጥ ተደብቀን የምንዋጋቸው የራሳችን ፍርሃቶች አሉን። ጌዲዮን ዳንኤል ግን የሁላችንንም ጩኸት በአራት ስንኞች ቋጥሮ አቀረበልን።

Comments